TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.5K photos
1.43K videos
206 files
3.96K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
አያቴን አፋልጉኝ⬆️

"አንድ አያት ነበረኝ የእናቴ አባት #አስመራ ነው የሚኖረው እና ከእናቴ ጋር ከተለያዩ 20 አመት አለፈ እና አሁን የኤርትራ እና የኢትዮጵያን መስማማት ስሰማ በጣም ነው ደስ ያለኝ እና አያቴን ያገኘሁ ያህል የተስማኝ እስቲፋኖስ ኢስሀቅ ይባላል ምን አልባት የሚየውቀው ካለ አድራሻ ቢጠቁመኝ ምስጋናዪ ወደር የለውም። ስልክ +251913736922"

@tsegabwolde @tikvahethiopia
አፋልጉን⬆️2ኛ አቢዮታዊ ሰራዊት 30 ኛ መካናይዝድ ብርጌድ 3ኛ መደፈኛ ሻለቃ የነበረው አቶ ጥላሁን ቦንገር አስመራ በነበረበት ጊዜ ልጅ እንዳለው ለቤተሰቦቹ ተናግሮ ነበር። አሁን አባታችን በህይወት ባይኖርም በኢትዮጵያ እና በ ኤርትራ በየተፈጠረው ሰላም እህታችንን ለመፈለግ ጥሩ አጋጣሚ ተፈጥሮልናል። #አስመራ አካባቢ ያላቹሁ እህታችንን እንድታፋልጉን በአክብሮት እጠይቃለን።

ፈላጊ፦ የአቶ ጥላሁን ቦንገር ልጆች
0913073414
0911372002
0913342037
0912168281

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update ምፅዋ ወደብ⬆️

የኢትዮጵያ የንግድ መርከብ ዛሬ #ምጽዋ ወደብ ላይ መልህቋን ጥላለች፡፡ የንግድ መርከቧ መልህቋን የጣለችው ከሁለት አስርት ዓመታት በኋላ ነው ተብሏል፡፡

የንግድ መርከቧ 11 ሺህ ቶን ዚንክ በመጫን ወደ ቻይና እንደምታቀናም ይጠበቃል፡፡ ወደ ምጽዋ ያቀናችው የንግድ መርከብ “መቐለ” ተብላ የምትጠራ መሆኗም ተገልጿል፡፡

ኢትዮጵያና ኤርትራ የሰላምና የወዳጅነት ስምምነት ካደረጉ በኋላ አዲስ የግንኙነት ምእራፍ ውስጥ ገብተዋል፡፡

ከዚህ ቀደምም የሁለቱ ሀገራት የህዝብ ለህዝብ ቡድኖች ወደ አዲስ አበባ እና #አስመራ ማቅናታቸው ይታወሳል፡፡

እንዲሁም በአስመራና በአዲስ አበባ መካከል የንግድ የአየር ትራንስፖርት በይፋ ተጀምሯል፡፡

©fbc
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update ቡሬ-ድባይ ድንበር⬇️

የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር #አብይ_አህመድ እና የኤርትራው ፕሬዚዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ የቡሬ – ድባይ ሲማ ድንበርን በይፋ ከፈቱ፡፡

ሁለቱ መሪዎች አዲስ ዓመትን ምክንት በማድረግ ነው ድንበሩን በይፋ የከፈቱት ተብሏል፡፡

የድንበሩ መከፈት በሁለቱ ሀገራት መካከል ለዓመታት ተቋርጦ የነበረውን የየብስ #ትራንስፖርት ግንኙነት ዳግም እንዲጀምር ያስችለዋል፡፡

ከድንበሩ መከፈት በኋላም ሁለቱ መሪዎች ወደ #አስመራ ማቅናታቸው ተገልጿል፡፡

የአስመራ ቆታቸውን እንዳጠናቀቁ ደግሞ ወደ ዛላምበሳ በማቅናት በተመሳሳይ በሁለቱ ሀገራት መካከል ለዓመታት ተዘግቶ የቆየውን ድንበር በይፋ እንደሚከፍቱ ከኤርትራ የማስታወቂያ ሚኒስትር የማነ ገብረመስቀል በትዊተር ገፃቸው ገልፀዋል።

©fbc
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update አስመራ⬆️

የኢትዮጵያ መንግሥት ባለሥልጣናት እና የኦጋዴን ነፃ አውጪ ግንባር (ኦብነግ) አመራሮች በኤርትራ ዋና ከተማ #አስመራ ተገናኝተው ተወያይተዋል። በውይይቱ የኢትዮጵያ መንግሥትን በመወከል የኮምዩንኬሽን ጉዳዮች ፅሕፈት ቤት ኃላፊ እና የሶሕዴፓ ሊቀ-መንበር በሆኑት አቶ አሕመድ ሽዴ የተመራ የልዑካን ቡድን ተገኝቷል። የሶማሌ ክልል ፕሬዝዳንት አቶ ሙስጠፋ ኡመር ከልዑካን ቡድኑ አባላት መካከል ይገኙበታል። የኦብነግን ልዑካን ቡድን የመሩት ሊቀመንበሩ አድሚራል ሞሐመድ ኦማር ናቸው። ከመግባባት ላይ የደረሱባቸው የውይይት ርዕሰ-ጉዳዮች በቅርቡ እንደሚጠናቀቁ የኤርትራ የኢንፎርሜሽን ሚኒስትር አቶ የማነ ገብረ-መስቀል በትዊተር ገፃቸው ገልጸዋል።

©ShegerTribune
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#UpdateSport በኤርትራ ዋና ከተማ #አስመራ ሲካሄድ የቆየው የአፍሪካ ብስክሌት ዋንጫ ውድድር ትላንት ተጠናቋል። የኢትዮጵያ የብስክሌት ቡድን ከአፍሪካ 3ኛ ደረጃን በመያዝ ውድድሩን አጠናቋል።

ምንጭ፦ EPA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ እና የኬንያው ፕሬዚዳንት ኡሁሩ ኬንያታ ዛሬ ጥዋት ኤርትራ #አስመራ ገብተዋል። መሪዎቹ አስመራ አለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱም የሀገሪቱ ፕሬዚዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ አቀባበል አድርገውላቸዋል።

Via fbc
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update ከጅዳ ወደ አዲስ አበባ በመጓዝ ላይ የነበረ የሳዑዲ አየር መንገድ አውሮፕላን በአንዲት መንገደኛ ድንገተኛ ምጥ ምክንያት በኤርትራ ዋና ከተማ #አስመራ አረፈ። ጀነቲ ሑሴን ከጅዳ ወደ አዲስ አበባ ስትጓዝ የስምንት ወር እርጉዝ እንደነበረች በአስመራ የሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ አስታውቋል። ጀነቲ ባለፈው ቅዳሜ በጉዞ ላይ ሳለች ከጠዋቱ 1 ሰዓት ከ15 ደቂቃ ምጥ ሲጀምራት ከአዲስ አበባ በመብረር ላይ የነበረው የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከኤርትራ የአየር ተቆጣጣሪዎች ጋር በመነጋገር አስመራ ማረፉን የኢትዮጵያ ኤምባሲ አስታውቋል። ኤምባሲው "አውሮፕላኑ እንዳረፈ የኤርትራ ጤና ጥበቃ አምቡላንስ በምጥ ስትሰቃይ የነበረችው ጀነቲ ሁሴንን በፍጥነት በአስመራ ከተማ ትልቁ ወደሆነው ኦሮታ ሪፈራል ሆስፒታል ወስደዋት በኤርትራውያን አዋላጅ ሀኪሞች እርዳታ ሁለት ሴት መንታ ልጆችን በሰላም ተገላገለች" ሲል ኹኔታውን አብራርቷል። ጊዜያቸው ሳይደርስ የተወለዱ የጀነቲ ልጆች በአስመራ ከተማ በሚገኘው የኦሮታ ሪፈራል ሆስፒታል ክትትል እየተደረገላቸው ይገኛል። የኢትዮጵያ ኤምባሲ ከሕክምና ባለሙያዎች አገኘሁ ባለው መረጃ መሰረት መንታዎቹ ልጆች እስከ መጪው ሐሙስ ክትትል እየተደረገላቸው ይቆያሉ።

ምንጭ፦ የጀርመን ራድዮ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#አስመራ

በኤርትራ ጉብኝት እያደረጉ ያሉት የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ ከሀገሪቱ ፕሬዚዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ ጋር ተወያዩ።

መሪዎቹ በሁለቱ ሀገራት መካከል እየተከናወነ ያለውን ዘላቂ ሰላም የማስፈን ሂደትን ማጠናከር በሚቻልበት ሁኔታ ላይ መምከራቸውን ነው የኤርትራ የማስታወቂያ ሚኒስትሩ አቶ የማነ ገብረመስቀል በትዊተር ገፃቸው ያስታወቁት።

በተጨማሪም የዛሬ ዓመት ሁለቱ ሀገራት በተፈራረሙት ባለ አምስት ነጥብ የሰላም እና የትብብር ስምምነት መሰረት ሁሉን አቀፍ ትብብር ማድረግ በሚችሉበት ዙሪያም ተወያይተዋል።

መሪዎቹ አወንታዊ ለውጥ እየታየበት ያለውን የሀገራቱን ግኑኝነት እና በአፍሪካ ቀንድ ሰላም የማስፈን ጥረትን የበለጠ ለማስፋት ተስማምተዋል።

በመጨረሻም በጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ የተመራው ልዑክ ከፕሬዚዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ ጋር በመሆን የተለያዩ የልማት ፕሮጀክቶችን ጎብኝቷል።

Via #EPA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#EthiopianAirlines

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ' ሙሉ በሙሉ ' የኮቪድ-19 ክትባት በወሰዱ ሰራተኞች በረራ ማድረግ መጀመሩን ዛሬ አሳውቋል።

የአየር መንገዱ ዋና ሥራ አስፈፃሚ የሆኑት አቶ ተወልደ ገብረማርያም ፥ በረራዎችን ሙሉ በሙሉ ክትባት በወሰዱ ሠራተኞች በማድረጋችን ተደስተናል ብለዋል።

አክለውም ፥ "ይህንን ማድረጋችን የሰራተኞቻችንን እና የደንበኞቻችንን የጤና ደህንነት በመጠበቅ ረገድ ትልቅ እርምጃ ነው" ሲሉ ገልፀዋል።

አቶ ተወልደ፥ በመላው ዓለም በኮቪድ-19 ክትባት በመተማመን ለንግድ ፣ ለቪኤፍአር እና ለቱሪዝም የሚጓዙ መንገደኞች ቁጥር እየጨመረ በመሄዱ ተበረታተናል ብለዋል።

አየር መንገዱ ለሰራተኞቹ እንዲሁም ለባለድርሻ አካላቱ ከ37,000 በላይ የክትባቶችን ገዝቶ ማስገባቱን አቶ ተወልደ አሳውቀዋል።

በሌላ የኢትዮጵያ አየር መንገድ መረጃ ፦ ወደ ኤርትራ #አስመራ ተቋርጦ የነበረው የመንገደኞች የበረራ አገልግሎት ከዛሬ ሰኔ 16 ቀን 2013 ጀምሮ የሚቀጥል መሆኑን አሳውቋል።

@tikvahethiopia