TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.8K photos
1.44K videos
207 files
3.99K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
#StayHomeSaveLives

ዶክተሮች ፣ ነርሶች ሁሉም የጤና ባለሞያዎች ከፍተኛ ዋጋ እየከፈሉ ነው ፤ በኮቪድ-19 እየሞቱብን ነው ፣ እየተጠቁብን ነው፤ እባካችሁ ከፈጣሪ በታች ያሉን እነሱ ናቸውና #ጤና እንዲሆኑልን የሚሉንን እንስማ፤ የሚነግሩንን እንተግብር!

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#StayHomeSaveLives

ለጤና ባለሞያዎች ክብር አለን!

በበርካታ ሀገራት በኮሮና ቫይረስ ምክንያት ትምህርት ቤቶች ፣ ዩኒቨርሲቲዎች ተዘግተዋል፤ መስሪያ ቤቶችም ተዘግተዋል ፣ ሰራተኞችም ቤታቸው ሆነው እንዲሰሩ ተድርጓል ፣ የንግድ ማዕከላትም ተዘግተዋል ፣ በረራዎች፣ ዝግጅቶች ተሰርዘዋል።

ይህ ሁሉ ሲሆን ግን በሁሉም ሀገራት ሆስፒታሎች 24 ሰዓት ክፍት ናቸው። የሰዎችን ህይወት ለማትረፍ ይረባረባሉ። ዶክተሮች ፣ የጤና ባለሞያዎች የራሳቸውን ህይወት አደጋ ላይ ጥለው ህመምተኞችን ለማዳን የሚችሉት ያደርጋሉ። ለእኛ ጤና እነሱ አሉልን ፤ ለእነሱ ጤና ደግሞ እኛ ቤት ውስጥ እንሁንላቸው ፤ የሚሉንን፣ የሚመክሩንን እናዳምጣቸው።

ክብር ይገባቸዋል!

ረጅም እድሜን ከጤና ጋር እንመኝላችኃለን!
ሰላም እደሩ!
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ፊሊፒንስ ውስጥ 9 ዶክተሮች በኮሮና ቫይረስ ተጠቅተው መሞታቸው ተሰምቷል። የሰዎችን ህይወት ለማትረፍ ከፍተኛ ትግል እያደረጉ ያሉት የፊሊፒንስ የጤና ባለሞያዎች በቂ መከላከያ እያገኙ አይደለም ተብሏል።

#StayHomeSaveLives
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ጣልያን!

በ24 ሰዓት የተመዘገበው የ919 ሰዎች ሞት የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ከጀመረ አንስቶ የተመዘገበ ከፍተኛው የሟቾች ቁጥር ነው። እንደምታስታውሱት MARCH 21 ነበር 793 ሰዎች በአንድ ቀን የሞቱት።

#StayHomeSaveLives
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#StayHomeSaveLives #TikvahEthiopia

ከተለያዩ ዩኒቨርሲቲዎች ወደቤታችሁ የገባችሁ በብዙ ሺህ የምትቆጠሩ ተማሪዎች ለእናተም ለምትወዷቸው ሰዎችም ስትሉ ከቤት ባለመውጣት የሰው ህይወት ታደጉ!

በሁሉም የሀገሪቱ ክፍል የምትገኙ እና መንግስት ለጤናችሁ ሲባል በቤታችሁ ሆናችሁ ስሩ ያላችሁ ሰራተኞችም ችግሩን እንዳታባብሱት ከቤታችሁ እንዳትወጡ!

ወቅቱ ሻይ ቡና የምንልበት፣ ተሰባስበን የምንገባበዝበት፣ ወጥተን የምንዝናናበት፣ የተለያዩ ዝግጅቶችን የምንታደምበት አይደለምና ለሰው ልጅ ህልውና እራሳችንን እንጠብቅ!

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia