TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
59.4K photos
1.51K videos
215 files
4.12K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#update ታንዛኒያ ሰሞኑን 1 ሺህ 900 ኢትዮጵያዊያን ስደተኛ እስረኞችን #ለመልቀቅ ተስማምታለች፡፡ እስረኞቹ የሚለቀቁት በዳሬሰላም የኢትዮጵያ ኢምባሲ ከታንዛኒያ መንግሥት ባለሥልጣናት ጋር ባደረገው ስምምነት መሠረት መሆኑን የኬንያው ዴይሊ ኔሽን አስነብቧል፡፡ ስደተኞቹ በምን ወንጀል እንደታሰሩ ባይገለጽም በርካታ ስደተኞች በየጊዜው በሕገ ወጥ መንገድ በታንዛኒያ በኩል አቋርጠው ወደ ደቡብ አፍሪካ ሊሻገሩ ሲሉ እንደሚያዙ ተደጋግሞ ተዘግቧል፡፡

Via wazemaradio
@tsegabwolde @tikvahethiopia
“የህዳሴ ግድብን #ለማጠናቀቅ ተጨማሪ ማራዘሚያ ጊዜ ሊኖር አይገባም” ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር #ደመቀ_መኮንን
.
.
ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብን በተያዘው የጊዜ መርሃ-ግብር ለማጠናቀቅ ርብርብ መደረግ እንደሚገባ የግድቡ ህዝባዊ ተሳትፎ አስተባባሪ ብሄራዊ ምክር ቤት ሰብሳቢ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን ገለጹ።

በአምስት ዓመታት ጊዜ ውስጥ ለማጠናቀቅ ዕቅድ ተይዞለት የነበረው ግድቡ ስምንት ዓመታት አለመጠናቀቁን የተናገሩት ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ ለዚህም በኢትዮጵያ ብረታ ብረትና ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን (ሜቴክ) መሰራት የነበረበት የግድቡ ኤሌክትሮ ሜካኒካልና ተያያዥ ተግባራት አፈፃፀም #በመጓተቱ ነው ብለዋል።

በዚህም የተነሳ ፕሮጀክቱን ለማጠናቀቅ ተጨማሪ አራት ዓመታት አስፈልጓል፤ ይሁንና አሁን ላይ መንግስት ለጉዳዩ ትኩረት በመስጠት ፕሮጀክቱን በተያዘው የጊዜ ገደብ በጥራትና በብቃት ለማጠናቀቅ ከፍተኛ ክትትል ያደርጋል ብለዋል ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ።

ምንጭ፦ ኢ.ፕ.ድ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update በመንግስትና በኦሮሞ ነፃነት ግንባር (ኦነግ) መካከል እርቅ ለማውረድ የተቋቋመው የቴክኒክ ኮሚቴ የፊታችን ረቡዕ ወደተለያዩ የኦሮሚያ ዞኖች እንደሚሰማራ ለጋዜጠኞች በሰጠው መግለጫ አስታውቋል፡፡ ኮሚቴው ወደ ወለጋ ዞኖች፣ ጉጂ ዞኖችና ቦረና ዞን፣ ሰሜን ሸዋ፣ ኢሉ አባቦራና ፈንታሌ ዞኖች እንደሚሰማራ ገልጿል፡፡ ኮሚቴው ከሁለቱም አካላት ጋር ውይይት ማድረጉንና ከዚህ ቀደም ተወስኖ የነበረው ቀነ ገደብ ላይ ተጨማሪ 10 ቀናት መጨመሩን የቀድሞ የቱለማ አባገዳ #በየነ_ሰንበቶ ገልጸዋል፡፡

ምንጭ:- OBN
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ሀዋሳ🔝

በበደቡብ ብሄር ብሄረሰቦችና ህዝቦች ክልላዊ መንግስት #በሃዋሳ ከተማ የታክስ ንቅናቄ መድረክ የገቢዎች ሚኒስትር ወ/ሮ #አዳነች_አቤቤ በተገኙበት በይፋ ተከፈተ።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update በህዝብ ተወካዮች ም/ቤት የተሰየሙት የእርቀ ሰላም ኮሚሽን አባላት ዛሬ ትውውቅ አድርገዋል። በትውውቅ ፕሮግራሙ ለእርቀ ሰላም ኮሚሽን ተልዕኮ ስኬት መንግሥት አስፈላጊውን ድጋፍ እንደሚያደርግ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን ገልፀዋል።

ምንጭ:- ም/ጠ/ሚ ፅ/ቤት
@tsegabwolde @tikvahethiopia
የአማራ ክልል ፖሊስ‼️

በህገ ወጥ መንገድ ሲዘዋወሩ የነበሩ 43 ክላሽ ሸንኮቭ የጦር መሳሪያና 1 ሺህ 300 ጥይቶች በቁጥ ጥር ስር ማዋሉን #የአማራ_ክልል_ፖሊስ አስታወቀ።

#የጦር_መሳሪያዎቹን ከጋምቤላ ወደ አማራ ክልል ጎንደር ከተማ በኤፍ ኤስ አር የጭነት ተሽከርካሪ በማስገባት ላይ እያለ በቁጥጥር ስር የዋለ ሲሆን፥ የመኪናው አሽከርካሪም በቁጥጥር ሥር መዋሉን የአማራ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን
ገልጿል።

በህገ ወጥ መንገድ ሲዘዋወሩ የነበሩ የጦር መሳሪያዎች ላይ ተጨማሪ የምርመራ ሥራ እያከናወነ መሆኑንም ነው ኮሚሽኑ የገለፀው።

ምንጭ፦ አብመድ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
መካነሰላም🔝

ሰሞኑን በደቡብ ጎንደር ዞን እስቴ ወረዳ #የተቃጠሉ መስጊዶችን መልሶ ለመገንባት ያለመ የገቢ ማሰባሰቢያ መርሐግብር በእስቴ መካነሰላም ከተማ ተካሂዷል።

Via ELU
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ከ250,000 ብር በላይ ድጋፍ ተደርገ🔝

በባህርዳርና በደብረ ታቦር የሚኖሩ የአስቴ ወረዳ ነዋሪዎች በቅርቡ የተቃጠሉትን ሁለት መስጅዶች ለመስራት የሚያስችል ሩብ ሚሊዮን ብርና #የሲሚንቶ ድጋፍ አደረጉ፡፡

ተወላጆቹ በራሳቸው ተነሳችነት ብሩን ከመሰብሰብ ባለፈ ቦታው ደረስ በመሄድ የጎዳቱን ሁኔታ በመመልከት የአለኝታነት ድጋፋቸውን እንዳሳዩ የአማራ ክልል መንግስት ኮሙኒኬሽን ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ መላኩ አላምረው ለኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን
በዛሬው ዕለት ገልጸዋል፡፡

ተወላጆቹ ለመስጅዶች ግንባታ አስተባባሪ ኮሚቴ ካስረከቡት 250 ሺህ ብር በተጨማሪም ለግንባታው የሚውል 100 ኩንታል ሲሚንቶ አበርክተዋል፡፡

ተወላጆቹ ድርጊቱን አውግዘው ምንም ዓይነት እኩይ ዓላማ ያለው አካል ትንኮሳ #ቢፈፅም የሁለቱ እምነት ተከታዮች አንድነት የበለጠ ይጠናከራል እንጂ ምንም ዓይነት የሚፈጠር ነገር የለም ብለዋል፡፡

ድጋፉን ያሰባሰቡት የሁለቱም እምነት ተከታይ የወረዳዋ ተወላጆች አጥፊዎቹ ታድነው ተገቢው ቅጣት እንዲሰጣቸውም በድጋፍ ርክክቡ ወቅት ጠይቀዋል፡፡

አጥፊዎችን ለመለየት ከተያዙት 6 #ተጠርጣሪዎች በተጨማሪ ምርመራው #ተጠናክሮ መቀጠሉንም አቶ መላኩ ገልጸዋል፡፡ የተቃጠሉት መስጅዶች ግንባታ በፍጥነት እንደሚጀመር ተመልክቷል፡፡

በተመሳሳይ መልኩ በደቡብ ጎንደር አንዳቤት ወረዳ ላይ የተቃጠለውን የጃራ ገዶ መስጅድ የአካባቢው ማህበረሰብ 27 ሺህ ብር በማዋጣት መልሶ የመስራት ሂደቱን እንደጀመረ የክልሉ መንግስት ኮሚኒኬሽን ለኢቢሲ አመልክቷል፡፡

ምንጭ፦ ebc
@tsegabwolde @tikvahethiopia