TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
59.4K photos
1.51K videos
215 files
4.12K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#update ‹‹ሰላም #ዋናው ትኩረታችን ነው፡፡›› ሲሉ የሽግግር አካል ኦነግ ሊቀመንበር አቶ #ገላሳ_ዲልቦ አስታወቁ፡፡ ለውጡ በመልካም መንገድ ላይ ነው የሚል እምነት እንዳላቸውም ገለጹ፡፡ ሊቀመንበሩ አቶ ገላሳ ዲልቦ በተለይ ለአዲስ ዘመን ጋዜጣ እንደተናገሩት፤በሀገሪቱ ችግሮች ቢስተዋሉም፤ የሚታይ ለውጥም አለ፡፡ ችግሩን ደግሞ ታግሎ መፍታት ይቻላል፡፡ ‹‹ህዝቡ ምን ይዛችሁ መጣችሁ የሚለን ከሆነ የህዝቡ ጥያቄ እንዳለ ሆኖ አንዱ ዋና ትኩረታችን ሰላም መሆኑን እገልጻለሁ፡፡ ሲሉ ሊቀመንበሩ አስታውቀዋል፡፡

via ENA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
የኮቪድ-19 ክትባት ሲገባ ቅድሚያ የሚሰጣቸው ዜጎች ...

ዶ/ር ሊያ ታደሰ የጤና ሚኒስቴር ሚኒስትር ፦

"የጤና ባለሞያዎችና ሰራተኞች እንዲሁም በተመሳሳይ ስራ መስክ ውስጥ ያሉ ፣ የህዝብ ትራንስፖርት ላይ አገልግሎት የሚሰጡ ፣ እድሜያቸው የገፋ ፣ ተጓዳኝ በሽታ ያለባቸው ፣ በስራቸው ምክንያት ተጋላጭ የሚሆኑ እንደ አስተማሪዎች ፣ የፀጥታ አካላት ዋና ዋናዎቹ ናቸው።

እንደ ሀገር ክትባቱን ለማምጣት እና ተደራሽ ለማድረግ ዘርፈ ብዙ ስራዎች እየተሰሩ ሲሆን በምን ያህል ፍጥነት ክትባቱ ይዳረሳል የሚለው እየተሰራ ያለው እቅድ እንዳለ ሆኖ በዓለም አቀፍ የክትባት አምራቾች አቅርቦት መጠን የሚወሰን ሲሆን ክትባቱ ቢመጣም በሚቀጥለው 1 ዓመት ውስጥ ሁሉንም ማህበረሰብ ማዳረስ ስለማይቻል አሁንም #ዋናው_ትኩረታችን የመከላከል ስራዎችን አጠንክረን መቀጠል ነው መሆን ያለበት።"

@tikvahethiopia @tikvahethopiaBOT
Audio
#ለጥንቃቄ⚠️

እንዲህ ካሉ አጭበርባሪዎች ተጠንቀቁ።

ከላይ የምትሰሙት የድምፅ ቅጂ ከአንድ የቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባል የተላከ ነው።

አጭበርባሪው ደዋይ ግለሰብ ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ #ዋናው_ቢሮ እንደደወለ በማስመሰል በኦንላይን ዘረፋ ለመፈፀም ሞክሯል።

የደወለው #የባንክ_ሰራተኛ ጋር መሆኑን አላወቀም ነበር።

ሰራተኛው ግለሰቡ የሚለፈልፈውን ሁሉ እስከ መጨረሻ ድረስ አዳመጠው።

በኃላም የአንድ የባንኩን ቅርንጫፍ ዋና ስራ አስኪያጅ ስምን ይጠይቀዋል።

በዚህ ግዜ ከዋናው መ/ቤት ነኝ ያለው አጭበርባሪ ምን ይዋጠው ? መቀባጠር ይጀምራል።

በመጨረሻ ውርደቱን ተከናንቦ ስልኩን ዘግቷል።

እንዲህ ያሉ የማጭበርበር ስልቶች አንድ ሰሞን እንደጉድ ተበራክተው ነበር። አሁን ደግሞ ሰሞነኛውን የንግድ ባንክን ሁኔታ ተከትሎ እንደ አዲስ ተስፋፍተዋል።

ውድ ቤተሰቦቻችን ፦
* የማታውቋቸው የግል ስልኮችን ባለማንሳት ፣
* #የሚስጥር_ቁጥሮችን ባለመስጠት እራሳችሁን ከአጭበርባሪዎች ጠብቁ። የሚመለከታቸው አካላትም ይህን ነገር እንደ ቀላል ከማየት የማጭበርበር ስራ ላይ የተሰማሩ ሰዎች #በደወሉበት_ስልክ ክትትል በማድረግ ወደ ህግ ማቀረብ አለባቸው።

(የድምፅ ቅጂውን ለላከው የቤተሰባችን አባል ምስጋና እናቀርባለን)

@tikvahethiopia