TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
59.4K photos
1.51K videos
215 files
4.12K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
ጅግጅጋ🔝

ቀዳማይት እመቤት ዝናሽ ታያቸው በጅግጅጋ ተገኝተው ስምንተኛውን የኢትዮጵያ ከተሞች ፎረም አካል የሆነውን የከተሞች ኤግዚቢሽን ጎብኝተዋል።

በተያያዘ ዜና...

ቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸው በሱማሌ ክልል ጅግጅጋ ከተማ ለሚገነባው “የአመንጄ ዮጎል” የ2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ዛሬ የመሰረት ድንገጋይ ያስቀምጣሉ፡፡ ቀዳማዊት እመቤቷ በፅ/ቤታቸው በኩል ከሚሰሯቸው ተግባራት መካከል አንዱ ከረጂ ድርጅቶች በሚያገኙት ገንዘብ የተለያዩ መሠረተ ልማቶችን መገንባት ነው።

Via EPA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
አሳዛኝ ዜና‼️

በዛሬው ዕለት በአዲስ አበባ ከተማ ኮተቤ ዩኒ ቨርሲቲ አካባቢ በግንባታ ላይ የነበረ #ድልድይ አርማታ #ተደርምሶ 12 ሰዎች #ጉዳት ደረሰባቸው፡፡ ጉዳት የደረሰባቸው ሰዎች ወደ #ሆስፒታል ተወስደዋል። በአደጋው #ህይወቱ ያለፈ ሰው ስለመኖሩ #የታወቀ ነገር የለም።

Via EBC
ፎቶ፦m & jes(tikvahethiopia)
@tsegabwolde @tikvahethiopia
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
#update በአዲስ አበባ ከተማ ኮተቤ ዩኒቨርስቲ አካባቢ በግንባታ ላይ የነበረ ድልድይ #ተደርምሶ በሰዎች ላይ ጉዳት ደረሰ።

via etv
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ዴዶ ሆስፒታል🔝

በጅማ ዞን #ዴዶ_ወረዳ የሚገኝው የዴዶ ሆስፒታል በ35 ሚሊዮን ብር ወጪ የተገነባ ሲሆን ሆስፒታሉ በቅርቡ አገልግሎት መስጠት የሚያስችለውን የሰው ሃይልና የህክምና መሣሪያዎችን #እያሟላ እንደሚገኝ ተገልጿል። የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታሉ ለ100 መቶ ሺህ ሰዎች አገልግሎት እንደሚሰጥ ይጠበቃል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
አሳዛኝ ዜና‼️

በምሥራቅ ጎጃም ዞን ደብረ ማርቆስ ከተማ ቀበሌ 07 ልዩ ስሙ ጨሞጋ አውራ ጎዳና ዛሬ ከረፋዱ 3:00 አካባቢ በደረሰ #የተሽከርካሪ_መገልበጥ አደጋ 16 ሰዎች ጉዳት ደርሶባቸዋል፡፡

ከደብረ ማርቆስ ወደ የጁቤ በመሄድ ላይ የነበረ የሕዝብ ማመላለሻ መኪና ተገልብጦ ነው አደጋው የደረሰው፡፡

በአደጋው ጉዳት የደረሰባቸው 16 ሰዎች በደብረማርቆስ ሪፈራል ሆስፒታል የሕክምና ዕርዳታ እየተደረገላቸው ነው፡፡

አደጋው የተከሰተው በፍጥነት በማሽከርከር መሆኑም ታውቋል፤ የመገልበጥ አደጋ ያደረሰው አሽከርካሪ ደግሞ ለጊዜው ተሰውሯል፡፡

#ተጠርጣሪውን በቁጥጥር ስር ለማዋል ፖሊስ ጥረት እያደረገ መሆኑን የምሥራቅ ጎጃም ዞን ፖሊስ መምሪያ የሕዝብ ግንኙነት አስተባባሪ ኢንስፔክተር ጎበዜ ይርሳው ተናግረዋል፡፡

ምንጭ፦ አብመድ
@tsegabwolde @tikvahethiopia