TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.8K photos
1.44K videos
207 files
3.99K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#WKU

" አሳይመንቱን ቤት ድረስ አምጥተሽ ስጪን " በማለት ተማሪውን ደፍሯል የተባለው የዩኒቨርሲቲ መምህር ጉዳዩ በፍርድ ቤት እየታየ ይገኛል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ ሰሞኑን ከወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ #ሴት ተማሪዎች መልዕክቶችን ተቀብሏል።

ይህም " የሴቶች ጥቃት አሳስቦናል " የሚል ነው።

ተማሪዎቹ የመደፈር እና የጥቃት ወንጀል በመምህር ሳይቀር መፈጸሙን በመግለጽ ስጋታቸውን ገልጻዋል።

በየጊዜው እንዲህ ያለ ነገርም እንሰማለን ነው ያሉት።

ከጠቆሙት አንዱ ጉዳይ በመምህሯ የተደፈረችን ተማሪ የሚመለከት ነው።

በተማሪዎች ስለሚነሳው ጉዳይ ተቋሙ ምን ይላል ? በማለት ጥያቄ አቅርበናል።

ስማቸው እንዲገለጽ ያልፈለጉ የዩኒቨርሲቲው አመራር የመምህሩ ጉዳይ #ከ2_ወራት_በፊት መከሰቱን እና ከአስገድዶ መድፈር ጋር በተያያዘ በቅርብ የተፈጸመ ጥቃት አለመኖሩን ገልጸዋል።

" ወንጀሉን ከ2 ወራት በፊት እንደፈጸሙ የተጠረጠሩት መምህር በህግ ቁጥጥር ስር ውለው ፍርዳቸውን እየተጠባበቁ ነው " ብለዋል።

ድርጊቱ እንዴት ተፈጸመ ?

በወቅቱ አንድ የሂሳብ መምህር በክፍል ውስጥ ሆነው ከተማሪዎቻቸው አሳይንመንት በመቀበል ላይ ነበሩ። የአንደኛዋን ተማሪያቸውን ወረቀት ግን ሳይቀበሉ ነበር የወጡት።

ይሁንና " #አልቀበልሽም " የተባለችው ተማሪም ምን አድርጌ / ምንስ አጥፍቼ ነው ? ብላ በምትጨነቅበት ሰአት ከክፍሉ ተጠሪ ያገኙትን ስልክ ተጠቅመው የደወሉላት መምህር  " አሳይመንትሽን ቤቴ መጥተሽ ማስረከብ ትችያለሽ " ይሏታል።

ተማሪዋም በተሰጣት አድራሻ ተመርታ ወደተባለችው ቦታ ትሄዳለች። የጠበቃት ግን አሳይመንቱን መቀበል ሳይሆን ሌላ ነበር።

ተማሪዋ እያነባች ጓደኛዋን ይዛ ወደሆስፒታል ካመራች በኃላ በሆስፒታል ህክምና አግኝታለች።

የሆስፒታል ማስረጃዋን ይዛም ወደ ዩኒቨርሲቲዉ ሂዳ አመልክታቸለች።

በወቅቱ ዩኒቨርሲቲው በተማሪዋ አቤቱታና በቀረበዉ የህክምና ማስረጃ  መሰረት ጉዳዩን ወደ #ዲስፕሊን በመዉሰድ በፍጥነት መምህሩን ከስራ ሊያግድ ችሏል።

መምህሩ ድርጊቱን ከፈጸመ በኋላ #ራሱን_ደብቆ እና ስልኩን አጥፍቶ ቆይቷል ተብሏል።

የዩኒቨርስቲው አስተዳደር #የስራ_እግድ ማሳለፉንም ተከትሎ ከተደበቀበት በመዉጣት ሲመለስ ጉዳዩን ከዩኒቨርስቲው በመረከብ ይዞ መምህሩን ሲያፈላልግ የነበረው ፖሊስ #በቁጥጥር_ስር ሊያውለው ችሏል።

አሁን ላይ የምርመራ ሂደቱ አልቆ ፍርዱን እየተጠባበቀ ሲሆን ወደፊት የፍርድ ሂደቱ የሚገለጽ መሆኑን ለማወቅ ተችሏል።

ከሰሞኑ በዚሁ በወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ ውስጥ አንድ ሽጉጥ የታጠቀ ወጣት በዩኒቨርሲቲው ውስጥ ተኩስ በመክፈቱ አንዲት ተመራቂ ወጣት ተማሪና አንድ መምህር መጉዳቱን መረጃ መለዋወጣችን ይታወሳል👉 https://t.iss.one/tikvahethiopia/88025

@tikvahethiopia