TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.6K photos
1.43K videos
206 files
3.97K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
አሳዛኝ ዜና‼️

በደሴ ከተማ በደረሰ የትራፊክ አደጋ የሶስት ሰዎች ህይዎት ማለፉን ፖሊስ አስታወቀ። በአማራ ክልል ደሴ ከተማ #በሳላይሽ ክፍለ ከተማ ዛሬ ከረፋዱ 2:00 አካባቢ ነው አደጋው የደረሰው።

በከተማው በአስፓልት መንገድ ላይ ኳስ ሲጫወቱ የነበሩ ሶስት ወጣቶች ኮድ 3 የሰሌዳ ቁጥር 11 491 FSR የጭነት መኪና ባደረሰው ግጭት ህይዎታቸው አልፏል።

በደሴ ከተማ ፖሊስ መምሪያ የመንገድ ትራፊክ ደኅንነት ማረጋገጫ ዋና የስራ ሂደት ባለቤት ኮማንደር #ሙሃመድ_አበጋዝ ለአብመድ እንደተናገሩት የአደጋው ምክንያት እየተጣራ ነው።

ህብረተሰቡ ልጆቹ በመንገድ ላይ እንዳይጫወቱ በማድረግ የመኪና አደጋዎች እንዳይፈጠሩ መከላከል እንዳለበትም ኮማንደር ሙሃመድ መክረዋል፡፡ አደጋውን ያደረሰው አሽከርካሪ እስካሁን በቁጥጥር ስር አለመዋሉንም አስታውቀዋል፡፡

Via AMMA
@tsegabwolde @tikvahethiopia