TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.5K photos
1.43K videos
206 files
3.96K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#update በአማራና በኦሮሚያ ክልል አዋሳኝ አካባቢዎች አልፎ አልፎ የሚፈጠሩ የፀጥታ ችሮችን ለመቅረፍ የሚያስችል የጋራ እቅድ አዘጋጅተው ስራ መጀመራቸዉን የሁለቱም ክልሎች የፀጥታ ቢሮዎች አስታወቁ፡፡ የአማራ ክልል አስተዳደር ጉዳዮች የሰላምና ደህንነት ቢሮ ምክትል ኃላፊ ኮሎኔል አለበል አማረ እና የኦሮሚያ ክልል የአስተዳደር ጉዳዮች የሰላምና የፀጥታ ቢሮ ምክትል ኃላፊ ኮሎኔል አበበ ገረሱ ዛሬ በጋራ በባህር ዳር መግለጫ ሰጥተዋል፡፡ በመግለጫው የሁለቱም ክልሎች ህዝቦች ባህላዊና ኢኮኖሚያዊ ትስስር አላቸው፤ በሀገሪቱ ለውጥ እንዲመጣ አብረው ታግለዋል ብለዋል፡፡ የክልሎቹን ግንኙነት ለማሻከር ሰሞኑን በሰሜን ሸዋ በምንጃር ሸንኮራ ወረዳ የተከሰተው እኩይ ተግባር የሁለቱን ክልል ህዝቦች አይወክልም፤ ይህም በፖለቲካ ነጋዴዎች የተቀነባበረ ነው ያሉት፡፡ ኢቢሲ እንደዘገበው የህግ የበላይነትን ለማስከበርና የህዝቦችን ሰላምና ደህንነት ለማስጠበቅ በጋራ እንደሚሰሩም አረጋገጠዋል፡፡ ከቀዬያቸው የተፈናቀሉ ዜጎችን ወደ መኖሪያቸው ለመመለስና ሰላምና የህግ የበላይነት ለማረጋገጥ የአጭር የመካከለኛና የረጅም ጊዜ መፍትሄዎች ማስቀመጣቸዉንም ጠቁመዋል፡፡ በሁለቱ ክልሎች መካከል የተጀመረው ዘላቂና አስማማኝ ሰላም ለማሰፈን የተጀመሩ ስራዎች ከሌሎች ክልሎች ጋር ተጠናክሮ ይቀጥላል ብለዋል፡፡

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ፌስቡክ የነጭ ብሔረተኝነትናና የተገንጣይ አመለካከት አራማጆችን ሊያግድ ነው‼️
.
.
ፌስቡክ ከሚቀጥለው ሳምንት ጀምሮ "የነጮችን ብሔርተኝነትና መለየትን የሚያሞግሱና የሚደግፉ" ፅሁፎችን ከፌስቡክና ከኢንስተገራም ገፆች ላይ እንደሚያግድ አሳወቀ።

ትልቁ የማህበራዊ ሚዲያ ፌስቡክ የሽብርተኝነት ይዘት ያላቸውን ይዘቶች ከድህረገፁ ላይ ለመለየትና ለማስወገድ እንደሚሰራም ቃል ገብቷል።

ቁጣን የሚቀሰቅሱ አባባሎችን የሚፈልጉ የፌስቡክ ተጠቃሚዎች እንደዚህ ዓይነት አስተሳሰብ ወደ የሚከላከሉ የበጎ አድራጎት ገጾች በመምራት ድግፍ እንዲያገኙ ያደርጋል።

በኒውዚላንድ የሁለት መስኪዶች ላይ የተፈጸሙ ጥቃቶች በቀጥታ በማህበራዊ ሚዲያዎች ላይ ከተላለፈ በኋላ የማህበራዊ ሚዲያዎች ጫና በዝቶባቸዋል።

ፌስቡክ ከዚህ በፊት የነጮችን ብሔርተኝነት የሚያሳዩ ይዘቶችን እንደ ዘረኝነት ስለማይቆጥራቸው በገፁ ላይ እንዲገኙ ፈቅዶ ነበር።

"የአሜሪካ አክራሪ የነጮች ቡድንና በስፔን ያለው የባስክ ተገጣይ ቡድኖች አስፈላጊ የሰዎች ማንነት ክፍል እንደመሆኑት ሁሉ" የነጭ ብሔርተኝነትም ተቀባይነት ያለው እንደሆነ ይቀበል ነበር።

ነገር ግን ረቡዕ እለት ገፁ ላይ ባሰፈረው ፅሁፍ ፌስቡክ ለሦስት ወራት "ከህብረተሰብ አካላትና ምሁራን" ጋር ምክክር ካደረገ በኋላ የነጮችን ብሔርተኝነት ከነጮች የበላይነትና ከሌሎች የተደራጁ የጥላቻ ቡድኖች "መለየት" አይቻልም ብሏል።

በኒውዚላንድ የተደረገውን ጥቃት ተከትሎ ብዙ መሪዎች የማህበራዊ ሚዲያዎች በገፆቻቸው ላይ ለሚለጠፏቸው ፅንፈኛ ይዘቶችን ሃላፊነት እንዲወስዱ አስጠንቅቀዋል።

የኒውዚላንዷ ጠቅላይ ሚኒስትር ጃሲንዳ አርደርን ስለማህበራዊ ሚዲያዎች ስትናገር "መልዕክቱን የለቀቀው ሰው ብቻ ሳይሆን አሳታሚዎቹም" እንደዚህ አይነት ይዘቶች ሲለቀቁ ሃላፊነት አለባቸው ብለዋል።

50 ሰዎችን የገደለው የኒውዚላንዱ ጥቃት ምስል ከማህበራዊ መድረኩ ላይ ከመውረዱ በፊት ከ4 ሺህ ጊዜ በላይ እንደታየ ፌስቡክ አስታውቋል።

ድርጅቱ በ24 ሰዓት ውስጥ የምስሉ 1.2 ሚሊዮን ቅጂዎችን ከመለቀቅ የከለከለ ሲሆን 300 ሺህ የሚሆኑትን ደግሞ ከድረ ገፁ ላይ አጥፍቷል።

የፈረንሳይ ሙስሊሞችን የሚወክል አንድ ቡድን ፌስቡክና ዩትዩብ ምስሉን በገፃቸው ስላስተላለፉ ከሷቸዋል።

Via #BBC
@tsegabwolde @tikvahethiopia
መከላከያ ሰራዊት‼️

የኢፌድሪ መከላከያ ሚነስቴር እያካሄደ ያለው #ሪፎርም በተጠናከረ ሁኔታ ቀጥሏል፡፡ የተጀመረውን ሪፎርም ለማስቀጠልና በታሰበለት መልኩ ለማሳካት የሚያስችል ስልጠናም እየተሰጠ ይገኛል፡፡ ስልጠናው ሰራዊቱ ሪፎርሙን እውን በማድረግና የሪፎርሙን የአሰራር ስርዓት በማስቀጠል ወደፊት ለሚኖረው የግዳጅ አፈፃፃም ተልዕኮ ከፍተኛ አስተዋፅኦ እንደሚኖረው ታምኖበታል፡፡ የወታደራዊ አመራሩን አቅምን ለማሳደግ የታለመው ይኸው ስልጠና በሁሉም የሰራዊቱ ክፍሎች በመሰጠት ላይ የሚገኝ ሲሆን ከታክቲካል እስከ ኦፕሬሽናል አመራር እርከን ያሉ የሰራዊት አባላትን ያጠቃለለ ነው፡፡ በተጨማሪም ስልጠናው ሰራዊቱ ለህዝቡና ለህገ መንገስቱ ያለውን ታማኝነት በፅናት የሚያረጋግጥበትን አቅም ከፍ የሚያደርግና የሪፎርሙን ግቦች በማሳካት በኩልም ከፍተኛ ሚና እንደሚኖረው ታምኖበታል፡፡ ለስምንት ቀናት በሚቆየው በዚሁ ስልጠናም የተለያዩ ፅሁፎች ቀርበው ውይይት እየተደረገባቸው ይገኛል፡፡

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ውድ የTIKVAH-ETH ቤተሰብ አባላት፦

(የሰጣችሁት ገንዘብ ሳይሆን ለሀገራችሁ እና ለህዝባችሁ ያሳያችሁትን ክብር እና ፍቅር ትልቅ ነው)

ከሳምንታት በፊት በጌዴኦ ዞን የሚገኙ ተፈናቃዮች ችግር ላይ እንደወደቁ እና ትኩረት እንደሚያስፈልጋቸው የዲላ ወጣቶች በነገሩን መሰረት የበኩላችችን ድጋፍ ለማድረግ እንደተንቀሳቀስን ይታወቃል።

በወቅቱ ተፈናቃዮች አሉበት የተባለውን አካባቢ በአካል ሄደው የጎበኙ የtikvah-eth ቤተሰብ አባላት ለተቸገሩት ዜጎች ምንም ትኩረት እንዳልተሰጠና አስቸኳይ ድጋፍ እንደሚያሰፈልጋቸው ገልፀው ነበር። ሀሳቡን እንደሰማንም በቤተሰባችን በኩል ሁኔታውን ለህዝብ ማዳረስ የችግሩን ስፋት ማስመልከት እንዲሁም የአቅማችንን ለማገዝ ሰርተናል።

በገንዘብ ለማሰባሰብ አቅደን የተነሳነውም በሶስት ዙር 500,000 ብር እንደነበር አይዘነጋም። በመጀመሪያው ምዕራፍ በ24 ሰዓት ውስጥ 100,000 ብር እናተው ሰጥታችኃል። በቀጣዮቹ ሁለት ቀናትም 60,000 ብር ለማግኘት ተችሏል። ከዚህ በኃላ በነበረው ሰፊ የህዝብ እንቅስቃሴ እና ተፈናቃዮችም ከፍተኛ ትኩረት በማግኘታቸው እንዲሁም በውጭ የሚገኙ ዜጎች ከፍተኛ መጠን ያለው ገንዘብ በማሰባሰባቸው ከምንም በላይ ሁሉም ወገኖቻችን ብሎ በማሰቡና በመቆርቆሩ የገንዘብ ማሰባሰቡን ስራ አቁመነዋል።

የተሰባሰበው ገንዘብ የት ደረሰ?

ከተሰበሰበው 160,000 ሺ ብር ውስጥ 100,000 ብር ከባንክ ወጥቶ ለተፈባቃዮች ድጋድ ተደርጓል። 60,000 ብር አሁንም በባንክ አለ(ለሌላ ድጋፍ በሚውልበት ሁኔታ ላይ ሁላችንም እንነጋገራለን)

100,000 ብሩ ወጥቶ የተፈፀሙ ግዢዎችን ከታች ባለው ወረቀት ሰፍሯል። እንያንዳንዷ ብር የት እንደገባችም በግልፅ ተቀምጧል!

በቀረው 60,000 ብር ደግሞ ሌሎች በችግር ላይ ያሉ ወገኖቻችን ለማገዝ ታስቧል። ገንዘቡ የናተው ስለሆነ ሀሳባችሁን ማካፈል ትችላላችሁ!

ከምንም በላይ አማራ፣ ኦሮሞ፣ ትግሬ፣ ወላይታ፣ ሲዳማ፣ ሱማሌ፣ ጋምቤላ....ሳንባባል ለመልካምነት መዝመታችን ሀገራችን ከኛ ገና ብዙ እንደምትጠብቅ ማሳያ ነው።

ሁላችሁንም ላደረጋችሁት ነገር ፈጣሪ ያክብራችሁ!

ግዢውን ተመልከቱ👇👇
#TIKVAH_ETH🔝ያዋጣችሁት ገንዘብ ምን ላይ እንደዋለ #የሚያሳይ መረጃ (ግዢ ተፈፀመበት ደረሰኝም ጭምር)👆ላደረጋችሁት ነገር ሁሉ ፈጣሪ #ያክብራችሁ፤ ረጅም እድሜና ጤናን ይስጣችሁ! #ኢትዮጵያ #ጌዴኦ

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#FREE_NAZRAWIT_ABERA🔝

#የጎንደር_ወጣቶች ጋርድ ማህበር ጎንደር ላይ ፍትህ ለናዝራዊት ይላል!! #ናዝራዊት

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update የኦሮሞ ዴሞክራቲክ ፓርቲ (ኦዲፒ) ማእከላዊ ኮሚቴ በዶክተር ወርቅነህ ገበየሁ ምትክ አቶ ኡመር ሁሴንን የፓርቲው ስራ አስፈፃሚ አባል አድርጎ መረጠ።

የኦዲፒ ማእከላዊ ኮሚቴ ለሶስት ቀናት ሲያካሂድ የነበረውን ስብሰባውን በዛሬው እለት አጠናቋል።

የኦዲፒ ማእከላዊ ጽህፈት ቤት ሃላፊ ዶክተር አለሙ ስሜ ስብሰባውንብ በማስመልከት በሰጡት መግለጫ፥ የማእከላዊ ኮሚቴ ስብሰባው የተለያዩ ውሳኔዎችንና ምትክ የስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባል በመምረጥ መጠናቀቁን አስታውቀዋል።

በዚህም መሰረት የኦዲፒ ማእከላዊ ኮሚቴ በስራ ምክንያት ከፓርቲው ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባልነት በለቀቁት ዶክተር ወርቅነህ ገበየሁ ምትክ አቶ ኡመር ሁሴንን የስራ አስፈፃሚ አባል አድርጎ መምረጡን አስታውቀዋል።

በዚሁ መሰረት የኦዲፒ ስራ አስፈፃሚ አባላትም፦

1 ዶክተር አብይ አህመድ

2 አቶ ለማ መገርሳ

3 አቶ ኡመር ሁሴን

4 ዶክተር አለሙ ስሜ

5 አቶ ሽመልስ አብዲሳ

6 አቶ አዲሱ አረጋ

7 ወይዘሮ አዳነች አቤቤ

8 አቶ ፍቃዱ ተሰማ

9 አቶ ፀብርሃኑ ፀጋዬ መሆናቸውን የፅህፈት ቤት ሀላፊው በመግለጫቸው አስታውቀዋል።

የኢፌዴሪ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዶክተር ወርቅነህ ገበየሁ በቅርቡ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ረዳት ዋና ጸሀፊ ሆነው መሾማቸው ይታወሳል።

በዚሁ መሰረት ዶክተር ወርቅነህ ገበየሁ መቀመጫውን ኬንያ ናይሮቢ ያደረገውን የተመድ ዋና ጽህፈት ቤት የመምራት እና የማስተባበር ሃላፊነት ተሰጥቷቸዋል።

Via FBC
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update የኦሮሞ ዴሞክራቲክ ፓርቲ (ኦዲፒ) ማእከላዊ ኮሚቴ ላለፉት 3 ቀናት ሲያካሂድ የነበረውን ግምገማ አጠናቋል። #ODP #ኦዴፓ

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update 6 ተቃዋሚ የፖለቲካ ድርጅቶች አንድ ሀገራዊ ፓርቲ ለመቋቋም እየሰራን ነው ብለዋል ዛሬ በጋራ በሰጡት መግለጫ፡፡ ድርጅቶቹ አርበኞች ግንቦት 7፣ መኢአድ፣ ኢዴፓ፣ ሰማያዊ፣ የጋምቤላ ክልላዊ ንቅነቄና የቀድሞ የአንድነት ፓርቲ አመራሮችና አባላት መሆናቸውን ኢዲስ ስታንዳርድ ዘግቧል፡፡ የሚቋቋመው ፓርቲ ለማኅበራዊ ፍትህ የሚታገል፣ የዜግነት ፖለቲካን መሠረት ያደረገ እንደሚሆንም ተገልጧል፡፡ ውህደቱን እውን ለማድረግም የተለያዩ ግብረ ሃይሎች ተቋቁመዋል፡፡ ፓርቲው በመጭው ግንቦት 1 በይፋ እንደሚመሠረት ይጠበቃል፡፡

Via አዲስ ስታንዳርድ(በዋዜማ)
@tsegabwolde @tikvahethiopia