TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.5K photos
1.43K videos
206 files
3.96K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#update አዲስ አበባ ከአንዳንድ አካባቢዎች በስተቀር ፖሊስ ሁኔታዎችን እየተቆጣጠረ ይገኛል። ውጥረት በነበረባቸው አካባቢዎች የንግድ እንቅስቃሴ ቆሟል።

▪️ከሰዓታት በፊት ጠ/ሚ ዶ/ር አብይ አህመድ ሰው #እንዲረጋጋ እና ችግሮችን በንግግር እና በፍቅር እንዲፈታ ጥሪ አቅርበዋል።

በሌላ በኩል⬇️

የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር #ዘይኑ_ጀማል ተቋማቸው የህዝቡን ፀጥታ እና ሰላም ለማስጠበቅ አስፈላጊውን #እርምጃ ሊወስድ እንደሚችል ጠቁመዋል። ቅዳሜ ወደ ሀገር የሚገቡትን የኦነግ አመራሮች ለመቀበል የፀጥታ ተቋሙ በቂ ዝግጅት ማድረጉም ገልፀዋል።

@tsegabwolde @tikvhethiopia
#update ፌደራል ፖሊስ-አልታገስም አለ⬆️

ወደ ሀገር ቤት የሚገቡ የድርጅት አመራሮችን ለመቀበል በሚደረግ ቅድመ ዝግጅት ላይ በወጣቶች መካከል እየተፈጠረ ያለውን ግጭትና ህገወጥ ተግባር ከዚህ በኋላ #እንደማይትገስ የፌደራል ፖሊስ አስታወቀ።

የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ጀነራል ዘይኑ ጀማል ከአርበኞች ግንቦት 7 ንቅናቄ ሊቀመንበር ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ እና ከኦሮሞ ነጻነት ግንባር የስራ አስፈጻሚ አባል አቶ ኢብሳ ነገዎ ጋር በመሆን መግለጫ ሰጥተዋል።

በመግለጫው ላይም ኮሚሽነር #ዘይኑ_ጀማል፥ በትናንትናው እለት እና ዛሬ ወደ ሀገር ቤት የሚገቡ የድርጅት አመራሮችን ለመቀበል በሚደረግ ቅድመ ዝግጅት ላይ በወጣቶች መካከል ግጭት መፈጠሩን አስታውቀዋል።

በአቶ ዳውድ ኢብሳ የሚመራውን #የኦነግ ቡድን ለመቀበል እየተደረገ ባለ ቅድመ ዝግጅት ወቅት ወጣቶች የድርጅቱን አርማ ለመስቀል ዝግጅት እያደረጉ ነበር፤ ይህንን የከለከላቸው አካል የለም ያሉት ኮሚሽነር ዘይኑ፥ ሆኖም ግን አስፋልትን ጨምሮ የተለያዩ ተቋማትን እንዳያቀልሙ ተከልክው፤ ይህንንም ተወያይተን እሺ ብለው ተቀብለው ትተው ነበር ብለዋል።

ሆኖም ግን ማንም ያልፈቀደላቸው አካላት የእነሱን ባንዲራ አውርደው የሌላ ለመስቀል ሲሉ ግጭት ተፈጥሯል ሲሉም ገልፀዋል።

ግጭቱ ለማንም ጠቃሚ አይደለም ያሉት ኮሚሽነር ዘይኑ፥ ችግሩን #በውይይት መፍታት ሲቻል ወደ አላስፈላጊ ግጭት መግባት ተገቢ አይደለም ሲሉም ተናግረዋል።

ፖሊስ የህግ የበላይነትን የማስከበር ሀላፊነት ስላለበት ከዚህ በኋ እንዲህ አይነት #ግጭቶችን በትእግስት እንደማያልፍም ኮሚሽነር ዘይኑ አሳስበዋል።

የአርበኞች ግንቦት ሰባት ንቅናቄ ሊቀመንበር ፕሮፌሰር #ብርሃኑ_ነጋ፥ የዴሞክራሲ ስርዓትን እንገንባ ብለን ስንሰና ስርዓቱን ለመገንባት የሚያስፈልግ እነዚህን ባህሪያትን ተቀብለን ካልተነሳን ግን ስርዓቱን መገንባት እንችልም ብለዋል።

የዴሞክራሲ ስርዓት ግንባታ ውስጥ ልዩነቶችን መቀበል የግድ ነው ያሉት ፕሮፌሰር ብርሃኑ፥ ልዩነቶቹ ደግሞ ሀሳቦችን፣ አርማዎችን እና ባንዲራዎችን ሊያጠቃልል ይችላል ብለዋል።

ትናንትና እና ዛሬ በአዲስ አበባ የተስተዋሉ ችግሮች ደግሞ ከዚህ ጋር የሚፃረሩ ነው ያሉት ፕሮፌሰር ብርሃኑ፥ ማንኛውም አካል ስሜቴን ይገልፅልኛል ያለውን አርማ የመያዝ እና የማውለብለብ #መብት አለው ሲሉም ተናግረዋል።

የኦሮሞ ነጻነት ግንባር የስራ አስፈጻሚ አባል አቶ #ኢብሳ_ነገዎ በበኩላቸው፥ ሰሞኑን በአዲስ አበባ እና አካባቢዋ የተስተዋለው ችግር #ተቀባይነት የሌለው መሆኑን አንስተዋል።

ወጣቱም ከዚህ አይነት እንቅስቃሴዎች ሊቆጠብ እንደሚገባም አቶ ኢብሳ ጥሪ አስተላልፈዋል።

አሁን ላይ እየታየ ያለው ግጭት እና ያልተገባ #ፉክክር ድርጅታቸውን የማይወክል መሆኑንም ነው አቶ ኢንብሳ ተናግረዋል።

©Fbc
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update ኮሚሽነር ዘይኑ⬆️

በዛሬው ዕለት 240 የሚሆኑ የመብት ጥያቄ ያላቸው የመከላከያ ሠራዊት አባላት ከእነ ትጥቃቸው ወደ ቤተ መንግሥት በማምራታቸው ተፈጥሮ የነበረው መደናገጥ መረጋጋቱን የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር #ዘይኑ_ጀማል ለአሜሪካ ድምፅ ገለፁ።

ወታደሮቹ ከሃዋሳ የቡራዩን ጉዳይ ለማብረድ የተጠሩ መሆናቸውንና ግዳጃቸውን ጨርሰው ወደ ምደባ ቦታቸው በሚመለሱበት ጊዜ “ዶ/ር *አብይ ነው ችግራችንን የሚፈታው” በሚል ወደ ቤተመንግስቱ በቀጥታ ማምራታቸውን ኮሚሽነር ገልፀዋል።

በመጨረሻም #ትጥቃቸውን ፈተው ከጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አሕመድ ጋር #ውይይት አድርገዋል ተበሏል። ወታደሮቹ ዓላማቸው ምን እንደሆነ እስኪታወቅ ድረስም ሌላ ኃይል ተጠርቶ አካባቢው በጥበቃ ስር እንደነበር ተናግረዋል።

ምንጭ፦ VOA(የአማርኛው አገልግሎት)
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update "ስለ አዲስ አበባ ዝም አንልም" በሚል የአዲስ አበባ ወጣቶች ከጦላይ እዲለቀቁ የ3 ቀን የማህበራዊ ሚዲያ ዘመቻ እየተካሄደ እንደሆነ ለማየት ተችሏል። ባለፈው ሳምንት የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር #ዘይኑ_ጀማል ጦላይ የተላኩት ወጣቶች "እያሰለጠናቸው" እንገኛለን በቀናት ውስጥ ይፈታሉ ብለው ለሚዲያ ተናግረው ነበር። ወጣቶቹ እስካሁኗ ሰዓት ድረስ ከጦላይ እንዳልተለቀቁ ለማወቅ ተችሏል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update የአዲስ አበባ ወጣቶች ከጦላይ እዲለቀቁ የ3 ቀን የማህበራዊ ሚዲያ ዘመቻ እየተካሄደ ይታወቃል። ዘመቻው ዛሬ ለሁለተኛ ቀን ቀጥሏል። ባለፈው ሳምንት የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር #ዘይኑ_ጀማል ጦላይ የተላኩት ወጣቶች "እያሰለጠናቸው" እንገኛለን በቀናት ውስጥ ይፈታሉ ብለው ለሚዲያ ተናግረው ነበር። ወጣቶቹ እስካሁኗ ሰዓት ድረስ ከጦላይ እንዳልተለቀቁ ለማወቅ ተችሏል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ወጣቶቹ ሀሙስ ይለቀቃሉ⬆️

ከአዲስ አበባ ከተማ የተለያዩ ቦታዎች ተይዘው ወደ ጦላይ ወታደራዊ ማሰልጠኛ የነበሩ 1 ሺሕ 204 ወጣቶች ከነገ በስቲያ ሐሙስ #እንደሚለቀቁ የፌደራል ፖሊስ አስታውቋል።

የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር #ዘይኑ_ጀማል ለአሜሪካ ድምፅ እንደተናገሩት፤ ወጣቶቹ ከመስከረም 2 እስከ 8/2011 በአዲስ አበባ ከተማ በነበረው ብጥብጥ ተሳትፎ የነበራቸው እንደሆኑ ገልፀው፤ ጦላይ በነበራቸው ቆይታ የሕግ የበላይነትና የሰላም አስፈላጊነት ላይ ስልጠና ተሰጥቷቸዋል ብለዋል። ከትናንት ጀመሮ የወጣቶቹ እስር ከሕግ ውጪ መሆኑን በመግለፅ እንዲለቀቁ የሚወተውት የሦስት ቀን ዘመቻ በማኅበራዊ ሚዲያ እየተካሄደ ነበር።

ምንጭ፦ የአሜሪካ ድምፅ ራድዮ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
አቶ እንደሻው ጣሰው‼️

አቶ #እንደሻው_ጣሰው የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ሆነው ተሾሙ። አቶ #ዘይኑ_ጀማል የሰላም ሚኒስትር ሚኒስትር ዴኤታ ሆነው መሾማቸውን ተከትሎ የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ሆነው የተሾሙት።

አቶ እንደሻው ጣሰው ማናቸው??

ከ1983 ጀምሮ በሀገር መከላከያ ሚኒስቴር ከመምህርነት እስከ ክፍለ ጦር አመራርነት በትምህርቱ ዘርፍ እስከ 1992 ድረስ አገልግለዋል።

ከመከላከያ በኋላ በአዲስ አበባ የተለያዪ የሃላፊነት ቦታዎች ከወረዳ ጀምሮ እስከ ከተማ ድረስ በትጋት የህዝብንና የመንግስትን ሃላፊነት ሲወጡ የቆዪ ሲሆን አቶ እንደሻው በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በቦሌ ክፍለ ከተማ በምክትል አስተዳዳሪ ማዕረግ የዴሞክራሲ ግንባታ
ማስተባበሪያ ማስተባበሪያ ማዕከል ዋና አስተባባሪ፣ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የከንቲባው የህዝብ ግንኙነት አማካሪ እና የአዲስ አበባ ከተማ ትምህርት ቢሮ ሃላፊ ሆነው ያገለገሉ ሲሆን በሰሩባቸው ቦታዎች ውጤታማ መሆናቸውን ያስመሰከሩ ሰው ናቸው።

አቶ እንደሻው የመጀመሪያ ዲግሪያቸውን በጅማ ዩኒቨርሲቲ፤ ሁለተኛ ዲግሪያቸውን ደግሞ ከሐገር ውጭ ተከታትለው በከፍተኛ ውጤት ያጠናቀቁ ናቸው፡፡

ምንጭ፦ EPRDF
@tsegabwolde @tikvahethiopia
አፋር🕊ሱማሌ!!

ሰሞኑን በአፋርና ሶማሌ ክልሎች አዋሳኝ አካባቢዎች ተፈጥሮ የነበረውን #ግጭት ለመፍታት የሁለቱ ክልሎች የሃይማኖት መሪዎችና የሀገር ሽማግሌዎች #ተስማሙ

በቅርቡ በሁለቱ ክልሎች የተፈጠረውን ግጭት ተከትሎ የሁለቱ ክልሎች የሃይማኖት አባቶች፣ የሀገር ሽማግሌዎች፣ የሰላም ሚኒስቴር ዴኤታና ባለድርሻ አካላት የተሳተፉበት የውይይት መድረክ ተካሂዷል።

በውይይቱም የተፈጠረውን ግጭት  ለመፍታት የሁለቱ ክልሎች የሃይማኖት መሪዎችና የሃገር ሽማግሌዎች መስማማታቸው ነው የተገለፀው።

ከዚህ ባሻገርም የተፈጠረውን ግጭት  መንስኤ ለማጣራትና ግጭቱ ዳግም እንዳይከሰት ለማድረግ ከሁለቱ ክልሎች  የተውጣጣ የጋራ ኮቴ ተቋቁሟል።

በውይይቱ ላይ ንግግር ያደረጉት ኡስታዝ አቡበክር ሁለቱ ህዝቦች በሃይማኖት በባህል እና በጋብቻ ተሳስረው የኖሩ በመሆናቸው በመካከላቸው መሰል ግጭት መፈጠሩ አግባብ አለመሆኑን ተናግረዋል።

ስለሆነም የሁለቱ ክልሎች የሃይማኖት አባቶችና የሀገር ሽማግሌዎች በቀጣይ ምንም ዓይነት ግጭት እንዳይከሰትና ሰላምና ለማውረድ መስማማታቸውን ገልፀዋል።

ስለሆነም የሃይማኖት አባቶችና የሀገር ሽማግሌዎች ከስምምነት ባሻገር ወደ ህብረተሰቡ ወርደው ለጋራ  ሰላም መስራት እንደሚገባቸው አሳስበዋል።

የሰላም ሚኒስቴር ዴኤታ አቶ #ዘይኑ_ጀማል በበኩላቸው መንግስት በአካባቢው ግጭት ከተከሰተበት ጊዜ አንስቶ የተለያዩ ስራዎችን እየሰራ መሆኑን አስታውቀዋል።

በዚህ መሰረትም ከሁለቱ ክልሎች ርዕሰ መስተዳድሮች እና የፀጥታ አካላት ጋር ውይይት በማድረግ የጋራ ግብረ ኃይል ተቋቁሞ የግጭቱን መንስኤ ለማጣራት እና ዳግም እናዳይከሰት ለማድረግ እየተሰራ መሆኑን አንስተዋል።

ከዚህ ባለፈም መንግስት በአካባቢው ሰላምን ለማስፈን ለሚሰራው ስራ የሃይማኖት አባቶች እና የሀገር ሽማግሌዎች ድርሻ ከፍተኛ መሆኑን  ጠቁመዋል።

ምንጭ፦ fbc
@tsegabwolde @tikvahethiopia
በጅግጅጋ በተከሰተ #ግጭት ሁለት ሰዎች ተገደሉ‼️
.
.

ትናንት በሶማሌ ክልል መዲና- ጅግጅጋ የሃይማኖት ክብረ በዓልን ተከትሎ በተፈጠረ ግጭት ሁለት ሰዎች መገደላቸው ተነገረ።

የከተማዋ ነዋሪዎች የኦርቶዶክስ ዕምነት ተከታይ የሆኑ የጂግጂጋ ከተማ ነዋሪዎች የአስተርዮ ማርያም ክብረ በዓልን ከጂግጂጋ ከተማ 35 ኪ.ሜ ርቀት ላይ በምትገኘው ጉርሱም ወረዳ አክብረው ወደ ከተማው ሲመለሱ በተደራጁ ወጣቶች በድንጋይ መደብደባቸውን ነግረውናል።

በስፍራው የሚገኘው የቢቢሲ ሶማልኛ ጋዜጠኛም ሁለት ሰዎች መገደላቸውን እና አራት ሰዎች ደግሞ ለጉዳት መዳረጋቸውን ዘግቧል።

የበዓሉ ተሳታፊ የነበሩ አንድ የሃይማኖት አባት "ከቤተክርስቲያን መልስ ከተማው መግቢያ ላይ የተደራጁ ወጣቶች ድንጋይ በመወርወር ሰዎች ፈነከቱ፤ መኪኖችንም ሰባበሩ" ብለዋል።

የሃይማኖት አባቱ እንደሚሉት በጥይት ተመትተው የሞቱት ሁለቱ ሰዎች የኦርቶዶክስ ዕምነት ተከታዮች ናቸው፤ ግጭቱን ለመበተን ከመጡ የጸጥታ አስከባሪዎች ጋር በተከሰተ ግጭት ሁለቱ ሰዎች መገደላቸውንም አስረድተዋል።

ሌላው BBC ያነጋገራቸው የጂግጂጋ ዩኒቨርሲቲ መምህር ትናንት ከአዲስ አበባ ወደ ጂግጂጋ እየተመለሱ እንደነበረ በማስታወስ ትናንት አመሻሽ ላይ ሐረር ከተማ ሲደርሱ ወደ ጂግጂጋ ከተማ ዘልቀው መግባት እንደማይችሉ ከተነገራቸው በኋላ ሐረር ከተማ ለማደር መገደዳቸውን ይናገራሉ።

የዩኒቨርሲቲ መምህሩ እንደሚሉት ዛሬ ጠዋት ወደ ጂግጂጋ እንደተመለሱ እና ከተማዋ ላይ የተለመደው ዓይነት እንቅስቃሴ እንደሌለ ይናገራሉ።

የሃይማኖት አባቱ በበኩላቸው በከፊል መንገዶች ዝግ እንደሆኑ እና የመኪና እና የንግድ እንቅስቃሴ በከተማዋ አይታይም ብለዋል።

የግጭቱ መንስኤ እና ጥቃቱ እንዴት እንደተፈጸም እንዲያስረዱን በስልክ የጠየቅናቸው የኮሚኒኬሽን ቢሮ ኃላፊው አብዱላሂ ሞሃመድ መውሊድ ''ጉዳዩን እያጣራን ስለሆነ አሁን አስተያየት መስጠት አልችልም'' የሚል ምላሽ ሰጥተዋል።

ከዚህ ቀደም በጂግጂጋ ተከስቶ ለነበረው ሃይማኖት ተኮር ግጭት መንግሥት 'ሄጎ' ተብሎ የሚጠራውን ቡድን ተጠያቂ አድርጎ ነበር።

ሐምሌ 27፣ 2010 ዓ. ም. ጂግጂጋን ጨምሮ በክልሉ የተለያዩ ከተሞች 96 ሰዎች መሞታቸውን እና ለግድያውም 'ሄጎ' የተባለው ቡድን ተጠያቂ እንደሆነ በወቅቱ የፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ጄኔራል የነበሩት #ዘይኑ_ጀማል ለቢቢሲ ገልጸው ነበር።

የቀድሞ የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽነር ሄጎ የሚባለውን ቡድን የፈጠሩትና እቅዱን ያቀነባበሩት የቀድሞ የክልሉ ከፍተኛ የመንግሥት ባለስልጣናት ናቸው ብለው ነበር።

ምንጭ፦ bbc
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update በአፋር እና በሱማሌ ክልሎች #አዋሳኝ አካባቢዎች ምንም አይነት የፀጥታ ችግር እንዳይከሰት እንደሚሰሩ የሁለቱ ክልል ከፍተኛ ርዕሰ መሰተዳደሮች ገለፁ፡፡

የሱማሌ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አቶ #ሙስጠፋ_መሀመድ እና የአፋር ክልል ርዕሰ መሰተዳደር አቶ #አወል_አርባ ዛሬ በአዲስ አበባ በሁለቱ ክልሎች የፀጥታ ችግር መፍትሄ ዙሪያ ላይ ተወያይተዋል፡፡ በውይይታቸውም በሁለቱ ክልል አዋሳኝ ቦታዎች አንድም ሰው እንዳይሞት እና ግጭት እንዳይከሰት የማድረግ ሰራ እንደሚሰሩ ተናግረዋል፡፡

የሰላም ሚኒስትር ዲኤታው አቶ #ዘይኑ_ጀማል በበኩላቸው ችግር በተፈጠረባቸው አካባቢዎች በአስቸኳይ የሀገር ሽማግሌዎች ቡድን እንዲቋቋምና ችግሩ በዘላቂነት ሊፈታ እደሚገባው ተናግረዋል፡፡ በአጠቃላይ ጉዳይ ላይም በህዝብ ለህዝብ #ውይይት ሊፈታ እንደሚገባ ተናግረዋል፡፡ ክልሎቹ #ከማንነት እና #ከወሰን ጋር ያሉ ችግሮችን ዘላቂ መፍትሄ እንዲያገኙ እንደሚሰሩ ተናግረዋል፡፡

Via ebc
@tsegabwolde @tikvahethiopia