TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.8K photos
1.44K videos
207 files
3.99K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
ወላይታ 🕊 ሲዳማ!

የወላይታና የሲዳማ ህዝቦች ሰላም ወዳድ፣ ጠንካራ #ፍቅር ያላቸውና ተለያይተው መኖር የማይችሉ መሆናቸውን አረጋግጠናል ሲሉ የሲዳማና ወላይታ ገለልተኛ አስታራቂ አባቶች ገለጹ፡፡

በህዝቦች መካከል ለዘመናት የቆየው አብሮነትና አንድነት ከጠፋ አገሪቱን ወደሚፈለገው የዕድገት ደረጃ ላይ ማድረስ ስለማይቻል ህዝቡ ሰላምና አብሮነቱን ማጠናከር እንዳለበት አባቶቹ መክረዋል።

በወላይታና ሲዳማ ተወላጆች መካከል ተከስቶ የነበረውን አለመግባባት ወደሰላም ለመመለስ ፈታኝና እልህ አስጨራሽ የእርቅ ሂደት ማለፋቸውን የተናገሩት አስታራቂ አባቶቹ ሁለቱ ህዝቦች ሰላም ወዳድ፣ እርስ በርስ ፍቅር ያላቸውና መለያየት እንደማይችሉ ማረጋገጣቸውን ገልጸዋል።

የገለልተኛ አስታራቂ ኮሚቴው ሰብሳቢ መጋቢ ጌቱ አያሌው እርቅ ለማውረድ በተደረገው ጥረት በሁለቱ ወንድማማች ህዝብ መካከል ተፈጥሮ የነበረው የጥል ግድግዳ መፍረሱንና በእዚህም ደስተኛ መሆናቸውን ገልጸዋል፡፡

“ሁለቱን ህዝብ ለማስታረቅ እልህ አስጨራሽና ፈታኝ ወቅት አልፈናል” ያሉት መጋቤ ጌቱ፣ ሠላምና እርቅ የማይፈልጉ ሁለቱንም ብሄር የማይወክሉ ግለሰቦች በአካልና በማህበራዊ ሚዲያ ስም የማጥፋት፣ የማስፈራራትና ተስፋ የማስቆረጥ ሥራዎችን ቢሰሩም እርቁ በስኬት መጠናቀቁን ገልጸዋል።

ዕርቀ ሰላሙን ለማውረድ ከሁለቱም ብሔር አገር ሸማግሌዎች ጋር ለአራት ወራት የመከሩ ሲሆን በእዚህም ሁለቱም ህዝቦች ሰላም ወዳድ ከመሆናቸው ባለፈ እርስ በርስ የሚፋቀሩና ተለያይተው መኖር የማይችሉ ናቸው።

በህዝቦች መካከል ያለውን አብሮነትና አንድነት በመጠበቅ በአገሪቱ የሚፈለገውን እድገት ለማምጣት ተረባርቦ መስራት እንደሚገባም  አሳስበዋል፡፡

የሃዋሳ ቅዱስ ገብርኤል ገዳም አስተዳዳሪ መላከ ምህረት ቆሞስ አባ ጌዲዮን ብርሃን በበኩላቸው መነጣጠል የማይችሉ ሁለቱ ህዝቦች በመታረቃቸው ከማንም በላይ የተለየ ደስታ እንደተሰማቸው ነው የገለጹት።

በእርቅ ሂደት ውስጥ የሲዳማና የወላይታ አገር ሸማግሌዎች ሠላም ለማውረድ ከፍተኛ እገዛ ማድረጋቸውንና የክልሉና የሁለቱ ዞን የመንግስት አካላትም ላሳዩት ቀና ትብብር ምስጋናቸውን አቅርበዋል፡፡

የእርቀ ሠላም ጉባኤው ለኢትዮጵያውንና ህዝብን ለማበጣበጥና የአገሪቱን ሠላም ለማድፍረስ ደፋ ቀና ለሚሉ አካላት ትልቅ ትምህርት የሰጠ መሆኑንም ተናግረዋል፡፡

“ኢትዮጵያውያን ያለንን አብሮነትና አንድነት ካጣን ወደምናስበው የእድገት ደረጃ መድረስ ስለማንችል ቆም ብለን ልናስብ ይገባል” ሲሉም መላከ ምህረት ቆሞስ አባ ጌዲዮን አመልክተዋል፡፡

የኢትዮጵያ ወጣት ፍቅርና አንድነቱን ጠብቆ በማቆየት ሰላምና ልማቷ የተረጋገጠ አገር ለቀጣይ ትውልድ ማስተላለፍ እንዳለበት አውቆ ለእዚያ መንቀሳቀስ እንዳለበትም መክረዋል፡፡

ከአላህ ዘንድ የተሰጣቸውን ትልቅ ኃላፊነት በስኬት በማጠናቀቃቸው ሀሴት እንደተሰማቸው የገለጹት ደግሞ የደቡብ ክልል እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት ምክትል ፕሬዚዳንትና የገለልተኛ አስታራቂ ኮሚቴ አባል ሃጂ አህባበብ አባ ጀማል ናቸው፡፡

የሲዳማና የወላይታ አገር ሸማግሌዎች ሰላም የሚሹ ፣ የተጎራበቱ፣ የተጋቡና የተዋለዱ መሆናቸውን ያረጋገጡበት የእርቅ ሂደት መሆኑን የገለጹት ሃጂ አህባበብ፣ ሰላም አንዲወርድ እንደኮሚቴ ከፍተኛ ጥረት ማድረጋቸውን ተናግረዋል፡፡

ለአብሮነትና ለሠላም ቅርብ በሆኑ ህዝቦች መካከል ተፈጥሮ በነበረው ግጭት የተከሰተው መራራቅና አለመተማመን በአሁኑ ወቅት መፈታቱንና በቀጣይም ለዘላቂ ሰላም በቅንጅት እንደሚሰሩ ገልጸዋል፡፡

በቅርቡ በሃዋሳና በሶዶ ከተማ የተካሄደው የሁለቱ ህዝቦች የይቅርታና እርቅ ኮንፈረንስ በገለልተኛ አስታራቂ ሽማግሌዎች ላለፉት አራት ወራት የተለያዩ ሂደቶችን ያለፈ መሆኑን ታውቋል፡፡

ምንጭ፦ ኢ.ዜ.አ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
የደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ🔝

‹‹እኛ ተማሪዎች ለህዝባችን አንድነት ምሰሶ ፤ #ለችግሮቻችን መፍቻ ቁልፍ እንጂ ለቁርሾዎች መነሻ መሆን የለብንም። ተማሪዎች ህዝባችንን #በድህነት ያስቀሩ ድክመቶቻችን የምንቀርፍ ኃይሎች እንጂ የቁርሾ መመስረቻዎች መሆን አንፈልግም፡፡›› የደብረ ማርቆስ ተማሪዎች

ተማሪዎቹ በትላንትናው ዕለት ባካሄዱት ሰላማዊ ሰልፍ #አብሮነትን የሚያጠናክሩ ሀሳቦች ተነስተዋል፡፡

• የአማራ እና ኦሮሞ ህዝቦች አንድነት #ለኢትዮጵያውያን ደኅንነት እንዲሆን አሻራችንን እናሳርፋለን ። እኛ አንድ ህዝቦች ነን ። አንድ ህዝብ መሆናችን ዩኒቨርሲቲዎች ምሳሌ እንዲሆኑ እንሰራለን ።

• እኛ ተማሪዎች ህዝባችንን በድህነት ያስቀሩ ድክመቶቻችን የምንቀርፍ ሀይሎች እንጂ የቁርሾ መመስረቻዎች መሆን አንፈልግም።

• ወደ ቤተሰቦቻችን ይዘን የምንመለሰው #ፍቅር እና #መፍትሄን እንጂ #ልዩነት አይሆንም።

• የምንማረው ህዝባችንን በፍቅር ለመምራት ነው ፤ #አንድነታችንን የሚያሳጡ ሀሳቦች እንዳይተባበሩ እናድርግ።

• ደም የመተካኪያ ፍሬ እንጂ ከዛሬ በኋላ የልዮነት ሀሳብ ሁኖ #ለሚከፋፍሉን እድል ሰጥቶ ወደኋላ የሚመልሰን ሊሆን አይገባም።

በደም ተለያይተን በድህነት ውስጥ መኖር በለውጡ ትውልድ አይቀጥልም፤ የሚል ሰላማዊ ሰልፍ ግቢያቸው ላይ በማድረግ ሀሳባቸውን ገልፀዋል።

ምንጭ፦ አብመድ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ሰበር ዜና‼️

ጉዞ ዓድዋ 6 ተጀመረ!! ታሪካዊቷ የሐረር ከተማ የዘንድሮ ጉዞ መነሻ ተደርጋ ተመርጣለች።

"ፍቅር ለኢትዮጵያ" የሚል መርሕ የያዘው የዘንድሮ የእግር ጉዞ መነሻውን ከሀረር ከተማ በማድረግ ጥር 7 ቀን 2011 ዓ.ም ከአዲስ አበባ የሚነሱ ተጓዦችን በመቀላቀል የካቲት 23 ቀን 2011 ዓ.ም. በታሪካዊቷ ዓድዋ ከተማ ይጠናቀቃል።

በትናትናው ምሽት በድሬዳዋ ከተማ በተካሔደው የመሸኛ ስነሥርዓት ላይ የተገኙት የድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አቶ ኢብራሂም ኡስማን ባደረጉት ንግግር "ዓድዋ የመላው ኢትዮጵያዊያን ህብረት ያታየበት ሁላችንም የምንኮራበት ድላችን መሆኑን ጠቅሰው፤ ይህንን ድል ለመዘከር በየአመቱ የሚዘጋጀውን የጉዞ ዓድዋ እንቅስቃሴ የከተማ አስተዳደሩ ቅድሚያ ሰጥቶ እንደሚያግዝ አረጋግጠው የዘንድሮው 123ኛ የዓድዋ ድል በዓል አከባበር መጀመሩን በይፋ አብስረው፤ ለተጓዦች መልካም መንገድ ተመኝተዋል።

በታላቁ የዓድዋ ጦርነት ወቅት የምስራቅ ኢትዮጵያን ጦር የመሩት የቀዳሚው ጦር አዝማች ልዑል ራስ መኮንን ከተነሱበት የሐረር ከተማ በ5 ተጓዦች የተጀመረው የዘንድሮው ጉዞ ዓድዋ በተለያዩ ደማቅ ሥነስርዓቶች ለመካሔድ በዛሬው እለት ታህሳስ 21 ቀን 2011 ዓ.ም. ተጀምሯል።
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ ኢንጂነር ታከለ ኡማ ለጉዞ ዓድዋ አዘጋጆች በስልክ እንዳረጋገጡት የከተማ አስተዳደሩ ከሀረር የተነሱ ተጓዦችን ተቀብሎ በመሸኘት እና ከአዲስ አበባ የሚነሱ ተጓዦችን አሰፈላጊውን ስንቅ አሟልቶ በመሸኘት የከተማ አስተዳደሩ አጋርነቱን ያሳያል።

፨፨፨
የፍቅር ዘመቻው ሠላምን እና አብሮነትን ሰንቆ በዓድዋ ተራሮች አናት ላይ የካቲት 23 ቀን በድል ይጠናቀቃል።
የጉዞ ዓድዋ አስተባባሪዎች
መሐመድ ካሳ
ያሬድ ሹመቴ
#ፍቅር_ለኢትዮጵያ
#ኢትዮጵያዊነት_ይለምልም !!
#ጉዞ_ዓድዋ_6
#ከሐረር_አዲስ_አበባ_ዓድዋ
#1540ኪ .ሜ

ምንጭ፦ ያሬድ ሹመቴ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
አዋሽ!

"ሰላም ፀግሽ! ቃልኪዳን እንባላለሁ ከአዲስ አበባ ወደ ሀረር በመጓዝ ላይ ሳለሁ ነበር ትላንት አዋሽ ላይ መንግድ የተዘጋው፤ መንገዱ ከተዘጋበት እስከተከፈተበት ሰዓት ድረስ የአዋሽ ህዝብ ላሳየን ትልቅ #እንክብካቤ እና #ፍቅር በጣም ማመስገን እፈልጋለሁ። መንገድ የዘጉ ወጣቶች ሳይቀር ተቃውሟቸው ፍፁም ሰላማዊ ነበር። ለዚህም የአፋርን ህዝብ ማመስገን ፈልጋለሁ። እግዚያብሄር ኢትዮጵያን ይባርክ።"

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ጉዞ ሉሲ ለአንድነት እና ለፍቅር!

ጉዞ ሉሲ የአንድነት እና የፍቅር ፕሮጀክት የካቲት 14 ይጀምራል፡፡ ጉዞ ሉሲ የሰላምና የፍቅር ጉዞ ነው፡፡ በዚህ ፕሮጀክት ሁሉም #ኢትዮጵያውያን የአንድ #የሉሲ ልጆች መሆናችንን በማሳወቅ #ሰላምና #ፍቅር በኢትዮጵያ እንዲነግስ የማድረግ ዓላማን የያዘ ነው፡፡ ሀገራችን የዓለም ዘር መገኛ መሆኗን በመገንዘብ ለትውልዱ የተመቸች እና የበለጸገች ኢትዮጵያን መፍጠር ያለመ ነውም ተብሏል፡፡ ያለፈውን ቂምና ጥላቻ በመተው በመደመር እና እርቀ ሰላም እንዲመጣ በሁሉም ክልሎች ሉሲን በአስታራቂነት እና በሰላም አምባሳደርነት በመጠቀም በሀገሪቱ ሰላምና ፍቅርን በመስበክ አንድነትን በማጉላት የተሻለች ኢትዮጵያን መፍጠርም ሌላው ዓላማ ነው፡፡

ምንጭ፦ AMMA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#ጉዞ_ዓድዋ_6🔝

ታላቁን የዓድዋ ድል ለመዘከር በየአመቱ የሚካሔደው የእግር ጉዞ ዘንድሮም ለ6ኛ ግዜ ቀጥሏል። ከሐረርና አዲስ አበባ የተነሱት ተጓዦች በድምሩ ከሺህ በላይ ኪሎሜትሮችን አቋርጠው #መቐለ_ከተማ እንደገቡ ታላቁን ኢትዮጵያዊ ጀግና ራስ አሉላ እንግዳን (አባ ነጋ) ለማስታወስ የሽሬ ልጆች መቐለ ከተማ በመግባት የአዲስ አበባ እና የሐረር ተጓዦችን ተቀላቅለዋል።

ብዛታቸው 5 የሆኑት #የሽሬ_ልጆች ከመቐለ እስከ ዓድዋ እናት ሀገራቸው ኢትዮጵያን እና ታላቁን የዓድዋ ድል ለማግዘፍ እንደ ታላቁ ራስ አሉላ አባ ነጋ ከወንድም እህቶቻቸው ጋር ተቀላቅለዋል።
"ታሪካዊ #ጀግኖቻችን የልዩነታችን ምክንያት ሳይሆኑ የአንድነታችን መሰረት ናቸው"

#ፍቅር_ለኢትዮጵያ !!
#የምናቋርጣቸው_የሀገራችንን_መንደሮች_እንጂ_ድንበሮች_አይደለም
#ኢትዮጵያዊነት_ይለምልም

Via Yared Shumete
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#WKU እጅግ በጣም እናመሰግናለን፤ ያደረጋቹልን ታሪካዊው የአቀባበል ሁሌም በአባላቶቻችን ዘንድ ሲታወስ ይኖራል። የመጣንበትን አላማ እንዲሰካ ለማድረግ የደከማችሁ ቅን ሰዎች እናመሰግናለን!! መላው የተቋሙን አመራሮች፤ ሰራተኞች እና የወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ ማህበረሰብ በጠቅላላ #እናመሰግናለን!! የተማሪዎች ህብረቱ በ3 ቀን የእንመጣለን መልዕክት ዝግጅት አድርጎ በትልቅ ክብር ስለተቀበለን እናመሰግናለን!!

#ፍቅር_አሸንፏል!!
የጥላቻ ንግግር ይቁም!!
የጥላቻ ንግግር ሀገር ያፈርሳል!!

ሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ በዚህ ሳምንት🔁 #StopHateSpeech!!

@tsegabwolde @tikvahethiopia
የሰላም ተምሳሌት-ሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ!!

በነገው ዕለት ከ3 ዩኒቨርሲቲዎች የተውጣጡ #የTIKVAH_ETHIOPIA ቤተሰብ አባላት ሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ይገባሉ። ከሁሉም የሀገሪቱ ክፍል #የተሰባሰቡት እኚህ #ወጣቶች ሀገራችን ኢትዮጵያ ላይ #ፍቅር እንዲነግስ ጥላቻ እንዲወገድ፤ የማህበራዊ ሚዲያ አጠቃቀማችን እንዲታረም መልዕክት ያስተላልፋሉ።

የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ አካላት፤ ተማሪዎች ህብረት የተለያዩ ማህበራት እና ክበባት እኚህን የሰላም እና የፍቅር መልዕክተኞች፤ የንፁህ ልብ ባለቤት #ወጣቶችን ለመቀበል እየተዘጋጁ ይገኛሉ።

የኢትዮጵያ ተስፋ እኛ የሀገሪቱ ወጣቶች ነን!!
በፍቅር ተደጋግፈን ሀገራችንን እንገነባለን!!

ቦታ - የአፍሪካ ህብረት አዳራሽ
ሰዓት - ምሽት 12:00

ፍቅር፤ ተስፋ፤ አንድነት!
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ህብረ ብሄራዊቷን ኢትዮጵያ አትፈልጓት እኛ ውስጥ ናት ይሏችኃል የTIKVAH-ETH ቤተሰቦች! #ሰላም #ፍቅር #አንድነት

ከፈጣሪ ቀጥሎ ኢትዮጵያን የሚታደጓት እኚህ👆ከተለያዩ የሀገሪቱ ክፍል #የተሰባሰቡ የፍቅር እና የሰላም አምባሳደር ወጣቶች ናቸው።

የሀገሬ ሠዎች አትስጉ፤ ተስፋም አትቁረጡ በፍቅር አትዮጵያን ትልቅ እናደርጋታለን!! አርማችን ነጩ የሰላም ምልክት!!

@tsegabwolde @tikvahethiopia
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
የአንድ እናት ልጆች ነን መስመር አይለየን...
የአንድ ቤት ልጆች ነን መስመር አይለየን...

#መቐለ_ዩኒቨርሲቲ የሰላም አምባሳደር!
#ፍቅር #ተስፋ #አንድነት #መቐለ_ዩኒቨርሲቲ
#የወላይታ_ሶዶ ከተማ እየተካሄደ የሚገኘው ሰላማዊ ሰልፍ ማጠቃለያውን በሶዶ ስታዲየም እያደረገ ይገኛል፦

√ጋሞ፣ ጎፋ፣ ሲዳማ፣ ዳውሮ የወላይታ #ወንድም ሕዝቦች ናቸው!

√ኢትዮጵያዊነት #ፀጋ እንጂ ኩነኔ ሊሆን አይገባም!

√የኢንዱስትሪ ፓርኮች #ለወላይታ!

√ወላይታ #የብሔር ጠላት የለውም!

√ልማት ለወላይታ፣ #ፍትህ ለወላይታ

√ለሕገመንግስታዊ ጥያቄ ሕገመንግስታዊ መልስ ይሰጠን!

√ወላይታ #ፍቅር ነው ሁሉን #ያቅፋል!

Via ናትናኤል መኮንን & TIKVAH-ETHIOPIA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ማሳሰቢያ፦ TIKVAH-ETH ከየትኛውም የመንግስትም ሆነ መንግስታዊ ያልሆነ ተቋም ጋር ግንኙነት የለውም። TIKVAH-ETH ትክክለኛ የኢትዮጵያን ቀለም የያያዙ #የጀግና ሀገር ወዳድ ወጣቶች ስብስብ ነው።

በተለይ የStopHateSpeech ጉዞ ከየትኛውም ወገን ድጋፍ የለውም፦ ዩኒቨርሲቲዎች የሚሰጡን #መኪና ብቻ ነው። አንዳንድ ዩኒቨርሲቲዎች ለተማሪዎቻቸው ለጉዞ የሚሆን ጥቂት ገንዘብ/ለድንገተኛ ጉዳዮች/ የሚሰጡት ካልሆነ ምንም አይነት አበል የለውም/እስካሁን የተሰጠውንም በቀጣይ ሳምንት ይፋ አደርጋለሁ/። ተማሪዎች የሚመገቡት በዩኒቨርሲቲ ካፌ ነው። "አበላችን እና ክፍያችን #ፍቅር ነው" ይህ ነው ቃላቸው!!

ሌላው፦
√በራሪ ወረቀት፣ ባነር የሚያሳትምልን ድርጅት ባለመኖሩ በራሳችን ወጪ ነው የምንሰራው።
√ተማሪው በጉዞ መሃል ለሚያፈልግው ወጪ ከራሱ ከኪሱ ነው የሚጠቀመው።
√ቢታመም እንኳን ገንዘብ ሳይኖረው ነው ለእናት ሀገር ሰላም የሚጓዘው።

ወጣቶቹ ትምህርታቸውን ጥለው፣ በአካዳሚክ ጉዳዮች ተጎድተው፣ ተንገላተው፣ ተርበው፣ ለፍተው እየዞሩ ያሉት ለፍቅር ነው፤ ለትውልዱ ሰርቶ ለማለፍ ነው፤ ሀገር ሲበጠበጥ ቁጭ ብሎ ላለማውራት ነው፤ ከህሊና እዳ ነፃ ለመሆን ነው፤ ለሀገሬ ምን ልስራላት በማለት ነው፤ ለሀገር ሰላም እና አንድነት መምጣት ከወጣቶች ውጪ አማራጭ ስለሌለ ነው።

መላው የኢትዮጵያ ህዝብ እነዚህን #ወጣቶች የሚያስታውስበት ቀን እሩቅ አይደለም፤ ለምን እንደሚዞሩም የሚረዳበት ቀን ሩቅ አይሆንም፤ በሀገራችን ለተፈጠሩ እና እየተፈጠሩ ላሉ ግጭቶች ዋነኛው መንስኤ የጥላቻ ንግግር እና ጥላቻ ነው።

•ኦሮሚያ
•ትግራይ
•አማራ
•ደቡብ በፍቅር አቅፍችሁ #ስለተቀበላችሁን እናመሰግናለን!!

ኑ ኢትዮጵያን በፍቅር እንገንባ!!
@tsegabwolde
የዕለቱ መልዕክት፦

"ጨለማ ጨለማን አያጠፋም፤ ብርሃን እንጂ! ጥላቻ ጥላቻን አያጠፋም፤ #ፍቅር እንጂ!"

"Darkness cannot drive out darkness; only light can do that. #Hate cannot drive out hate; only #love can do that."

ሰላም እደሩ!
@tsegabwolde @tikvahethiopia
የዕለቱ መልዕክት፦

ከጭፍን ጥላቻ መላቀቅ ይቻላል!

አብዛኞቹ ሰዎች ጭፍን ጥላቻን በመሠረተ ሐሳብ ደረጃ የሚያወግዙ ቢሆኑም ከጭፍን ጥላቻ መዳፍ የሚላቀቁ ግን ጥቂቶች ናቸው። እንዲያውም ሥር የሰደደ ጭፍን ጥላቻ ያላቸው ብዙ ሰዎች ጥላቻ እንደሌላቸው ሊናገሩ ይችላሉ። ሌሎች ደግሞ ሰዎች ጭፍን ጥላቻቸውን ይፋ እስካላወጡ ድረስ ምንም ጉዳት የለውም ይላሉ።

ይሁን እንጂ ጭፍን ጥላቻ ሰዎችን የሚጎዳና የሚከፋፍል መጥፎ ነገር ነው። ጭፍን ጥላቻ የድንቁርና ልጅ ነው ቢባል የልጅ ልጁ ደግሞ ጠላትነት ነው። ቻርልስ ካለብ ኮልተን የተባሉት ደራሲ (1780-1832) “አንዳንድ ሰዎችን ስለማናውቃቸው #እንጠላቸዋለን። ስለምንጠላቸውም #ልናውቃቸው አንችልም” ብለዋል። ጭፍን ጥላቻን ሰዎች መማር እንደሚችሉ ሁሉ ማስወገድም ይችላሉ።

Via #JW

#ፍቅር #ሰላም #አንድነት #ተስፋ #ኢትዮጵያ

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#ድሬዳዋ

የድሬዳዋን የፍቅር ፣የሰላምና የአንድነት መገለጫ እሴቶች ለመመለስ ሁሉም ኃላፊነቱን እንዲወጣ የከተማዋ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ አህመድ መሐመድ ጥሪ አቀረቡ፡፡ “አንድ ዕድል ለሰላም” በሚል መሪ ሃሳብ የዛፍ ጥላ ሥር የእርቅ ሰላም ውይይት በድሬደዋ ተካሄዷል። በውይይቱ ተሳተፉት ምክትል ከንቲባው እንደተናገሩት ድሬዳዋ ሁሉም የሀገሪቱ ህዝቦች በፍቅርና በአንድነት የሚኖርባት የፍቅር አርአያ ናት፡፡ ይህ ለሀገር አርአያ የሆነውን #ፍቅር ከጊዜ ወደ ጊዜ ለመሸርሸር የሚደረገው ጥረት ቦታ እንደሌለው ገልጸዋል፡፡ የድሬዳዋ አርአያዊ አንድነትን ለመጠበቅና በትውልድ ውስጥ የትላንቱን ታላቅ የህብረት ስብዕና ለመመለስ ሁሉም ኃላፊነቱን እንዲወጣ አመልክተዋል፡፡

Via #ENA
@tsegabwolde @tikvahethiopia