#update ከሁለት ቀናት በፊት ከሊቢያ የተነሱ 117 የሚጠጉ ስደተኞች የደረሱበት እንዳልታወቀ የዓለም አቀፍ የስደተኞች ጉዳይ ድርጅት «IOM» ዛሬ አስታወቀ። እነዚሁ ስደተኞች ተሳፍረውበት ከነበረው ጀልባ የተረፉ ሶስት ስደተኞች ለድርጅቱ እንደተናገሩት ከጋራቡሊ ሊቢያ ሀሙስ ሌሊት ሲሳፈሩ 120 ነበሩ። ለ 10 ሰዓት ገደማም ከተጓዙ በኋላ ጀልባው እና ሰዎች መስመጥ መጀመራቸውን ተናግረዋል። ጀልባው ላይ የተሳፈሩት ስደተኞች በብዛት ምዕራብ አፍሪቃውያን ሲሆኑ ከነዚህም ውስጥ 10 ሴቶች እና ሁለት ህፃናት አብረዋቸው እንደነበሩ የተረፉት ስደተኞች ጠቁመዋል። የኢጣሊያ የጦር አይሮፕላን ዓርብ ዕለት የሚሰምጥ ጀልባ ተመልክቶ በነዳጅ እጦት ከመመለሱ በፊት ሁለት መንሳፈፊያ ወደ ባህር መወርወሩ ተዘግቦ ነበር። ኋላም ሶስቱ ስደተኞች በአንድ ሄሊኮፕተር አማካኝነት እንደተረፉ እና ወደ ላምፔዱዛ ደሴት እንደተወሰዱ ተገልጿል። የዓለም አቀፍ የስደተኞች ጉዳይ ድርጅት ባለፈው በጎርጎሮሲያዊ 2018 ዓም 2297 ስደተኞች ባህር ሰምጠው መሞታቸውን ዛሬ በዘገባው አክሎ ገልጿል።
ምንጭ፦ የጀርመን ድምፅ ራድዮ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ምንጭ፦ የጀርመን ድምፅ ራድዮ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
አሳዛኝ ዜና‼️
በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል #ካማሽ_ዞን ዛሬ በደረሰ የትራፊክ አደጋ የአራት ሰዎች ሕይወት ማለፉን ፖሊስ አስታወቀ፡፡
በዞኑ ፖሊስ የትራፊክ ክፍል ኃላፊ ኢንሰፔክተር #ጉልማ_ገዛኸኝ እንደገለጹት÷ አደጋው የደረሰው ዛሬ 40 ያህል ሰዎችን አሳፍሮ ከካማሽ ከተማ ወደ ያሶ የሚጓዝ ተሽከርካሪ በመገልበጡ ነው።
አደጋው ከቀኑ 7ሰዓት 30 ላይ የሠሌዳ ቁጥሩ ኢት ኮድ 3-88590 በሆነው መለስተኛ የጭነት ተሸከርካሪ ጀሎ በተባለው አካባቢ እንደደረሰም አስረድተዋል፡፡
በዚሁ ተሸከርካሪ ከተሳፈሩ መንገደኞች መካከል አራቱ ወዲያውኑ ህይወታቸው ሲያልፍ÷ ከሟቾቹ መካከል አንድ የሁለት ዓመት ህጻን ይገኝበታል ብለዋል፡፡
በሌሎች 25 ሰዎች ላይ ከባድና ቀላል ጉዳት የደረሰ ሲሆን÷ በካማሽ ጤና ጣቢያ የሕክምና እርዳታ እየተደረገላቸው መሆኑን ኃላፊው ገልጸዋል፡፡
ምንጭ፡- ኢ.ዜ.አ

ጅማ🔝በጅማ ከተማ ያለው የነዳጅ እጥረት ለስራቸው ፈተና እንደሆነባቸው አሽከርካሪዎች እና የከተማ ነዋሪዎች ገልፀዋል። የሚመለከተው የመንግስት አካል መፍትሄ እንዲፈልግም ጠይቀዋል።
@tsegabwolde @tikvahethiopia
@tsegabwolde @tikvahethiopia
መቀለ ዩኒቨርሲቲ🔝
"ትላንት የመቀለ ዩኒቨርሲቲ ጤና ሳይንስ ኮሌጅ #ተመራቂ ተማሪዎች ለጎዳና ተዳዳሪዎች የተለያዩ ልብሶችን ከተማሪዎች በማሰባሰብ ሲሰጡ ውለዋል፡፡ ባለፈው ሳምንትም በበጎ አድራጎት ስራ ላይ መዋላቸው ይታወሳል፡፡ መልካምነት፣ ፍቅር እና ሰላም ለኢትዮጵያ!"
ለሌላውም ወጣት ትልቅ ትምህርት እየሰጣችሁ ስለምትግኙ በቻናሉ ስም ትልቅ ምስጋና እናቀርባለን!!

#update የትግራይ ክልል ምክር ቤት ከፊታችን ጥር 14 ቀን ጀምሮ እስከ ጥር 19 ቀን 2011 ዓ.ም በሚያካሂደው ጉባዔ የክልሉን መንግስትና የክልሉን ምክር ቤት የስድስት ወራት የስራ አፈፃፀም ገምግሞ ያፀድቃል ተብሎ ይጠበቃል። ከዚህ ባለፈም የክልሉን ፍርድ ቤት የስድስት ወራት የሥራ አፈፃፀምና የክልሉን የስድስት ወራት ኦዲት ሪፖርት ያደምጣል።
@tsegabwolde @tikvahethiopia
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ከጩኮ...
"ሰላም! ሙሉቀን ነኝ ከጩኮ ፀግሽ ዛሬ በአለታ ጩኮ የጥምቀት በአል #በሰላም እንዲጠናቀቅ የአለታ ጩኮ ወጣቶች ያደረጉት ተሳትፎ እጅግ አስደሳች ነበር፡፡"
@tsegabwolde @tikvahethiopia
"ሰላም! ሙሉቀን ነኝ ከጩኮ ፀግሽ ዛሬ በአለታ ጩኮ የጥምቀት በአል #በሰላም እንዲጠናቀቅ የአለታ ጩኮ ወጣቶች ያደረጉት ተሳትፎ እጅግ አስደሳች ነበር፡፡"
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ቡሌሆራ🔝የጥምቀት በዓል በቡሌ ሆራ ከተማ በሰላም ተከብሯል! ለበዐሉ በሰላም መከበር የከተማው ወጣቶች እና የዩኒቨርሲቲው ተማሪዎች ላደረጉት አስተዋፅኦ ቻናላችን ሊያመሰግናቸው ይወዳል።
@tsegabwolde @tikvahethiopia
@tsegabwolde @tikvahethiopia