TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.6K photos
1.43K videos
206 files
3.96K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
“...ካለብን ታሪካዊ እና ሞራላዊ ኃላፊነት አንጻር ናሚቢያውያን ይቅር እንዲሉን እንጠይቃለን” - ሄኮ ማስ

ጀርመን ናሚቢያን ቅኝ በገዛችበት ወቅት ጅምላ ጭፍጨፋዎችን መፈጸሟን አመነች፡፡

ጀርመን እአአ ከ1904-08 ባሉት ዓመታት በናሚቢያ ዜጎች ላይ የፈጸመችውን ግድያ በጅምላ ጭፍጨፋነት ለመቀበል ስታቅማማ ቆይታለች፡፡

ነገር ግን 5 ዓመታትን በወሰደ ንግግር ጭፍጨፋውን ስለመፈጸሟ አምና ተቀብላለች።

ይህን ተከትሎ በተደረሰ ስምምነት መሰረት ለተለያዩ ልማቶች የሚውል የ1.3 ቢሊዬን ዶላር ድጋፍ ለማድረግ ተስማምታለች።

ጄኔራል ሎታር ቮን ትሮታ በሄሬሮ ጎሳዎች የተነሳውን የጸረ ቅኝ ግዛት ተቃውሞ ለማርገብ በማሰብ ሙሉ የጎሳው አባላት ላይ እርምጃ እንዲወሰድ በማዘዝ 65 ሺ ገደማ የጎሳው አባላት መጨፍጨፋቸውን እና በትንሹ 1 ሺ የናማ ጎሳ አባላት መገደላቸውን የታሪክ አዋቂዎች ይናገራሉ።

የጀርመን ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሄኮ ማስ “ካለብን ታሪካዊ እና ሞራላዊ ኃላፊነት አንጻር ናሚቢያውያን ይቅር እንዲሉን እንጠይቃለን” ብለዋል ባወጡት መግለጫ፡፡

ማስ በመግለጫቸው “ዓላማችን ተጎጂዎቹ የሚታወሱበትን እውነተኛ የእርቅ መንገድ መፈለግ ነው” ብለዋል፡፡

ውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ፥ በዛሬዋ ናሚቢያ ቅኝ ግዛት ዘመን የተፈጸሙ የጭካኔ ድርጊቶችን “በይፋ ጅምላ ጭፍጨፋ ብለን እንጠራቸዋለን” ሲሉ ተናግረዋል።

#አልዓይን #AP

@tikvahethiopia
የአምባሳደር ዲና ሙፍቲ ሳምንታዊ መግለጫ ፦

የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር ዲና ሙፍቲ ዛሬ ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥተዋል።

አምባሳደር ዲና ፥ የተለያዩ ጉዳዮችን ያነሱ ሲሆን ፣ ከአሜሪካ ጋር የተፈጠረው አለመግባባት የመግለጫቸው ዋነኛ አጀንዳ ነበር፡፡

ቃል አቀባዩ ምን አሉ ?

- አሜሪካ የጣለችውን እገዳ በማስመልከት የኦሮሚያ ክልል ፕሬዜዳንት ሽመልስ አብዲሳ “የነቀዘ ስንዴ ነው የሚቀርብን” ማለት ያሰሙትን ንግግር በተመለከተ አምባሳደር ዲና ሙፍቲ ፥ “ግለሰቦች የመናገር መብት አላቸው ፤ ይህም የግል አስተያየትና ስሜታቸው ነው” ብለዋል፡፡

- የኦሮሚያ ፕሬዜዳንት አቶ ሽመልስ አብዲሳ “የነቀዘ ስንዴ” ሲሉ የተናገሩት ንግግር የመንግስት አቋም ሳይሆን የግላቸው አስተያየት መሆኑን አምባሳደር ዲና ገልፀዋል።

- በውጭ ጉዳይ ደረጃ “ጉዳዩን የማጋጋል ፍላጎት የለንም” ብለዋል ፤ “የተፈጠረው ጉዳይ በዲፕሎማሲያዊ መንገድ እንዲፈታ በጋራ ወዳጆቻችን በኩል እየተነጋገርን ነው ያለነው” ሲሉ አሳውቀዋል።

- የሴናተር ጂም ኢንሆፌ ጉብኝት በኢትዮጵያ እና በአሜሪካ መካከል የተፈጠረውን ጉዳይ ለመፍታት እየተኬደ ያለበት የዴፕሎማሲ መንገድ አካል ሊሆን እንደሚችል ጠቁመዋል ፤ "የአሜሪካ አቋም ይቀየራል ብለን ነው የምናምነው ፣ መቼና እንዴት የሚለው ግን እነሱን የሚመለከት ነው” ብለዋል።

- ሴናተር ጂም ኢንሆፌ ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ እንዲሁም ከምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን ጋር መገናኘታቸውን እና “ውጤታማ ጉብኝት” አድርገዋል ብለዋል።

ያንብቡ : telegra.ph/AL-AIN-06-02

#አልዓይን

@tikvahethiopia
"...በሰሜን የገጠመን ግጭት እስካሁን ከገጠሙን ከሁሉም የከፋው ነው" - ጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ አህመድ

የኢፌድሪ ጠ/ሚር ዶክተር ዐቢይ አህመድ ያለፉት ሦስት ዓመታት ዋና ዋና ንግግሮቻቸውን የያዘ ''ዐሻራ'' የተሰኘ መጽሐፍ የምረቃ ስነስርዓት እና በኢፕድ 80ኛ ዓመት በዓል ላይ ተገኝተው ነበር።

በዚህም ወቅት ላይ የ3 ዓመታቱን ፈተናዎች በተመለከተ ንግግር አድርገዋል፡፡

ከተናገሩት መካከል ፦

" ተደጋጋሚ ችግር ያሳለፍንባቸው ያለፉት ሶስት ዓመታት ፣ በፊት ከነበሩት 10 ዓመታት ጋር ሲነፃፀሩ ቢያንስ ከጂኦ ፖለቲካ አንፃር የከፉ ጊዜያት ናቸው።

በሰሜን የገጠመንን ግጭት አንዳንዶች ከኢትዮ-ኤርትራ ጦርነት፣ ከካራማራው ጦርነት ጋር ሊያነፃፅሩ ይሞክራሉ ፣ ነገር ግን ወታደርም ስለሆንኩ ከሁሉም የከፋው ግጭት ነው።

ከጣልያን ጋር ስንዋጋ በጎራዴም ቢሆን እኛ ጎራዴያችንን ይዘን እነሱም በመሳሪያቸው ተዋግተናል። በኤርትራ እና ካራማራውም እኛም እነሱም ባለን ነው የተዋጋነው።

አሁን ግን የነበረው ውጊያ የኛን ትጥቅ እና የኛን መከላከያ በማፍረስ ነው ከኛ ጋር የነበረው ወጊያ።

ባለፉት ሶስት ዓመታት ብዙ ፈተናዎች ውስጥ ሆነን በሰላሙ ጊዜ ተጀምረው መጠናቀቅ ካልቻሉ 10 ትላልቅ የስኳር ፋብሪካዎች 7ቱን አጠናቀናል፤ ሌሎች ብዙ ፕሮጀክቶችንም እንዲሁ።"

#አልዓይን

ፎቶ : የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት

@tikvahethiopia
የግብፅ የውጭ ጉዳይ እና መስኖ ሚኒስትሮች በሱዳን የአንድ ቀን ይፋዊ ጉብኝት አድርገዋል።

የግብፅ ባለስልጣናቱ ከሱዳን አቻዎቻቸው ጋር ሆነው የጋራ መግለጫ አውጥተዋል፡፡

በመግለጫቸው የሕዳሴ ግድቡን ጉዳይ በተመለከተ ሁለገብ ስምምነት ላይ ለመድረስ “ኢትዮጵያ በቁም ነገር ፣ በታማኝነት እና በእውነተኛ የፖለቲካ ፍላጎት እንድትደራደር በቀጣና ፣ በአህጉር እና በዓለም አቀፍ ደረጃዎች ግፊት እንዲደረግ ሁለቱ ሀገራት በጋራ እንደሚሰሩ” አስታውቀዋል፡፡

በዚህም በሕዳሴው ግድብ ሙሌት እና አስተዳደር ላይ “ፍትሃዊ እና ህጋዊ አስገዳጅ ስምምነት እንዲደረስ እንደሚሰሩ” ገልጸዋል፡፡

በቀጠናው እና በአፍሪካ አህጉር ፀጥታ ፣ ሰላም እና መረጋጋትን ለማስጠበቅ ፣ “የግብፅ እና የሱዳን ቅንጅት አስፈላጊነት” ላይ መስማማታቸውንም የሚያትተው መግለጫው ፣ ለዚህም “ኢትዮጵያ በግድቡ ጉዳይ የያዘችውን ፖሊሲ መቀጠሏ የሚያስከትለውን አደጋ ለመከላከል የአለም አቀፉን ማህበረሰብ ንቁ ጣልቃ ገብነትን ይጠይቃል” ብለዋል፡፡

ኢትዮጵያ በመጪው የክረምት ወቅት “የሕዳሴውን ግድብ ለመሙላት የጀመረችውን ጉዞ ዓለም አቀፉ ማሕበረሰብ እንዲያስቆም” ነው በመግለጫቸው የጠየቁት፡፡

አስገዳጅ ስምምነት ሳይደረስ የግድቡን ሁለተኛ ዙር ሙሌት ማከናወን እንደሚያሰጋቸው ሁለቱ ሀገራት በድጋሚ ገልጸዋል፡፡

ሁለቱን የታችኛው ተፋሰስ ሀገራት የመጉዳት ፍላጎት እንደሌላት በተደጋጋሚ የገለጸችው ኢትዮጵያ ፣ አስገዳጅ ስምምነት የመፈረም ፍላጎት የላትም ፤ የግድቡን ሁለተኛ ዙር የውሃ ሙሌትም በተያዘው ጊዜ እንደምታከናውን ቁርጠኛ አቋም ይዛለች፡፡

#አልዓይን

@tikvahethipia
የአረብ ሊግ ስብሰባ እና የኢትዮጵያ ምላሽ :

የዐረብ ሊግ የተመድ ጸጥታው ም/ቤት ኢትዮጵያ በዓባይ ወንዝ ላይ እየገነባች ባለችው ታላቁ የሕዳሴ ግድብ ዙሪያ ስንብሰባ እንዲያደርግ ትላንት ባደረገው ስበባ ጠይቋል።

የሊጉ አባል አገራት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች ባደረጉት ሰብሰባ የሁሉንም አካላት ፍላጎት የሚያሳካ አስገዳጅ ስምምነት ላይ መደረስ እንዳለበት አንስተዋል።

የዐረብ ሊግ አባል ሀገራት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች በአፍሪካ ህብረት አስተባባሪነት እየተካሄደ ያለውን ድርድር አዝጋሚ ነው ሲል ገልጾታል።

ሚኒስትሮቹ በኳታር መዲና ዶኃ ባደረጉት ስብሰባ በአፍሪካ ሕብረት ስር እየተካሄደ ያለው ድርድር አዝጋሚ በመሆኑ የጸጥታው ም/ቤት በግድቡ ዙሪያ ስብሰባ እንዲያደርግ ጥሪ አቅርበዋል።

የሊጉ ዋና ፀሀፊ አህመድ አብዱል ጌት እንዳሉት የግብፅና የሱዳን የውሃ ደህንነት ጉዳይ የዐረብ ሀገራት ደህንነት አካል መሆኑን መግባባት ላይ መደረሱን አስታውቀዋል።

የሕዳሴ ግድብን በተመለከተ የዐረብ ሊግ ለሱዳን እና ለግብፅ ድጋፍ እንዳለውም ዋና ጸሐፊው ገልጸዋል።

ኢትዮጵያ የአረብ ሊግ የህዳሴው ግድብን በተመለከተ በኳታር ተወያይቶ ያሳለፈው ውሳኔ ተቀባይነት የሌለው መሆኑን በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በኩል አሳውቃለች።

የአረብ ሊግ የግብጽ እና የሱዳንን መሰረተ ቢስ ውንጀላ ላይ ሳይመሰረት በህዳሴ ግድቡ ድርድር ዙሪያ ገንቢ ሚና መጫወት ሲገባው ሚዛናዊነት የጎደለው እና ወደ አንድ ወገን ያደለ ውሳኔ መወሰኑ ተቀባይነት እንደሌለው ገልጻለች።

ውሳኔው በቀጠናው የአባይን ወንዝ በትብብርና በዘላቂነት ለመጠቅም የሚያስችል መንገድ አለመሆኑንም አሳውቃለች።

የአርብ ሊግ አባል ሀገራት የአባይ ወንዝን አጠቃቀም እና የኢትዮጵያን ነባር አቋም በሚገባ ሊያውቁ ይገባቸዋልም ብላለች።

#ኢብኮ #አልዓይን

@tikvahethiopia
#ምርጫ2013

ኢሰመኮ ዛሬ በይፋዊ ፌስቡክ ገፁ ባወጣው መረጃ በምርጫው የሰብዓዊ መብት ሁኔታዎችን የሚከታተሉ ባለሙያዎችን እንዳሰማራ አሳውቋል።

ኢሰመኮ ባለሙያዎቹን ያሰማራው በተሻሻለው የኮሚሽኑ ማቋቋሚያ አዋጅ አንቀፅ 6 በተሰጠው ስልጣንና ሀላፊነት
መሰረት ነው።

በዚህም ምርጫ በሚካሄድባቸው በሁሉም ክልሎች የክትትል ቡድኖችን ማሰማራቱን አስታውቋል፡፡

ቡድኖቹ በሚሰማሩባቸው ስፍራዎች ሁሉ በምርጫው እለት እና ከምርጫው በኋላ ባሉት ቀናት በምርጫ ጣቢያዎች በመገኘት ምልከታ ያደርጋሉ ያለው ኮሚሽኑ መራጮችን፣ የምርጫ አስተባባሪዎችን፣ የፀጥታ አካላትን፣ የፖለቲካ ፓርቲዎችን፣ እጩዎችን፣ ታዛቢዎችን እና ሌሎች ባለድርሻ አካላትን በማነጋገር መረጃዎችን እንደሚሰባስቡ ገልጿል፡፡

በፖሊስ ጣቢያዎች እና በሕክምና ተቋማት በመገኘት አስፈላጊውን ክትትል እንደሚያደርጉም ነው ያስታወቀው።

የኮሚሽኑን መለያ ካርድ (ባጅ) በመያዝ ለሚሰማሩት የክትትል ቡድኑ አባላት አስፈላጊው ትብብር እንዲደረግላቸው ዋና ኮሚሽነር ዶክተር ዳንኤል በቀለ ጥሪ አቅርበዋል፡፡

#አልዓይን

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Tigray የኢፌዴሪ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን በወቅታዊ የትግራይ ሁኔታ ላይ ለዴፕሎማቲክ ማህበረሰብ ማብራሪያ እየሰጡ ነው። ምን አሉ ? - የኢትዮጵያ መንግሥት በትግራይ የተከሰተውን ቀውስ ለመፍታት እና ዘላቂ ሰላም ለማስፈን #በሕጋዊ መንገድ ከተመዘገቡ ፖለቲካ ፓርቲዎች፣ ከሲቪል ማኅብረሰቡ እና ከአገር ሽማግሌዎች ጋር ለመወያየት እቅድ አለው ብለዋል። -…
#Tigray

"... የህወሓት ሃይል በኮረም በኩል ተኩስ ከፍቶ ነበር" - አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን

የፌደራል መንግስት የተናጠል የተኩስ አቁም ቢያደርግም ህወሓት ግን አሁንም ግጭት እያስነሳ መሆኑን አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን ገለፁ::

ይህን የገለፁት መቀመጫቸውን በአዲስ አበባ ላደረጉ የዲፕሎማሲ ማህበረሰብ አባላት ማብራሪያ ከተሰጠ በኋላ ከጋዜጠኞች ጋር ባደረጉት ቆይታ ነው::

ፌዴራል መንግስት ሰብዓዊንት ላይ የተመሰረተ የተናጠል ተኩስ አቁም ካወጀ በኃላ የህወሓት ኃይል በኮረም በኩል ተኩስ ከፍቶ እንደነበር አምባሳደር ሬድዋን ተናግረዋል፡፡

በሌላ በኩል መንግስት ያወጀው የተናጠል ተኩስ አቁሙ እርምጃን ዓለም አቀፍ ማህበረሰቡ እንዳደነቀው ገልፀዋል::

የባንክ፣ የመብራትና የስልክ አገልግሎቶችን ለማስጀመር ህወሓት እንቅፋት መሆኑን ገልፀዋል::

ባንኮች በሚመለከት ለትርፍ ስለሚሰሩ፤ ዋስትና ካልተገባላቸው ለመስራት እንደሚቸገሩ ያኑሰት አምባሳደር ሬድዋን፤ መንግስት ግን ባንኮችን አስገድዶ ባንኮችን አግልገሎት ጀምሩ ማለት እንደማይችል አንስተዋል።

ህወሓት የመብራትና የስልክ አገልግሎት መስመሮችን ቆርጦ እንደነበር የገለጹት አምባሳደር ሬድዋን እነዚህን መሰረተ ልማቶች መንግስት ጠግኖ ወደ አገልግሎት መልሶ እንደነበር ገልጸዋል። 

ህወሃት የመብራትና የስልክ አገልግሎት መስመሮችን ለመጠገን ወደ ትግራይ የሄዱ መሃንድሶችን መግደሉንም አስታውሰዋል።

በመሆኑም ህወሓት ይህንን የግድያ ወንጀል እየቀጠለ ባለበት በዚህ ሁኔታ የመብራትና የስልክ አገልግሎት ወደ ስራ ለማስገባት የፌዴራል መንግስት እንደሚቸገር አስታውቀዋል::

#አልዓይን

@tikvahethiopia
#Ethiopia

የUSAID አስተዳዳሪ የሆኑት ሳማንታ ፓወር ወደ ኢትዮጵያ የመጣሁት ሰብዓዊነት አሳስቦኝ ነው ሲሉ መናገራቸውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር ዲና ሙፍቲ ተናገሩ፡፡

አምባሳደሩ ዛሬ በሰጡት ሳምንታዊ መግለጫ ስለሳማንታ ፓወር ጉብኝት ማብራሪያ ሰጥተዋል።

አምባሳደር ዲና ሳማንታ “ሰብዓዊነት አሳስቦኝ ነው ወደ ኢትዮጵያ የመጣሁት" ሲሉ መናገራቸውን እንደሚወራው "መንግስት ለመቀየር እንዳልመጡ ፤ ይልቁንም ሰብዓዊነት እንደሚያሳስባቸው” መናገራቸውን ገልፀዋል።

ሲመጡ ጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይን እና ምክትላቸውን አቶ ደመቀን ለማግኘት አቅደው የነበሩት ሰማንታ ፓወር 2ቱንም ሳያገኟቸው ቀርተዋል። በዚህ ጉዳይ አስተያየታቸውን የሰጡት አምባሳደር ዲና ፥ “በነበረባቸው የስራ ጫና (ዶ/ር ዐቢይና አቶ ደመቀ)” ምክንያት ፍላጎታቸው ተሳክቶ ሳያገኟቸው ቀርተዋል ብለዋል።

ምንም እንኳን እነሱን ማግኘት ባይችሉም ከእርሳቸው ተቋም ተግባር ጋር በሚገናኙ ስራዎች ዙሪያ የተሰማሩ የመንግስት ባለስልጣናትን እንደሚያገኙ ተነግሯቸው አግኝተዋል ሲሉ አክለዋል።

ሳማንታ ፓወር ካገኟቸው ባለስልጣናት መካከል ወ/ሮ ሙፈሪያት ካሚል የሚገኙበት ሲሆን "ህወሃት" የተጀመረውን ሃገራዊ ለውጥ ረግጦ መውጣቱን ለሳማንታ መናገራቸውን ገልፀዋል።

ፓወር፥ “አሜሪካ ከኢትዮጵያ ጋር ያላትን ግንኙነት በጣም ዋጋ ትሰጣለች” ያሉ ሲሆን ጉዳዩ እዚህ ደረጃ መድረስ አልነበረበትም ስለማለታቸውም ተናግረዋል፡፡

በሌላ በኩል ድርድርና ውይይትን በተመለከተ የተጠየቁት አምባሳደር ዲና ምናልባት በመጪው መስከረም ወር መጨረሻ በሚመሰረተው አዲስ መንግስት ሁሉን አቀፍ (All inclusive) ውይይት እንደሚደረግና ምናልባት የህወሓት አባል የነበሩ ሰዎች ወደዚህ ውይይት ሊመጡ እንደሚችሉ ተናግረዋል።

#አልዓይን

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#SUDAN : " ጠ/ሚ አብደላ ሀምዶክ እኔ ቤት ነው ያለው " - ሌ/ጀነራል አብዱል ፈታህ አልቡርሀን የሱዳን ጦር አዛዥ ሌተናንት ጀነራል አብዱል ፈታህ አልቡርሀን ዛሬ መግለጫ ሰጥተዋል። ሌተናንት ጀነራል አብዱል ፈታህ አልቡርሀን በመግለጫቸው በሱዳን ጦር በቁጥጥር ስር የዋሉት ጠቅላይ ሚኒስትር በአብደላ ሀምዶክ ያሉበትን አስታውቀዋል። አልቡርሃን ፥ “ጠቅላይ ሚኒስትር አብደላ ሀምዶክ እኔ ቤት ነው…
#SUDAN : መፈንቅለ መንግስት የተካሄደባቸ እና ወዳልታወቀ ቦታ ተውስደዋል የተባሉት አብደላ ሃምዶክ ከነበሩበት ስፍራ ትላንት ምሽት ወደቤታቸው ገብተዋል።

ትላንት የሱዳን ጦር አዛዥ አብዱን ፈታህ አልቡርሃን " ጠ/ሚ አብደላ ሃምዶክ ለደህንነታቸው ሲባል እኔ ቤት ነው ያሉት" ብለው ነበር።

ሀምዶክ ትናንት ምሽት ከታሰሩበት ስፍራ ወደመኖሪያ ቤታቸው እንደተመለሱ የተዘገበ ሲሆን ወደቤታቸው ከተመለሱ በኃላ ከአሜሪካ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንቶኒ ብሊንከን ጋር በስልክ አውርተዋል፡፡

ብሊንከን በትዊተር ባሰራጩህ ፅሁፍ በሀምዶክ መፈታት መደሰታቸውን ገልጸው አሁንም በእስር ላይ ያሉ ሌሎች የሲቪል አስተዳደር አመራሮች እንዲፈቱ አሳስበዋል፡፡

#አልዓይን

@tikvahethiopi
#የምርመራ_ሪፖርት

ፍትህ ሚኒስቴር በአማራ ክልል በሰሜን እና ደቡብ ጎንደር ዞኖች እንዲሁም በአፋር ክልል በሚገኙ ወረዳዎች በንጹሃን ዜጎች ላይ የተፈጸመውን ወንጀል ምርመራንና የመጀመሪያ ደረጃ ግኝቶችን አስመልክቶ ዛሬ መግለጫ ሰጥቷል።

ምርመራው የተካሄደው በህወሃት ተይዘው በነበሩና በኃላም ነጻ በወጡ አካባቢዎች ነው።

በዚህ መሰረት ህወሓት በሰሜን ጎንደር ዞን ለጊዜው በዝርዝር ማስረጃ የተለዩ፦
- የ96 ሰዎች ሞት
- 53 የአካል ጉዳት
- 29 አስገድዶ መደፈር
- 11 ኢ-ሰብዓዊ አያያዝ
- 6 እገታ እንዲሁም የመንግስት፣ የግልና የሀይማኖት የተለያዩ ተቋማት ንብረቶች ላይ መጠነ ሰፊ ዘረፋና ውደመት ፈፅሟል ሲል ሚኒስቴሩ አሳውቋል።

በደቡብ ጎንደር ዞን ባሉ አምስት ወረዳዎች በድምሩ፦
- የ129 ሰዎች ሞት
- የ54 ሰዎች የአካል ጉዳት
- በንፋስ መውጫ ከተማ ብቻ የ73 ሴቶች የአስገድዶ መድፈር ወንጀል እንዲሁም በርካታ ግለሰቦች ንብረት ላይ ውድመት መድረሱ ተገልጿል።

በአፋር ክልል ነሃሴ 29/2013 ዓ.ም በጋሊኮማ ቀበሌ መጠለያ ጣቢያ ላይ በተፈጸመ ጥቃት፦
- የ240 ሰዎች ሞት
- 42 ሰዎች የአካል ጉዳት ደርሶባቸዋል።

በቀሪዎቹ ሶስት ወረዳዎች ደግሞ የ17 ሰዎች ሞት እና ለ17 ሰዎች የአካል ጉዳት እንዲሁም 7 ሴቶች የአስገድዶ መድፈር ወንጀሎች ተፈፅሟል።

በሁለቱም ክልሎች በሰላማዊ ዜጎች ንብረት ላይ በመንግስት እና በግል ተቋማት ላይ ዘረፋና ውድመት በስፋት መድረሱን ሚኒስቴሩ ገልጿል።

በአጠቃላይ ምርመራው በሂደት ላይ ያለ መሆኑን ሚኒስቴሩ ገልጿል።

እስከ አሁን በተደረሰበት ግን ሁለቱም ክልሎች በተፈጸሙት የወንጀል ድርጊቶች 482 ሞት፣ 165 የአካል ጉዳት እና 109 የአስገድዶ መድፈር ኢሰብዓዊ ድርጊቶች መፈጸማቸው በሪፖርቱ ተመላክቷል። #አልዓይን

@tikvahethiopia