TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.5K photos
1.43K videos
206 files
3.96K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
Audio
"በምዕራብ ወለጋ 10 ባንኮች ተዘርፈዋል"- የዞኑ አስተዳዳሪ

በኦሮሚያ ክልል ምዕራብ ወለጋ ዞን 10 ባንኮች በታጣቂዎች መዘረፋቸውን የዞኑ አስተዳዳሪ ለDW ተናግረዋል። ታጣቂዎቹ በዞኑ የአራት ወረዳዎች የመንግስት መስሪያ ቤቶችን ማቃጠላቸውን እና በሌሎቹ ወረዳዎች #ዝርፊያ መፈጸማቸውን ገልጸዋል።

የምዕራብ ወለጋ ዞን አስተዳዳሪ አቶ ገመቺስ ተመስገን ለDW እንደተናገሩት በመንግስት እና የግል ባንኮች ላይ ዝርፊያው የተፈጸመው ትላንት 10 ሰዓት ገደማ ነው። አስተዳዳሪው የታጠቁ ባሏቸው ኃይሎች ተፈጸመ ያሉት ዝርፊያ የተከናወነው በተመሳሳይ ሰዓት መሆኑንም ገልጸዋል።

“የታጠቀው ኃይል እዚህ አካባቢ ላይ ከፍተኛ ጉዳት እያደረሰ ነው። እስካሁን ባለው ተጨባጭ ሁኔታ እና በደረሰን መረጃ መሰረት 10 የሚሆኑ የመንግስት እና የግል ባንኮች ተዘርፈዋል” ብለዋል የዞኑ አስተዳዳሪ። ከተዘረፉት ውስጥ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ፣ አዋሽ ባንክ፣ ሕብረት ባንክ እንዲሁም የኦሮሚያ ብድር እና ቁጠባ ባንክ እንደሚገኙበት አስረድተዋል። በባንኮቹ ዝርፊያ የተወሰደው ገንዘብ መጠኑ ግን እስካሁን አለመታወቁን ጨምረው ገልጸዋል።

ምንጭ፦ DW AMHARIC
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#ዝርፊያ

የኤሌክትሮኒክ ትራንስፖርት አገልግሎት የሚሰጡ ዜጎች በተለያየ ጊዜ ዘረፋን ጨምሮ እስከ ግድያ የሚደረስ ወንጀል ይፈፀምባቸዋል።

ከዚህ ቀደም ተደጋጋሚ የወንጀል ድርጊት ሲፈፀም ሰምተናል።

ከሰሞኑን አንድ በዚሁ በኤሌክቶኒክ የትራንስፖርት አገልግሎት ላይ ሚሰራ ሰራተኛ ዝርፊያ እንደተፈፀመበት አመክቷል።

ስሙ ሚኪያስ ተፈሪ የተባለው ወንድማችን ራሱንና ቤተሰቡን ለማስተዳደር የሚሰራባትን መኪና ይዞ ቆሞ ሥራ ሲጠባበቅ ነበር (ባለፈው ረቡዕ ምሽት)።

ከአገግልሎት ሰጪ ድርጅቱ ተደውሎ ከሳሪስ ጀሞ ሥራ እንዲሄድ ይጠየቃል ፤ የድርጅቱን ትእዛዝ ተቀብሎ ሦስት ሰዎችን አሳፍሮ ወደታዘዘበት ጀሞ ይሄዳል።

ደንበኞቹ ያሉበት ጀሞ ደረሱ። " ሂሳብ ስንት ቆጠረ?" ብለው ጠየቁ። ሂሳቡን ነገራቸው። እነርሱ ግን በያዙት ስለት አስፈራርተው መኪናውን ነጥቀው ተሰውሩ።

ሚኪያስ ቤተሰቡን የሚያስተዳድርበትን መኪና በዚህ መንገድ ተነጥቋል። ሚኪያስ ለፖሊስ ጣቢያ ድርጊቱን አሳውቋል። እስከዛሬ ሰኞ ድረስ አንዳችም ፍንጭ አልተሰማ።

መኪናው ከላይ በፎቶው የተያያዘ ሲሆን ታፋልጉት ዘንድ ጥሪ አቅርቧል ፤ (0922875988)

በሌላ በኩል ፤ በመሰል ስራ ላይ እራሳቸውን እና ቤተሰባቸውን የሚያስተዳድሩ ወገኖች በተደጋጋሚ የሚሰሙት ዝርፊ እና ወንጀል ለስራቸው ስጋትን እየፈጠረ መሆኑን በመግለፅ የደህንነት ጉዳይ ይታሰብበት ፤ ወንጀለኞችንም ተከታትሎ አድኖ መያዝ ይገባል ሲሉ አስገንዝበዋል።

@tikvahethiopia