TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.6K photos
1.43K videos
206 files
3.97K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
ትላንት በትራፊክ አደጋ ከ15 በላይ ሰዎች ህይወት ማለፉን ተዘግቦ ነበር፦

• ከሟቾቹ ውስጥ ሦስቱ ጓደኛማቾች ይገኙበታል
• 3ቱም የ3ኛ ዓመት የአርኪዮሎጂ ተማሪዎች ናቸው
• ያቤሎ በሀዘን ተመታለች!
• እንደወጣን አንመለስም! …

በኦሮሚያ ክልል በቦረና ዞን ያቤሎ ወረዳ በደረሰ የትራፊክ አደጋ ከ15 በላይ ሰዎች ህይወት አልፏል።

አደጋው የተከሰተው ከኦሮሚያ ክልል ቦረና ዞን ያቤሎ ከተማ ወደ ደቡብ ክልል ኮንሶ ከተማ ኮንትሮባንድ ጭኖ በፍጥነት ሲጓዝ የነበረ ተሽርካሪ ከከባድ የጭነት ተሽከርካሪ ጋር በመጋጨቱ ነው።

በደረሰው ከባድ የትራፊክ አደጋ ከ15 ሰዎች በላይ ህይወት አልፏል። ከቦራና ወደ #ወላይታ_ሶዶ ዩኒቨርሲቲ ለ2ኛ ሴምስተር ምዝገባ ሲጓዙ የነበሩት የ3ኛ ዓመት የ#አርኪዮሎጂ #archeology ተማሪዎች የሆኑት ተማሪ #መቅደስ_ተሰፋዬ፣ ተማሪ #ትዝታ_ይድነቃቸው እና ተማሪ #ከና_ሚፊታ በመኪና አደጋ ሕይዋታቸው ተነጥቋል፡፡

ከሟቾቹ ውስጥ ከላይ በፎቶው የምትመለከቷቸው ሦስት ጓደኛሞች የአደጋው ሰለባ ሆነዋል፡፡ በወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ የዘንድሮ #ተመራቂ ተማሪዎች ነበሩ::

• (በመንገድ ላይ እየቀረን ነው)

ያገሬ ልጆች እንደወጡ አይመለሱም፤ አንመለስም!

ነፍስ ይማር!

Via Getu Temsegen
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#WSU የዛሬው እንግዳ ዶክተር ታከለ ናቸው! ውድ የTIKVAH-ETH ቤተሰብ አባላት ሰዓት ይከበር። #ወላይታ_ሶዶ_ዩኒቨርሲቲ

#StopHateSpeech

•ከምሽቱ 2:00 ጀምሮ
•ቦታው፦ ከፕሬዘዳንት ህንፃ ፊት ለፊት
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#ወላይታ_ሶዶ_ዩኒቨርሲቲ

የወ/ሶዶ ዩኒቨርሲቲ በ11ኛው ዙር የተማሪዎች የምረቃ ስነ ስርዓት በተለያዩ የትምህርት መስኮች ያሰለጠናቸውን ከ4000 በላይ ተማሪዎችን በድምቀት አስመርቋል። በምርቃት ስነ ስርዓቱ ላይ የማህበረሰብ አቀፍ አገልግሎቶችን በመስጠት ሲሳተፉ ለነበሩ ሁለት ኢትዮጵያዊያን የክብር ዶክትሬት ዲግሪ ተበርክቶላቸዋል። ክቡር ዶክተር ዘብዲዮስ ጨማ ላለፉት 40 ዓመታት በወላይታ ባህል፣ ቋንቋ፣ እና በወላይታ ታሪክ ላይ በስፋት ለሰሯቸው ስራዎች የእውቅናና የክብር ዶክትሬት ዲግሪ ተበርክቶላቸዋል። ሌላኛው የክብር ዶክትሬት የተበረከተላቸው ኢትዮጵያዊ ደጃዝማች ወልደሰማያት ገ/ወልድ ሲሆኑ ክቡር ዶ/ር ወልደሰማያት ገ/ወልድ 7ቱን የወላይታ ወረዳዎች በመቆርቆር የሚታወቁ የልማት አርበኛ እንደሆኑ ተነግሮላቸዋል። ህይወታቸውን በሙሉ በወላይታ ውስጥ ሲሰሩ በነበሩ የልማት ስራዎች ላይ ላደረጉት ትልቅ አስተዋፆ የክብር ዶክትሬት ዲግሪ ተበርክቶላቸዋል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
Congratulations !

የተለያዩ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ዛሬ ተማሪዎቻቸውን አስመርቀዋል።

#ወላይታ_ሶዶ_ዩኒቨርሲቲ

የወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ በተለያዩ የትምህርት መስኮች ያሰለጠናቸውን 5 ሺህ 726 ተማሪዎች አስመርቋል፡፡

ዩኒቨርሲቲው ዛሬ ለ13ኛ ጊዜ ባካሄደው የተማሪዎች ምረቃ ሥነ ስርዐት 5 ሺህ 726 ተማሪዎችን በመጀመሪያ፣ 2ኛ እና 3ኛ ዲግሪ አስመርቋል።

ከተመራቂዎቹ 448ቱ በ2ኛ ዲግሪ እንዲሁም ሰባቱ በ3ኛ ዲግሪ ትምህርታቸውን የተከታተሉ ሲሆኑ ከጠቅላላ ተመራቂዎቹ 2 ሺህ 31ዱ ሴቶች ናቸው።

#ወራቤ_ዩኒቨርሲቲ

ወራቤ ዩኒቨርሲቲ በተለያዩ የትምህርት መስኮች ያሰለጠናቸውን 1 ሺህ 132 ተማሪዎች አስመርቋል፡፡

ተመራቂዎቹ በመደበኛ እና በተከታታይ መርሃ ግብሮች ትምህርታቸውን የተከታተሉ ናቸው፡፡

#ኦዳቡልቱም_ዩኒቨርሲቲ

ኦዳ ቡልቱም ዩኒቨርሲቲ በመጀመሪያ ዲግሪ ያሰለጠናቸውን 1 ሺህ 354 ተማሪዎች አስመርቋል፡፡

ዛሬ ዩኒቨርሲቲው ባካሄደው 3ኛ ዙር የምረቃ ስነስርዐት የተመረቁ ተማሪዎች፤ በመደበኛ፣ በኤክስቴንሽን እና በቅዳሜና እሁድ መርሃ ግብሮች ስልጠናቸውን የተከታተሉ ናቸው።

#ሰላሌ_ዩኒቨርሲቲ

ሰላሌ ዩኒቨርሲቲ በተለያዩ የትምህርት መስኮች ያሰለጠናቸውን 1 ሺህ 54 ተማሪዎች አስመርቋል።

3ኛ ዙር ተመራቂዎቹ በዩኒቨርሲቲው አራት ኮሌጆች በመጀመሪያ ዲግሪ በመደበኛና ኤክስቴንሽን መርሃ ግብሮች ስልጠናቸውን ያጠናቀቁ ናቸው። ዛሬ ከተመረቁት ተማሪዎች 428ቱ ሴቶች ናቸው።

በሌላ በኩል ፦

የተለያዩ የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ያሰለጠኗቸውን ተማሪዎች አስመርቀዋል።

ጌጅ ዩኒቨርሲቲ ኮሌጅ፣ ኩዊንስ ኮሌጅ፣ ግሬት ኮሌጅና ኤልኤም ኢንተርናሽናል የሆቴልና ቱሪዝም ማሰልጠኛ ተቋማት ያስተማሯቸውን ተማሪዎች አስመርቀዋል።

Source : @tikvahuniversity