TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.5K photos
1.43K videos
206 files
3.96K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
ጎንደር🔝

#የጥምቀት_በዓል ከመድረሱ በፊት የማዕከላዊ #ጎንደር ዞን የባሕል ሳምንት ያካሂዳል፡፡ የባሕል ሳምንቱም የአካባቢውን ትውፊታዊ ማንነት እና አጋጊያጥን ጨምሮ ለጎብኝዎች በጎዳና ላይ ትርኢት ያሳያል፡፡ የጎዳና ላይ ትርኢቱም የጥምቀት በዓል ከመከበሩ በፊት የሚካሄድ በመሆኑ የአካባቢውን ባሕል በአምባሳደሮቹ አማካኝነት ፍንትው አድርጎ በማሳየት ትልቅ ሚና እንደተወጣም ተነግሯል፡፡ ስምንተኛው የባህል ሳምንት ፌስቲባል በጎንደር ከጥር 7 እስከ 9/2011 ሲከበር ቆይቶ ከማዕከላዊ ጎንደር የተወጣጡ የባሕል አምባሳደሮች ዛሬ ትርኢታቸውን በጎዳና ላይ በማቅረብ አጠናቅቀዋል፡

ምንጭ፦ አብመድ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update በታላቁ የህዳሴ ግድብ ወቅታዊ ጉዳዮች ዙሪያ መንግስታዊና መንግስታዊ ያልሆኑ ተቋማት ውይይት እያደረጉ ነው። የውይይቱ ዓለማ #የተቀዛቀዘውን ህዝባዊ ተሳትፎ ለመመለስ እንደሆነ ተገልጿል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update የጀርመኑ ፕሬዝዳንት ኢትዮጵያን ይጎበኛሉ፡፡ በአዲስ አበባ የጀርመን ኢምባሲ ባሰራጨው መረጃ ፕሬዝዳንት ፍራንክ ቫልተር ሽታንማየር ከጥር 19-22 ባሉት ለቀናት በሚያደርጉት ጉብኝት ከፕሬዳንት ሳህለ ወርቅ ዘውዴና ከጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ አሕመድ ጋር ይወያያሉ፡፡ ላሊበላ የጉብኝታቸው አንዷ አካል ናት፡፡

Via wazemaradio
@tsegabwolde @tikvahethiopia
የሟቾች ቁጥር 21 ደረሰ‼️

በኬንያ ዋና ከተማ ናይሮቢ ውስጥ በሚገኝ ባለ አምስት ኮከቡ ዱሲት ዲ2 ሆቴልና የንግድ ማዕከል ባሳለፍነው ማክሰኞ #በታጠቁ_ኃይሎች በተፈጸመው ጥቃት የሞቱት ሰዎች ቁጥር 21 ደርሷል።

ጥቃቱ ከተከፈተበት ቅንጡ ሆቴልና የገበያ ማዕከል በመቶዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ጉዳት ሳይደርስባቸው የወጡ ሲሆን 28 ሰዎች ቆስለዋል። የኬንያ ቀይ መስቀል ማህበር እንዳስታወቀው 19 ሰዎች እስካሁን የገቡበት አልታወቀም።

አልሸባብ እጄ አለበት ያለውን ጥቃት ለመቆጣጠር የፀጥታ ኃይሎች 19 ሰዓታት ወስዶባቸዋል።

የኬንያው ፕሬዚዳንት ኡሁሩ ኬንያታ ትናንት በበብሔራዊ ቴሌቪዥን ባደረጉት ንግግር ጥቃተን የፈፀሙት #አምስት ታጣቂዎችን #በመግደል የኦፕሬሽን ስራው #መጠናቀቁን ተናግረዋል።

ከጥቃቱ ጋር ግንኙነት እንዳላቸው የተጠረጠሩ ሁለት ሰዎች በቁጥጥር ስር መዋላቸውን አዣንስ ፍራንስ ፕሬስ ዘግቧል።

ኬንያ አልሸባብን ለመዋጋት ወታደሮቿን ወደ ሶማሊያ ከላከችበትከፈረንጆቹ 2011 ጥቅምት ጀምሮ የሽብር ቡድኑ የጥቃት ዒላማ ሆናለች።

ምንጭ፦ ቢቢሲ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update ወይዘሮ ዝናሽ ታያቸው ሰበታ ዓይነ ስውራን ትምህርት ቤትን እየጎበኙ ነው፡፡ጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ አህመድ በቅርቡ ከመምህራን ጋር ውይይት ባደረጉበት ወቅት ከሰበታ አይነስውራን ት/ቤት የተወከሉ መምህር ጠቅላይ ሚኒስትሩ ት/ቤቱን እንዲጎበኙ ጠይቀዋቸው የነበረ ሲሆን ዶ/ር ዐቢይም ከቻሉ እርሳቸው ካልቻሉ ግን ቀዳማይ እመቤት ወ/ሮ ዝናሽ ታያቸው እንደሚጎበኟቸው ቃል መግባታቸው ይታወሳል፡፡

Via ENA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update አትሌት ደራርቱ ቱሉ የአድዋን ድል ለመዘከር በባዶ እግሯ 500 ሜትር ልትሮጥ ነው። የአድዋ ድልን የሚዘክር የ10 ኪሎ ሜትር የጎዳና ላይ ሩጫ በአዲስ አበባ የካቲት 24 ቀን 2011 ዓ.ም ሊካሄድ ነው። የውድድሩ የክብር አምባሳደር የሆነችው አትሌት ደራርቱ ቱሉ በጎዳና ሩጫው ላይ እንደምትሳተፍ ገልጻለች። ''ለመጨረሻ ጊዜ በውድድር የተሳተፍኩት ከስምንት ዓመት በፊት ነው፤ ከሁለት ዓመት በፊት በህዳሴው ግድብ ሩጫ ተሳትፎ ነበረኝ፤ ለአድዋው ሩጫ ልምምድ ሰርቼ 9 ነጥብ 5 ኪሎ ሜትሩን በጫማ የተቀረውን 500 ሜትር በባዶ እግሬ ለመሮጥ ቃል እገባለሁ'' ብላለች። ኢዜአ እንደዘገበው የውድድሩ አምባሳደር ሆና በመመረጧ ከፍተኛ ኩራትና ክብር እንዲሁም እድለኝነት እንደተሰማት ተናግራለች። በአድዋ ድል እናቶችና አባቶቻችን ደማቸውን አፍሰው ያቆዩትን ታሪክና ጀግንነት ሁሉም በተሰማራበት መስክ ውጤታማ በመሆን በስራው ጀግና መሆን እንዳለበትነው የጠቆመችው።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ምዕራብ ጉጂ ዞን‼️

በኦሮሚያ ክልል በምዕራብ ጉጂ ዞን በፀጥታ ችግር ተዘግተው የነበሩ 33 ትምህርት ቤቶች #ማስተማር ጀምረዋል። በአሁኑ ወቅት በአካባቢው ተፈጥሮ የነበረው የፀጥታ ችግር ተሻሽሎ  አንጻራዊ ሰላም መስፈኑን ዋና አስተዳዳሪው አቶ አበራ ቡኖ ተናግረዋል። በዞኑ ተከስቶ የነበረው የፀጥታ ችግር በማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ እንቅስቃሴ ላይ አሉታዊ ተፅዕኖ ፈጥሮ እንደነበርም ገልጸዋል። በአባገዳዎች ሰብሳቢነት አስተዳደሩ ከኦሮሞ ነፃነት ግንባር (ኦነግ) አባላት ጋር በመወያየት በአሁኑ ወቅት በአካባቢው አንጻራዊ ሰላም መስፈኑን ጠቁመዋል። በዞኑ በሚገኙ ዘጠኝ ወረዳዎችና በሁለት ከተሞች የተካሄደውን የሰላም ውይይት ተከትሎ ተዘግተው የነበሩ 33 ትምህርት ቤቶች ተከፍተው ማስተማር መጀመራቸውን ጠቅሰዋል።

በፀጥታ ችግር አገልግሎት መስጠት ያቆሙ የመሰረተ ልማት ተቋማትም በአብዛኛው ሥራ መጀመራቸውን አስታውቀዋል። በዱግዳ ዳዋና ቡሌ ሆራ ዙሪያ ወረዳ ያልተከፈቱ አንዳንድ ትምህርት ቤቶችን ሥራ ለማስጀመር በአሁኑ ወቅት ከአካባቢው ነዋሪዎች ጋር ውይይት እየተካሄደ መሆኑንም አቶ አበራ አመልክተዋል፡፡ በጉጂ ዞን በአሁኑ ወቅት 592 ትምህርት ቤቶች የመማር ማስተማር ተግባራቸውን በአግባቡ እየተወጡ ይገኛሉ። በትምህርት ቤቶቹ ከ300 ሺህ የሚበልጡ ተማሪዎችም መደበኛ ትምህርታቸውን እየተከታተሉ መሆኑን ከዞኑ የተገኘው መረጃ ያስረዳል።

ምንጭ፦ኢዜአ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ጅማ🔝በጅማ ከተማ #የነዳጅ_እጥረት መከሱትን የTIKVAH-ETH ቤተሰብ አባላት ገልፀዋል። መንግስት ችግሩን እንዲቀርፍም ጠይቀዋል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ብርጋዴር ጀኔራል #አሳምነው_ጽጌ

"በቅማንት ስም የሚንቀሳቀሱ ታጣቂ ኃይሎች በሰነዘሩት ጥቃት #በአንድ መንደር 200 ቤቶች ተቃጥለዋል፤ 2 ሺ ዜጎች ተፈናቅለዋል፤ 55 ሰዎች ሞተዋል፡፡"
.
.

"ከሌላ አካባቢ መጥተው #በግጭት ሲሳተፉ የነበሩና የሞቱ ሶስት ሰዎች መኖራቸውን መታወቂያቸውን በመመልከት #አረጋግጠናል፡፡"
.
.

"ጥፋት #ለመፈጸም የተደራጀው ኃይል ለጊዜው #ተገቷል፤ የታጠቁ ኃይሎች በመሸጉበት ስፍራ ተደምስሰዋል፡፡ በአማራ ክልል በኦሮሚያ ልዩ ዞን ባቲ አካባቢና በጎረቤት ክልልም ሕገወጥ ወታደራዊ ማሰልጠኛ ጣቢያዎች በቅርብ ርቀት አሉ። የእኛን እርምጃ ወስደናል፡፡ የቀረውንም ከሚመለከታቸው ጋር #መፍትሄ ለመስጠት በቅንጅት እየሰራን ነው፡፡"

©አዲስ ዘመን
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ሰበታ ዓይነ ስውራን ትምህርት ቤት🔝

ቀዳማዊት እመቤት ወይዘሮ #ዝናሽ_ታያቸው በሰበታ የሚገኘውን የሰበታ ዓይነ ስውራን ትምህርት ቤት ጎብኝተዋል። ቀዳማዊት እመቤት ወይዘሮ ዝናሽ ታያቸው በጉብኝቱ ወቅትም ከባለድርሻ አካላት ጋር በትምህርት ቤቱ ዙሪያ ውይይት አደርገዋል። በቆይታቸውም በትምህርት ቤቱ አሉ በተባሉ ችግሮች ዙሪያ እና በመፍትሄዎቻቸው ላይ ምክክር ተደርጓል።

Via EPA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ሻለቃ መስፍን‼️

የፌደራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 10ኛ ወንጀል ችሎት በዛሬ ውሎው በቀድሞው ብረታ ብረትና ኢንጅነሪንግ ኮርፖሬሽን /ሜቴክ/ የብረት ማኑፋክቸሪንግ ግንባታ ኢንዱስትሪ ምክትል ስራ አስኪያጅ ሻለቃ #መስፍን_ስዩም ላይ የአስር ቀናት የክስ መመስረቻ ጊዜ ፈቀደ። ሻለቃ መስፍን ስዩም የቀድሞው ብረታ ብረትና ኢንጅነሪንግ ኮርፖሬሽን የብረት ማኒፋክቸሪንግ ግንባታ ኢንዱስትሪ ምክትል ስራ አስኪያጅና የግብይትና ሽያጭ ኃላፊ በነበሩበት ወቅት ስልጣናቸውን በመጠቀም ያለግልጽ ጨረታ ግዥ በመፈጸም ተጠርጥረው ምርመራ ሲደረግባቸው መቆየቱ ይታወሳል፡፡

@tsegabwolde @tikvahethiopia
የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን‼️

የከተራና የጥምቀት በዓላት በሰላም እንዲከበሩ የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ዝግጅቱን አጠናቆ ወደ ስራ መግባቱን አስታወቀ፡፡

የከተራ እና የጥምቀት በዓላት ያለምንም የፀጥታ ችግር በሰላም እንዲከበሩ ከበዓሉ አዘጋጅ ኮሚቴ፣ ከሌሎች የፀጥታ እና የፍትህ አካላት እንዲሁም የፀጥታው ዋና ባለቤት ከሆነው የአዲስ አበባ ከተማ ነዋሪዎች ጋር እየሰራ መሆኑን የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን አስታውቋል፡፡

ኮሚሽኑ በዓላቱ በሰላም ተጀምረው እንዲጠናቀቁ ለወንጀል እና ትራፊክ አደጋ መከላከል ተግባሩ ልዩ ትኩረት በመስጠት በርካታ የሰው ኃይል ማሰማራቱን ገልጿል።

በታቦት ማደሪያ ስፍራዎች በተለይም በርካታ የበዓሉ ታዳሚዎች በሚገኙበት ጃን ሜዳ ጊዜያዊ ፖሊስ ጣቢያ ተከፍተው አግልጋሎት የሚሰጡ መሆኑ ነው የተገለፀው።

ፀበል በሚረጭበት ወቅትም በሚፈጠር ግፊያ ምዕመናኑ ጉዳት እንዳይደርስበት፣ ንብረቶቹ እንዳይሰረቁበት እንዲሁም ከስፍራ ወደ ስፍራ ሲንቀሳቀሱ የትራፊክ አደጋ እንዳይከሰት ተገቢውን ጥንቃቄ ማድረግ እንዳለበት ተገልጿል።

የእምነቱ ተከታዮች በተለይ ወጣቶች ከዚህ በፊት እንደሚያደርጉት ሁሉ በተደራጀ መንገድ ከፖሊስ እና ከሌሎች የፀጥታ አካላት ጎን በመቆም ለበዓሉ በሰላም መከበር እያደረጉት ያለውን አስተዋፅኦ አጠናክረው ሊቀጥሉ ይገባል ተብሏል።

ህብረተሰቡ በማንኛውም ወቅት ከፀጥታ ስራ ጋር ተያይዥ እና አጠራጣሪ ነገሮች ሲመለከት እና ማንኛውንም የፖሊስ አገልግሎትን ለማግኘት በስልክ ቁጥር 01-11-26-43-77 ፣ 01-11-26-43-59 ፣ 01-18-27-41-51፣ 01-11-11-01-11 አሊያም በ991 ነፃ
የስልክ መስመር በመጠቀም ጥቆማ እንዲሰጥ ጥሪ ቀርቧል።

በተጨማሪም ኮሚሽኑ ከጥር 10 ቀን 2011 ዓ.ም ጀምሮ በዓሉ እስከሚጠናቀቅ ድረስ በጃን ሜዳ ዙሪያ ተሽከርካሪ አቁሞ መሄድ ክልክል መሆኑንና አሽከርካሪዎች ተገንዝበው አማራጭ የማቆሚያ ስፍራዎችን እንዲጠቀሙ አሳስቧል፡፡

ምንጭ፦ fbc
@tsegabwolde @tikvahethiopia