TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
59.4K photos
1.51K videos
215 files
4.12K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
ከ100 በላይ አመራሮች ከሃላፊነት ተነስተዋል‼️

በታራሚዎች ላይ የሚደርሰው የሰብዓዊ መብት ጥሰትን ለመከላከል እና በማረሚያ ቤቶች ውስጥ ያለውን ችግር ለማስቀረት ቀደም ሲል በየማረሚያ ቤቶች የነበሩ ከአንድ መቶ በላይ አመራሮችን ከሃላፊነት ማንሳቱን የፌደራል ማረሚያ ቤቶች አስተዳደር ተናገረ፡፡

አስተዳደሩ እንደተናገረው በፍትህ ተቋማት ላይ ከፍተኛ #የመብት_ጥሰቶች ሲፈፀሙ ቆይተዋል፡፡ ከነዚህም ተቋማት ውስጥ ማረሚያ ቤቶች እንደሚገኙበትና ይህንንም ለማስተካከል በፌደራል ማረሚያ ቤቶች አስተዳደር ስር የነበሩ ከአንድ መቶ በላይ የሚሆኑ አመራሮች ከሀላፊነት እንዲነሱ መደረጉን ተናግረዋል፡፡

የፌደራል ማረሚያ ቤቶች አስተዳደር ዋና ዳይሬክተሩ አቶ ጀማል አባሶ ዛሬ ጋዜጠኞችን ጠርተው ሲነገሩ እንደተሰማው በየማረሚያ ቤቶቹ ላይ ከዚህ ቀደም ሲፈፀም እንደነበረው የመብት ጥሰት እና የሰብዓዊ መብት ረገጣ እንዳይኖር ከፍተኛ ክትትል እየተደረገ ይገኛል፡፡ አሁን ላይም ሙሉ ለሙሉ ባይሆንም ከዚህ ቀደም የነበረው ችግር አለመኖሩን ባደረግነው ክትትል አረጋግጠናል ብለዋል። ሙሉ ለሙሉ ለማረጋገጥም የዳሰሳ ጥናት መደረጉንና ይህም ራሳቸውን ታራሚዎች፣ ጠቅላይ ዐቃቤ ህግ፣ ፍርድ ቤቶች እና ሌሎች ወገኖች የተሳተፉበት ስራ ተሰርቷል ብለዋል፡፡

ዋነኛ የለውጥ ስራ ለማድረግም በማረሚያ ቤቶች የሚገኙ ሀላፊዎችን በአዲስ እንዲተኩ መደረጉን ተናግረዋል፡፡

በማረሚያ ቤቶች ያለውን የታራሚዎች አያያዝ ይበልጥ ለማሻሻልም በፌደራል ማረሚያ ቤቶች አስተዳደር ስር የሚገኙ አራት ማረሚያ ቤቶች በአዲስ እየተገነቡ እንደሆነ ዋና ዳይሬክተሩ አቶ ጀማል አባሶ ተናግረዋል፡፡

በአዲስ አበባ የሚገነባው ማረሚያ ቤት ግንባታው 96 በመቶ ደርሷል የተባለ ሲሆን በዚህ አመት ስራ ይጀምራል ተብሏል፡፡

በዚህ አመት ከየማረሚያ ቤቶቹ ከ6 ሺ በላይ ታራሚዎች በይቅርታና በምህረት እንዲፈቱ ተደርጓል መባሉን ተሰምቷል።

ምንጭ፦ ሸገር 102.1
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ለሰው ልጆች ፍቅር
ለሰው ልጆች ሰላም
ለሰው ልጆች በዓለም ዙሪያ ሁሉ
ሰላም ይሁን ምድሩ ሁሉ።

ፈጣሪ እስከዘላለሙ አፋቅሮ ያኑረን።
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ከጥር 1 እስከ ጥር 21...

የምንሰራቸው ስራዎች፦

1. በየዕለቱ ሰላምን ፍቅርን እና አድነትን የሚመለከቱ በቻናላችን የሚተላለፉ መልዕክቶችን ሁላችንም በፌስቡክ ገፃችን ላይ መለጠፍ።

2. ስለሰላም፣ ፍቅር እና አንድነት የሚገልፁ መልዕክቶችን ለወዳጆቻችሁ መላክ።

3. #ጥላቻ እና #ዘረኝነትን የሚሰብኩ የፌስቡክ ጓደኞችን #ብሎክ ማድረግ።

4. የተለያዩ የሀሰተኛ መረጃዎች የሚሰራጩባቸውን የፌስቡክ ገፆች አለመከተል።

5. ስድብ፣ ሰዎችን ማንቋሸሽ፣ ብሄር ተኮር ጥላቻዎችን የምትሰሙባቸውን ሚዲያዎች ማግለል።

የቻናላችን አባላት በሚገኙበት ቦታ ሁሉ ከጥር 1 እስከ ጥር 21 የሰላም፣ የፍቅር እና አንድነት ሳምንታት ታውጇል!!

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ርዕሰ መስተዳድር አቶ #ገዱ_አንዳርጋቸው

‹‹ሁኔታው አሳዛኝ ብቻ ሳይሆን ምንም ዓይነት ምክንያት ይቅረብለት በዚህ ዓይነት የግጭት ወቅት ንጹኃንን መጠበቅና ጥንቃቄ ማድረግ ይገባ ነበር፡፡››

‹‹ኃላፊነት የጎደለው፣ ትክክለኛ ያልሆነ እርምጃ ተወስዷል፤ በደረሰው ጉዳት ኃላፊነት መውሰድ ያለበት አካል ኃላፊነት መውሰድ ይኖርበታል፡፡››

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#Update የኢትዮጵያ ወጣት ብሔራዊ ቡድን አራት ሀገራት ይካፈሉበታል ተብሎ በሚጠበቀውና በአስመራ አስተናጋጅነት በሚካሄደው “የሠላም እና የወዳጅነት ዋንጫ” ላይ እንደሚሳተፍ ፌዴሬሽኑ ማረጋገጫ ሰጠ። በየካቲት ወር በአስመራ አስተናጋጅነት በሚካሄደውና በኤርትራ፣ ኢትዮጵያ፣ ጅቡቲ እና ሶማሊያ ወጣት ቡድኖች መካከል በሚደረገው ‘የሠላም እና ወዳጅነት ዋንጫ’ ላይ የኢትዮጵያ ወጣት ብሔራዊ ቡድን እንደሚሳተፍ ፌዴሬሽኑ አሳውቋል። የአራቱን አባል ሀገራት ወዳጅነት እና የዞኑን የእግርኳስ ትስስር ለማጠናከር ታስቦ ለመጀመርያ ጊዜ በሚካሄደው በዚህ ውድድር ላይ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን እንደሚካፈል እና ከቀናት በኋላ ዝግጅት እንደሚጀምር ተነግሯል።

ምንጭ፡-ሶከር ኢትዮጵያ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ሰላም፣ ፍቅር እና አንድነት!

‹‹ዩኒቨርሲቲዎች የሰላም፣ ፍቅር እና አንድነት መጠናከሪያ እንጂ #የነውጥ እና #የጥላቻ መነሻ መሆን #አይገባቸውም፡፡›› የወሎ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች

‹‹ማኅበረሰቡ፣ የሃይማኖት አባቶች እና የሀገረ ሽማግሌዎች የተቋሙን #ሰላም ለማስጠበቅ ከዩኒቨርሲቲው ጋር በመቀናጀት እየተሠሩ ነው›› የደሴ ከተማ ነዋሪዎች

‹‹ዩኒቨርሲቲውን እየፈተኑ ያሉት በውስጥ የሚፈጠሩ ችግሮች ሳይሆኑ #የውጭ ተፅዕኖዎች ናቸው፡፡›› የወሎ ዩኒቨርሲቲ

https://telegra.ph/ውሎ-ዩኒቨርሲቲ-01-10
#Update አቃቤ ህግ በሜጀር ጄኔራል #ክንፈ_ዳኘው እና ሌሎች ተጠርጣሪዎች ላይ ክስ መሠረተ። በከባድ የሙስና ወንጀል የተጠረጠሩት የቀድሞው የብረታ ብረትና ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን (ሜቴክ) ዋና ዳይሬክተር ሜጄር ጄኔራል ክንፈ ዳኘው በመዝገብ ቁጥር 229396 ዛሬ በአቃቤ ህግ ክስ ተመስርቶባቸዋል። ከእርሳቸው በተጨማሪ በተመሳሳይ ወንጀል የተጠረጠሩት አቶ ረመዳን ሙሳ፣ ኮሎኔል ደሴ ዘለቀ፣ አቶ ቸርነት ዳና ላይ ክስ መመስረቱን አቃቤ ህግ ለከፍተኛው ፍርድ ቤት 10ኛ ወንጀል ችሎት አስታውቋል። በዚህም መሠረት ተጠርጣሪዎቹ በ10ኛ ወንጀል ችሎት የነበራቸው መዝገብ ተዘግቶ ጉዳያቸው በ15ኛ ወንጀል ችሎት እንዲታይ ተደርጓል።

ምንጭ፦ ኢ.ዜ.አ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#Update የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ #ደመቀ_መኮንን ከጥር 3 – 4 ቀን 2011 ዓ.ም በሴራሊኒዮን ጉብኝት ያደርጋሉ፡፡ ጉብኝቱ የሚካሄደው የሴራሊዮን ፕሬዝዳንት ጁልየስ ማዳቢዩ ባደረጉላቸው ግብዣ መሰረት ነው፡፡ የውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ፅ/ቤት እንዳስታወቀው የሴራሊዮን ኢትዮጵያን ወዳጅነት ሊያጠናክር የሚችል ምክክር የሚደርግ ሲሆን የመግባቢያ ስምምነት ይፈረማል ተብሎ ይጠበቃል፡፡

@tsegabwolde @tikvahethiopia
Audio
ጄነራል ብርሃኑ ጁላ‼️

የሃገሪቱ ጦር ኃይሎች ምክትል ኤታ ማዦር ሹም ጄነራል ብርሃኑ ጁላ ስለ ሕገ ወጥ የመሳሪያ ዝውውርና ስለ መከላከያ ዩኒፎርም ተጠይቀዋል። ምዕራብ ኦሮሚያ፣ ምዕራብ ጎንደርና ትግራይ መከላከያው የወሰደው እርምጃና ያሳየው ትዕግስት አድሎአዊ ነው ስለመባሉም ተጠይቀዋል።

“ኢትዮጵያ ውስጥ ያለውን ያለመረጋጋት አጋጣሚ በመጠቀም ራሳቸውን በገንዘብ ማበልፀግ የሚፈልጉ ሰዎች በጦር መሣሪያ ንግድ ላይ ተሠማርተው ተገኝተዋል” ሲሉ የሃገሪቱ ጦር ኃይሎች ምክትል ኤታ ማዦር ሹም ጄነራል ብርሃኑ ጁላ ለቪኦኤ ገልፀዋል። ይህ ሁኔታም በተለያየ ቦታ “ሕገወጥ የመሣሪያ ዝውውር እንዲኖር መንገድ ከፍቷል” ብለዋል።

ለሁለቱም ችግሮች መፍትኄ ለማግኘት መንግሥታቸው እየሠራ መሆኑን የጦር አዛዡ ተናግረዋል። ጄኔራል ብርሃኑ በሃገሪቱ የፀጥታ ሁኔታ ላይ በዚህ ሣምንት ፓርላማው ፊት ቀርበው የሰጡትን ማብራሪያ፤ በሌላ በኩል ደግሞ በምዕራብ ኦሮምያ፣ በትግራይና በአማራ ክልሎች ውስጥና በመካከላቸውም ያለውን የፀጥታ ሁኔታ አስመልክቶ መሥሪያ ቤታቸው ሰሞኑን ስለሚሠነዘሩበት ወቀሳዎች፤ እንዲሁም ካለመረጋጋቱ ጋር ተያይዞ ‘የአዲሱ ጠቅላይ ሚኒስትር አስተዳደር አገሪቱን መምራት አቅቶታል’ እየተባለ ስለሚወራው ጉዳይ ተጠይቀው ምላሽ ሰጥተዋል።

ምንጭ፦ VOA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
አ.ሳ.ቴ.ዩ‼️

በአዳማ ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ 3 ተማሪዎች ሞተው ከተገኙ በኃላ የተቋሙ ተማሪዎች ለደህንነታችን ስጋት ገብቶናል፤ ተማሪዎቹ በምን ምክንያት እንደሞቱ ይነገረን ካለበለዚያ ትምህርት መቀጠል ይከብደናል ሲሉ ገልፀዋል። በተማሪዎቹ ቅሬታም ረቡዕ ሊሰጥ የነበረው የMid Exam ሳይሰጥ ቀርቷል። በዛሬው ዕለት ደግሞ ግቢውን ለቀን እንሄዳለ ባሉ ተማሪዎች እና በዩኒቨርሲቲው መካከል አለመግባባት ተፈጥሮ ነበር። ዩኒቨር ሲቲው ረቡዕ የተቋረጠው ፈተና በመጭው ሰኞ እንዲቀጥል ሲል ማስታወቂያ አውጥቷል።

🔹ፖሊስ ምርመራ እያደረኩ ነው በቅርቡም የምርመራ ውጤቱን ይፋ አደርጋለሁ ሲል ከቀናት በፊት ገልጿል። የተማሪዎቹ ሞት ከሚጡበት አካባቢ ጋር የተያያዘ ስላለመሆኑ ፖሊስ ገልጿል፦ "ተማሪዎቹ ከመጡበት አካባቢ ጋር ተያይዞ ጥቃት እንደደረሰባቸው የሚያሳይ ምንም አይነት መረጃ አላገኝንም፤ ተማሪዎቹም ከተለያየ አካባቢ ነው የመጡት" የአዳማ ፖሊስ መምሪያ ሃላፊ ኮማንደር ደረጀ ሙልዕታ 
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#Update የኢህአዴግ ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ከሰኞ ጥር 6 ቀን 2011 ዓም ጀምሮ መደበኛ ስብሰባውን ያካሂዳል፡፡ ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴው በ11ኛው ድርጅታዊ ጉባዔ የተቀመጡ አቅጣጫዎች አፈጻጸም፤ በሀገራችን ወቅታዊ ሁኔታ እና የለዉጥ እንቅስቃሰ ሂደት፤ እንዲሁም የድርጅት እና የመንግስት የስራ አፈጻጸም ጉዳዮች ላይ ትኩረት በማድረግ በጥልቀት ተወያይቶ አቅጣጫዎችን ያስቀምጣል ተብሎ ይጠበቃል፡፡

ምንጭ:- EPRDF Official
@tsegabwolde @tikvqhethiopia
#Update የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ከፍተኛ አመራሮች እና ከ60 በላይ የኢፌዴሪ አምባሳደሮች በመጪው ሰኞ ከጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ ጋር ይወያያሉ፡፡ የሚኒስቴሩ ከፍተኛ አመራሮችና አምባሳደሮች የአገሪቱ ቀጣይ ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት በሚዳብርበት ሁኔታ ላይ ከጠቅላይ ሚኒስትሩ ጋር ይመክራሉ ተብሏል፡፡

ምንጭ፦ አሃዱ ራድዮ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ሹመት!

አቶ #ነቢያት_ጌታቸው የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ሆነው ተሾሙ። የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ የነበሩት አቶ መለስ አለም የኬንያ አምባሳደር ሆነው መሾማቸውን ተከትሎ አቶ ነቢያት ጌታቸው ቃል አቀባይ ሆነው የተሾሙት።

አቶ ነቢያት በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ለበርካታ አመታት ያገለገሉ ሲሆን በዲፕሎማሲ ልምድ አካብተዋል። በሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ የሰሜን አሜሪካ፣ ደቡብ አሜሪካና ካሪቢያን ጉዳዮች ዳይሬክተር ሆነውም አገልግለዋል። በካናዳ የኢትዮጵያ ኤምባሲ የፖለቲካና የአኢኮኖሚ ትብብር አማካሪ፤ በስዊድንና በኮሪያ የኢትዮጵያ ኤምባሲዎች የፖለቲካ ደስክ ዲፕሎማት ነበሩ።

አቶ ነቢያት ከእንግሊዙ ሊድስ ዩኒቨርስቲ በአለም አቀፍ ኮሚዪኒኬሽን ማስተርስ ዲግሪ ያገኙ ሲሆን፤ የመጀመሪያ ዲግሪያቸውን የሰሩት ደግሞ በአዲስ አበባ ዪኒቨርስቲ ነው።

ምንጭ፦ BBC
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#Update የኢትዮጵያ ብሔራዊ የምርጫ ቦርድ ያዘጋጀውን የተፎካካሪ ፖለቲካ ፓርቲዎች መካከል የሚደረገው ውይይት የሚመራበት ስርዓትና ደንብ ጥልቅ ውይይት ከተካሄደበት በኋላ በተሳታፊ የፖለቲካ ፓርቲዎች ፊርማ #ፀደቀ

ደንቡ የፖለቲካ ፓርቲዎች በውይይት ወቅት የሚመሩበት መርሆዎች፣ ውይይቱ የሚካሄድበት ስርዓት፣ ከውይይቱ ተሳታፊዎች የሚጠበቅ ኃላፊነት፣ የአወያዮች ኃላፊነትና ግዴታ፣ የመገናኛ ብዙኃን ሚና እና ሌሎች አንቀፆች ያካተተ ነው።

ምንጭ፦ የኢትዮጵያ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ሙጋቤ 4 ሚሊዮን ብር ተዘረፉ‼️

ከቀድሞው የዚምባብዌ ፕሬዝዳንት #ሮበርት_ሙጋቤ ላይ አራት ነጥብ ሁለት ሚሊየን ብር ሰርቀው ተሰውረዋል የተባሉ ሶስት #ተጠርጣሪዎች ፍርድ ቤት ቀረቡ።

ተጠርጣሪዎቹ የሰረቁትን ገንዘብ መኪና፣ቤትና እንስሳት ለመግዛት እንዳዋሉት የተገለጸ ሲሆን የቀድሞው ፕሬዝዳንት ዘመድ ደግሞ ከተጠርጣሪዎቹ መካከል አንዷ እንደሆነች አንድ የሃገሪቱ ጣቢያ ዘግቧል።

ዚምባ በተባለችው ገጠራማ የሃገሪቱ ክፍል የሚገኘው የቀድሞው ፕሬዝዳንት ቤት ቁልፍ በተጠርጣሪዋ እጅ በመሆኑ ዝርፊያውን ለመፈጸም ቀላል እንዳደረገላቸው ተገልጿል።

ሌሎቹ ተጠርጣሪዎች ደግሞ በቀድሞው ፕሬዝዳንት ቤት ውስጥ ከአንድ ወር በፊት በጽዳት ሰራተኝነት ተቀጥረው ይሰሩ ነበር።

ጆሃን ማፑሪሻ የተባለችው ተጠርጣሪ 20 ሺ ዶላር የሚያወጣ መኖሪያ ቤትና ተሽከርካሪ እንደገዛች የተገለፀ ሲሆን ሌላኛዋ ተጠርጣሪ ደግሞ አንድ ተሽከርካሪና ብዙ ቁጥር ያላቸው አሳማዎችና ከብቶች ገዝታለች ተብሏል።

የ94 ዓመቱ ሮበርት ሙጋቤ ባሳለፍነው ዓመት ነበር በሃገሪቱ ወታደራዊ ሃይሎች ከስልጣናች እንዲለቁ የተደረጉት። መጀመሪያ በጠቅላይ ሚኒስትርነት በመቀጠልም በፕሬዝዳንትነት ሃገሪቷን ለ37 ዓመታት መርተዋል።

ሃገሪቱ በከባድ ኢኮኖሚያዊ ችግር ውስጥ ሆና እንኳን ሮበርት ሙጋቤ እጅግ የተንደላቀቀ ህይወት ይመሩ እንደነበር ይነገራል።

የቀድሞው ፕሬዝዳንት ከስልጣናቸው ከወረዱ በኋላ የመራመድ ችግር አጋጥሟቸው የነበረ ሲሆነ በሲንጋፖር የህክምና ክትትል ሲያደርጉ ነበር ተብሏል።

ሙጋቤ ስርቆቱ ሲፈጸም በቤታቸው ይኑሩ አይኑሩ የተገለጸ ነገር የለም። ተጠርጣሪዎቹ ግን በዋስ እንደተለቀቁ 'ኤኤፍፒ' ዘግቧል።

ምንጭ፦ BBC
@tsegabwoldw @tikvahethiopia