TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.8K photos
1.44K videos
207 files
3.99K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
ኤርፖርት ...

በፎቶው 👆 ላይ የምትመለከቷቸው አቶ ነቢዩ ሲራክ ይባላሉ ፤ በአንደኛው ፎቶ ላይ አብሯቸው የሚታየው ልጃቸው ነው።

ትላንት ምሽት ለስራ ወደ ውጭ ሀገር የሚሄደውን ልጃቸውን ለመሸኘት ቦሌ ኤርፖርት በነበሩበት ወቅት አንድ የኢሚግሬሽን ሰራተኛ ልጃቸው ላይ ፍፁም ከስነምግባር ያፈነገጠ ተግባር መፈፀሙን ገልጸዋል።

ልጃቸው ምንም እንኳን በሱዑዲ አረቢያ ተወልዶ ቢያድግም አማርኛ አቀላጥፎ የሚናገርና ሀገሩን ኢትዮጵያን ወዶ ወደዚህ የተመለሰ ፣ እዚህም በስራ ላይ የተሰማራ ነው።

የትላንት ጉዞውም የስራ ነበር።

ልጃቸው አስፈላጊውን ዶክመንት ሁሉ አሟልቶ የሚጠበቅበትን አድርጎ ኢሚግሬሽን ቢሮ ሲደርስ አንድ ሰራተኛ  " የት ነው የምትሄደው ? " ይለዋል። ልጅም ቦታውን ይናገራል። " ስራህ ምንድነው ? " ሲል ሌላ ጥያቄ ያስከትላል " ስራዬን ሴልስ ማን ነው " ሲል ይመልስለታል።

ከዚህ በኃላ የኢሚግሬሽን ሰራተኛው ፓስፖርቱን ንጥቆ ወርውሮ ፣ ከዚህ ሂድ በማለት ያንገላታዋል ፤ ልጅም " ፓስፖርቴን መልስልኝ " ሲለው " ፓስፖርትህን አልሰጥም ሂድ ውጣ " በማለት እስከ ድብደባ ሊደርስ እንደነበር አባት በሃዘን ስሜት ውስጥ ሆነው ተናግረዋል።

በኃላም አባት ለኢሚግሬሽንና ደህንነት መስሪያ ቤት ኃላፊና ለሚመለከታቸው አካላት በማሳወቅ በተደረገው ማጣራት ከአንድ ሰዓት መጉላላት በኃላ ኢሚግሬሽን አልፎ ጉዞውን ማድረግ ችሏል።

" ህጋዊ ወረቀት ፓስፖርት ቪዛ ይዞ የሄደውን ሰው በዚህ ደረጃ ለምን ማንገላታት ያስፈልጋል ? ለምን ፓስፖርት መወርወር አስፈለገ ? ግልምጫ ማንጓጠጡስ ለምን አስፈለገ ? " ሲሉ ጠይቀዋል።

በአንዳንድ የኢሚግሬሽን እና ደህንነት ሰራተኞች የሚፈፀም ህገወጥ አሰራር ፣ እጅግ በጣም የብዙ ሰዎችን ልብ እየሰበረ መሆኑን ፤ ለጥቅም ተብሎ በሚሰራ ስራ እጅግ ከፍተኛ ግፍ እና በደል እየተፈፀመ መሆኑን ገልጸዋል።

አቶ ነብዩ ፤ እንዲህ ያለው አሳዛኝ እና ህገወጥ ተግባር በሁሉም ሰራተኞች ይፈፀማል ባይባልም በአንዳንድ ሰራተኞች የሚፈፀም ህገወጥ ተግባር የተቋሙን የቅን አገልጋዮችን ስም እንደሚያጎፍ እና ማረም እንደሚገባ አፅንኦት ሰጥተውበታል።

አቶ ነብዩ ሲራክ ፤ ለረጅም አመታት የህገ ወጥ ስደትን በመቃወምና በመከላከል ፣ በህገወጥ መንገድ ወጥተው ሌላ ሀገር እየተቸገሩ ስላሉ ዜጎች ጉዳይ ላይ ስራ እንዲሰራ ብዙ እየደከሙ ያሉ ሰው ናቸው።

ይህ የአንድ ሰው ገጠመኝና በማህበራዊ ሚዲያ የወጣ ይሁን እንጂ በተለይ በተለይ በቦሌ ኤርፖርት በአንዳንድ  ፦
- ስነምግባር በጎደላቸው
- የገዛ ዜጋቸውን በማያከብሩ
- ስራቸውን አክበረው በማይሰሩ፣
- ገንዘብ እና ጥቅም በሚያሳድዱ የኢሚግሬሽና ደህንነት ሰራተኞች ስንት ዜጎችን ተበድለው ፣ አንብተው ፣ የሚጮኹበት አጥተው ፣ መፍትሄ ተነፍገው ፣ መፍትሄ ፍለጋ የሚሄዱበትም ይሁን የሚደውሉበት አጥተው ይሁን ?

ተቋማት ፤ ሰራተኞቻቸው #ከህዝቡ በሚሰበሰብ ገንዘብ ደመወዝ እንደሚከፈላቸው በአግባቡ እንዲያወቁት በማድረግ ህዝብን #ጎንበስ ብለው ማስተናገድ እንዲለምዱ ፣ ሙስና እና ጥቅምን እንዲፀየፉ የማድረግ #ግዴታ አለባቸው።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
ኤርፖርት ... በፎቶው 👆 ላይ የምትመለከቷቸው አቶ ነቢዩ ሲራክ ይባላሉ ፤ በአንደኛው ፎቶ ላይ አብሯቸው የሚታየው ልጃቸው ነው። ትላንት ምሽት ለስራ ወደ ውጭ ሀገር የሚሄደውን ልጃቸውን ለመሸኘት ቦሌ ኤርፖርት በነበሩበት ወቅት አንድ የኢሚግሬሽን ሰራተኛ ልጃቸው ላይ ፍፁም ከስነምግባር ያፈነገጠ ተግባር መፈፀሙን ገልጸዋል። ልጃቸው ምንም እንኳን በሱዑዲ አረቢያ ተወልዶ ቢያድግም አማርኛ አቀላጥፎ የሚናገርና…
#ቦሌኤርፖርት

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ሰሞኑን በቦሌ አውሮፕላን ማረፊያ ከመንገደኞች አገልግሎት አሠጣጥ ጋር በተያያዘ በተለያዩ የማህበራዊ ትስስር ገጾች ላይ ቅሬታዎች እየተነሱ መሆኑን እንደተገነዘበ ገልጿል።

አየር መንገዱ ከደንበኞቹ ለሚቀርቡ ቅሬታዎች እና አስተያየቶች ከፍተኛ ትኩረት የሚሠጥ በመሆኑ ሂደቱን በጥሞና ሲከታተል መቆየቱን አመላክቷል።

በመሆኑም እየተሰሙ ያሉ ቅሬታዎችን መርምሮ መፍትሄ ለመስጠት አየር መንገዱ በአዲስ አበባ ቦሌ አውሮፕላን ማረፊያ ውስጥ አገልግሎት ከሚሰጡ ሌሎች ባለድርሻ አካላት ጋር ቅሬታዎችን የማጣራት ስራ እየሠራ መሆኑን አሳውቋል።

ይህንንም ተከትሎ በማጣራቱ ሥራ ላይ በሚገኙ ውጤቶች ላይ በመመርኮዝ ተገቢው የማስተካከያ እርምጃ በፍጥነት እንዲወሠድ ይደረጋል ብሏል።

በቦሌ ኤርፖርት ውስጥ በሚሰሩ የተለያዩ ህገወጥ ተግባራት እና ከስነምግባር ያፈነገጡ ድርጊቶች በርካቶች ተማረው ድምፃቸውን ሲያሰሙ ቆይተዋል።

በተለይ በኢሚግሬሽን ፣ በፍተሻ ቦታዎች ላይ በተጓዦች ላይ በአንዳንድ ሰራተኞች የሚፈፀሙ ከስነምግባር ያፈነገጡ ድርጊቶችን ተከትሎ የአየር መንገዱ ስም በተደጋጋሚ ይነሳል።

በቅርቡም አንድ አባት ልጃቸውን ወደ ውጭ ለመሸኘት በተገኙበት ወቅት ልጃቸው በኤርፖርት ኢሚግሬሽን ሰራተኛ ማንገላታት፣ ማመናጨቅና ፓስፖርትም እስከመወርወር የደረሰ ተግባር መፈፀሙ ይታወሳል።

ይህ የአንድ ሰው ገጠመኝና በማህበራዊ ሚዲያ የወጣ ይሁን እንጂ በተለይ በተለይ በቦሌ ኤርፖርት በአንዳንድ  ፦
- ስነምግባር በጎደላቸው
- የገዛ ዜጋቸውን በማያከብሩ
- ስራቸውን አክበረው በማይሰሩ፣
- ገንዘብ እና ጥቅም በሚያሳድዱ ሰራተኞች ስንት ዜጎች ተበድለው ፣ አንብተው ፣ የሚጮኹበት አጥተው ፣ መፍትሄ ተነፍገው ፣ መፍትሄ ፍለጋ የሚሄዱበት አጥተው ይሁን ? የሚል ጥያቄ አስነትቷል።

ተቋማት ፤ ሰራተኞቻቸው #ከህዝቡ በሚሰበሰብ ገንዘብ ደመወዝ እንደሚከፈላቸው በአግባቡ እንዲያወቁት በማድረግ ህዝብን #ጎንበስ ብለው ማስተናገድ እንዲለምዱ ፣ ሙስና እና ጥቅምን እንዲፀየፉ የማድረግ #ግዴታ አለባቸው።

@tikvahethiopia