TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.8K photos
1.44K videos
207 files
3.99K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
#ትግራይ " ህጋዊ ያልሆነ ጉባኤ ያካሄደው ህጋዊ ያልሆነው ቡድን የሚመድባቸው አስተዳዳሪዎች እና የስራ ሃላፊዎች የሚያስተዳድሩት ሃብት የለም " ሲል የትግራይ ጊዚያዊ አስተዳደር አስታወቀ። ጊዚያዊ አስተዳደሩ ይህን ያለው በፕሬዜዳንት ፅ/ቤት በኩል ባወጣው መግለጫ ነው። " ህጋዊ ያልሆነው ቡድን "  ሲል የገለፀው በደብረፅዮን ገ/ሚካኤል (ዶ/ር) የሚመራው ህወሓት ግልፅ የመንግስት ግልበጣ አካሂደዋል…
#Tigray

🔴 " ተኩስ ተከፍቶብኝ መኪናዬ ላይ ጉዳት ደርሷል " - አቶ ሰለሙን መዓሾ

🟠 " መረጃው ከእውነት የራቀ ነው። የተኮሰበት ሰው የለም " - አቶ ገብረ ተክለሃይማኖት

🔵 " ፓለቲከኞች የልዩነታችሁ ጣጣችሁን እዛው ጨርሱት ወደ ሰራዊቱ አታጋቡት " - ጀነራል ህንፃ ወ/ጊዮርጊስ

የትግራይ ክልል ጊዚያዊ አስተዳደር ከፍተኛ አመራር ከተቃጣባቸው የግድያ ሙከራ ማምለጣቸውን ተሰምቷል።

የጊዚያዊ አስተዳደሩ የማእከላዊ ዞን ዋና አስተዳዳሪ ሰለሙን መዓሾ ባለፈው እሁድ ህዳር 8/2017 ዓ.ም ከስራ ባለደርቦቻቸው ጋር ከአክሱም ወደ መቐለ ሰጓዙ የግድያ ሙከራ እንደ ተቃጣባቸውና ከግድያ ሙከራው እንደተረፉ ተናግረዋል።

የዞኑ ዋና አስተዳዳሪ ለቪኦኤ በሰጡት ቃል ከአክሱም ወደ መቐለ ሲመለሱ ማይቅነጣል ፈላፍል በተባለ ቦታ ሲደርሱ መኪናቸው ላይ ተኩስ እንደተከፍተባቸው ገልጸዋል።

ለጊዜው እነማን እንደተኮሱባቸው ማንነታቸውን / የታጣቂዎችን ማንነት ማወቅ እንዳልቻሉ ገልጸው በተተኮሰባቸው ጥይቶች መኪናቸው ላይ ጉዳት መድረሱን አስረድተዋል።

በጥይት የተመታው መኪናቸውን የሚያሳይ ፎቶም ይፋ አድርገዋል።

በመኪናው ውስጥ ከእሳቸው በተጨማሪ ጥበቃቸው እና የመኪናው ሹፌር ነበሩ።

ዋና አስተዳዳሪው የደረሰባቸው አካላዊ ጉዳት እንደሌለ አረጋግጠዋል።

እሁድ ህዳር 8 ቀን 2017 ዓ.ም በዋና አስተዳዳሪ ሰለሙን መዓሾ የመግደል ሙከራ መደረጉ በማህበራዊ የትስስር ገፆች ላይ በስፋት ከተሰራጨ በኃላ ቲክቫህ ኢትዮጵያ ወደ ማይቅነጣል ወረዳ ስልክ ቢደውልም ጉዳዩ የሚያረጋግጥ አካል አልተገኘም ነበር።

የዞኑ መቀመጫ ወደሆነችው አክሱም የሚገኝ ፓሊስ ማዘዣ ስልክ ቢደወልም የተጣራ መረጃ ማግኘት አልተቻለም።

ይህ በእንዲህ እያለ የመግደል መከራ ተቃጥቶበታል የተባለው ቦታ የሚያስተዳድረው የማይ ቅነጣል ወረዳ " ጉዳዩ አልተፈፀመም " የሚል መግለጫ አውጥቷል።

የማይቅነጣል ወረዳ አስተዳዳሪ አቶ ገብረ ተክለሃይማኖት ለቪኦኤ በሰጡት ቃል ደግሞ ፣ ጉዳዩን ከወረዳው የጸጥታና ፖሊስ አባላት ማጣራታቸውን ገልፀው፣ " መረጃው ከእውነት የራቀ ነው። የተኮሰበት ሰው የለም " ብለዋል።

ከዚህ ባለፈ " በአከባቢው አለ ጉዳዩ ፈፅሞታል " ተብሎ በማህበራዊ የትስስር ገፅ ተጠቃሚዎች ተደጋግሞ የተጠቀሰው የትግራይ ሰራዊት አርሚ 60 አዛዥ ጀነራል ህንፃ ወ/ጊዮርጊስ እሳቸው የሚያዙት በፀሃፊዎቹ የተገለፀው ሰራዊት በአከባቢው እንደሌለ በመግለፅ " ፓለቲከኞች የልዩነታችሁ ጣጣችሁን እዛው ጨርሱት ወደ ሰራዊቱ አታጋቡት " ሲሉ ተጠምደዋል።

ከአሁን በፊት በተለያዩ ጊዚያት መሰል የግደያ ሙከራዎች በጊዜያዊ አስተዳደሩ ከፍተኛ ሹማመንት በየነ መኩሩ ፣ ነጋ ኣሰፋ ፣ ሰሎሙን ትኩእ እንዲሁም በአክሱም ከተማ አስተዳደር ከፍተኛ አመራር መደረጋቸው የተነገረ ቢሆንም እስካሁን የድርጊቱ ፈፃሚዎች ተጣርተው የተወሰደ እርምጃ የለም።

#VOATigrigna #TikvahEthiopiaFamilyMekelle

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#ትግራይ " የፌደራል መንግስት ውስጣዊ ችግራችን በውይይት መፍታት ካልቻልን ትግራይን የማስተዳደር ስልጣኑን ብልፅግና በብቸኝነት እንደሚይዘው በግልፅ ነግሮናል " - አቶ ጌታቸው ረዳ የትግራይ ጊዚያዊ አስተዳደር ፕሬዜዳንት ጌታቸው ረዳ  ወደ ሁለት በተከፈሉ የህወሓት አመራሮች እየታመሰ የሚገኘው የክልሉ የፓለቲካ ሁኔታ ከመሻሻል ይልቅ ተባብሶ መቀጠሉ ተናግረዋል። " በምንገኝበት የአፍሪካ ቀንድ ከፍተኛ…
" አቶ ጌታቸው ረዳ የቀድሞ ፕሬዝዳንት ናቸው " - አቶ አማኑኤል አሰፋ

በደብረጽዮን ገብረሚካኤል (ዶ/ር) በሚመራው ህወሓት ጉባኤ ምክትል ሊቀመንበር ሆነው የተመረጡት አቶ አማኑኤል አሰፋ ዛሬ መግለጫ ሰጥተው ነበር።

በዚህ መግለጫቸው ላይ የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዝዳንት አቶ ጌታቸው ረዳ በባለፈው ጉባኤ ከሥልጣን የተነሱ በመሆናቸው " ፕሬዝደንትነታቸውን አንቀበልም " ብለዋል።

አቶ ጌታቸውን " የቀድሞው ፕሬዝዳንት " ሲሉም ጠርተዋቸዋል።

አቶ አማኑኤል " የጊዚያዊ አስተዳደሩ አመራሮች ህወሓትን በአመፅ ለመበተን ወጣቶች እያሰለጠኑ ናቸው ሲሉ " ወንጅለዋል።

ከዚህ በተጨማሪ ፦

- የትግራይ ጊዚያዊ አስተዳደር ለሁለት ዓመት ያለ እቅድ እየተመራ ይገኛል።

- ጊዚያዊ አስተዳደሩ ተቆጠረው የተሰጡት ተልእኮዎች ከመፈፀም ይልቅ በተቃራነው ነው እየሰራ ያለው።

- ህወሓት በጊዝያዊ አስተዳደሩ ያለውን የስልጣን ውክልና ካነሳ ወራት ተቆጥሯል።

- በጊዚያዊ አስተዳደሩ የስልጣን ክፍፍል ላይ ህወሓትን የሚተካ አመራር ከፌደራል መንግስት በመወያየት ይተገበራል። ይህንን ለመተግበር የሚያስችል ተከታታይ ውይይት ከፌደራል መንግስት እየተካሄድ ነው። ስምምነት ከተደረሰበት በኋላ መግለጫ ይሰጥበታል።

- በዲሞብላይዜሽን (DDR) አሰራር ታጣቂዎች ወደ ህብረተሰቡ መቀላቀል ከፌደራሉ የሀገር መከላከያ ሰራዊት ውጪ በትግራይ ግዛት ያሉ የውስጥ እና የውጪ ታጣቂዎች ተሟልተው ወጥተው ተፈናቃዮች ወደ ቄያቸው ከመመለስ ጎን ለጎን መፈፀም እንዳለበት የፕሪቶሪያ ውል አስቀምጠዋል አሁን ግን የታጣቃዎች ዲሞብላይዜሽን (DDR) እየተመራበት ያለው አሰራር ትክክል አይደለም።

- በዲሞብላይዜሽን ትግበራ (DDR) ለሚሰናበት ታጣቂ የሚሰጠው ማቋቋምያ አነስተኛ እና በቂ አይደለም። በዳታ አሰባሰብ (ባዮሜትሪክስ) ያለው አካሄድም ግልፅነት የጎደለው ነው።

- እየተካሄደ ያለው የDDR ትግበራ ከፕሪቶሪያ የሰላም ስምምነት አግባብ ውጪ ነው።

- ጊዚያዊ አስተዳሩ የተሰጡት ሃላፊነቶች ወደ ጎን በመተው ህወሓት በማፍረስና እና ሌላ ህወሓት በማዋለድ ይውላል።

- ሰራዊት ተቆጣጥሮ ወታደራዊ ስርዓት ለመትከል ይንቀሳቀሳል፤ በሪፎርም ስም የወረዳና የቀበሌ ምክር ቤቶች ያፈርሳል ፤ የህዝብ እና የሰራዊት አንድነት ለመበተን ይንቀሳቀሳል።

- የጊዚያዊ አስተዳደሩ ልኡክ በምርጫ ስልጣን የሚይዝ መንግስት እንዲቋቋም ምቹ ሁኔታ መፍጠር ነው። ይሁን እንጂ ተከታታይ ውይይቶች በማካሄድ ራሱ ወደ መደበኛ መንግስት ለመቀየር እየሰራ ነው።

... ብለዋል።

ከቀናት በፊት የጊዜያዊ አስተዳደሩ ፕሬዜዳንት አቶ ጌታቸው ረዳ መግለጫ በሰጡበት ወቅት በደብረጽዮን ገብረ ሚካኤል (ዶ/ር) የሚመራው ህወሓት ቡድን አስተዳደሩ ስራ እንዳይሰራ እያደናቀፈ ስለመሆኑ የወረዳ ምክር ቤቶችን በመጠቀምም አስተዳዳሪዎች እንዲነሱ እያደረገ መሆኑን ይህም " መፈንቅለ መንግስት " እንደሆነ መግለጻቸው ይታወሳል።

ከዚህ ባለፈ ለሁለት የተሰነጠቁት የህወሓት አመራሮች ተስማምተው ክልሉን መምራት ካልቻሉ ብልፅግና የትግራይ አስተዳደርን ሙሉ በሙሉ ለመረከብ እንደሚገደድ ከፌደራል መንግስት ጋር በተካሄደ ወይይት መነሳቱን ተናግረው ነበር።

NB. ዛሬ መግለጫ የሰጡት አቶ አማኑኤል አሰፋ ፤ አቶ ጌታቸው ረዳን የቀድሞ ፕሬዝዳንት ካሉና ህወሓት በአስተዳደሩ ያለውን ውክልና ካነሳ ወራት መቆጠሩን ከገለጹ በኃላ " በጊዚያዊ አስተዳደሩ የስልጣን ክፍፍል ህወሓትን የሚተካ አመራር ከፌደራል መንግስት በመወያየት ይተገበራል። ይህንን ለመተግበር የሚያስችል ተከታታይ ውይይት ከፌደራል መንግስት እየተካሄደ ነው " ሲሉ ቢገልጹም ከየትኛው የፌዴራል መንግስት አካል ጋር ንግግር እየተደረገ እንዳለ በግልጽ አውጥተው አልተናገሩም። የፌዴራል መንግስት እስካሁን በህወሓት አመራሮች ክፍልል ጉዳይ ምንም አይነት ይፋዊ ቃል ሰጥቶ አያውቅም።

#TikvahEthiopiaMekelle #VOATigrigna

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
" አቶ ጌታቸው ረዳ የቀድሞ ፕሬዝዳንት ናቸው " - አቶ አማኑኤል አሰፋ በደብረጽዮን ገብረሚካኤል (ዶ/ር) በሚመራው ህወሓት ጉባኤ ምክትል ሊቀመንበር ሆነው የተመረጡት አቶ አማኑኤል አሰፋ ዛሬ መግለጫ ሰጥተው ነበር። በዚህ መግለጫቸው ላይ የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዝዳንት አቶ ጌታቸው ረዳ በባለፈው ጉባኤ ከሥልጣን የተነሱ በመሆናቸው " ፕሬዝደንትነታቸውን አንቀበልም " ብለዋል። አቶ ጌታቸውን…
#TPLF

ለመሆኑ አቶ ጌታቸው ረዳ ' የቀድሞው ' ከተባሉ ክልሉን (ትግራይን) ማነው እያስተዳደረ ያለው ? ይህ በደብረጽዮን ገ/ሚካኤል (ዶ/ር) ለሚመራው ህወሓት ምክትል ሊቀመንበር አቶ አማኑኤል አሰፋ የቀረበ ጥያቄ ነው።

አቶ አማኑኤል አሰፋ ይህን ጥያቄ የተጠየቁት አቶ ጌታቸው ረዳን " የቀድሞው ፕዜዳንት " ብለው በመጥራታቸው ነው።

" የፕሬዜዳንት ውክልና ሲነሳ ፕሬዜዳንቱ በሌለበት ማን እንደሚሰራ ይታወቃል " ያሉት አቶ አማኑኤል " ኃላፊ በሌለበት ጊዜ እሱን ተክቶ የሚሰራ እንዳለ ይታወቃል ምንም የስልጣን ክፍተት አይፈጠርም ህወሓት የወከላቸውን የተወሰኑ ሰዎች ውክልና አንስቷል ውክልናውን ስላነሳን ነው የቀድሞ ፕሬዜዳንት የሚለውን ቃል የተጠቀምኩት " ሲሉ ለተነሳው ጥያቄ መልስ ሰጥተዋል።

በግልጽ አሁን ላይ በእሳቸው አመለካከት ክልሉን ማን እየመራ እንዳለ አልጠቀሱም።

" ፕሬዝዳንቱን የሚተካ ሰውን በሚመለከት ህወሓት ከፌዴራል መንግሥት ጋር እየተነጋገር ነው " ያሉት አቶ አማኑኤል " ውጤቱ ይፋ ይደረጋል " ብለዋል።

እዚህ ላይም ከየትኛው የፌዴራል አካል ጋር ንግግር እያደረጉ እንደሆነ በግልጽ አልተናገሩም። የፌዴራል መንግሥትም በህወሓት ክፍፍል ጉዳይ ምንም ቃል ሰጥቶ አያውቅም።

በሌላ በኩል ፤ ከቀናት በፊት የጊዜያዊ አስተዳደሩ ፕሬዝዳንት አቶ ጌታቸው ረዳ በሰጡት መግለጫ የህወሓት አመራሮች በውስጣቸው ያለውን ክፍፍልና ልዩነት ካልፈቱ የክልሉን አስተዳደር ፌዴራሉ መንግሥት ሊይዘው እንደሚችል ማሰስቡን ገልጸው ነበር።

አቶ አማኑኤል ግን " ይህ ከሀቅ የራቀ ነው " ሲሉ አጣጥለዋል።

" ' እዚህ ተስማምተን ካልተንቀሳቀስን 'የጊዜያዊ አስታዳደሩን ስልጣን ብልፅግና ይረከበዋል ተብሏል ' ተብሎ የተነገረው ፍጹም የተሳሳተ ነው ወደዚህ ደረጃም አልደረስንም እንዲህ አይነት መልስም አልተሰጠም። ከፌዴራል መንግሥት ጋር የተጀመረው ውይይት ይቀጥላል " ሲሉ ተናግረዋል።

በተጨማሪ አቶ አማኑኤል አሰፋ ፦
° ከባለፈው ጉባኤ በኃላ ፓርቲያቸው በወረዳና ከተሞች የአመራር ማስተካከያ ማድረጉን ፤
° የወረዳና ከተማች ምክር ቤት በህወሓት አብላጫ ወንበር የተያዘ በመሆኑ የተሻለ አመራር መመደቡን፤
° በጊዜያዊ አስተዳደሩ የሚገኙ ፕሬዜዳንቱን ጨምሮ 13 አመራሮች ውክልና ቀድሞ መነሳቱን ገልጸዋል።

" ህወሓትንም ሆነ የመንግሥት ስልጣንን በተመለከተ ድርድር አይደረግም " ያሉ ሲሆን " በመቶ ሺህ የሚቆጠር አባል ያለው ፓርቲ ነው ያለን ከፓርቲው የወጡ ሰዎች መመለስ ከፈለጉ በአሰራሩ መሰረት የይቅርታ ደብዳቤ በማስገባት ነው መመለስ የሚችሉት " ብለዋል።

የጊዜያዊ አስተዳደሩ ፕሬዜዳንት አቶ ጌታቸው ረዳ ፤ የደብረጽዮን (ዶ/ር) ቡድን አስተዳደሩ ስራ እንዳይሰራ እንቅፋት ከመሆን ባለፈ የወረዳ ምክር ቤቶችን በመጠቀም አስተዳዳሪዎችን ከቦታቸው እንዲነሱ እያደረገ ነው ይህ " መፈንቅለ መንግሥት ነው " ብለው ነበር።

#VOATigrigna

#TPLF #Tigray

@tikvahethiopia