TIKVAH-ETHIOPIA
#GoE የጠቅላይ ሚኒስትር ፕሬስ ሴክሬተሪያት ቢልለኔ ስዩም ዛሬ በሰጡት መግለጫ የተለያዩ ጉዳዮችን አስንተዋል። ከካነሷቸው ጉዳዮች አንዱ በሰላም አመራጭ ኮሚቴ በኩል ስለ ተዘጋጀው የሰላም ረቂቅ ሰነድ ነው። በዚህም የሰላም ረቂቅ ሰነዱ በሰሜኑ የሀገሪቱ ክፍል ለተከሰተው ግጭት ሰላማዊ መፍትሄ ለመስጠት፤ በመጪዎቹ ሳምንታት የተኩስ አቁም እንዲደረስ፣ የሰላም ውይይት እንዲሁም ሌሎች በእንጥልጥል የቀሩ…
#ETHIOPIA
ለዜጎች ሰላም እና ከጦርነት ጭንቀት እረፍት ይሰጣል ተብሎ የነበረው የተስፋ ጭላጭል " ሙሉ በሙሉ " ይከስም ይሆን ?
የኢትዮጵያ የፌዴራል መንግስት ዛሬ ፤ ረቡዕ ባወጣው መግለጫ " ህወሓት " በምስራቅ ግንባር በቢሶበር ፣ ዞብል ፣ እና ተኩለሽ በኩል ከለሊት 11 ሰዓት አንስቶ ጥቃት መፈፀሙን ገልጿል።
በዚህ እርምጃውም ተኩስ ማቆሙን በይፋ አፍርሷል ብሏል።
ዜጎችን ከ "ህወሓት" ጥቃት ለመጠበቅም አጠቃላይ የፀጥታ ኃይል በተጠንቀቅ መቆሙን አስገንዝቧል።
የለሊቱ ጥቃት ፤ ከሰሞኑን ከነበረው ትንኮሳ የቀጠለ መሆኑን የገለፀው የኢትዮጵያ መንግስት ፤ የኢትዮጵያ ሀገር መከላከያ ሰራዊትና አጠቃላይ የፀጥታ መዋቅሩ የተሰነዘረውን ጥቃት በድል እየመከቱት ይገኛሉ ብሏል።
ከኢትዮጵያ መንግስት መግለጫ ቀደም ብሎ ህወሓት የፌዴራል መንግስት ከለሊት 11:00 ጀምሮ በጩቤ በር ፣ ጃኖራ ፣ ጉባጋላ እና በያሎው አቅጣጫ ወደ አላማጣ ፣ ባላና ብሶበር መጠነሰፊ ጥቃት ከፍቷል ሲል ክስ አሰምቷል።
ባለፉት ቀናት ፤ በደቡብ ግንባር በየግንባሩ የነበሩትን እና ከሌላ አካባቢ የተሰባሰቡ የአማራ ልዩ ኃይል ክ/ጦሮች ፣ የወሎ ፋኖና ሚሊሻ ወደፊት የማስጠጋት እንቅስቃሴ ነበር በኃላም የፌዴራል መከላከያ ኃይል ተጨምሮ ዛሬ ጥቃት ተከፍቷል የሚል ክስ አቅርቧል።
የኢትዮጵያ የፌዴራል መንግስት ግን ይህ የህወሓት ክስ " ጅራፍ ራሱ ገርፎ እራሱ ይጮሃል " እንደሚባለው ቀድሞ የተካነበት የሀሰት ፕሮፖጋንዳ ነው ብሎታል።
ትንኮሳው በራሱ በ " ህወሓት " መፈፀሙን የገለፀው መንግስት ትንኮሳውን ከፈፀሙ በኃላ " እራሳቸው እየጮሁ " ነው ብሏል።
የዓለም አቀፉ ማህበረሰብ፤ የህወሓት ቡድን የትግራይ የወጣቶችን ለማስጨረስ እያደረገ ያለውን የጦርነት ጉሰማ እንዲያቆም ጠንካራ ግፊት ማድረግ አለበትም ሲል ጥሪ አቅርቧል።
የኢትዮጵያ መንግስት የሁሉም ኢትዮጵያውያን መፍትሄ የሚያገኘው በሰላም ነው ያለ ሲሆን ዛሬም ነገም የሰላም አማራጭ የመጀመሪያ መፍትሄ እንደሆነ በፅኑ እንደሚያምን ገልጿል።
ነገር ግን ህወሓት በትንኮሳው ከቀጠለ ሀገር የማዳን ህጋዊ፣ ታሪካዊ እና ሞራላዊ ግዴታ ስላለበት ህወሓት ወደደም ጠላም ወደ ሰላማዊ አማራጭ እንዲመጣ ለማድረግ እርምጃ እንደሚወስድ አስጠንቅቋል።
በሰሜን ኢትዮጵያ፤ አሁን አሁን ጠንከር ብለው እየታዩ ያሉት ምልክቶች ከዚህ ቀደም እንደነበረው የለየት ደም አፋሳሽ ግጭት እንዳይወልድ ብዙዎችን አስግቷል። የተጀመረው የሰላም ሂደትም እንዳይደናቀፍ ተፈርቷል።
ከወራት በፊት ለሰብዓዊ ድጋፍ ሲባል ግጭት የማቆም ውሳኔ መተላለፉ አይዘነጋም ፤ ይህን ተከትሎ የሰላም ጭላንጭሎች መታየት ችለው ፤ ዜጎችም ከጦርነት እና ግጭት ስጋት ይላቀቃሉ የሚል ተስፋን ሰጥቶ ነበር።
በኃላም ችግሩን በሰላም ድርድር ለመፍታት መወሰኑን ተከትሎ በርካቶች " እፎይ ሰላም ሊገኝ ነው " የሚለው ተስፋቸው እጅግ ተጠናክሮ፤ በዚህም ተደስተው ነበር ነገር ግን ይህ ከሆነ ወራት ሳይቆጠር ዳግም የጦርነት ድባብ አንዣቧል።
ዜጎች የከዚህ ቀደሙ ጉዳት እና ህመማቸው ሳይባባስ ፣ ምንም የማያውቁ ንፁሃን ህፃናት ፤ ሴቶች አረጋዊያን ሳይፈናቀሉ ፣ ምንም የሰው ህይወት ሳይጠፋ ፣ የሀገር ሀብት ከከዚህ ቀደሙ በበለጠ ሳይጎዳ ፤ አሁን እየታዩ ያሉት ምልክቶች ቆመው በፍጥነት ሰላም ወርዶ ፤ ችግሮች ተፈተው #አዲሱን_አመት በደስታ እንቀበለው ይሆን ? ተስፋ እናደርጋለን ! ለሰላም መቼም ጊዜው አይረፍድም።
@tikvahethiopia