TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.8K photos
1.44K videos
207 files
3.99K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
በደቡብ ጎንደር ተጨማሪ መስጊድ ተቃጠለ‼️

በአማራ ክልል ደቡብ ጎንደር ዞን በጃራ ገዱ አነስተኛ ከተማ ያለ መስጊድ ባልታወቁ ሰዎች ትላንት ለሊት መቃጠሉን የአካባቢው የእስልምና ጉዳይ ምክር ቤት እና የዞኑ አስተዳደር አስታወቁ። ቃጠሎው #ሆን_ተብሎ ለመደረጉ ጠቋሚ ምልክቶች መገኘታቸውንም ገልጿል።

ቃጠሎው የደረሰበት የጃራ ገዱ ከደቡብ ጎንደር ዞን ዋና ከተማ ደብረ ታቦር 100 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ ይገኛል። ከተማዋ የምትገኝበት የአንዳ ቤት ወረዳ የእስልምና ጉዳዮች ምክር ቤት (መጅሊስ) ዋና ጸሐፊ አቶ #እንድሪስ_ሱፊያን ለጀርመን ራድዮ እንደተናገሩት የትላንቱ ቃጠሎ የደረሰው ከለሊቱ ሰባት ሰዓት ገደማ ነው። በቃጠሎውም “ለአካባቢው ብቸኛ የሆነው መስጊድ ወድሟል” ብለዋል።

“ለሊት ላይ #የተኩስ ድምፅ ሰምተን ወደ ቦታው ሔድን፤ ማትረፍ አልተቻለም። ሁሉም ተያይዞ ነው ያገኘንው። በራፉን ሰብረው ገብተው ነው። ቁልፉ ራሱ የተቆለፈበት አልወጣም። እንዳለ ነው የተዘጋበትን ነቅለው ከውስጥ ያሉ አንዳንድ ቁሳቁሶችን አውጥተው አቃጥለውት ያገኘንው። አብዛኞቻችን ጣራው እና ግድግዳው በእሳት ተበልቶ ነው የደረስንው” ሲሉ ዋና ጸሐፊው የዓይን እማኝነታቸውን ሰጥተዋል።

አደጋው መድረሱን ያረጋገጠው የደቡብ ጎንደር የመንግስት ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽህፈት ቤት በበኩሉ መስጊዱ የተቃጠለው “በሩ ተሰብሮ ተከፍቶ ከውስጥ ያሉ መፅሀፍት ሲቃጠሉ ተያይዞ መስጊዱ በመቀጣጠሉ” መሆኑን በፌስ ቡክ ገጹ አስታውቋል። ድርጊቱን የፈጸመው አካል ማንነትን ለማጋለጥ ከአካባቢው ነዋሪ ጋር ዛሬ ስብሰባ መካሄዱንም ገልጿል። እስከ እኩለ ቀን በዘለቀው በዚሁ ስብሰባ የዞን እና የወረዳ ኃላፊዎች ተገኝተዋል ተብሏል።

መስጊዱን በማቃጠል የተጠረጠሩ ግለሰቦች እስካሁን አለመያዛቸውን የሚናገሩት የአካባቢው የእስልምና ጉዳዮች ምክር ቤት ዋና ጸሐፊ ድርጊቱ “ሆን ተብሎ የተፈጸመ ለመሆኑ አመላካች ናቸው” ያሏቸውን ለጀርመን ድምፅ ራድዮ ዘርዝረዋል። “ከፍርስራሹ ማየት እንደቻልነው መስጊድ ውስጥ ሆን ተብሎ ቁርአኖች ተሰብስበው አንድ ቦታ ነው የተቃጠሉት። ሁለተኛ ደግሞ ቁርአኖች የሚደረደሩበት መደርደሪያዎች ከቃጠሎው የተረፈው ነገር አልተገኘም፤ እንዳለ መውጣቱን ያመለክታል። ሌላኛው ደግሞ የመስጊዱ ምንጣፎች ሌላ ሰዋራ፣ ዘወር ያለ ቦታ ቁጥቋጦ ስር ደብቀውት ከረፈደ በኋላ እርሱንም ለማግኘት ተችሏል” ሲሉ አቶ እንድሪስ አስረድተዋል።

በደቡብ ጎንደር ዞን መስጊድ ሲቃጠል በአንድ ሳምንት ውስጥ የአሁኑ ለሶስተኛ ጊዜ ነው። የትላንትናው ቃጠሎ የደረሰበት የጃራ ገዶ ቀበሌ ሁለት መስጊዶች ከተቃጠሉበት የእስቴ ወረዳ በ50 ኪሎ ሜትር ገደማ ርቀት ላይ የሚገኝ ነው። በጃራ ገዱ ጊዜያዊ የመስገጃ ቦታ ለመቀለስ እና የተቃጠለውን መስጊድ መልሶ ለመገንባት የአካባቢው ነዋሪዎች በምክክር ላይ መሆናቸውን የአካባቢው የእስልምና ጉዳዮች ምክር ቤት ዋና ጸሐፊ ለጀርመን ራድዮ ተናግረዋል።

ምንጭ፦ የጀርመን ድምፅ ራድዮ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#ጋምቤላ የጋምቤላ ክልል መንግስት የኢሰመኮን ሪፖርት "ለጠላት የወገነ ነው " ሲል ገልጾ ሪፖርቱን እንደማይቀበለውና እንደሚያወግዘው ገለፀ። የጋምቤላ ክልል፤ "ኢሰመኮ ሰኔ 7/2014 ዓ.ም በጋምቤላ ክልል ጋምቤላ ከተማ ላይ ተፈጥሮ በነበረው ውጊያ ተከትሎ በክልሉ ልዩ ኃይሎች፣ ሚሊሽያ እና ተባባሪ ወጣቶችን ሲመሩ የነበሩ አመራሮች አማካይነት ደረሰ ባላቸው የሰብአዊ መብቶች ጥሰት ላይ ያወጣውን ሚዛናዊነት…
የጋምቤላ ክልል የኢሰመኮን ሪፖርት እንደማይቀበለው እና እንደሚያወግዝ በገለፀበት መግለጫ ምን አለ ?

- ሚዛናዊነት የጎደለው በመሆኑ ምርመራውን አልቀበለውም፤ በጥብቅም አወግዛለሁ።

- ሪፖርቱ የአንድ ክልል የፀጥታ ተቋምን ከተራ የአሸባሪ ቡድን ተላላኪ ጋር በአንድነት ያየ፤ በክልልና በአገር ላይ ይደርስ የነበረ ከፍተኛ ጥቃት በመቀልበስ ሂደት የህይወት መስዋዕትነት የከፈለውን የፀጥታ ተቋሙን በጅምላ የፈረጀ፤ የተገኘውንም ድል በዜሮ ያባዛ ነው።

- ሪፖርቱ የክልሉን የፀጥታ ኃይል ሞራል የሚያዳክም፤ ፀረ-ሠላም ኃይሉንና መንግሥትን በአንድ ሚዛን ላይ አድርጎ ያየ፤ በአጠቃላይ ለጠላት የወገነ ሪፖርት ነው።

- የመረጃ አሰባሰብና ምዘና ሥነ-ዘዴው ምክንያታዊ አሳማኝነት (Reasonable Grounds) ስልት ያልተከተለ ነው።

- መረጃው ከተወሰኑ የማህበረሰብ ክፍሎች ማለትም ከኦነግ ሸኔና ህወኃት ደጋፊዎች እንዲሁም በተለያዩ ወንጀሎች ሲጠረጠሩ ከነበሩ ግለሰቦች የተወሰደና በአንድ አካባቢ የታጠረ ነው።

- ሪፖርቱ የጋምቤላን ነባር ብሔረሰቦች እና አብረዋቸው ለረዥም ዘመናት ከሚኖሩ ወንድምና እህት ኢትዮጵያዊያን ጋር እርስ በርስ ለማጋጨት #ሆን_ተብሎ የተዘጋጀ ሪፖርት ነው።

- በጋምቤላ ክልል የሚገኘው የኮሚሽኑ ጽ/ቤት ባልደረቦች ተቋሙ የተቋቋመለትን ዓላማና ተልዕኮ በቅጡ ያልተገነዘቡ፣ የግል ፍላጎታቸው የታየበት፣ የክልሉን ህዝብና መንግሥት አለያይቶ ለማጋጨት የተደረገ ሴራ ነው።

-  ሪፖርቱ የክልሉን መንግሥትና ህዝብ ስም ለማጥፋት ሆን ተብሎ በተለያዩ ሚዲያዎች የክልሉ መንግሥት የሰጠውን መግለጫዎችና ጥንቃቄ የጎደላቸው የግል ሃሳቦችን እንደ ማጣቀሻ በመጠቀም ስህተት ተኮር የሪፖርት ስልት የተከተለ ነው።

የኢሰመኮ ሪፖርት : t.iss.one/tikvahethiopia/73948

@tikvahethiopia