TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
59.4K photos
1.51K videos
215 files
4.12K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
ኦነግ ላይ #ተሰነዘረ ስለተባለው የአየር ጥቃት! #ጋዜጠኛ_ኤልያስ_መሰረት(AP) ሰሞኑን አንዳንድ የሀገር ውስጥ ሚድያዎች በኦነግ ማሰልጠኛ ካምፖች ላይ የአየር ጥቃት መድረሱን ሲዘግቡ ሰንብተዋል። አንድ የኦሮሚያ ክልል ከፍተኛ ባለስልጣን ትናንት ምሽት anonymously የነገሩኝ ግን ፈፅሞ የተለየ ነበር፦ "ያው እንደምታውቀው መከላከያ የራሱ ስርአት ስላለው እና እኔም ወታደር ስላልሆንኩ ዝም ብዬ በነሱ…
"የአየር ጥቃት ተፈፅሟል" ኦነግ‼️

ዕሁድ ጠዋት የሀገር መከላከያ በምዕራብ ኦሮሚያ በሚገኙ የኦነግ ማሰልጠኛ ጣቢያዎች ላይ የአየር ጥቃት ሰንዝሯል የሚል መረጃ በስፋት ተሰራጭቶ ነበር።

የምዕራብ ወለጋ ዞን አስተዳዳሪ የሆኑት አቶ #ገመቺስ_ተመስገን በጉዳዩ ላይ BBC የአማርኛው አገልግሎት አስተያየታቸውን ጠይቆ፤ ''ይህ መረጃ እስካሁን አልደረሰኝም። በምዕራብ ኦሮሚያ የሀገር መከላከያ ሠራዊት ይንቀሳቀሳል። በተለያዩ አጋጣሚዎችም ከኦነግ ሠራዊት ጋር የተኩስ ልውውጥ አድርጓል። ዕሁድ ዕለት የአየር ጥቃት ተሰንዝሯል ወይም #አልተሰነዘረም ማለት #አልችልም'' ብለዋል።

በማኅበራዊ ሚዲያዎች ላይ የአየር ጥቃት የተፈጸመው በቤጊ እና ጊዳሚ ወረዳዎች አዋሳኝ ድንበር ላይ መሆኑ በስፋት ተነግሯል። ይሁን እንጂ BBC ያነጋገራቸው የአከባቢው ነዋሪዎች "የአየር ጥቃት ተፈጽሟል ሲባል ሰማን እንጂ ያየነው ነገር የለም" ይላሉ።

ነዋሪዎቹ እንደሚሉት፤ የአየር ጥቃት ሲፈጸም #ባይመለከቱም በአከባቢው የጦር ሄሊኮፕተሮች በብዛት ስለሚመላለሱ ከፍተኛ ስጋት ገብቷቸዋል።

#የኦነግ_ሸኔ የሥራ አሰፈጻሚ ኮሚቴ አባል የሆኑት አቶ #ሚካኤል_ቦረና ግን መንግሥት በቤጊ እና ጊዳሚ ወረዳዎች ውስጥ የአየር ጥቃት #እየሰነዘረ ነው ሕዝቡም እየተጎዳ ነው ብለዋል። አቶ ሚካኤል እንደሚናገሩት፤ የኦነግ ጦር የነበረበትን ስፍራ ሳይለቅ እራስን #የመከላከል እርምጃ እየወሰደ ነው።

ምንጭ፦ BBC
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ጃል ኤልያስ‼️

የደቡባዊ ዞን የኦነግ ጦር መሪ የሆኑት ጃል #ኤሊያስ_ጋምቤላ የአባገዳዎችን ጥር በመቀበል ጦራቸውን አስቀምጠው በሰላማዊ መልክ ለመታገል ወስነው ህዝባቸውን ተቀላቅለዋል።

ምንጭ፦ ደረጀ ገረፋ ቱሉ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
የጉጂ ኦሮሞ አባ ገዳዎች🕊

የደቡብ ዞን የኦነግ ጦር የጉጂ ኦሮሞ #አባ_ገዳዎች ያቀረቡለትን #የሰላም_ጥሪ ተቀበለ። የጉጂ ዞን የኦነግ ጦር አባ ገዳዎች ባወጁት የሰላም ሳምንት ወቅት የቀረበለትን የሰላም ጥሪ ተቀብሎ በትናንትናው እለት ወደ ሰላማዊ ትግል መመለሱ ታውቋል። የጉጂ አባ ገዳዎች ባሳለፍነው ሳምንት አውጀውት የነበረው የሰላም ሳምንት በዚህኛውም ሳምንት እንዲቀጥል ተወስኗል፡፡

Via Ahadu Radio
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update በኢትዮጵያ እና ኤርትራ መካከል #ህጋዊ የድንበር ላይ ንግድ ልውውጥ ለማስጀመርና ለመቆጣጠር አራት የንግድ ማስተላለፊያ ኬላዎችን ለመክፈት የልየታ ስራ ማጠናቀቁን የጉምሩክ ኮሚሽን አስታወቀ። ከሚከፈቱት ኬላዎች መካከል ሁለቱ በዛላምበሳና ራማ የሚገኙ ናቸው። በአገሮቹ መካከል ተፈጥሮ በነበረው ግጭት ሳቢያ ምጣኔ ኃብትን ጨምሮ አጠቃላይ ግንኙነታቸው ተቋርጦ ለሁለት አስርት ዓመታት ቆይቷል።

via ena
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update የኢህአዴግ ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ዛሬ መደበኛ ስብሰባውን ጀምሯል፡፡ ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴው በ11ኛው ድርጅታዊ ጉባዔ የተቀመጡ አቅጣጫዎችን አፈጻጸም፤ በሀገራችን ወቅታዊ ሁኔታ እና የለውጥ እንቅስቃሴ ሂደት፤ እንዲሁም የድርጅት እና የመንግስት የስራ አፈጻጸም ጉዳዮች ላይ ትኩረት በማድረግ በጥልቀት ተወያይቶ አቅጣጫዎችን ያስቀምጣል።

ምንጭ፡- የኢህአዴግ ም/ቤት ፅ/ቤት
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ባህር ዳር‼️

ባለፉት ሁለት ሳምንታት በባህርዳር ከተማ ተጠልለው የሚገኙ የቡሌ ሆራ ዩንቨርስቲ ተማሪዎች መፍትሄ እንዲሰጣቸው ለመጠየቅ ዛሬ ሰልፍ በወጡበት ወቅት ከፖሊስ ጋር #ተጋጭተዋል

ግጭቱ የተፈጠረው ተማሪዎቹ ከመንግስት ባለስልጣናት ጋር ያደረጉት ውይይት #ካለውጤት መጠናቀቁን ተከትሎ መከፋታቸውን ሀይል በተሞላበት ሁኔታ መግለጽ በመጀመራቸው ነው።

መንግስት ተማሪዎቹ ወደ ቡሌሆራ ተመልሰው መሄድ እንዳለባቸው የገለጸ ሲሆን፤ ተማሪዎቹ በአማራ ክልል በሚገኙ ዩንቨርስቲዎች እንመደብ በማለት ጠይቀዋል። ተማሪዎቹ ባለፉት ሳምንታት በተደጋጋሚ ጥያቄያቸውን በሰልፍ ማቅረባቸው ይታወሳል።

via elu
@tsegabwolde @tikvahethiopia
አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ‼️

ከበርካታ የሀገራችን #ከፍተኛ_ትምህርት_ተቋማት ተማሪዎች በተደጋጋሚ ከሚመጡልኝ ጥቆማዎች መካከል አንዱ የተማሪዎች ንብረት መዘረፍ ነው። እነዚህ ተደጋጋሚ የዘረፋ ጥቆማዎች ተቋማት ለተማሪዎቻቸው የሚያደርጉት ደህንነት እና ጥበቃን #ጥያቄ ውስጥ የሚያስገባ ነው።

ለማንኛውም ትላንት የ5 ኪሎ ተማሪዎች የሚኖሩበት 6 ኪሎ ግቢ ውስጥ እንዲህ ሆኗል፦

አጠቃላይ ግምታቸው 85,000 ብር የሚያወጡ ላፕቶፖች እና samsung ታብሌት ከህንፃ ቁጥር 52 ከማደሪያ ክፍል 322 መዘረፉን ተማሪዎች ጠቁመዋል። የጠፉት ንብረቶች በውስጣቸው ተማሪዎቹ በቅርቡ የሚያስረክቧቸው ፕሮጀክቶችን የያዙ ናቸው።

ተማሪዎቹ ስለሁኔታው ሲያስረዱ፦

"ትላንት ምሽት እራት ለመመገብ በራችንን ቆልፈን ወጣን በሩን ስለመቆለፋችን እርግጠኞች ነን፤ ስንመለስ በሩ ዝግ ነው፤ አጠቃላይ ንብረታችን ግን የለም፤ #ተዘርፈናል!! የተዘረፍነው 7 ላፕቶፕ እና 1 ሳምሰንግ ታብሌት ነው። በጠፉት ላፕቶፖች ውስጥ በቅርቡ የምናስረክባቸው ፕሮጀክቶች አሉ። የተፈጠረውን ነገር ለተቋሙ አሳውቀናል።"

@tsegabwolde @tikvahethiopia
40/60‼️

ከስድስት አመታት በፊት #ምዝገባው የተካሄደው የ40/60 የጋራ የመኖሪያ ቤት ፕሮጀክት አሁን ለባለ ዕድለኞች የሚወጣበት ቀን ተቃርቧል። ይሁንና ጉዳዩ ይመለከተናል በሚሉ ሶስት የመንግስት ተቋማት መካከል በዕጣው ማን ይካተት በሚለው ጉዳይ ዙሪያ መግባባት አልተቻለም። የአዲስ አበባ መስተዳድር፣ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክና የከተማ ልማትና ቤቶች ሚኒስቴር በመካከላቸው የተፈጠረው #ልዩነት ሊፈታ ባለመቻሉ ጉዳዩ ወደ ጠቅላይ ሚንስትር ፅህፈት ቤት አምርቷል።

Via wazemaradio
@tsegabwolde @tikvahethiopia
አማራ🕊ትግራይ!

የአማራ ክልል እና የትግራይ ክልል የሀገር ሽማግሌዎች እና የሀይማኖት አባቶች በሁለቱ ክልሎች #ሰላም ዙሪያ ተወያዩ።

በሁለቱ ክልሎች ሰላም ላይ ያተኮረው ውይይት በዛሬው እለት በአዲስ አበባ ከተማ መካሄዱን የሰላም ሚኒስቴር አስታውቋል።

በውይይቱ ላይ የተገኙት የሰላም ሚኒስቴር የሰላም ግንባታ ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ወይዘሮ #አልማዝ_መኮንን፥ በየትኛው የታሪክ አጋጣሚ ህዝብ ከህዝብ #ተጣልቶ አያውቅም ብለዋል።

የአማራ ክልል እና የትግራይ ክልል ህዝቦች ለዘመናት የኖረ #አብሮነት ያላቸው ተመሳሳይ ባህል የሚጋሩና የተዋለዱ ህዝቦች ናቸው ሲሉም ተናግረዋል።

በሁለቱ ክልሎች መካከል ዘላቂ ሰለም ለማሰፈን ችግሮችን ተሸክሞ የሚቆዝም ሰው ሳይሆን የይቅርታ ልብ ይዞ ህዝብን የሚያቀራርብ የሀገር ሽማግሌና የሀይማኖት አባቶች ያስፈልጉናልም ብለዋል።

ሚኒስቴር ዴኤታዋ የሀይማኖት አባቶች ከፖለቲካ ነፃ በመሆን መንግስት ሲሳሳት አደብ ግዛ ሊሉት እንደሚገባም ተናግረዋል።

የሁለቱ ክልሎች የሀገር ሽማግሌዎች ሰፊ የሃሳብ ለውውጥ ካደረጉ በኋላ እርስ በእርሳቸው በመተቃቀፍ በሁለቱ ክልል ህዝቦች መካከል ዘላቂ ሰላም ለማምጣትና ወንድማማችነታቸውን ለማጠናከር ቃል በመግባታ ተለያይተዋል።

በውይይቱ ላይ አትሌት ሃይሌ ገብረስላሴ፣ ፓስተር ዳንኤልና እና ሌሎች ታዋቂ ግለሰቦች ተገኝተው መልዕክት ማስተላለፋቸውን ከሚኒስቴሩ የተገኘው መረጃ ያመለክታል።
 
ምንጭ፦ ፋና ብሮድካስቲንግ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
"...ከተማውን ለቀው ይውጡ"‼️

"ከቡሌ ሆራ ዩኒቨርስቲ ወጥተው የቆዩ ተማሪወች መንግሥት የሰጣቸውን አቅጣጫ እና መፍትሔ #ካልተቀበሉ ከተማዋን ለቀው ይውጡ" - የባሕር ዳር ከተማ አስተዳደር
.
.

በባሕር ዳር ከተማ አስተዳደር ከቡሌ ሆራ ዩኒቨርስቲ ወጥተው የቆዩ ተማሪዎች መንግሥት የሰጣውን አቅጣጫ እና መፍትሔ የማይቀበሉ ከሆነ ከተማዋን ለቀው እንዲወጡ የከተማ አስተዳደሩ አስታውቋል፡፡

ከቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ በፀጥታ ችግር ምክንያት ወጥተው በባሕር ዳር በተቀመጡ ተማሪዎች እና በከተማዋ በሚስታዋሉ ወቅታዊ ጉዳዮች ላይ ከተማ አስተዳደሩ መግለጫ ሰጥቷል፡፡ የባሕር ዳር ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አቶ ሙሉቀን አየሁ ‹‹የባሕር ዳር ከተማ ከየትኛው ሀገር በችግር ለሚመጡ የማኅበረሰብ ክፍሎችን እየተቀበለ የሚችለውን ሁሉ እያደረገ ቆይቷል፡፡ ከቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ የመጡ ተማሪዎችንም ከሁለት ሳምንት በላይ ተንከባክቦ አስቀምጧቸዋል›› ብለዋል፡፡

አቶ ሙሉቀን የከተማዋ ማኅበረሰብ የተማሪዎችን ችግር በመረዳት አስፈላጊውን ድጋፍ ሲያርግ መቆየቱንም ተናግረዋል፡፡ ‹‹ተማሪዎች ግን በፍቀር የተቀበላቸውን ማበረሰብ እጁን አመድ አፋሽ አድርገውታል›› ነው ያሉት ከንቲባው።

ከቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ በፀጥታ ችግር ወደ ከተማዋ የመጡ ተማሪዎች መቀመጫቸውን በባሕር ዳር አድርገው የክልሉን መንግሥት ምላሽ እንዲሰጣቸው ጥያቄያቸውን ሲያቀርቡ ቆይተዋል፡፡ የክልሉ መንግሥትም ከተማሪዎች እና ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመምከር ውሳኔ ሰጥቷል፡፡

ከትላንት ጀምሮ ግን ጥያቄያቸውን በኃይል በማደረግ የከተማዋን ሰላም ለመበጥበጥ ጥረት ሲያርጉ እንደነበር ነው ከንቲባው የተናገሩት፡፡ ‹‹ተማሪዎቹ በከተማዋ እየተዘዋወሩ ቤት መትተዋል፤ ንበረት ላይ ጉዳት አድረሰዋል፡፡ በአጠቃላይ የፈጸሙት ተግባር አሳፋሪ እና የሽፍትነት ነው›› ብለዋል ከንቲባው፡፡

ተማሪዎቹ ሲንከባከባቸው የሰነበተውን ማኅበረሰብ ሲማቱ የፀጥታ ኃይሉ በመታገስ የሰው ሕይወት እንዳይጠፋና ንብረት እንዳይወድም በጥንቃቄ ኃላፊነቱን ለመወጣት ጥረት ማድረጉን ነው ከንቲባው የገለጹት፡፡

‹‹በዘሬው ዕለትም ተማሪዎቹ ከተማዋን ሲያበጣብጡ የከተማዋ ወጣቶች ችግሩን በትብብር አብርደውታል›› ነው ያሉት አቶ ሚሉቀን፡፡ ከንቲባው ወጣቶች፣ ማኅበረሰቡ እና የፀጥታ ኃይሉ ለሰላም ላደረጉት ትብብር ምስጋና እንደሚገባቸውም ተናግረዋል፡፡

‹‹ተማሪዎቹ ከአቅም በላይ ስለሆኑ መንግሥት በሰጣቸው አቅጣጫ የማይጓዙ ከሆነ ከተማችን ለቀው ይውጡ›› ሲሉ ነው ከንቲባው ያሳሰቡት፡፡ ወላጆቻቸው ልጆቻቸውን እንዲመክሩም ከንቲባው ጥሪ አስተላልፈዋል፡፡

የባሕር ዳር ከተማ አስተዳደር የሰላም ግንባታ እና የሕዝብ ደኅንነት ቢሮ ኃላፊ አቶ ዘውዱ ዘለቀ ‹‹ተማሪዎቹ መንግሥት በሚሰጣቸው መፍትሔ ላይ ሊስማሙ አልቻሉም፤ የሰላም መማር ማስተማር ሥርዓት እያከናወነ ያለውን የባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲን ጭምር እየገቡ እረብሸዋል›› ነው ያሉት፡፡

ኃላፊው በከተማዋ ስምንት ያክል መኪኖች የጫኑት እህል ያለአግባብ በተማሪዎቹ ምክንያት እንደተራገፈባቸው አስታውቀዋል፡፡ አቶ ዘውዱ ‹‹የፀጥታ ኃይሉ ደከመኝ ሰለቸኝ ሳይል ለሕዝቡ ደኅነነት እየሠራ ነው›› ሲሉም አመሥግነዋል፡፡ ተማሪዎቹን የሚገፋፋ ኃይል እንዳለ ያነሱት አቶ ዘውዱ ‹‹ሰላም ወዳዱ የከተማዋ ወጣት ተማሪዎቹ ከተማዋን ለቀው እንዲወጡ ወስኗል›› ነው ያሉት፡፡

የአማራ ክልል የሰላም ግንባታ እና የሕዝብ ደኅንነት ምክትል ኃላፊ አቶ ገደቤ ኃይሉም የተማሪዎችን ችግር ለመፍታት የክልሉ መንግሥት ሲሰራ መቆየቱን ገልጸዋል፡፡ ‹‹ተማሪዎች ግን በሚሰጣቸው አቅጣጫ ሁሉ ተስማሚ አልሆኑም›› ብለዋል፡፡

ተማሪዎቹ በየቤተሰቦቻቸው እንዲቆዩ እንጂ በአንድ ላይ እንዲሰበሰቡ ተፈቅዶ እንዳልነበር ያመለከቱት አቶ ገደቤ የቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር ተማሪዎቹ የሚያነሱትን ችግር በመፍታት በጉጉት እየጠበቃቸው እንደሆነ ተናግረዋል፡፡ አቶ ገደቤ ‹‹መንግሥት ችግሩን ተረድቶ ሲወያይ ቆይቷል፤ አሁንም መፍትሔ አስቀምጧል›› ነው ያሉት፡፡

በዚህም ‹‹ወደነበሩበት ዩኒቨርሲቲ መመለስ ካፈለጉ ወደየቤተሰቦቻቸው እንዲሄዱ ተወስኗል›› ብለዋል ምክትል ቢሮ ኃላፊው፡፡ በክልሉ የሚስተዋሉ ችግሮችን ለመፍታት ሕዝብን በባለቤትነት በመያዝ እየተሠራ እንደሆነም ተናግረዋል፡፡ በምዕራብ ጎንደር ተከስቶ የነበረው ችግር አንጻራዊ ሰላም እንደታየበት ገልጸው አካባቢው የተጠናከረ ጥበቃ እንደሚያስፈልገው ጠቁመዋል፤ በአፋር አካበቢ የሚነሳውን ችግርም በዘላቂነት ለመፍታት እየሠሩ መሆናቸውን አስታውቀዋል፡፡
 
ምንጭ፦የአማራ ብዙሃን መገናኛ ድርጅት
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update የአማራ ክልል ርእሰ መስተዳድር አቶ ገዱ አንዳርጋቸውና የትግራይ ክልል ምክትል ርእሰ መስተዳድር ዶ/ር ደብረፅዮን ገ/ሚካኤል በሁለቱ ክልሎች ባለው ወቅታዊ ሁኔታ ዙሪያ በአሁኑ ሰአት በአዲስ አበባ ሂልተን ሆቴል በመወያየት ላይ ናቸው።

Via ዋልታ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update የአማራ እና የትግራይ ክልሎች ርዕሰ መስተዳድሮች በዝግ እየመከሩ ነው። ርዕሰ መስተዳድር #ገዱ_አንዳርጋቸው እና ምክትል ርዕሰ መስተዳድር ዶክተር #ደብረጽዮን_ገብረሚካኤል አዲስ አበባ ሂልተን ሆቴል ላይ እየተወያዩ ነው፡፡ በሁለቱ ክልሎች ወቅታዊ ሁኔታና ሠላም ላይ ነው እየተወያዩ ያሉት፡፡ የሀይማኖት አባቶች እና የሀገር ሽማግሌዎችም አብረው እያወያዩዋቸው ይገኛሉ።

ምንጭ፦ አብመድ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ስምምነት ሊፈራረሙ ነው!

የአማራና ትግራይ ክልሎች ርዕሳ መስተዳድሮች ስምምነት ሊፈራረሙ ነው፡፡ የአማራና ትግራይ ክልሎች ርዕሳነ መስተዳድሮች በሁለቱ ክልሎች መካከል እየተስተዋሉ ያሉ ችግሮችን ለመፍታት #ስምምነት ዛሬ በሂልተን ሆቴል ከደቂቃዎች በኋላ #ይፈራማሉ፡፡

‹‹ሕዝቡ ችግሩ የአማራና ትግራይ ክልሎች መንግሥታት ነው›› ማለቱንና በሁለቱ ክልል ሕዝቦች መካከል ችግሮች አለመኖራቸውን የሃይማኖት አባቶችና የሀገር ሽማግሌዎች ተናግረዋል፡፡

የሁለቱን ክልል መንግሥታት መሪዎች ችግሮች መፍትሔ ለመፈለግ ለስድስት ወራት ሕዝቡንና በየደረጃው ያሉ አመራሮችን ያወያዩት የሃይማኖት አባቶችና የሀገር ሽማግሌዎች አሁን ሁለቱም ርዕሰ መስተዳድሮች ችግሩን ለመፍታት ጫፍ መድረሳቸውን አስታውቀዋል፡፡

የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ገዱ አንዳርጋቸው እና የትግራይ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳደር ዶ.ር ደብረፅዮን ገብረሚካኤል ናቸው ስምምነቱን ይፈራረማሉ፡፡

የማስማማት ሂደቱን የሃይማኖት አባቶችና የሀገር ሽማግሌዎች በራሳቸው ተነሳሽነት እንደጀመሩት ገልጸዋል፡፡

የኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ እና የሀገር ሺማግሌዎች ከስድስት ወራት በፊት በፈቃዳቸው ተገናኝተው ወደ ማሸማገል ሂደት መግባታቸውን ነው ያስረዱት፡፡

ምንጭ፦ አብመድ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
የኦሮሚያ ክልል መንግስት‼️

በምእራብ ኦሮሚያ በሚገኙ ዞኖች መንግስት #የአየር_ጥቃት ፈፅሟል በሚል የሚናፈሰው ወሬ #ከእውነት_የራቀ መሆኑን የኦሮሚያ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት አስታወቀ።

የክልሉ መንግስት ኮሙዩኒኬሸን ጉዳዮች ቢሮ ዛሬ ባወጣው መግለጫ፥ መንግስት የህግ የበላይነትን ለማስከበር እያደረገ ባለው እንቅስቃሴ ላይ የሀሰት መረጃዎችን በማሰራጨት ህዝቡን ለማደናገር ሙከራዎች እየተደረጉ ነው ብሏል።

የመንግስት ጦር በሰላማዊ ዜጎች ላይ እርምጃ እየወሰደ ነው የሚለው እና የአየር ጥቃት በመፈፀም ሰላማዊ ዜጎች ላይ ጉዳት እያደረሰ ነው በሚል የተሰራጨው መረጃም ከእውነት የራቀ መሆኑን ቢሮው አስታውቋል።

በዚህ ዙሪያ ያለው ሀቅ መንግስት የህግ የበላይነትን ለማስከበር ስራውን በጥናት ላይ በመመስረት እና ጥንቃቄ በተሞላበት መልኩ እያከናወነ መሆኑ ነው ብሏል።

ይህ በእንዲህ እንዳለ በአካባቢው ላይ ያለው የፀጥታ ችግር ይህን ያክል የአየር ጥቃት እስከመውሰድ የሚያደርስ አይደለም ሲልም ቢሮው አስታውቋል።

መንግስት አሁንም ቢሆን የህዝቡን ደህንነት ለማስጠበቅ ያለበትን ሀላፊነት እና ግዴታ ለመወጣት የጀመረውን ስራ ከፍተኛ ጥንቃቄ በተሞላበት መልኩ የሚያስቀጥል በመሆኑ የአካባቢው ህዝብ ወንጀለኞችን አሳልፎ መስጠቱን እንዲቀጥል እና ለሰላም የሚያደርገውን ትብበር አጠናክሮ እንዲቀጥል የክልሉ መንግስት ጥሪውን አቅርቧል።

ምንጭ፦ FBC
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update በተያዘላቸው ጊዜ ያልተጠናቀቁ ግዙፍ የመንግሥት ልማት ፕሮጄክቶች በሀገሪቱ ላይ የ1 ቢሊዮን ኪሳራ ማድረሳቸውን ብሄራዊ ፕላንና ልማት ኮሚሽንን ጠቅሶ ኢቢሲ ዘግቧል፡፡

@tsegabwolde @tikvahethiopia
የነዳጅ እጥረት በአዲስ አበባ‼️

በአዲስ አበባ ከተማ የተፈጠረው #የነዳጅ_እጥረት በአሽከርካሪዎች ላይ ጫና መፍጠሩን የታክሲና የባጃጅ አሽከርካሪዎች ገለጹ። የኢትዮጵያ ነዳጅ አቅራቢ ድርጅት ያጋጠመውን ወቅታዊ የነዳጅ አቅርቦት ችግር በቀጣዮቹ ሁለት ቀናት እንደሚፈታ አመልክቷል። የትራንስፖርት አገልግሎት የሚሰጡ ታክሲዎችና ባለሶስት እግር ተሽከርካሪዎች (ባጃጅ) አሽከርካሪዎች ከነዳጅ ማደያ ቤንዚን ለማግኘት በመቸገራቸው በእለት ኑሯቸው ላይ ጫና ማሳደሩን ጠቁመዋል። የእለት ገቢ እያገኙ ቤተሰቦቻቸውን የሚያስተዳድሩ በመሆኑ ረጅም ሰዓት በነዳጅ ማደያ ተሰልፈው በማሳለፋቸው ገቢ እያገኙ እንዳልሆነ ለኢዜአ ገልጸዋል።

ምንጭ፦ ኢዜአ
@tsegabwolde @tikvahethiopia