የሮሂንጊያ ስደተ ኞች‼️
የተባበሩት መንግሥታት የሮሂንጊያ ስደተኞችን ለመደገፍ ለዚህ ዓመት ብቻ 920 ሚሊየን ዶላር ያስፈልጋል አለ። የተባበሩት መንግስታት፣ የእርዳታ ድርጅቶችና መንግሥታዊ ያልሆኑ ተቋማት ለስደተኞቹ የገንዘብ ማሰባሰቢያ ንቅናቄን ትላንት አስጀምረዋል።
በተያዘው የፈረንጆቹ ዓመት ከ900 ሺህ በላይ የሚሆኑትን የሮሂንጊያ ስደተኞች ለማገዝ 920 ሚሊየን ዶላር እንደሚስፈልግ ገልጸዋል።
ሮሂንጊያዎች በፈረንጆቹ 2017 ማይናማር ውስጥ በደረሰባቸው አሰቃቂ ጥቃት አካባቢያቸውን ለቀው ከሀገር የወጡ ሲሆን በአሁኑ ወቅት በባንግላዴሽ በጊዜያዊ መጠለያዎች ይገኛሉ።
በዚህ ዓመት ከሚያስፈልገው ገንዘብ ውስጥ ግማሹ በጣም አስቸኳይ ለሆኑ እንደ ምግብ፣ ውሃ፣ የመጸዳጃ እና የመጠለያ ቁሳቁሶችን ለማቅረብ የሚውል ነው ተብሏል።
ቀሪው የጤና አገልገሎቶችን፣ አስተዳደራዊ ጉዳዮችን፣ ህፃናትን ጨምሮ ለስደተኞች የሚደረጉ የደህንነት ሥራዎችን ለማሟላት የሚውል ነው።
ገንዘቡ ሮሂንጊያዎች በሚገኙባቸው አካባቢ የሚኖሩ 330 ሺህ ባንግላዲሻውያንንም ታሳቢ ያደረገ መሆኑን የተባበሩት መንግሥታት የስደተኞች ኮሚሽንና ዓለም አቀፉ የስደተኞች ጉዳየ ድርጅት በጋራ ገልጸዋል።
ምንጭ፦አልጀዚራ
@tsegabwolde @tikvahethiopia

የኢሳት ቀን ~ አዲስ አበባ🔝
በርካታ #የመዲናይቱ ነዋሪዎች ለኢትዮጵያ ሳተላይት ሬድዮ እና ቴሌቪዥን #ጋዜጠኞች የእንኳን ደህና መጣችሁ #አቀባበል ለማድረግ ሚሊንየም አዳራሽ ተገኝተዋል።
@tsegabwolde @tikvahethiopia
በርካታ #የመዲናይቱ ነዋሪዎች ለኢትዮጵያ ሳተላይት ሬድዮ እና ቴሌቪዥን #ጋዜጠኞች የእንኳን ደህና መጣችሁ #አቀባበል ለማድረግ ሚሊንየም አዳራሽ ተገኝተዋል።
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ለሰራተኞቹ #ደሞዝ መክፈል አልቻለም‼️
(ተክለብርሀን አምባዬ ኮንስትራክሽን)
በሀገሪቱ ከሚንቀሳቀሱ የግንባታ ተቋራጮች መካከል አውራየሆነው ተክለ ብርሃን አምባዬ ኮንስትራክሽን በስሩ ከ1 ሺህ በላይ ጊዜያዊ እና ቋሚ ሰራተኞችን ይዞ የተለያዩ ፕሮጀክቶችን በመውሰድ #ሲሰራ ቆየታል፡፡ ከአንድ ቢሊየን ብር በላይ የሚተመኑ ስራዎችን በመሠራት የዘለቀው የግንባታ ድርጀቱ ከኢትዮጵያ ውጪም በሶማሊላንድ አውሮፕላን ማረያፊ እስከ መገንባት የደረሰ ሲሆን በዩጋንዳም በሪል ስቴት ኢንቨስትመንት ለመሰማራት ሃሳብ ነበረው፡፡
ነገር ግን የዚህ በጀት አመት ከጀመረበት ከሰኔ 2010 ጀምሮ ለኩባንያው ጥሩ ግዜ እንዳልሆነ ምንጮቻችን ይናገራሉ፡፡ ቀዳሚው ነገር የአቢይ አህመድ አስተዳደር በዚህ አመት አዳዲስ ፕሮጀክትን ለመገንባት ስራዎች ከመጀመር ይልቅ #ሳይጠናቀቁ የተጓተቱትን መጨረስ ላይ ማተኮሩ መሆኑን ያስቀምጣሉ፡፡ ቀድሞም ቢሆን የመንግስትን አጠቃላይ በጀት ቀመር እና የአመቱን ትኩረት በመለየት የግንበታው ዘርፍ ላይ በየአመቱ ዝግጅት ለሚያደርጉት የግንባታ ተቋራጭ ድርጅቶች ይህ የመንግስት ውሳኔ ስራቸው በእጅጉ #እንዲቀዛቀዝ ያደረገ ሆኗል።
በአንድ የግንባታ ድርጅት ውስጥ በፕሮጀክት አዋጭነት ላይ የሚሰራ ባለሙያ ሀሳቡን ለዋዜማ ሲናገር የእሱን ድርጅት ጨምሮ አብዛኞቹ በዘርፉ ላይ የተሰማሩ ተቋራጮች የአመቱን የስራ ትኩረት የሚለዩት መንግስት ከፍተኛውን ወጪ የመደበበትን ዘርፍ ቀድሞ በመለየት መሆኑን ያስታውሳል፡፡ ዘንድሮ ግን አዲስ የግንባታ ፕሮጅክቶች ላይ መንግስት የተከተለው አቅጣጫ ለዘርፉ ተዋናዮች መልካም ዜና አይደለም።
በግንባታው ዘርፍ ቀዳሚ ስም ካላቸው ተቃራጮች መካከል ተክለብርሃን አምባዬ ኮንስትራክሽን አውራ ነው፡፡ የድርጅቱ ሰራተኞች እንደነገሩን ደሞዝ ከተከፈላቸው 6 ወራት ተቆጥሯል። የዋዜማ ራድዮ ምንጮች እንደሚሉት ለቋሚ ሰራተኞቹ ያቀረበው “ለጥቂት ግዜ ታገሱኝ” ተማጽኖን በመቀበል አብዛኞቹ ሰራተኞች ቢቆዩም ጠዋት ገብተው ማታ ከመውጣት የዘለለ ስራ እየሰሩ አይደለም፡፡
በዚህ ሁኔታ ውስጥ ደግሞ ተክለ ብርሃን አምባይ ለረጅም ግዜ ሳይከፍል የቆየውን ግብር ከ68 ሚሊየን ብር በላይ ገንዘብ በቅርቡ እንዲከፍል መደረጉም ድርጅቱን ለተጨማሪ የፋይናንስ ጫና እንደዳረገው የዋዜማ ምንጮች ይናገራሉ፡፡
በሀገሪቱ ውስጥ በኢንቨስትመንት በስፋት ከሚንቀሳቀሱ ድርጅቶች መካከል የባንክ እዳ ጫና ካለባቸው ድርጅቶች ውስጥ ተክለብርሃን አምባዬ ከቀዳሚዎቹ ተርታ እንደሚሰለፍ ዋዜማ መረጃውን ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ምንጮቿ አረጋግጣለች፡፡ የሬድዮ ጣቢያው ምንጮች እንደሚሉት ድርጅቱ በእጁ የሚገኘው ሀብትና በባንክ ያለበት የእዳ ጫናም ተመጣጣኝ አይደለም፡፡
ምንጭ፦ ዋዜማ ራድዮ

ደቡብ ክልል❓
በደቡብ ክልል እየተነሱ ያሉ #የአደረጃጀት ጥያቄዎችን በተመለከተ ሳይንሳዊ ጥናት ለማድረግ ዝግጅት ማጠናቀቁን ጥናቱን የሚያከናውነው ፎረም አስታወቀ።
ላለፉት ሶስት ወራት ዝግጅት ሲያደርግ የቆየው ፎረሙ፤ በቀጣዮቹ አስር ቀናት መረጃ ሰብሳቢዎች ወደ ስራ ይገባሉ ብሏል።
ፎረሙ ጥናቱን ከአራት ወራት ባልበለጠ ጊዜ ውስጥ አጠናቆ ለክልሉ መንግስት እንደሚያቀርብም ነው ዛሬ በሰጠው መግለጫ ያስታወቀው።
ከተለያዩ የክልሉ አካባቢዎች እና የሙያ መስኮች የተውጣጣ 20 አባላት ያለው የጥናት ቡድን፤ የጥናቱን አካሄድ በተለመከተ ንድፈ ሀሳብ አዘጋጅቷል። አለም አቀፍ ተሞክሮዎችን ለማየት መሞከሩንም አንስቷል።
በዛሬው እለትም ከተለያዩ ዩኒቨርሲቲዎች ከተመለመሉ 22 የጥናቱ ሱፐርቫይዘሮች ጋር በአዲስ አበባ ውይይት አድርጓል።
በቀጣዩ ሳምንትም #በሀዋሳ ከ150 የመረጃ ሰብሳቢዎች ጋር እንደሚመክር ነው በመግለጫው የተነሳው።
የጥናቱ ስራ በአጭር ጊዜ ውስጥ እንዲጠናቀቅም ከሰው ሀይል ባሻገር #የሶፍትዌር ዝግጅት መደረጉን ፎረሙ የጥናትን መርህ እና አካሄድ ጠንቅቀው በሚያውቁ እስከ ሁለተኛ እና ሶስተኛ ዲግሪ ባላቸው የክልሉ ተወላጆች የሚደረገውን ጥናት ለክልሉ መንግስት እንደ ግብአት አቀርባለሁ ብሏል።
የጥናቱ ውጤት ውሳኔ ሰጪ ሳይሆን እንደ ምክረ ሀሳብ የሚቀርብ መሆኑንም ፎረሙ በመግለጫው አንስቷል።
ምንጭ፦ ፋና ብሮድካስቲንግ

ኢትዮጵያን በጋራ እንገንባ...!
ጥላቻው፣ ስድቡ፣ ብሽሽቁ፣ ተንኮሉ፣ ለጦርነት መንደርደሩ፣ ለመጠፋፋት መቸኮሉ፣ ሀገር #ለማፍረስ መሯሯጡ፣ ለመለያየት መንገብገቡ፣ ደም ለመፋሰስ መፎከሩ~~#ይቅርብን ወገኖቼ! ሰፊ ሀገር፤ ለሁላችም የምትበቃ፤ ለሁላችንም የምትሆን ለምለም ሀገር አለችን #ሰርተን እንደግባት። ቢያንስ ለኛ እና ለልጆቻችን #የምትመች ሀገር መገንባት ባንችል፤ ለልጅ ልጆቻችን የምትሆነዋን ሰላማዊ፤ ምቹ ሀገር፣ ሰዎች የሚከባበሩባትን ሀገር፣ ሰዎች ተቻችለው የሚኖሩባትን ሀገር በጋራ እንገንባ!
.
.
🔙የኃልዮሽ ጉዞ ይቅርብን!
#TIKVAHETHIOPIA #ቲክቫህኢትዮጵያ
#ሼር #share

የ12 ሰዓት ፌስቡክ ዘመቻ🔝ከላይ ያለውን #ፅሁፍ #ከፎቶዎቹ ጋር በፌስቡክ ገፃችን ላይ ፖስት በማድረግ እንደ TIKVAH-ETH ቤተሰብ አባልነት ሀላፊነታችንን እንወጣ!
@tsegabwolde @tikvahethiopia
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#ጉዞ_ዓድዋ_6🔝
ታላቁን የዓድዋ ድል ለመዘከር በየአመቱ የሚካሔደው የእግር ጉዞ ዘንድሮም ለ6ኛ ግዜ ቀጥሏል። ከሐረርና አዲስ አበባ የተነሱት ተጓዦች በድምሩ ከሺህ በላይ ኪሎሜትሮችን አቋርጠው #መቐለ_ከተማ እንደገቡ ታላቁን ኢትዮጵያዊ ጀግና ራስ አሉላ እንግዳን (አባ ነጋ) ለማስታወስ የሽሬ ልጆች መቐለ ከተማ በመግባት የአዲስ አበባ እና የሐረር ተጓዦችን ተቀላቅለዋል።
ብዛታቸው 5 የሆኑት #የሽሬ_ልጆች ከመቐለ እስከ ዓድዋ እናት ሀገራቸው ኢትዮጵያን እና ታላቁን የዓድዋ ድል ለማግዘፍ እንደ ታላቁ ራስ አሉላ አባ ነጋ ከወንድም እህቶቻቸው ጋር ተቀላቅለዋል።
"ታሪካዊ #ጀግኖቻችን የልዩነታችን ምክንያት ሳይሆኑ የአንድነታችን መሰረት ናቸው"
#ፍቅር_ለኢትዮጵያ !!
#የምናቋርጣቸው_የሀገራችንን_መንደሮች_እንጂ_ድንበሮች_አይደለም
#ኢትዮጵያዊነት_ይለምልም
Via Yared Shumete

ሜጀር ጄኔራል መሀሪ ዘውዴ🔝
ሜጀር ጄኔራል መሀሪ ዘውዴ ገ/ማሪያም የአብዬ #ጊዚያዊ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት #የጦር_ሀይል_አዛዥ ሆነው መሾማቸውን የተባበሩት መንግስታት ሴክሬታሪ ጄኔራል አንቶኒ ጉቴሬዝ አስታወቁ፡፡ ሜጀር ጄኔራል መሀሪ እንደ እ.ኤ.አ በሚያዝያ 23/ 2019 የስራ ጊዚያቸውን የሚያጠናቅቁትን ሜጀር ጄኔራል ገብሬ አድሃና ወልደዝጉን ተክተው ይሰራሉ ተብሏል፡፡
አንቶኒዮ ጉቴሬዝ ለተሰናባቹ ሜጀር ጄኔራል ገብሬ አድሃና ደከመኝ ሳይሉ ላደረጉት አገልግሎትና በተመድ ለነበራቸው ውጤታማ የአመራር ጊዜ #ምስጋናቸውን አቅርበዋል፡፡
ጄኔራል ሴክሬቴሪያቱ በንግግራቸው ሜጄር ጄኔራል መሀሪ ዘውዴ ከኢትዮጵያ የታጠቁ ሀይሎች ጋር በመሆን ለ37 ዓመታት ማገልገላቸውን ገልጸው በቅርቡ የኢትዮጵያ የመከላከያ የሰው ሀይል ኃላፊ በመሆንና ለምድር ጦሩ እና ለአጠቃላይ የመከላከያ ሀይሉ የሰው ሀይልና የአስተዳደር ስራ በሀላፊነት መስራታቸውን አክለዋ፡፡ የኢትዮጵያ ብሄራዊ የመከላከያ ሚኒስቴር የአማካሪ አባል በመሆን ከ2007 ጀምሮ ሰርተዋል፡፡
ለኢትዮጵያ አየር ሀይል ከ2001-2007 ምክትል ኮማንደር፣ ለምስራቁ የአየር ሀይል ዕዝ በኮማንደርነት በ1989-1997 እና በሌሎች ተሳትፎዎችም ከኢትዮጵያ ታጣቂ ሀይሎች ጋር አገልግለዋል፡፡ሜጀር ጄኔራል መሀሪ ዘውዴ በብሪታንያ ከሚገኘው ግሪን ዊች ዩኒቨርስቲ በሳይንስ የማሰተርስ ድግሪ አግኝተዋል፡፡
ምንጭ፦ etv

#update ላለፉት 2 ሳምንታት ዝግ ሆኖ የቆየው የጎንደር-መተማ/ሱዳን መንገድ #አገልግሎት መስጠት ጀምሯል። መንገዱ የተዘጋው በአካባቢው ግጭት መከሰቱን ተከትሎ ታጣቂዎች አሽከርካሪዎችንና መንገደኞችን በማገት የማስለቀቂያ ገንዘብ መጠየቅ በመጀመራቸው ነበር።
Via ELU
@tsegabwolde @tikvahethiopia
Via ELU
@tsegabwolde @tikvahethiopia