TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
59.4K photos
1.51K videos
215 files
4.12K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
መከላከያ ሰራዊት‼️

‹‹መከላከያ እራሱን #ተከላከለ እንጅ ሰው #አልገደለም፡፡››

‹‹ስህተት ከነበረበት መከላከያ ሠራዊት እንደ ሀገር ይቅርታ ከመጠየቅ አልፎ ለተጎጅዎች ቤተሰቦችም ካሳ ይከፍላል፡፡›› የኢፌዴሪ ሀገር መከላከያ ሠራዊት ምክትል ኤታማዦር ሹምና የዘመቻ መምሪያ ኃላፊ ጀነራል ብርሃኑ ጁላ
.
.
ከሰሞኑ በምዕራብ ጎንደር ዞን ገንዳውኃና ኮኪት አካባቢ የተከሰተውን ችግር አስመልክቶ የኢፌዴሪ ሀገር መከላከያ ሠራዊት ምክትል ኤታማዦር ሹምና የዘመቻ መምሪያ ኃላፊ ጀኔራል ብርሃኑ ጁላ ዛሬ መግለጫ ሰጥተዋል፡፡

አካባቢው ላለፉት ዓመታት የፀጥታ ችግር የነበረበት መሆኑን ተከትሎ መከላከያ ሠራዊት ሁል ጊዜም በአካባቢው ቅኝት ያደርግ እንደነበር ነው የገለጹት፡፡

በምዕራብ ጎንደር ኮኪትና ገንዳውኃ አካባቢ ለተከሰተው ችግር ምክንያቶችን ሲያስቀምጡም ‹‹ሠራዊቱ የእጀባ ግዳጅ ተሰጥቶት ሲሄድ ገንዳውኃ ላይ ‹ሕዝቡ ይፈተሸ› ባለው መሠረት ፍተሻው ተከናውኗል፡፡ ይህንን ፍተሻ ካለፈ በኋላ ግን ሌላ ፍተሻ ሲካሄድ በታጠቁ ኃይሎች በሠራዊቱ ላይ በደረሰ የደፈጣ ጥቃት ሁለት አባላት መቁሰላቸውን ተከትሎ መከላከያ ሠራዊት ራሱን ለመከላከል እርምጃ ወስዷል እንጅ ሰው አልገደለም›› ብለዋል፡፡

‹‹አድፍጦ የታጠቀ ኃይል ወደ ሠራዊቱ መተኮሱን ተከትሎ ሠራዊቲ ራሱን ለመካለከል የወሰደው እርምጃ ስህተት ከነበረበት መከላከያ ሠራዊት እንደ ሀገር ይቅርታ ከመጠየቅ አልፎ ለተጎጅዎች ቤተሰቦችም ካሳ ይከፍላል›› ነው ያሉት ጀኔራል ብርሃኑ ጁላ በመግለጫቸው፡፡

ውይይት መቅደም እንደነበረበት የተነሳላቸው ምክትል ኤታማዦር ሹሙ ‹‹ይህ እንደሚፈጠር አልጠበቅንም ነበር፤ ነገር ግን ከተከሰተም በኋላ ውይይት ለማድረግ ተኩሱ መቆም ነበረበት›› ብለዋል፡፡

ምንጭ፦ አብመድ
@tsegabwolde @tikvahethiopia