Fake news‼️
"ኢትዮጵያ የሶርያ ስደተኞችን #እያባረረች አይደለም። አንድ የመንግስት ባለሥልጣን እንደነገረኝ ጦርነትን ሸሽተው የመጡትን ሶሪያኖችን የማባረርም ስራም አልተሰራም፣ እቅድም የለም። እቅድ ካለም ወደ ስደተኝነት ማእቀፍ ለመግባት የሚፈልጉ ሶሪያውያንን ማገዝ ስራ ነው እየተሰራ ያለው።"
©ጋዜጠኛ ኤልያስ ገብረስላሴ
@tsegabwolde @tikvahethiopia

#update በቤኒሻንጉል ጉሙዝና ኦሮሚያ ክልል ምስራቅ ወለጋ ዞን አጎራባች ወረዳዎች በተከሰተው #ግጭት ምክንያት የተፈናቀሉ ወገኖች መልሶ በሚቋቋሙበት ሁኔታ ላይ ያተኮረ ውይይት ተካሄደ። በግጭቱ የተፈናቀሉ 180 ሺህ ወገኖች በሁለቱም ክልሎች በሚገኙ አጎራባች ወረዳዎች ተጠልለው አስቸጋሪ ህይወት እየመሩ ነው ተብሏል። በኦሮሚያ ክልል በምክትል ፕሬዚዳንት ማዕረግ የገጠር ክላስተር አስተባባሪ ዶክተር ግርማ አመንቴና የቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ አሻዲሊ ሐሰን በምስራቅ ወለጋ ዞን ሳሲጋ ወረዳ አንገር መጠለያ ጣቢያ የሚገኙ ተፈናቃዮችን አነጋግረዋል። የሁለቱ ክልል አመራሮች በተፈጠረው ግጭት ምክንያት በሰው ሕይወትና ንብረት ላይ የደረሰውን ጉዳት የሚያጣራ የጋራ ኮሚቴ በማዋቀርና በአካባቢው ሠላምን በማስፈን ተፈናቃዮቹ ወደ ቀያቸው በሚመለሱበት ሁኔታ ከችግሩ ሰለባዎች ጋር ተመካክረዋል።
Via ENA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
Via ENA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ጅማ🔝
በጅማ ከተማ "ንግዳችንን እናዘምን" በሚል መሪ ቃል የጎዳና ላይ ሩጫ ውድድር በዛሬ ዕለት ተካሄደ፡፡ አምስት ኪሎ ሜትርን የሸፈነው ሩጫ ውድድር የጅማ ከተማ የንግድና ዘርፍ ማህበራት ምክር ቤት 50ኛ ዓመት የምስረታ ክበረ-በዓልን በማስመልከት የተዘጋጀ ነው፡፡
ፎቶ፦ ጌትሽ(TIKVAH-ETH ጅማ)

#update ሼህ #መሃመድ_አል_አሙዲን ከእስር መፈታታቸውን የጠ/ሚኒስትሩ ፕሬስ ሴክሪቴሪያት አረጋግጧል። የፕሬስ ሴክሪቴሪያት ፅ/ቤቱ ለመላው ኢትዮጵያውያንና ለቤተሰቦቻቸው የእንኳን ደስ ያላችሁ መልእክት ያስተላለፈ ሲሆን የሚድሮክ ኢትዮጵያ ግሩፕ ዋና ስራ አስፈፃሚ ዶ/ር አረጋ ይርዳው በበኩላቸው ለዋልታ ቴሌቪዥን በላኩት መልእክት በሼህ አላሙዲን መፈታት የተሰማቸውን ደስታ ገልፀው ለጠ/ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድና ለሃገር ወዳዱ ባለሃብት መፈታት ጥረት ላደረጉ ወገኖች በሙሉ ምስጋና አቅርበዋል።
Via WALTA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
Via WALTA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ሚድሮክ‼️
በሳውዲ አረቢያ በእስር ላይ ይገኙ የነበሩት ትውልደ ኢትዮጵያዊው ባለሃብት ሼህ #ሙሃመድ_አላሙዲን መፈታታቸውን የሚድሮክ ስራ አስኪያጅ ዶ/ር #አረጋ_ይርዳው ለዋልታ አረጋግጠዋል።

የሼህ መሀመድ የህግ አማካሪ‼️
ትውልደ ኢትዮጵያዊው ቢሊየነር ሼህ መሃመድ ሁሴን አሊ አላሙዲ ከእስር መፈታታቸው ተሰማ። ፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ሼክ መሃመድ መፈታታቸውን ከህግ አማካሪያቸው #ተካ_አስፋው አረጋግጧል፡፡ሼክ መሃመድ በአሁኑ ወቅት በእስር ከቆዩበት ሪያድ በመነሳት ጅዳ ወደሚገኘው መኖሪያ ቤታቸው #በመጓዝ ላይ ይገኛሉ፡፡ ሼህ መሃመድን ከእስር ለማስፈታት የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ ተደጋጋሚ ጥረት ሲያደርጉ መቆየታቸው የሚታወስ ነው፡፡
via fbc

#update የሱዳኑ ፕሬዝዳንት #ኦማር_ሀሰን_አልበሽር በሀገራቸው አደባባይ የወጡ ተቃዋሚዎች የአረቡን ዓለም የጸደይ አብዩት ለመኮረጅ የሞከሩ ናቸው አሉ። አልበሽር በስም #ያልጠቀሷቸውን ነገር ግን ጎጂ ያሏቸው ድርጅቶች ቀጠናውን ለማመስ እየሰሩ ነው ብለዋል።
Via DW
@tsegabwolde @tikvahethiopia
Via DW
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ደብረማርቆስ🔝
የቀድሞ ጦር ማህበር #የምስረታ_ጉባዔ ዛሬ #በደብረማርቆስ ፖሊስ ኮሌጅ ተካሂዳ። በጉባዔው ከ4000 በላይ የቀድሞው ጦር አባላት ታድመዋል። ከምስረታ ጉባዔው ጎን ለጎን ለኮሪያና ለኮንጎ ዘማቾች የምስጋና መርሐግብር የተከናወነ ሲሆን በኦጋዴንና በኤርትራ ለኢትዮዽያ ዳር ድንበር መከበር አስተዋጾ ላበረከቱ እውቅና ተሰጧል።
Via ELU

ሼህ አላሙዲ‼️
"ሼህ አላሙዲ ወደ #አዲስ_አበባ ይምጡ፤ #ሳዑዲ ይቆዩ #አናውቅም"- ጠበቃቸው
.
.
ላለፈው አንድ ዓመት ከሁለት ወር በሳዑዲ አረቢያ በእስር ላይ የቆዩት ሼህ መሐመድ ሁሴን አላሙዲ ከእስር #መፈታታቸውን ጠበቃቸው ተናገሩ። ትውልደ ኢትዮጵያዊው ቱጃር ከእስር የተፈቱት ዛሬ ከሰዓት መሆኑን ጠበቃቸው አቶ ተካ አስፋው ለጀርመን ድምፅ ራድዮ ገልጸዋል።
አቶ ተካ ሼህ አላሙዲንን #በስልክ ባይነጋግሯቸውም ከወንድማቸው ጋር አብረው እንዳሉ #አረጋግጩያለሁ ብለዋል። “ዛሬ ተፈትተዋል። አሁን ከሪያድ ወደ ጅዳ እየሄዱ ነው፤ ወደ ቤታቸው ማለት ነው። አጠገባቸው ካለ ሰው ጋር ተገናኝተናል። አዲስ አበባ ይምጡ፣ እዚያው ይቆዩ የምናውቀው ነገር የለም። እኛ አሁን #በመፈታታቸው ብቻ ደስታ ላይ ነው ያለነው።”
ሼህ መሐመድ ሁሴን አላሙዲ የሳዑዲ አረቢያ መንግስት በከፈተው የጸረ-ሙስና ዘመቻ ከሌሎች ቱጃሮች፣ ልዑላን፣ ሚኒስትሮች እና ባለስልጣናት ጋር በጥቅምት ወር 2010 ዓ. ም. ነበር በቁጥጥር ስር የዋሉት። ከእርሳቸው ጋር ታስረው የነበሩ ቢሊየነሩ ልዑል አልዋሊድ ቢን ታላልን ጨምሮ ሌሎች ተጠርጣሪዎች ከሳዑዲ አረቢያ መንግስት ጋር ድርድር ካደረጉ በኋላ እንደተፈቱ ሲገለጽ ቆይቷል። ሼህ አላሙዲ ስለተፈቱበት ሂደት የተጠየቁት ጠበቃቸው “ዝርዝሩን አላወቅንም። እኛ የምናውቀው መፈታታቸውን ብቻ ነው” ሲሉ ለጀርመን ድምፅ ራድዮ ምላሽ ሰጥተዋል።
ሳዑዲ አረቢያ በወጣቱ አልጋወራሽ ልዑል መሐመድ ቢን ሳልማን የሚመራ የጸረ-ሙስና ኮሚቴ ካቋቋመች በኋላ 11 ልዑላንን ጨምሮ 200 ገደማ ባለስልጣናት እና ነጋዴዎችን አስራ ነበር። ልዑላኑ እና ቱጃሮቹ ለመጀመሪያዎቹ ጥቂት ሳምንታት በሪያድ በሚገኝ ባለአምስት ኮከቡ ቅንጡ ሆቴል እንዲታሰሩ መደረጉ መነጋገሪያ ሆኖ እንደነበር ይታወሳል። ተጠርጣሪዎቹ ሆቴሉን እንዲለቅቁ ከተደረጉ በኋላ በታሰሩበት ስፍራ የሰብዓዊ መብት ጥሰት ይፈጸምባቸዋል የሚል ወቀሳ ሲሰማ ቆይቷል።
ምንጭ፦ የጀርመን ድምፅ ራድዮ

#ሐዋሳ ላይ እየተካሄደ ባለው አራተኛው #የኢህአዴግ ወጣቶች ሊግ የኢህአዴግ ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ብናልፍ አንዱዓለም ያደረጉት ንግግር፦
https://telegra.ph/አራተኛው-የኢህአዴግ-ወጣቶች-ሊግ-ጉባኤ-01-27

Telegraph
አራተኛው የኢህአዴግ ወጣቶች ሊግ ጉባኤ፦
የተወደዳችሁ የኢትዮጵያ ወጣቶች፣ የተከበራችሁ የፌዴራልና የክልል የስራ ሃላፊዎች፣ የተከበራችሁ ጉባዔተኞችና ጥሪ የተደረገላችሁ እንግዶች፣ ክቡራትና ክቡራን፤ ከሁሉ አስቀድሜ እንኳን ለ4ኛው የኢሕአዴግ ወጣቶች ሊግ ጉባዔ አደረሳችሁ፣ አደረሰን እያልኩ፣፤ “በወጣቶች የተጠናከረ ትግል የተጀመረውን ሀገራዊ ለዉጥ ወደፊት!” በሚል መሪ ቃል በሃዋሳ ከተማ በሚካሄደው በዚህ ታላቅ ጉባዔ ላይ ተገኝቼ መልዕክት ለማስተላለፍ…
#update ለአራት ቀናት በመቀለ ሲካሄድ የቆየው የትግራይ ክልላዊ መንግስት ምክር ቤት የአምስተኛው ዘመን 14ኛው መደበኛ ጉባኤ አዋጆችንና ሹመቶችን በማጽደቅ #ተጠናቀቀ። ምክር ቤቱ ከ600 ሚሊዮን ብር በላይ ተጨማሪ በጀት ያጸደቀ ሲሆን የተለያዩ አዋጆችና የዳኞችና የሬጅስትራሮችን ሹመት አጽድቋል።
Via ENA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
Via ENA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
መከላከያ‼️
ድሬዳዋን ሰላምና ፀጥታ #አስተማማኝ በማድረግ የህዝብ የልማትና የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎች እንዲፈቱ እንደሚሰራ #በምስራቅ_ዕዝ_መከላከያ የሚመራው ጊዜያዊ የፀጥታ ጥምር ኮሚቴ አስታወቀ።
ኮሚቴው ምሽት ላይ በሰጠው #መግለጫ #በመልካ_ጀብዱ የሞቱት ሁለት ሰዎች ሰሞኑን ከተከሰተው የወጣቶች ተቃውሞና ሰልፍ ጋር አይገናኝም፡፡
ጊዜያዊው የፀጥታ ጥምር ኮሚቴ በሰጠው መግለጫ ሰሞኑን ሁከትና ተቃውሞ የተነሳባቸው አካባቢዎች ሰላምና ፀጥታ ሰፍኖ ማህበራዊና ምጣኔ ሃብታዊ እንቅስቃሴዎች እንደወትሮው እየተከናወኑ ይገኛሉ፡፡
ኮሚቴው ገለልተኛ ሆኖ የህግ የበላይነት ማረጋገጥና የህዝብ ሰላምና ደህንነት የመጠበቁን ተግባራት በቋሚ ስፍራዎች ሰራዊት በመመደብና በተንቀሳቃሽ መኪኖች በመታገዝ እያከናወነ ይገኛል፡፡
የጥምር ኮሚቴው አባልና የድሬዳዋ አስተዳደር ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ጌታቸው አስረስ “በቁጥጥር ሥር ከዋሉት ሁለት መቶ ተጠርጣሪዎች መካከል ከጉዳዩ ጋር የማይገናኙት እየተለቀቁ ናቸው” ብለዋል።
ሌሎቹን መርማሪዎች ቃል እየተቀበሉ ይገኛሉ፤መረጃና ማስረጃ እየተሰባሰበባቸው በመሆኑ ይህ እንደተጠናቀቀ ፍርድ ቤት ይቀርባሉ ብለዋል፤ ታዳጊ ወጣቶች ተገቢው ምክርና ትምህርት ተሰቷቸው መለቀቃቸውንም ተናግረዋል።
ጂቲ ዜድ በተባለ ስፍራ በተካሄደው ሁከትና ብጥብጥ ሶስት ሸጉጥና ሁለት ክላሽንኮቭ ጠመንጃ መያዙን ተናግረዋል።
የጥምር ኮሚቴው አባል የፌደራል ፖሊስ የምስራቅ ክላስተር ኃላፊ ኮማንደር ሰለሞን ከበደ በበኩላቸው “ትላንት በመልካ ቀበሌ የተከሰተው ግጭት አስቀድሞም ለዓመታት የዘለቀና በአካባቢው ነዋሪዎች መካከል ሲፈጠር የነበረ እንጂ ከሰሞኑ ችግር ጋር አይገናኝም” ብለዋል፡፡
በግጭቱ ወደ አዲሱ ምድር ባቡር ሰው ሊያደርስ ሲጓዝ የነበረ ወጣት የታክሲ ሹፌርና አንድ ሌላ ሰው መሞታቸውን ተናግረዋል፡፡
ወንጀሉን የፈጸሙ አምስት ሰዎች በህግ ቁጥጥር ሥር መዋላቸውንም ገልፀው ሌሎቹንም በቁጥጥር ሥር የማዋል ስራ እየተከናወነ ይገኛል ብለዋል፡፡
የፀጥታ አካሉ በድሬዳዋ አስተማማኝ ሰላም ለማምጣት የጀመረው ሥራ ስኬታማ እንዲሆን ህብረተሰቡ አስፈላጊውን ድጋፍና ትብብር ማድረግ እንዳለበት የተናገሩት ደግሞ የኮሚቴው አባል የድሬዳዋ ፍትህ ፀጥታና የህግ ጉዳዮች ቢሮ ኃላፊ አቶ ኢብራሂም ዩሱፍ ናቸው፡፡
ችግሩ ከኃይማኖትና ከብሔር ግጭት ጋር ምንም ዓይነት ግንኙነት እንደሌለው አስረድተው ለዚህም ሌት ተቀን የሚሰሩ አካላት መኖራቸውን በመገንዘብ ህብረተሰቡ ከፍተኛ ጥንቃቄ ማድረግ እንዳለበት አሳስበዋል፡፡
“አስተማማኝ ሰላምና ፀጥታ ከሰፈነ በኋላ የፖለቲካ አመራሩ የወጣቱን የልማትና የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎች የመፍታት ስራ ያከናውናል” ብለዋል፡፡
የጥምር ኮሚቴው ሰብሳቢ የምስራቅ ዕዝ የኢንዶክትሬሽንና ህዝብ ግንኙነት ኃላፊ ኮሎኔል ፍስሃ ተክለሃይማኖት በበኩላቸው ፀጥታው አስተማማኝ ደረጃ እስኪደርስ ሰራዊቱ ከህብረተሰቡ ጋር በመቀናጀት እያከናወነ የሚገኘውን ተግባር አጠናክሮ እንዲቀጥል ጠይቀዋል፡፡
ምንጭ፦ ኢዜአ

TIKVAH-ETH ማጠቃለያ🗞ጥር 19/2011 ዓ.ም.
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ያስገነባው ስካይ ላይት ሆቴል ዛሬ ጠቅላይ ሚንስትር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ በተገኙበት በይፋ ተመርቆ ተከፍቷል፡፡
.
.
#ሐሰተኛ_የማስተርስና_የዶክትሬት ዲግሪዎች እንዲሰጡ አድርገዋል የተባሉት የሜቴክ ኃላፊዎች ላይ ክስ ተመስርቷል።
.
.
በአዲስ አበባ ከተማ የሚኖሩ #የድሬዳዋ ተወላጆች በዛሬው ዕለት በፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ተገኝተው ያላቸው ተቃውሞ እና ቅሬታ አሰምተዋል። የፌደራሉ መንግስት ለድሬዳዋ ከተማ ልዩ ትኩረት እንዲሰጥና ያሉ ችግሮችን እንዲፈታ ጠይቀዋል።
.
.
#የሰላሌ_ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ትናንት ቅዳሜ "አንድ ቀን ለማህበረሰቤ" በሚል መሪ ሀሳብ #ፍቼ ከተማን ሲያፀዱ ውለዋል።
.
.
ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ #ደመቀ_መኮንን በደቡብ ክልል በጋሞ ዞን ቆላማ አካባቢ የስንዴ ግብርና ልማት የሙከራ ፕሮጀክትን ጎብኝተዋል።
.
.
4ኛው የኢህአዴግ የወጣቶች ሊግ ድርጅታዊ ጉባዔ #በሃዋሳ_ከተማ ዛሬ ተጀምሯል። ጉባዔው "በተጠናከረ የወጣቶች ትግል ሀገራዊ ለውጡን ወደፊት" በሚል መሪ ቃል እስከ ጥር 19 እስከ 21 በተለያዩ ወቅታዊ ሀገራዊ ጉዳዮች ላይ እየመከረ ይቆያል፡፡
.
.
በቤኒሻንጉል ጉሙዝና ኦሮሚያ ክልል ምስራቅ ወለጋ ዞን አጎራባች ወረዳዎች በተከሰተው #ግጭት ምክንያት የተፈናቀሉ ወገኖች መልሶ በሚቋቋሙበት ሁኔታ ላይ ያተኮረ ውይይት ተካሂዷል።
.
.
በጅማ ከተማ "ንግዳችንን እናዘምን" በሚል መሪ ቃል የጎዳና ላይ ሩጫ ውድድር በዛሬ ዕለት ተካሂዷል።
.
.
ትውልደ ኢትዮጵያዊው ቢሊየነር ሼህ መሃመድ ሁሴን አሊ አላሙዲ ከእስር መፈታታቸው ተሰምቷል።
.
.
የቀድሞ ጦር ማህበር #የምስረታ_ጉባዔ ዛሬ #በደብረማርቆስ ፖሊስ ኮሌጅ ተካሂዷል።
.
.
ለአራት ቀናት በመቀለ ሲካሄድ የቆየው የትግራይ ክልላዊ መንግስት ምክር ቤት የአምስተኛው ዘመን 14ኛው መደበኛ ጉባኤ አዋጆችንና ሹመቶችን በማጽደቅ #ተጠናቋል።
.
.
የድሬዳዋን ሰላምና ፀጥታ #አስተማማኝ በማድረግ የህዝብ የልማትና የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎች እንዲፈቱ እንደሚሰራ #በምስራቅ_ዕዝ_መከላከያ የሚመራው ጊዜያዊ የፀጥታ ጥምር ኮሚቴ አስታውቋል።
.
.
ምንጭ፦ ኢዜአ፣ DW፣ ኢ.ፕ.ድ.፣ የጠ/ሚ ፅ/ቤት፣ የምክትል ጠ/ሚ ፅ/ቤት፣ etv፣ ዋልታ፣ ፋና፣ የTIKVAH-ETH ቤተሰብ አባላት
.
.
ሰላም እደሩ!!
የነገ ሰው ይበለን!!
ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር!!