TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.5K photos
1.43K videos
206 files
3.96K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
መከላከያ መማክርት🔝

#የመከላከያ_መማክርት (ካውንስል) ዛሬ በጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት ውይይት አድርጓል፡፡

የአገር መከላከያ ሰራዊት በሕጋዊ መዕቀፎች፣ በአደረጃጀት፣ በመፈጸም ብቃትና በትጥቅ ከፍተኛ የለውጥ ጎደና ላይ እንደሚገኝ የተገለጸ ሲሆን፣ ይህንን ለውጥ በሁሉም ደረጃ ተፈጻሚ ከማድረግና ወደታች ከማውረድ አንፃር የተገኙ ተጨባጭ ውጤቶች፣ የታዩ ክፍተቶችና ቀጣይ አቅጣጫዎች ላይ ውይይት ተደርጓል፡፡

ውይይቱን የመሩት የጦር ኃይሎች ጠቅላይ አዛዥ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ ሲሆኑ፣ መከላከያ እስከሁን ያደረጋቸው የተቋማዊ ሪፎርም ስራዎች ምን ያህል ርቀት እንደተጓዙ በመገምገም ቀጣይ አቅጣጫዎችን አስቀምጠዋል፡፡

መከላከያ የአገሪቱ አቅም በፈቀደ መጠን ቴክኖሎጂን የሚታጠቅ፣ በራሱ አቅም መጠገን፣ ማሳደግ ብሎም መፍጠር የሚችል እንዲሆን በርካታ የአቅም ግንባታ ስራዎች እየተሰሩ መሆናቸው በውይይቱ ላይ ተገልጿል፡፡

መከላከያ ከቴክኖሎጂ ጋር ጥብቅ ቁርኝት ያለውና እንደ ሌሎች አገራት ከራሱም አልፎ ለሌሎች የቴክኖሎጂ ዘርፎች ምንጭ መሆን የሚችል እንዲሆን ለማድረግ እየተሰሩ ያሉ ስራዎችም ተገምግመዋል፡፡

መከላከያው በሁሉም ደረጃዎች የሁሉም ብሔር ብሔረሰቦች ተዋጽኦ የጠበቀ ለማድረግ እየተከናወኑ ያሉ ተግባራትም ተገምግመዋል፡፡

የአገሪቱን ውስጣዊና ካባቢያዊ ሁኔታን ታሳቢ ያደረገ የሰራዊት አሰፋፈር እንዲኖር የተጀመረው እንቅስቃሴ ላይ ሰፊ ውይይት የተደረገ ሲሆን፣ በዚህም የመከላከያ ሰራዊት አሰፋፈር ወቅታዊ፣ ተጨባጭና ታሳቢ ስጋትን መሰረት ባደረገ መልኩ የሚወናወን በመሆኑ ሕብረተሰቡም በዚህ መልኩ እንዲረዳው ማድረግ አስፈላጊ መሆኑም በውይይቱ ላይ ተነስቷል፡፡

ምንጭ:- የጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#Update የኃይማኖት መሪዎችና የአገር ሽማግሌዎች ከትግራይ ክልል ምክትል ርእሰ-መስተዳድር ዶ/ር ደብረፅዮን ገብረሚካኤል ጋር በወቅታዊ አገራዊ ጉዳዮች ላይ በመቀሌ ከተማ ተወያይተዋል፡፡የሰላም ሀሳብ በመያዝ ወደ ትግራይ ክልል ያቀኑት የኃይማኖት አባቶችና የአገር ሽማግሌዎች ዶ/ር ደብረፅዮን ገብረሚካኤልን በፅፈት ቤታቸው ተገኝተው አነጋግረዋል፡፡ የኃይማኖት መሪዎቹ በኢትዮጵያ ከእንግዲህ ማንም ሲፈናቀል፣ ህፃናት ሲጎዱና መንገዶች ሲዘጉ ማየት እንደማይፈልጉ ለክልሉ ርእሰ-መስተዳደር ገልጸውላቸዋል፡፡ ዶ/ር ደብረፅዮን በበኩላቸው የትግራይ ህዝብና መንግስት ዋነኛ አጀንዳ ከድህነትና ኋላቀርነት በመውጣት የህብረተሰቡን ኑሮ ማሻሻል እንደሆነ ገልፀዋል፡፡ አሁን በአገሪቱ የተፈጠሩ ችግሮችን ለመቅረፍ የክልል መንግስታት እና የፖለቲካ መሪዎች በጋራ ለሰላም መስራት እንዳለባቸውም የሀይማኖት አባቶቹ ማሳሰባቸውን EBC ዘግቧል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
የእሳት አደጋ~አዲስ አበባ‼️

በዛሬው ዕለት በመዲናዋ ሶስት ቦታዎች #የእሳት_አደጋ መከሰቱን የእሳትና ድንገተኛ አደጋዎች መቆጣጠርና መከላከል ባለስልጣን ገለጸ፡፡

የአዲስ አበባ እሳትና ድንገተኛ አደጋዎች መቆጣጠርና መከላከል ባለስልጣን የኮሙዩኒኬሽን ባለሙያ አቶ ስለሺ ተስፋዬ ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት እንዳስታወቁት፥ ዛሬ ጠዋት 1 ሰዓት ከ30 በአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ወረዳ 5 በተለምዶ ቁስቋም ተብሎ በሚጠራው ስፍራ በሚገኝ ንብረትነቱ የንግድ ባንክ በሆነ የቤት እቃዎች መጋዘን ላይ በደረሰ የእሳት ቃጠሎ 300 ሺህ ብር የሚገመት ንብረት ወድሟል።

ባለስልጣኑም ሁለት ከባድ ተሽከርካሪ፣ 5 ሺህ ሊትር ውሃና 7 የእሳትና ድንገተኛ አደጋ ሰራተኞችን በማሰማራት 3 ሚሊየን ብር የሚገመት ንብረት ማዳን መቻሉን ገልጸዋል፡፡

በተመሳሳይ መልኩ በአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ በሚገኘው የባለስልጣኑ መስሪያ ቤት ቅርንጫፍ ጀርባ በሚገኝ አንድ የመኪና ጋራዥ ላይ በደረሰ የእሳት ቃጠሎ አንድ ተሽከርካሪና 10 ሺህ ብር የሚገመት ንብረት ሲወድም፥ ግምቱ ከ300 ሺህ ብር በላይ የሆነ ንብረት ማዳን ተችሏል።

ከዚህም ሌላ ዛሬ ከሰዓት በአንዋር መስኪድ የሴቶች መግቢያ በር ላይ በሚገኝ አንድ የንግድ ሱቅ ላይ በተነሳ የእሳት አደጋ 30 ሺህ ብር የሚገመት ንብረት ወድሟል።
ከአደጋው 1 ነጥብ 5 ሚሊየን ብር የሚገመት ንብረት ማዳን መቻሉን የባለስልጣን መስሪያ ቤቱ መረጃ ያመለክታል፡፡

ምንጭ፦ fbc
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ጎንደር‼️

በጎንደር በተከሰተው ግጭት ዙሪያ የሚወጡ #የተምታቱ መረጃዎች ለውጡን የሚጎዱ መሆናቸውን የኢፌዴሪ መከላከያ ሚኒስቴር አስታወቀ።

በወቅታዊ ጉዳይ ላይ መግለጫ የሰጡት የኢፌዴሪ ጦር ሃይሎች ምክትል ኤታ ማጆር ሹምና የዘመቻ መምሪያ ሀላፊ ጀነራል #ብርሃኑ_ጁላ እንደተናገሩት በጎንደር በተከሰተው ግጭት ዙሪያ የተምታቱ መግለጫዎች እየወጡ ነው፡፡

ስለ ክስተቱ ተገቢው የማጣራት ስራ ሊሰራ ይገባል፡፡ ተገቢው #የማጣራት ስራ ሳይሰራ መከላከያው ህዝብን ገድሏል ተብሎ እየተሰጡ ያሉ መግለጫዎችና በማህበራዊ ሚዲያዎች እየተሰራጩ ያሉ መረጃዎች ተገቢነት የጎደላቸው ናቸው፤ የተጀመረውን ለውጥም የሚጎዳ ነው ብለዋል፡፡

ምንጭ፦ EPA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
አብን🤝አዴፓ‼️

የአማራ ዲሞክራሲያዊ ፓርቲ (አዴፓ) እና የአማራ ብሄራዊ ንቅናቄ (አብን) #በጋራ_ለመሥራት ተሥማሙ፡፡

ሁለቱ ፓርቲዎች አሁን ያለውን የፖለቲካ አሠላለፍ ታሳቢ ያደረገ የሁለትዮሽ ውይይት በሥራ አሥፈጻሚዎቻቸው በኩል በአቶ ደመቀ መኮንን እና በዶ/ር ደሳለኝ ሠብሳቢነት ጥር 1 ቀን 2011 ዓ.ም በአዲስ አበባ ተገናኝተው መክረዋል።

ከአዴፓ 11 የሥራ አሥፈጻሚ አባላት የተገኙ ሲሆን በአንብ በኩል 9 የሥራ አሥፈጻሚ አባላት በውይይቱ ላይ መገኘት ችለዋል።

በዚህም መሠረት ሁለቱ ፓርቲዎቹ፦
1. በጸጥታ ጉዳይ
2. በሠላምና ደህንነት
3. በልማትና የአማራ ህዝብ የጋራ ጉዳዮች ላይ አብሮ ለመሥራት በሁለቱም ፓርቲዎች በኩል በተመረጡ ሥራ አሥፈጻሚዎች በኩል የጋራ ኮሚቴ አቋቁመዋል።

ከሁለቱ ፓርቲዎች ሥራ አሥፈጻሚዎች የተመረጡት የጥምር ኮሚቴው አባላት ወደ ፊት ዝርዝር ጉዳዮችን የሚያሳውቁ መሆኑን አዴፓ አስታውቋል፡፡

ምንጭ፦ አብመድ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
መከላከያ ሰራዊት‼️

‹‹መከላከያ እራሱን #ተከላከለ እንጅ ሰው #አልገደለም፡፡››

‹‹ስህተት ከነበረበት መከላከያ ሠራዊት እንደ ሀገር ይቅርታ ከመጠየቅ አልፎ ለተጎጅዎች ቤተሰቦችም ካሳ ይከፍላል፡፡›› የኢፌዴሪ ሀገር መከላከያ ሠራዊት ምክትል ኤታማዦር ሹምና የዘመቻ መምሪያ ኃላፊ ጀነራል ብርሃኑ ጁላ
.
.
ከሰሞኑ በምዕራብ ጎንደር ዞን ገንዳውኃና ኮኪት አካባቢ የተከሰተውን ችግር አስመልክቶ የኢፌዴሪ ሀገር መከላከያ ሠራዊት ምክትል ኤታማዦር ሹምና የዘመቻ መምሪያ ኃላፊ ጀኔራል ብርሃኑ ጁላ ዛሬ መግለጫ ሰጥተዋል፡፡

አካባቢው ላለፉት ዓመታት የፀጥታ ችግር የነበረበት መሆኑን ተከትሎ መከላከያ ሠራዊት ሁል ጊዜም በአካባቢው ቅኝት ያደርግ እንደነበር ነው የገለጹት፡፡

በምዕራብ ጎንደር ኮኪትና ገንዳውኃ አካባቢ ለተከሰተው ችግር ምክንያቶችን ሲያስቀምጡም ‹‹ሠራዊቱ የእጀባ ግዳጅ ተሰጥቶት ሲሄድ ገንዳውኃ ላይ ‹ሕዝቡ ይፈተሸ› ባለው መሠረት ፍተሻው ተከናውኗል፡፡ ይህንን ፍተሻ ካለፈ በኋላ ግን ሌላ ፍተሻ ሲካሄድ በታጠቁ ኃይሎች በሠራዊቱ ላይ በደረሰ የደፈጣ ጥቃት ሁለት አባላት መቁሰላቸውን ተከትሎ መከላከያ ሠራዊት ራሱን ለመከላከል እርምጃ ወስዷል እንጅ ሰው አልገደለም›› ብለዋል፡፡

‹‹አድፍጦ የታጠቀ ኃይል ወደ ሠራዊቱ መተኮሱን ተከትሎ ሠራዊቲ ራሱን ለመካለከል የወሰደው እርምጃ ስህተት ከነበረበት መከላከያ ሠራዊት እንደ ሀገር ይቅርታ ከመጠየቅ አልፎ ለተጎጅዎች ቤተሰቦችም ካሳ ይከፍላል›› ነው ያሉት ጀኔራል ብርሃኑ ጁላ በመግለጫቸው፡፡

ውይይት መቅደም እንደነበረበት የተነሳላቸው ምክትል ኤታማዦር ሹሙ ‹‹ይህ እንደሚፈጠር አልጠበቅንም ነበር፤ ነገር ግን ከተከሰተም በኋላ ውይይት ለማድረግ ተኩሱ መቆም ነበረበት›› ብለዋል፡፡

ምንጭ፦ አብመድ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
አቶ ኤርሚያስ ፍርድ ቤት ቀረቡ‼️

የአክሰስ ሪል ስቴት ባለቤትና መስራች አቶ #ኤርሚያስ_አመልጋ በኢምፔሪያል ሆቴል ግዢ ጋር በተያያዘ ተጠርጥረው ፍርድ ቤት ቀረቡ።

እንደ ኤፍ ቢ ሲ ዘገባ አቶ ኤርሚያስ አመልጋ ከትናንት በስቲያ ነበር በቁጥጥር ስር የዋሉ ሲሆን፥ በዛሬው እለት በፌደራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 10ኛ የወንጀል ችሎት ቀርበዋል።

የኢፌዴሪ ብረታብረት እና ኢንጂነሪን ኮርፖሬሽን የኢምፔሪያል ሆቴልን ከአክሰስ ሪል እስቴት አክሲዮን ማህበር በሚገዛበት ወቅት ያለአግባብ በ72 ሚሊየን ብር እንዲገዛ መደረጉንና ድርድር በሚደረግበት ወቅትም ንብረቱን በሚመለከት ያለውን ችግር በወቅቱ ባለመፍታት እስካሁን ድረስ ወደ ኮርፖሬሽኑ የሆቴሉ የስም ዝውውር እንዳልተደረገ አቃቤ ህግ ቀደም ሲል በነበሩ ችሎቶች ሲጠቅስ ነበር።

via fbc
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ጄነራል ብርሃኑ ጁላ‼️

በምዕራብ ኦሮሚያ ከፍተኛ የፀጥታ ችግር መከሰቱን እና አሁን ግን #በቁጥጥር_ሥር እየዋለ መሆኑን የጦር ኃይሎች ምክትል ኤታማዦር ሹም አስታወቁ። ጀነራል #ብርሃኑ_ጁላ ዛሬ ከቀትር በኋላ አዲስ አበባ ላይ በሰጡት መግለጫ በተጠቀሰው አካባቢ ተስፋ ሰንቆ ከውጭ የገቡ አካላትን የተቀበለው ሕዝብ መልሶ ለከፍተኛ ጉዳት መዳረጉን አመልክተዋል። አሁን እየተወሰደ ባለው #ጠንካራ_እርምጃ አማካኝትም የተዘጉ መንገዶች እና አደጋ ላይ የወደቁ የመንግሥት የመዋቅር ሥፍራዎች መከፈታቸውንም ዘርዝረዋል።

ከተማዎቹን እየዞሩ ያተራምሱ ነበር ያሏቸው አባ ቶርቤ በሚል መጠሪያ የሚታወቁ ኃይሎችም በመንግስት ቁጥጥር ሥር መግባታቸውንም ምክትል ኤታማዦር ሹሙ ገልጸዋል።

«አሁን #ትጥቅ_ማስፈታት ጀምረናል፤ እነዚያ የተዘጉ ከተሞች ነጻ አውጥተናቸዋል። የተዘጉ መንገዶች ተከፍተዋል፤ ሰዎች እንደተዘረፉ አውቃለሁ፤ ሸሽተው አዲስ አበባ የገቡ እንዳሉ አውቃለሁ፤ አባ ቶርቤ የሚባል በየከተማው እየዞረ ነፍስ የሚገድል ፤ የሚያስፈራራ ይሄን ለቅመነዋል።» ብለዋል።

በምዕራብ ጎንደር ዞን ከሰሞኑ በተከሰተው ወቅታዊ ሁኔታ መከላከያ ሰው አልገደለም ያሉት ጀነራሉ ክስተቱ #እንዲጣራ መወሰኑን፤ ድርጊቱ ተፈፅሞም ከሆነ መከላከያ ይቅርታ እንደሚጠይቅ #ካሳም እንደሚከፍል አመልክተዋል። ባለሥልጣኑ በተለያዩ አካባቢዎች ስለደረሰዉ ጉዳት ምንም አይነት አሃዛዊ መረጃ መስጠት እንደማይፈልጉ ገልፀዋል።

ምንጭ፦ DW
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ጎንደር🔝በምዕራብ ጎንደር ሁለት ሹፌሮች በታጣቂዎች መገደላቸውን ተከትሎ ዛሬ በጎንደር ከተማ የተቃውሞ ሰልፍ ተካሂዷል። በተያያዘ መረጃ በምዕራብ ጎንደር ዛሬ በተፈጠረ ግጭት ቢያንስ 12 ሰዎች ተጎድተው ወደ ቋራ ሆስፒታል ተወስደዋል።

via~ELU
@tsegabwolde @tikvahethiopia
184 የፖሊስ አባላት ተሰናበቱ‼️

አዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ከተቋሙ ተልኮ በተፃረረ መልኩ በተለያዩ የወንጀል ድርጊት የተሳተፉ እና የስነ-ምግባር ችግር ያለባቸውን 184 የፖሊስ አባላትን ከሰራዊቱ #ማሰናበቱን ገለፀ።

ኮሚሽኑ ለfbc በላከው መግለጫ፥ በአገር አቀፍ ብሎም በከተማዋ ተግባራዊ የሆነውን ለውጥ ተከትሎ ከዚህ ቀደም በተቋሙ አገልግሎት አሰጣጥ ዙሪያ የሚስተዋሉ ችግሮችን በማስተካከል ለከተማችንን የሚመጥን ፖሊሳዊ አገልግሎት ለመስጠት ልዩ ልዩ የለውጥና የመልሶ ማደራጀት ወይም #የሪፎርም ስራዎችን እያከናወነ መሆኑን ገልጿል።

ኮሚሽኑ ከህብረተሰቡ የተሰጡ ጥቆማዎች እና ከሌሎች ባለድርሻ አካላት የደረሱትን መረጃዎች መነሻ በማድረግ መላው የፖሊስ አባላትን ያሳተፈ ግምገማ ከማእከል እስከ ፖሊስ ጣቢያ ባለው መዋቅር የአጥርቶ ማጥራት ስራ በመስራት ከኮሚሽኑ ተልዕኮ ተፃራሪ በመሆን በልዩ ልዩ ከባድ ወንጀል ላይ የተሳተፉ እንዲሁም ከፖሊሳዊ ስነ-ምግባር ውጭ ሲንቀሳቀሱ የነበሩ 184 የፖሊስ አባላት ከሰራዊቱ ማሰናበቱን ነው ያስታወቀው።

በልዩ ልዩ የወንጀል ድርጊት ውስጥ ገብተው የተገኙ የፖሊስ አባለት በቁጥጥር ስር ውለው ምርመራ እየተጣራባቸው መሆኑንም ኮሚሽኑ ገልጿል።

የተጀመረውን ለውጥ ለማስቀጠልና ተቋሙ ህዝብና መንግስት የጣሉበትን ከፍተኛ ኃላፊነት በብቃት ለመወጣት ቀጣይነት ያለው የማጥራት ስራዎችን አጠናክሮ የሚቀጥል መሆኑን በመግለፅ፥ በቅርብ ጊዜ መላውን አባልና አመራር ያሳተፈ ስልጠናዊ ግምገማ ለማድረግ ዝግጅቱን ማጠናቀቁን አስታውቋል።

በመጨረሻም ለኮሚሽኑ ስራ መሳካት ህብረተሰቡና ሌሎች ባለድርሻ አካላት እያደረጉለት ላለው ቀና ትብብር የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ምስጋናውን አቅርቦ ነዋሪው በአገልገሎት አሰጣጥ ይሁን የስነ-ምግባር ችግር ያለባቸውን የፖሊስ አባለት ሲያጋጥሙት በየአካባቢው በሚገኙ ፖሊስ ጣቢያዎች፣ ፖሊስ መምሪያዎች እና ፖሊስ ኮሚሽን ድረስ በአካል በመቅረብ እንዲሁም በነፃ የስልክ መስመር 991 ወይም 01-11-11-01-11 ጥቆማ መስጠት እንደሚቻል ገልጿል።

ምንጭ፦ FBC
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#Update የኢትዮጵያ አየር መንገድ ባለአምስት ኮከብ ሆቴል በአዲስ አበባ #ሊያስመርቅ ነው፡፡ ቦሌ አካባቢ የተገነባው ሆቴል በፈረንጆቹ ጥር 28 ተመርቆ ወደ ስራ ይገባል፡፡

ምንጭ፦ አፍሪካ ኒውስ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#Update ሱዳን ውስጥ በፕሬዝደንቱ ላይ የተነሳው ተቃውሞ ዛሬም #ተጠናክሮ ዋና ከተማዋን ጨምሮ በተለያዩ ከተሞች ቀጥሏል። የሀገሪቱ ፖሊስም በኻርቱም እና ኦምዱርማን ከተሞች ከዕለተ ዓርቡ የጸሎት ሥርዓት በኋላ ወደ ጎዳና በወጡት ተቃዋሚዎች ላይ አስለቃሽ ጭስ መተኮሱን የፈረንሳይ የዜና ወኪል ዘግቧል። ተቃዋሚ ሰልፈኞቹ «ነፃነት፣ ሰላም፣ ፍትሕ» የሚሉ መፈክሮችን ያሰሙ እንደነበርም አመልክቷል። የሱዳን ባለሙያዎች ማሕበር ለፊታችን እሁድም ታላቅ ሰልፍ በኻርቱም ከተማ ለማካሄድ የጠራ ሲሆን ተመሳሳይ ተቃውሞች በተለያዩ የሀገሪቱ ከተሞች እና መንደሮች እንደሚቀጥልም አስታውቋል። ሱዳን ውስጥ ተቃውሞው የተቀሰቀሰው ከኑሮ ውድነት ጋር በተያያዘ ሲሆን፤ ፕሬዝደንት ኦማር አልበሽር እና ሌሎች ባለስልጣናት ለኤኮኖሚው ድቀት ዩናይትድ ስቴትስን ተጠያቂ ያደርጋሉ።

በሌላ በኩል...

ሱዳንን ባናወጠው የፀረ-መንግስት ተቃውሞ 22 ሰዎች መሞታቸውን አፍሪካ ኒው ስ ዘግቧል፡፡ 22 ግለሰቦች መገደላቸውን ኃላፊዎች ሲገልፁ መሰረቱን በኒውዮርክ ያደረገው የሰብአዊ መብት ተሟጋችና ታዛቢ ቡድን ህፃናትን አጠቃሎ 40 የሚጠጉ ህይወታቸው ማለፉን አስታውቋል፡፡

ምንጭ፦ DW እና አፍሪካኒውስ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#Update የኢትዮጵያ የታህሳስ ወር የዋጋ ግሽበት 10 ነጥብ 4 በመቶ ሆኖ ተመዝግቧል።
@tsegabwolde @tikvahethiopia
በዴ.ሪ. ኮንጎ የሰው ህይወት ጠፋ‼️

በዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ የምርጫ ውጤት ይፋ መሆንን ተከትሎ በተነሳ #ግጭት የሰው ህይወት አለፈ፡፡

በሃገሪቱ ደቡባዊ ምዕራብ በምትገኘው ኪክዊት ከተማ በተነሳ ግጭት ሁለት የፖሊስ ባልደቦችና ሁለት ንጹሃን ዜጎች #መገደላቸው ተነግሯል፡፡

ግጭቱ በሃገሪቱ የተካሄደው ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ ውጤት ይፋ መሆንን ተከትሎ መነሳቱን ፖሊስ አስታውቋል።

በግጭቱ ከሞቱት በተጨማሪ 12 ዜጎች መቁሰላቸውም ነው የተገለጸው፡፡
በምርጫው ፌሊክስ ሺሴኬዲ አሸናፊ መሆናቸውን የሀገሪቱ የምርጫ ኮሚሽን ይፋ አድርጓል።

ይሁን እንጅ የእርሳቸው ተፎካካሪ የሆኑትና በካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን ድጋፍ አላቸው የሚባሉት ማርቲን ፋዩሉ ውጤቱን እንደማይቀበሉት ገልጸዋል። ይህን ተከትሎም ግጭት ተቀስቅሷል ነው የተባለው።

የዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ ከሁለት አመት መዘግየት በኋላ በተጠናቀቀው 2018 የመጨረሻ ቀን መካሄዱ ይታወሳል።

የምርጫው ውጤት ፀድቆ ሰላማዊ የስልጣን ሽግግር የሚደረግ ከሆነ፥ ሃገሪቱ ነጻነቷን ከተጎናጸፈችበት የፈረንጆቹ 19 60 ወዲህ የመጀመሪያው ይሆናል።

ምንጭ፦ሲ ጂ ቲ ኤን
@tsegabwolde @tikvahethiopia