TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
59.4K photos
1.51K videos
215 files
4.12K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#update በምዕራብ ኦሮሚያና ደቡብ ምስራቅ ጉጂ አካባቢ ተፈጥሮ የነበረው ችግር #እየተቀረፈ በመምጣቱ ነዋሪው ወደ #ሰላማዊው እንቅስቃሴ መመለሱ የኦሮሚያ ክልል የመንግሥት ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ አስታውቋል፡፡

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ፎቶ~ትግራይ🔝

"የጉዞ አድዋ" የእግር ተጓዦች #በትግራይ! #ጉዞ_ዓድዋ_6! ሰላም፤ ፍቅር፤ አንድነት! #ኢትዮጵያ #ETHIOPIA

@tsegabwolde @tikvahethiopia
በመኪና አደጋ የሰው ህይወት አለፈ🔝

"ሃይ ፀግሽ በወሊሶ እና ወልቂጤ መሀል እኛ #የነበርንበት መኪና ከሀይሩፍ መኪና ጋር ተጋጭቶ እስካሁን አራት ሰዉ እንደሞተ አይቻለሁ። ነፍስ ይማር።"
.
.
አደጋው የደረሰው #ሀይሩፍ እየተባለ የሚጠራ መኪና ከሌላ የህዝብ ማመላለሻ መኪና ጋር በመጋጨቱ ነው። አደጋው የደረሰው በወልቂጤና ወሊሶ መሃል ነው።
.
.
• ዉዱ የሰው ልጅ ህይወት ዛሬም በትራፊክ አደጋ እየጠፋ ነው፤ ምን ይሻላል?? ምን ይበጀናል?? በነገራችን ላይ ከሚላኩልኝ የትራፊክ አደጋ መልዕክቶች እኔ የማቀርበው ጥቂቱን ብቻ ነው።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
መቐለ🔝

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር አድዋ ላይ ለሚገነባው #የፓን_አፍሪካ_ዩኒቨርሲቲ ግንባታ ማስጀመሪያ የ10 ሚሊዮን ብር ድጋፍ አደረገ፡፡

44ኛው የህወሓት የምስረታ በዓልን ምክንያት በማድረግ ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የተውጣጡ ወጣቶችን ቡድን በመመምራት የከተማ አስተዳድር ምክትል ከንቲባ ዶ/ር ሰለሞን ኪዳኔ በመቐለ ከተማ ጉብኝት እያደረጉ ነው፡፡

ዶ/ር #ሰለሞን እንዳሉት ለፓን አፍሪካ ዩኒቨርሲቲ ግንባታ የከተማ አስተዳድሩ አሁን ከሰጠው ድጋፍ በተጨማሪ በቀጣይም ድጋፉን ተጠናክሮ እንደሚቀጥል አመልክተዋል፡፡ ምክትል ከንቲባው በመቐለ ከተማ ለሰመዓታት የአበባ ጉን ጉን አኑረዋል፡፡

Via ETV
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ከጎንደር ዩኒቨርሲቲ🔝

"ጎንደር ዩኒቨርስቲ በዛሬው እለት በቴክኖሎጂ ኢንሰቲትዩት ግቢ የኪነ ሕንፃ (አርክቴክቸር) 5 አመት ከ5 ወር ያስተማራቸውን ተማሪዎችን እያስመረቀ ይገኛል።"

@tsegabwolde @tikvahethiopia