TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
59.4K photos
1.51K videos
215 files
4.12K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
አሳዛኝ ዜና‼️

በምሥራቅ ጎጃም ዞን ደብረ ማርቆስ ከተማ ቀበሌ 07 ልዩ ስሙ ጨሞጋ አውራ ጎዳና ዛሬ ከረፋዱ 3:00 አካባቢ በደረሰ #የተሽከርካሪ_መገልበጥ አደጋ 16 ሰዎች ጉዳት ደርሶባቸዋል፡፡

ከደብረ ማርቆስ ወደ የጁቤ በመሄድ ላይ የነበረ የሕዝብ ማመላለሻ መኪና ተገልብጦ ነው አደጋው የደረሰው፡፡

በአደጋው ጉዳት የደረሰባቸው 16 ሰዎች በደብረማርቆስ ሪፈራል ሆስፒታል የሕክምና ዕርዳታ እየተደረገላቸው ነው፡፡

አደጋው የተከሰተው በፍጥነት በማሽከርከር መሆኑም ታውቋል፤ የመገልበጥ አደጋ ያደረሰው አሽከርካሪ ደግሞ ለጊዜው ተሰውሯል፡፡

#ተጠርጣሪውን በቁጥጥር ስር ለማዋል ፖሊስ ጥረት እያደረገ መሆኑን የምሥራቅ ጎጃም ዞን ፖሊስ መምሪያ የሕዝብ ግንኙነት አስተባባሪ ኢንስፔክተር ጎበዜ ይርሳው ተናግረዋል፡፡

ምንጭ፦ አብመድ
@tsegabwolde @tikvahethiopia