ኢትዮጵያን🇪🇹ትወዳታለህ?
እንግዲያዉስ ከጎንህ ላለዉ አንድ ሰዉ አንድነትንና ፍቅርን አስተምር፣ ጥቅሙን ተናገር! በአሁኑ ሰዓት ለኢትዮጵያ የምታደርግላት #ትልቁ ዉለታ ይህ ነዉ!!
#የንጋትብርሃን
@tsegabwolde @tikvahethiopia

ምዕራብ ጎንደር🕊
የምዕራብ ጎንደር ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ #አደባባይ_ሙሉጌታ ከአብመድ ጋር በነበራቸው ቆይታ ዞኑ ወደ #ተረጋጋ ሕይወት መመለሱንና ዘላቂ ሰላም ለማረጋገጥ እየተሠራ መሆኑን ተናግረዋል። የዞኑን ሕዝብ ዕድገት እና ተጠቃሚነት ከማረጋገጥ ይልቅ የራሳቸውን ጥቅም ለማስጠበቅ በማንነት ስም እየማሉና እየተገዘቱ ባሉ ጥቅመኞች የተሳሳተ አስተሳሰብ የተወለደ ግጭት ምክንያት የሰዎች ሕይወት ማለፉ፣ ንጹኃን ለጉዳት መዳረጋቸው፣ በርካታ ንብረቶች መውደማቸውና ሰዎች ቤት ንብረታቸውን አጥተው መፈናቀላቸው ትውልድ የማይዘነጋው የቅርብ ጊዜ ታሪክ መሆኑን ነው ዋና አስዳዳሪው ያስታወቁት።
በርካቶችም ለሰብዓዊ፣ ኢኮኖሚያዊ፣ አካላዊ እና ሥነ-ልቦናዊ ቀውስ መጋለጣቸውን ያብራሩት አቶ አደባባይ ‹‹ቁጥራቸው ቀላል የማይባሉ ከእርሻ ማሳቸው ርቀው ጉልበታቸውን አቅፈው በባይተዋርነት ተቀምጠዋል›› ነው ያሉት። ችግሩን ለመፍታት መንግሥትና ሕዝብ ከፀጥታ አካላት ጋር በመሆን እየሠሩ እንደሆነና በተሠራው የሰላም ማስከበር ተግባር በዞኑ አንጻራዊ ሰላም እንዲሰፍን ማድረግ መቻሉንም አብራርተዋል። በዞኑ ይስተዋላሉ የነበሩ ‹‹የግድያና እና ተደራጅቶ የመጠቃቃት፣ የመፈናቀል እና ሌሎች ወንጀሎችን ማስቆም ተችሏል›› ብለዋል።
ተዘግተው የነበሩ 12 ትምህርት ቤቶች፣ ሦስት የጤና እና ሁለት የሕግ አገልግሎት መስጫ ተቋማት ተከፍተው አገልግሎት እየሰጡ መሆኑንም ገልጸዋል። ከፍተኛ የስጋት ምንጭ የነበሩ ዋና ዋና መንገዶችም ከስጋት ነጻ ሆነው ሰላማዊ የትራንስፖርት አገልግሎት እየሰጡ እንደሆነ ተነግሯል።
በግጭቱ ወቅት ተዘርፎ የነበረ አምስት ሺህ የሚጠጋ የቤት ክዳን ቆርቆሮ፣ ከብቶች እና ሌሎች ንብረቶች ለባለቤቶቻቸው መመለሳቸውንም ዋና አስተዳዳሪው አስታውቀዋል። በዞኑ በተሠራው የሕግ ማስከበር ሥራ በግጭቱ ተሳትፈዋል ተብለው የተጠረጠሩ ግለሰቦችም በሕግ ቁጥጥር ስር ውለው ጉዳያቸው እየተጣራ መሆኑ ተነግሯል።
ማደኛ ወጥቶባቸው የነበሩ 46 ግለሰቦችና ሌሎች 68 እጅ ከፍንጅ የተያዙ ግለሰቦች በድምሩ 114 ግለሰቦች በሕግ ቁጥጥር ስር ውለው ጉዳያቸው እየተጣራ እንደሆነም ዋና አስተዳዳሪው አስታውቀዋል። ተጠርጣሪዎቹ ጉዳያቸው በሕግ አግባብ እየታዬ እንደሚገኝና ውሳኔም እንደ ጥፋታቸው ተሳትፎና እንደ ነፃነታቸው የሚወሰን እንደሆነ አስረድተዋል። የተፈናቀሉ ወገኖችን በቋሚነት በማቋቋም ሰላማዊ ኑሮ እንዲጀምሩ እየተሠራ መሆኑንም አስታውቀዋል። ከመላው የዞኑ ሕዝብ ከተውጣጡ የሀገር ሽማግሌዎች፣ የሃይማኖት አባቶች፣ ሴቶች እና ወጣቶች ጋር ውይይት መደረጉንና በውይይቱም መሠረት ሕዝቡ የሰላምን አስፈላጊነት በመረዳት እርቀሰላም እንዲወርድ መጠየቁን ለአብመድ ተናግረዋል።
በተወሰኑ አካባቢዎች በአማራ ብሔርና እና ቅማንት ማኅበረሰብ መካከል እርቀ ሰላም መውረዱን ያስታወቀት አቶ አደባባይ ‹‹የተፈናቀሉትን በዘላቂነት ወደ ቀያቸው ለመመለስ በዞኑ የሚገኙ
ሁሉንም የአማራንና የቅማንት ማኅበረሰብ ለማስታረቅ እየተሠራ ነው። ይህንን እርቅ ተግባራዊ ለማድረግ ከሁለቱ ወገን የሃይማኖት አባቶች፣ የሀገር ሽማግሌዎች፣ ወጣቶች፣ እናቶች እና ነዋሪዎች የተካተቱበት ኮሚቴ ተቋቁሟል›› ብለዋል።
ኅብረተሰቡን በቋሚነት ለማቋቋም ዞኑ 15 ሚሊዮን ብር ለመሰብሰብ አቅዶ እስከ ቀበሌ ድረስ እንቅስቃሴ እንደጀመረና ሕዝቡም ድጋፍ ለማድረግ ፍቃደኛነቱን እያሳየ መሆኑንም ዋና
አስተዳዳሪው አስታውቀዋል።
ምንጭ፦ አብመድ

#update በግንቢቹ ወረዳ ቱሉ ፈራ ቀበሌ ውስጥ በተከሰከሰው ቦይነግ 737 ማክስ 8 ህይወታቸው ላለፈው 157 ሰዎች የወረዳው አባ ገዳ ዎች እና የጨፌ ዶንሳ ከተማ ነዋሪወች ክተለያዩ የውጭ ሀገርልት ዜጎች ጋር በጋራ በመሆን በአከባቢው ላይ ችግኝ በመትከል ማስታወሻ አኑረዋል ያረፉትን ወንድሞቻችን እግዚአብሄር ነብሳቸውን በገነት ያኑርልን በማለት የተሰማቸውን ጥልቅ ሃዘን በመግለጽ በቦታውላይ ለሟቾች ምስታወሻ ይሚ ሆን ለመስራትም እየተወያዩ ነው።
@tsegabwolde @tikvahethiopi
@tsegabwolde @tikvahethiopi
#update ባለፈው አንድ ዓመት በሀገሪቱ ውስጥ የመጣውን ለውጥ ተከትሎ የተሰሩ ስራዎችና ያጋጠሙ ችግሮች ላይ ያተኮረ መድረክ በጠቅላይ ሚኒስትር ፅህፈት ቤት አዘጋጅነት በሸራተን አዲስ እየተካሄደ ነው፡፡
Via FBC
Photo:Elias Mesrest & fbc
@tsegabwolde @tikvahethiopia
Via FBC
Photo:Elias Mesrest & fbc
@tsegabwolde @tikvahethiopia
የኢትዮጵያ አየር መንገድ‼️
በኒውዮርክ ታይምስ እና በአንዳንድ ሌሎች የመገናኛ ብዙሃን እየወጣ ያለው የተሳሳተ እና የተዛባ ዘገባ የኢትዮጵያ አየር መንገድን ያሳዘነ መሆኑን አየገለፀ፤ ትክክለኛውን መረጃ እንደሚከተለው ያቀርባል።
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ቦይንግ 737 ማክስ አብራሪዎች ቦይንግ ባወጣው እና በFAA በፀደቀው በቦይንግ 737 NG እና በቦይንግ 737 ማክስ ያለውን ልዩነት ስልጠና በሚገባ የወሰዱ፣ በቦይንግ 737 ማክስ ወደ አየር መንገዱ ከመግባቱ አስቀድሞ እና በረራ ከመጀመራቸው በፊት የተጠናቀቀ ስልጠና የወሰዱ መሆኑን አየር መንገዱ ያረጋግጣል።
በቀጣይነትም #በኢንዶኔዥያው ላይን ኤር የደረሰውን አደጋ ተከትሎ የአሜሪካው FAA ያወጣው ተጨማሪ መመሪያ ለሁሉም የሚመለከታቸው አብራሪዎች እንዲያውቁት መደረጉንና ደረጃውን የጠበቀ አስፈላጊ ገለፃ ተደርጓል። በዚህም መሰረት የመመሪያው ይዘት ሙሉ በሙሉ በስልጠና ማኑዋል፣ በኦፕሬሽን ዝርዝር መመሪያዎች እና በዕለት ተዕለት ስራዎች ዝርዝር መመሪያዎች ተካተዋል።
በዚህ አጋጣሚ አየር መንገዱ መግለፅ የሚፈልገው ቦይንግ 737 ማክስ ምስለ በረራ አሁን በዓለማችን አከራካሪ የሆነውንና ለአደጋውም ዋና መንስኤ ይሆናል ተብሎ የሚገመተውን MCAS (Maneuvering Characteristics Augmentation System) ችግር ለማሳየት ታስቦ እንዳልተሰራ ነው።
የኢትዮጵያ አየር መንገድ የአለም አቀፍ የአደጋ ምርመራ ስነ-ስርዓት እና ህጎች መከተል ስላለበት የምርመራውን ውጤት በትዕግስት እየተጠባበቀ ለሚመለከታቸው ሁሉ ማለትም የሀገር ውስጥም ሆነ የአለም አቀፍ የመገናኛ ብዙሃን የአደጋውን መንስዔ መላምት ከማስቀመጥና በተሳሳተ መረጃ ህዝብ ከማሳሳት እንዲቆጠቡ ያሳስባል።
Via የኢትዮጵያ አየር መንገድ

#update ኢ/ር ታከለ ኡማ እና የከተማዋ አስተዳደሩ ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎች ለጌዲዮ ተፈናቃዮች የተወሰነውን የ30 ሚሊዮን ብር ድጋፍ በገደብ ወረዳ በመገኘት ለተፈናቃዮች አስረክበዋል።
በተጨማሪም ከአዲስ አበባ ነዋሪዎች የተሰባሰበዉን 26.5ሚሊየን ብር የሚገመት የቁሳቁስ ድጋፍም በዛሬው ዕለት ለተጎጂዎች አስረክቧል።
ኢንጅነር ታከለ የሁሉም ኢትዮጵያውያን የጋራ ከተማ የሆነችው አዲስአበባ በሌሎች የሃገሪቱ ክፍሎች ለተፈናቀሉ ወገኖችም በተመሳሳይ መልኩ የከተማዋን ነዋሪዎች በማስተባበር ድጋፍ እንደሚያደርግ ተናግረዋል።
Via mayorofficeAA