TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.8K photos
1.44K videos
207 files
3.99K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
 
#USAID #OCHA

በትግራይ የሰብዓዊ ረድዔት ሠራተኞች ችግር ላይ ያሉ ማህበረሰቦችን ለመድረስ በሚያደርጉት እንቅስቃሴዎች ላይ የሚገጥማቸው መሰናክል ተባብሷል ሲል የተመድ የሰብዓዊ ጉዳዮች ቢሮ (OCHA) አሳስቧል።

አጣዳፊ የምግብ እርዳታ ከሚያስፈልገው 5.2 ሚሊዮን ህዝብ ውስጥ ከመጋቢት ወር መጨረሻ ወዲህ ለመድረስ የተቻለው 1.8 ሚሊዮኑን ብቻ ነው ብሏል።

በክልሉ አሁን ካለው የከፋ የተመጣጠነ ምግብ ዕጥረት እንዳይከሰት አስቸኳይ የገንዘብ ድጋፍ እንደሚያስፈልግ ያስታወቀው ኦቻ እርዳታ ለሚያስፈልጋቸው ሁሉ እስከዚህ የአውሮፓ 2021 ማብቂያ ድረስ በቂ እርዳታ ለማቅረብ 853 ሚሊዮን ዶላር እስከፊታችን ሃምሌ መጨረሻ ደግሞ 200 ሚሊዮን ዶላር ድጋፍ ያስፈልጋል ብሏል።

በሌላ መረጃ ፦ የአሜሪካ ዓለም አቀፍ ልማት ተራድዖ ድርጅት ወይም USAID/ አስተዳዳሪ ሳማንታ ፓወር የትግራይ ግጭት እጅግ የከበደ ረሃብ እያስከተለ እንደሆነ እና ከ5 ሚሊዮን የሚበልጥ ህዝብ እርዳታ የሚያስፈልገው መሆኑን አሳስበዋል።

ሳምንታ ፓዎር "የቅድመ ማስጠንቀቂያ ቅኝታችን አጣዳፊ የምግብ ችግር መኖሩን ይጠቁማል" ያሉ ሲሆን ችግሩ እጅግ አስከፊው ደረጃ ላይ ደርሷል ብለዋል።

የኢትዮጲያ መንግሥት ግጭቱን ለማቆም እንዲሁም የሰብዓዊ ረድዔት ሠራተኞች የተቸገረውን ህዝብ ለመድረስ እንዲችሉ አሁኑኑ እርምጃ መውሰድ አለበት ሲሉ ገልፀዋል። #VOA

@tikvahethiopia
#ትግራይ

እአአ እስከ ሐምሌ መጨረሻ ድረስ ትግራይ ውስጥ የሕይወት አድን ድጋፍ ለመስጠት ለሰብዓዊ አጋሮች 200 ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላር የሚጠጋ ገንዘብ እንደሚያስፈልግ #OCHA ዛሬ አሳውቋል።

@tikvahethiopia
#OCHA

የተባበሩት መንግስታት ድርጅት (ተመድ) የሰብአዊ ጉዳዮች ማስተባበሪያ ጽ/ቤት(ኦቻ) የተዛቡ መግለጫዎች ከመስጠት እንዲቆጠብ የኢትዮጵያ መንግስት ጠየቀ፡፡

መንግስት ኦቻ በትግራይ ሁኔታ የተዛቡ መግለጫዎች ሲያወጣ ነበር ብሏል፡፡

መንግስት ኦቻ የሚያከናውናቸውን ገንቢ ያልሆኑ ተግባራት ኢትዮጵያ ከተቋሙ ጋር በፈረንጆቹ ከ1984 አንስቶ የገነባቸውን ግንኙነት የሚሸረሽር በመሆኑ ድርጊቱን በመቃወም ለተ.መ.ድ. ዋና ጸሃፊ ድበዳቤ መፃፉን አስታውቋል።

የፌዴራል መንግስት የትግራይን ሁኔታ በተመለከተ የህግ ማስከበሩ ዘመቻ ከተጀመረ ጊዜ አንስቶ “OCHA የነበረው ሚና እና የሚያወጣቸው የተዛቡ ሪፖርቶች ገንቢ አልነበሩም” ብሎ እንደሚያምንም መንግስት አስታውቋል፡፡

የኦቻ ሪፖርቶች የህወሐትን የተሳሳተ አስተሳሰብን የሚያጠናክር ፣የሚበራታታ እና ለማወደስ የተቀየሰ እንዲሁም ዓለም አቀፉ ማህበረሰብ በክልሉ ያለውን ሁኔታ በተሳሳተ መንገድ እንዲረዳ የሚያደርግ ይመስላል ብሏል።

OCHA ፓርላማ በአሸባሪነት የፈረጀውን ህገ-ወጥ ቡድን የትግራይ መከላከያ ሰራዊት /TDF/ እያለ የሚጠራ ተቋም ነው” ያለው መንግስት ከመስል ድርጊቱ እንዲቆጠብ እንዲሁም ለተቋሙ እና ኢትዮጵያ የቆየ ግንኙነት ሲባል የእርምት እርምጃዎች እንዲወስድ ሲል ጠይቋል፡፡ 

ያንብቡ : telegra.ph/Tigray-07-09

ምንጭ፦ አል ዓይን ኒውስ

@tikvahethiopia
#Amhara #OCHA

የአማራ ክልል ፕሬዜዳንት አቶ አገኘሁ ተሻገር ከተባበሩት መንግሥታት የሰብዓዊ ጉዳዮች ማስተባበሪያ ቢሮ (UNOCHA) የኢትዮጵያ ኃላፊ ማርሲ ቪጎዳ ጋር ውይይት አድርገዋል።

አቶ አገኘሁ በሽብርተኛ ድርጅትነት የተፈረጀው "ህወሓት" በአማራ ክልል ወረራ ፈጽሞ ሰብዓዊና ቁሳዊ ጥቃት እየፈጸመ መሆኑን ለማርሲ ቪጎዳ ገልፀዋል።

ቡድኑ ንጹሐን ዜጎችን በአስቃቂ ሁኔታ እየገደለና እያሳደደ መሆኑን የገለፁት ፕሬዜዳንቱ በክልሉ በከፈተው ጦርነት ከ550 ሺ በላይ ዜጎች መፈናቀላቸውን አመልክተዋል።

ቡድኑ ሀገር የማፍረስ ተግባር እና በዜጎች ላይ ያደረሰውን ጥቃት ዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ ሊገነዘብ ይገባል ብለዋል።

የሽብር ቡድኑ እያሳደዳቸውና እያፈናቀላቸው ላሉ ዜጎቻችን ሰብዓዊ ድጋፍ ከማቅረብ ጀምሮ አጋርነታቸውን በተግባር ማሳየት አለባቸው ብለዋል።

"እየተሳደዱ እየተጠቁ ላሉት ዜጎቻችን ድምጽ የሚሆኗቸውና ከጎናቸው የሚሆኑ ዓለም አቀፍ ተቋማትን ማዬት እንሻለን" ያሉት አቶ አገኘሁ "የተባበሩት መንግሥታት የሰብዓዊ ጉዳዮች ማስተባበሪያ ቢሮም የተፈናቀሉ ዜጎቻችንን ጉዳይ ተረድቶ ድጋፍ እንዲያደርግ እንፈልጋለን ነው" ሲሉ ተናግረዋል።

የተመድ የሰብዓዊ ጉዳዮች ማስተባበሪያ ቢሮ የኢትዮጵያ ኀላፊ ማርሲ ቪጎዳ ተቋማቸው ለአማራ ክልል ለሰብዓዊ ድጋፍ የሚውል 148 ሚሊዮን ብር መመደባቸውን ገልጸዋል፡፡

UNOCHA በፍትሐዊነት ላይ የተመሰረተ ድጋፍ የሚያደርግ በመሆኑ በቀጣይ ድጋፍ የሚሹ ወገኖችን ለመርዳት ዝግጁ ነን ማለታቸውን ከአሚኮ የተገኘው መረጃ ያሳያል።

@tikvahethiopia
#OCHA

በተመድ የሠብዓዊ ጉዳዮች ማስተባበሪያ ጽ/ቤት (ኦቻ) ፥ በደቡብ ኦሮሚያ ቦረና ዞን የተከሰተው ድርቅና የደህንነት ችግር በአስፈላጊ የጤና አገልግሎት ቀጣይነት ላይ እንቅፋት እየፈጠረ መሆኑን ገልጿል።

የትምህርት ማቋረጥ እየጨመረ ፣ የሰብል ምርት ኪሳራ እየታየ ፣ የዋጋ ጭማሪ እና የውሃ እጦት ችግር መቀጠሉ ሪፖርት እየተደረገ ነው ብሏል።

ኦቻ ለቦረና ድርቅ ምላሽ ለመስጠት የሰብአዊ ድጋፍ ቅንጅት እና ግብአት የማሰባሰብ ስራ ተጠናክሮ መቀጠል አለበት ሲል አስገንዝቧል።

የሰብዓዊ ድጋፍ አጋሮች ውስን የሆነ ምላሽ እየሰጡ ይገኛሉ ፤ ነገር ግን የፋይናንስ እና የሰው ኃይል አቅም እጦት ፈተና መሆኑን ኦቻ ገልጿል።

@tikvahethiopia