TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.5K photos
1.43K videos
206 files
3.96K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#ቦረና

በኦሮሚያ ፣ ቦረና በድርቅ ሳቢያ በርካታ ወገኖቻችን ዛሬም ችግር ላይ ናቸው። እነዚህ ወገኖች በድርቁ ምክንያት ያላቸውን ከብቶች ስላጡ እጅግ በጣም ፈታኝ በሆነ ሁኔታ ውስጥ ነው የሚኖሩት።

በድርቅ ተፈናቅለው መጠለያ ውስጥ ያሉ ወገኖች ሰሞኑን ቃላቸውን ለቪኦኤ ሬድዮ ሰጥተው የነበረ ሲሆን ያሉበት ሁኔታ እጅግ በጣም አሳዛኝ ነው።

(በድብሉቅ ወረዳ የሚገኙ ተፈናቃዮች)

የ7 ልጆች እናት ወ/ሮ ጂሎ ጉራቻ ፦

" የዘንድሮው ድርቅ የነበሩንን ከብቶች እና ሁሉንም ንብረቶችን ነው ያወደመብን። ባዶ እጃችንን ስንሆን ወደዚህ መጣን ፤ እዚህ ከመጣን በኃላ በምግብ እና ውሃ እጥረት እየተቸገርን ነው። በተለይም ህፃናት ነፍሰጡር ሴቶች፣ አዛውንቶች በምግብ እጥረት እየተጎዱ ናቸው። እኛ እዚህ ከሰፈርን ከ6 ወር በላይ ሆኖናል። በመጠለያው በጣም ብዙ ቤተሰቦች ነው ያሉት። በቆይታችን አንዴ ብቻ ነው ለተወሰኑ ቤተሰቦች የምግብ ድጋፍ የተሰጠው እንጂ ምንም አላገኘንም። ስለዚህ በጣም ችግር ላይ ውስጥ ነው ያለነው። "

የ6 ልጆች አባት ዳለቻ ዲዳ ፦

" ምንጠጣው ውሃ በጣም የቆሸሸ ነው። እንስሳት ሲሞቱ ከሚጣሉበት ነው ልጆቻችን የሚቀዱልን። በዛ ላይ የመፀዳጃ ቦታም የለንም። እንዲሁ በበሩ ደጃፍ ነው ይህ ሁሉ በዚህ የሰፈረው ህዝብ የሚፀዳዳው ስለዚህ የበሽታ ወረርሽኝ ፍራቻ አለብን። ሌላው የመጠለያ ቦታና ላስቲክ ሰጥተውናል። ይህ ላስቲክ #ብርድ የሚከላከል አይደለም። እናም በጣም ችግር ውስጥ ነን። "

የልጆች እናቷ ትዬ አደንጌ ፦

" #ብርዱ_በጣም_አስቸጋሪ_ነው። ለምግብ ፍለጋ ነው ከእሳት አጠገብ የምንነሳው። በዛ ላይ የምንለብሰው ልብስ የለንም። በጣም አስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ ነው ያለነው። "

ያንብቡ : https://telegra.ph/Borana-08-23 #ገልሞ_ዳዊት

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#ቦረና

በኦሮሚያ ክልል፤ ቦረና ዞን በተራዘመ ድርቅ በርካታ የቤት እንስሳት አልቀው የሚላስ የሚቀመስ ያጡ ነዋሪዎችም ከድርቁ ጋር በተያያዘ መሞት መጀመራቸውን ነዋሪዎችን ዋቢ በማድረግ ዶቼ ቨለ ሬድዮ ዘግቧል።

ቦረና ዞን የተራዘመው ድርቅ የአርሶ አደሮችን በሚሊየኖች የሚቆጠሩ የቀንድ እና የጋማ ከብቶቻቸውን በመግደል አስከፊነቱን የቀጠለ ሲሆን የሰዎችም ህይወት በድርቁ ሳቢያ እያለፈ ነው ተብሏል።

በቦረና ዞን ተልተሌ ወረዳ ነዋሪው አርብቶ አደር ማሊቻ ሞሌ ከድርቁ ጋር በተያያዘ ሰዎች እየሞቱ ስለመሆኑ ለሬድዮ ጣቢያው እንዲህ ሲሉ ተናግረዋል ፦

" ... በድርቁ ሰው የከፋ ችግር ውስጥ ነው ያለው ። ያላቸው ከብቶች በግ እና ፍየል እንኳ ሳይቀር አልቀዋል። ጠብ ያለ ዝናብ ባለመኖሩ የሚወጣ እህል የለም።

የሚሸጥ ከብት በሙሉ በድርቁ አልቀዋል። አሁን ሰው በችግሩ በሕይወት እስከማለፍ ደርሷል። የሚቀመስ በመጥፋቱ በዚሁ ዓመት ብቻ በዚህች ቀበሌያችን አራት ሰው የሚደርስ ተጎሳቅለው አልፈዋል ። "

በደቡብ ኢትዮጵያ በተለያዩ አከባቢዎች በተለይም በኦሮሚያ ክልል ቦረና ዞን እና ሶማሌ ክልል ደቡባዊ ክፍሎች ድርቁ የከፋ መሆኑን ሬድዮ ጣቢያው ዘግቧል።

ፎቶ ፦ ፋይል

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#ቦረና በኦሮሚያ ክልል፤ ቦረና ዞን በተራዘመ ድርቅ በርካታ የቤት እንስሳት አልቀው የሚላስ የሚቀመስ ያጡ ነዋሪዎችም ከድርቁ ጋር በተያያዘ መሞት መጀመራቸውን ነዋሪዎችን ዋቢ በማድረግ ዶቼ ቨለ ሬድዮ ዘግቧል። ቦረና ዞን የተራዘመው ድርቅ የአርሶ አደሮችን በሚሊየኖች የሚቆጠሩ የቀንድ እና የጋማ ከብቶቻቸውን በመግደል አስከፊነቱን የቀጠለ ሲሆን የሰዎችም ህይወት በድርቁ ሳቢያ እያለፈ ነው ተብሏል። በቦረና…
#ቦረና

- በቦረና ዞን ካሉት የቀንድ ከብቶች ውስጥ 10 በመቶውን ለመታደግ 4 ነጥብ 4 ሚሊየን እስር ሳር ያስፈልጋል።

- በድርቁ ምክንያት በዞኑ ከ3 ሚሊየን በላይ እንስሳት የሞቱ ሲሆን ፥ ከዚህ ውስጥ 85 በመቶዎቹ የቀንድ ከብቶች ናቸው።

- በዞኑ የቀሩት 230 ሺህ የቀንድ ከብቶች ሲሆኑ፤ ለ3 ወር የቀንድ ከብቶቹን ለመታደግ ቢያንስ 4 ነጥብ 4 ሚሊየን እስር ሳር ማቅረብ ያስፈልጋል። በተጨማሪ 135 ሺህ ኩንታል መኖ የሚያስፈልግ ሲሆን በዞኑ ማቅረብ የተቻለው አንድ በመቶ ብቻ ነው።

- እየተደረገ ያለው ድጋፍ በቂ ባለመሆኑ የታሰበውን ያህል ችግር ውስጥ የሚገኙ ከብቶችን መታደግ ከባድ ሊሆን ይችላል።

- እስካሁን በቀንድ ከብቶች ሞት ምክንያት 33 ቢሊየን የሚገመት ብር ታጥቷል።

(የቦረና ዞን አስተዳደሪ ጃርሶ ቦሩ ለኤፍ ቢ ሲ ከሰጡት ቃል)

#ኤፍቢሲ

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#ቦረና - በቦረና ዞን ካሉት የቀንድ ከብቶች ውስጥ 10 በመቶውን ለመታደግ 4 ነጥብ 4 ሚሊየን እስር ሳር ያስፈልጋል። - በድርቁ ምክንያት በዞኑ ከ3 ሚሊየን በላይ እንስሳት የሞቱ ሲሆን ፥ ከዚህ ውስጥ 85 በመቶዎቹ የቀንድ ከብቶች ናቸው። - በዞኑ የቀሩት 230 ሺህ የቀንድ ከብቶች ሲሆኑ፤ ለ3 ወር የቀንድ ከብቶቹን ለመታደግ ቢያንስ 4 ነጥብ 4 ሚሊየን እስር ሳር ማቅረብ ያስፈልጋል። በተጨማሪ…
#ቦረና

የቡሳ ጎኖፋ ምክትል ኃላፊ ዶ/ር ማሊቻ ሎጄ ለኢትዮጵያ ቴሌቪዥን የሰጡት ቃል ፦

- ቦረና ዞን በተፈጠረው ድርቅ ምክንያት የተረጂዎች ቁጥር እየጨመረ መጥቶ ቁጥሩ ከ604 ሺህ በላይ ደርሷል።

- ድርቁ በቦረና ብቻ ሳይሆን ሁለቱን የጉጂ ዞኖች ጨምሮ በ10 ዞኖች የተከሰተ ነው። ቦረና ግን ቆላማነቱ ከሌሎቹ አካባቢዎች ከፍተኛ በመሆኑ የጉዳቱ መጠንም በዚያው መጠን ሊጨምር ችሏል።

- በሁለት ወቅቶች (የካቲት እና ሰኔ) የድርቁ ሁኔታ ያለበትን ለማወቅ ጥናት ይካሄዳል በዚሁ መሠረት ዘንድሮም ድርቁ መቀጠሉ ስለተረጋገጠ ክልሉ ዕቅዶችን አውጥቶ በየደረጃው እየተንቀሳቀሰ ነው።

- ለድርቁ ምላሽ ለመስጠት ለተጋላጮችም እገዛ ለማድረግ ሰፊ ርብርብ እየተደረገ ቢሆንም ካለው የችግር ስፋት አኳያ የሚፈለገውን እርዳታ ማድረግ አልተቻለም።

- አስቸኳይ የመድኃኒት አቅርቦት፣ የእናቶች እና ሕፃናት አልሚ ምግቦች እና ሌሎች ሕይወት አድን ድጋፎች ስለሚያስፈልጉ ሁሉም አካላት በትብብር ሊሠሩ ይገባል።

ያንብቡ ; https://telegra.ph/EBC-02-23

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#ቦረና በኦሮሚያ ክልል፤ ቦረና ዞን በተራዘመ ድርቅ በርካታ የቤት እንስሳት አልቀው የሚላስ የሚቀመስ ያጡ ነዋሪዎችም ከድርቁ ጋር በተያያዘ መሞት መጀመራቸውን ነዋሪዎችን ዋቢ በማድረግ ዶቼ ቨለ ሬድዮ ዘግቧል። ቦረና ዞን የተራዘመው ድርቅ የአርሶ አደሮችን በሚሊየኖች የሚቆጠሩ የቀንድ እና የጋማ ከብቶቻቸውን በመግደል አስከፊነቱን የቀጠለ ሲሆን የሰዎችም ህይወት በድርቁ ሳቢያ እያለፈ ነው ተብሏል። በቦረና…
#ቦረና

" የሚላስ የሚቀመስ ያጡ ነዋሪዎች ከድርቁ ጋር በተያያዘ መሞት ጀምረዋል " - የተልተሌ  አርሶ አደር

" በርሃብ ምክንያት የሞተ ሰው የለም " - ቡሳ ጎኖፋ ኦሮሚያ

በቦረና ዞን በድርቁ ምክንያት ሰዎች በምግብ አጦት ሰውነታቸው እየተጎዳ ቢሆን " በርሃብ ምክንያት የሞተ ሰው የለም ይህንን ቦታው ድረስ ተገኝተን አረጋግጠናል " ሲል ቡሳ ጎኖፋ ኦሮሚያ ገለፀ።

ቡሳ ጎኖፋ "የሰዎች ህይወት አላለፈም" ሲል ቃሉ የሰጠው ለኢትዮጵያ ቴሌቪዥን ነው።

የቡሳ ጎኖፋ ምክትል ኃላፊ ዶክተር ማሊቻ ሎጂ ፤ " በድርቅ ወደ ተጎዳው ቦረና ዞን በማምራት ያለውን ሁኔታ ተመልክቻለሁ " ያሉ ሲሆን " በድርቁ ምክንያት ሰዎች በምግብ እጥረት ሰውነታቸን እንደተጎዳ ታዝቢያለሁ " ብለዋል።

" ነገር ግን በረሃብ ምክንያት የሞተ ሰው እንደሌለ ቦታው ድረስ ተገኝቼ በአካባቢው ከሚገኙ ሰዎች አረጋግጫለሁ " ሲሉ ለብሔራዊ ቴሌቪዥን ጣቢያው ተናግረዋል።

ከሰሞኑን ቦረና ዞን በተራዘመ ድርቅ በርካታ የቤት እንስሳት አልቀው የሚላስ የሚቀመስ ያጡ ነዋሪዎችም ከድርቁ ጋር በተያያዘ መሞት መጀመራቸውን ነዋሪዎችን ለዶቼ ቨለ ሬድዮ መናገራቸው ይታወሴ።

ለሬድዮ ጣቢያው ቃላቸውን ሰጥተው የነበረው በቦረና ዞን ተልተሌ ወረዳ ነዋሪ የሆኑት አርብቶ አደር ማሊቻ ሞሌ ከድርቁ ጋር በተያያዘ ሰዎች እየሞቱ ስለመሆኑ እንዲህ ሲሉ ነበር የተናገሩት ፦

" ... በድርቁ ሰው የከፋ ችግር ውስጥ ነው ያለው ። ያላቸው ከብቶች በግ እና ፍየል እንኳ ሳይቀር አልቀዋል። ጠብ ያለ ዝናብ ባለመኖሩ የሚወጣ እህል የለም።

የሚሸጥ ከብት በሙሉ በድርቁ አልቀዋል። አሁን ሰው በችግሩ በሕይወት እስከማለፍ ደርሷል። የሚቀመስ በመጥፋቱ በዚሁ ዓመት ብቻ በዚህች ቀበሌያችን አራት ሰው የሚደርስ ተጎሳቅለው አልፈዋል ። "

ፎቶ ፦ ፋይል

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Oromia ኦሮሚያ ውስጥ የሚንቀሳቀሱ የሀገር ውስጥ መንግሥታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች በችግር ላይ ላሉ ወገኖች አስቸኳይ የሰብዓዊ ዕርዳታ እንዲደረግላቸው የጋራ ጥሪ አቅርበዋል። በአጠቃላይ 12 መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች በኦሮሚያ ያለውን ሁኔታ በተመለከተ መግለጫ አውጥተዋል። በመግለጫቸው፤ በኦሮሚያ እየተከሰተ ያለውን የሰብዓዊ ቀውስ ለመፍታት ሁሉም ባለድርሻ አካላት ትኩረት እንዲሰጡ ጠይቀዋል። " በድርቅ…
#ቦረና

#ቦረና በታሪክ እጅግ አስከፊ በተባለው ድርቅ ሳቢያ የተጎዱ ወገኖቻችንን ለመርዳት የምትፈልጉ በ " #ALCHIISOO_PASTORALIST_UP " በኩል መርዳት ትችላላሁ።

የዚህ መንግስታዊ ያልሆነ ድርጅት (NGO) የባንክ አካውንቶች ፦

👉 የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ - 1000522499823 (Swift Code: CBETETAA)

👉 የኦሮሚያ ህብረት ስራ ባንክ -  1011800084313 (Swift code: CBO RETAA)

👉 አዋሽ ባንክ - 013081084782900
(Swift code:  AWINETAA)

👉 ኦሮሚያ ባንክ - 1548414100001
(Swift code: ORIRETAA)

ቁጥሮች ስለ ቦረና ምን ይናግሩናል ?

- በቦረና ዞን 807 ሺህ ሰዎች እርዳታ ይፈልጋሉ። ከነዚህ ውስጥ 167 ሺህ የሚሆኑ ሰዎች አስቸኳይና ተከታታይ ድጋፍ የሚፈልጉ ናቸው።

- በዞኑ ካሉት የቀንድ ከብቶች ውስጥ 10 በመቶውን ለመታደግ 4 ነጥብ 4 ሚሊየን እስር ሳር ያስፈልጋል።

- በድርቁ ምክንያት በዞኑ ከ3 ሚሊየን በላይ እንስሳት የሞቱ ሲሆን ከዚህ ውስጥ 85 % የቀንድ ከብቶች ናቸው።

- በዞኑ የቀሩት 230 ሺህ የቀንድ ከብቶች ሲሆኑ፤ ለ3 ወር የቀንድ ከብቶቹን ለመታደግ ቢያንስ 4 ነጥብ 4 ሚሊየን እስር ሳር ማቅረብ ያስፈልጋል። በተጨማሪ 135 ሺህ ኩንታል መኖ የሚያስፈልግ ሲሆን በዞኑ ማቅረብ የተቻለው አንድ በመቶ ብቻ ነው።

- የተከሰተው ድርቅ በዞኑ 13 ወረዳዎች አጥቅቷል ፤ በዞኑ ከሚገኘው 60 በመቶ የሚሆነው ህብረተሰብ ድጋፍ ይፈልጋል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#ቦረና

🗣 የቦረና ዞን ተልተሌ ወረዳ ነዋሪ የሆኑት አቶ ጉዮ ቱሩ ፦

" ቆሪ ጉዮ የተባለው ልጄ 16 ዓመቱ ነበር። ጤናማ እና ጠንካራ ነበር። ነገር ግን በረሃብ ምክንያት ታመመ። ምንም አልነበረንም። የነበሩን ከብቶች በድርቁ አልቀዋል።

ሆስፒታል ወስደነው ነበር። ችግሩ ከምግብ እጥረት ጋር የተያያዘ ነው አሉን። ከዚያ ከሆስፒታል እንደተመለሰ ሞተ። "

🗣 የቦረና ዞን የተልተሌ ወረዳ አስተዳዳሪ የሆኑት አቶ ኤንጌ ዋሪዮ፦

" በወረዳው ከተከሰተ የምግብ እጥረት ጋር ተያይዞ የሰባት ሰዎች ሕይወት አልፏል።

ከምግብ እጥረት ጋር በተያያዘ ሕይወታቸውን ካጡት መካከል የሁለት ወር ጨቅላ ይገኝበታል።

በተልተሌ ወረዳ፣ ከሁለት ወር ህጻን ጀምሮ እስከ አዛውንቶች ድረስ በረሃብ ምክንያት ሰባት የሚሆኑ ሰዎች ሞተዋል።

ሰዎች ያለ ምግብ ብዙ ቀን እየቆዩ ነው። ያሏቸውም ከብቶች አልቀውባቸዋል። "

🗣 የተልተሌ ወረዳ የአደጋ መከላከል እና ምግብ ዋስትና ኃላፊ ገልመ ሞሉ፦

" በረሃብ ምክንያት ሰዎች እየሞቱ ነው ለሚለው ስለሚለው የደረሰኝ መረጃ የለም።

ይሁን እንጂ ሕጻናት አረጋውያን በምግብ እጥረት ምክንያት ከቀላል በሽታዎች ማገገም እየቻሉ አይደለም። "

CREDIT : #BBC

@tikvahethiopia
#ቦረና

" በቡድንም ሆነ በተናጠል ድጋፍ መሰብሰብ አይቻልም " - የኦሮሚያ ክልል መንግሥት

በቦረና ዞን በተከሰተው ድርቅ ምክንያት ድጋፍ ለማድረግ በቡድንም ሆነ በተናጠል መሰብሰብ እንደማይፈቀድ የኦሮሚያ ክልል መንግስት አሳሰበ።

የክልሉ መንግስት ፤ በክልሉ አንዳንድ ዞኖች በተለይ በቦረና ዞን በተከታታይ አምስት የዝናብ ወቅት ዝናብ አለመጣሉን ተከትሎ ድርቅ መከሰቱ አስታውሷል።

በተከሰተዉ ድርቅ ምክንያትም መንግስት ባቀረበዉ ጥሪ መሠረት ለችግር ለተጋለጡ ዜጎች በተለያዩ መንገዶች በገንዘብና በዓይነት ድጋፍ እየተሰበሰበ ይገኛል ብሏል።

ከዚህ በኋላ ከኦሮሚያ ክልል መንግስት ወይም ከኦሮሚያ ቡሳ ጎኖፋ እዉቅና ዉጭ #በቡድንም ሆነ #በተናጠል ድጋፍ ማድረግ የማይፈቀድ መሆኑን አሳስቧል።

ይህም የሚሰበሰበዉን ድጋፍ በአግባቡ ለማስተዳደር፣ ፍትሓዊ በሆነና ግልፅነት ባለዉ መንገድ ለችግር ለተጋለጡ ወገኖች ተደራሽ ለማድረግ ያለመ ውሳኔ መሆኑን የክልሉ መንግሥት ገልጿል።

#ኦቢኤን

@tikvahethiopia
#ቦረና

በ ' ሃጫሉ ሁንዴሳ ፋውንዴሽን ' የተሰራ የውሃ ፕሮጀክት ተመረቀ።

ፋውንዴሽኑ በቦረና ዞን ሚዮ ወረዳ፣ በቦኩ ሉቦማ መንደር እና ዱቡሉቅ ወረዳ የንፁህ ውሃ ፕሮጀክቶችን አጠናቅቆ አስመርቋል።

ፕሮጀክቱ ከ26 ሚሊዮን ብር በላይ እንደወጣበት ተመላክቷል።

በዝግጅቱ ላይ የአርቲስቱ ቤተሰቦች፣ የአካባቢው ማህበረሰብ እና የመንግስት ተወካዮች ተገኝተዋል።

የውሃ ፕሮጀክቱ የሁለቱን ወረዳዎች 52,325 ነዋሪዎችን የመጠጥ ውሃ ችግር ያቃልላል ተብሎ ይጠበቃል።

ፎቶ፦ ሃጫሉ ሁንዴሳ ፋውንዴሽን

@tikvahethiopia