TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.8K photos
1.44K videos
207 files
3.99K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
#BREAKING የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የፀጥታው ም/ቤት ስብሰባ ተቀምጦ ነበር። በዚህም ም/ቤቱ በዩክሬን ጉዳይ የተባበሩት መንግስታት ጠቅላላ ጉባኤ [የ193 አባል ሀገራት] አስቸኳይ ልዩ ስብሰባ እንዲጠራ በድምፅ ወስኗል። ስብሰባው ዛሬ ሰኞ ይካሄዳል። ሩስያ ስትቃወም [ድምፅን በድምፅ የመሻር /veto power/ መብቷ እዚህ ላይ ተግባራዊ አይሆንም] ፤ ቻይና ፣ ህንድ እና የተባበሩት አረብ…
#Update

የተባበሩት መንግስታት ጠቅላላ ጉባኤ #ሩሲያን በማውገዝ እና ወታደሮቿን ከዩክሬን እንድታስወጣ በቀረበ የውሳኔ ሀሳብ ላይ ዛሬ ድምፅ ሠጠ።

በዚህም ከ193 ሀገራት መካከል 141 ሀገራት ድጋፍ ሲሰጡ ፣ 5 ሀገራት ውሳኔ ሀሳቡን ተቃውመዋል፣ 35 ሀገራት ደግሞ ድምፀ ተአቅቦ አድርገዋል።

#ኢትዮጵያን 🇪🇹 ጨምሮ 13 ሀገራት በድምፅ አሰጣጡ ላይ ሙሉ በሙሉ አልተሳተፉም።

የውሳኔ ሀሳቡን የተቃወሙ ሀገራት ፦

🇷🇺 ሩስያ
🇧🇾 ቤላሩስ
🇪🇷 ኤርትራ
🇰🇵 ሰሜን ኮሪያ
🇸🇾 ሶሪያ ናቸው።

ድምፀ ተአቅቦ ካደረጉት መካከል ፦

🇩🇿 አልጄሪያ
🇦🇴 አንጎላ
🇧🇮 ቡሩንዲ
🇨🇬 ኮንጎ
🇨🇫 ማዕከላዊ ሪፐብሊክ አፍሪካ
🇲🇬 ማዳጋስካር
🇲🇱 ማሊ
🇳🇦 ናሚቢያ
🇲🇿 ሞዛምቢክ
🇸🇳 ሴኔጋል
🇸🇸 ደቡብ ሱዳን
🇸🇩 ሱዳን
🇿🇦 ደቡብ አፍሪካ
🇿🇼 ዝምባብዌ
🇺🇬 ዩጋንዳ
🇵🇰 ፓኪስታን
🇨🇺 ኩባ
🇮🇳 ህንድ
🇮🇷 ኢራን
🇮🇶 ኢራቅ
🇨🇳 ቻይና ይገኙበታል።

የውሳኔ ሀሳቡ በህጋዊ መንገድ አስገዳጅ ሳይሆን የተ.መ.ድ አባል ሀገራት እይታ የተንፀባረቀበት እና በሩስያ እና ቤላሩስ ላይ ጫና ለመፍጠር ያለመ ነው።

@tikvahethiopia