TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.5K photos
1.43K videos
206 files
3.96K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
አላማጣ‼️

በትግራይ ክልል ደቡባዊ ዞን ከተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች የተውጣጡ ተሳታፊዎች የተገኙበት ውይይት በአላማጣ በመካሄድ ላይ ይገኛል፡፡

በስብሰባው የትግራይ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር ዶክተር #ደብረጽዮን_ገብረሚካኤል እና ሌሎች የክልሉ የስራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል፡፡

ውይይቱ በወቅታዊ ጉዮች ላይና በአካባቢው ባለው የልማት እንቅስቃሴ ላይ ትኩረት እንዳደረገም ተገልጿል።

በውይይቶቹ ለሚነሱ ጥያቄዎች እና አስተያየቶች ምላሽ ለመስጠት የዞኑ አስተዳዳሪ አቶ ረዳዒ ኃለፎምን ጨምሮ ሌሎች የክልሉና የዞኑ የስራ ኋላፊዎች በመድረኩ ተገኝተዋል፡፡

“ብዙ ከመናገር ብዙ መስራት” በሚል መሪ ቃል እየተካሄደ ባለው ውይይት ላይ ተሳታፊዎቹ የተለያዩ ጥያቄዎችን አንስተዋል፡፡

ከተነሱት ጥያቄዎች መካከል የመሰረተ ልማት ዝርጋታና መልካም አስተዳደርን ጨምሮ የተለያዩ ጥያቄዎች የተነሱ ሲሆን፥ ከግምገማ ባለፈ ወደ ተግባር መች ነው የሚገባው? የመሰረተ ልማት ጥያቄ እንጂ የማንነት ጥያቄ የለንም የሚሉ ጥያቄዎችንና አስተያየቶችን አንስተዋል፡፡

የአገልግሎት አሰጣጥን በሚመለከት ቀልጣፋ አለመሆኑን ተናግረዋል፤ ከዚህ በተጨማሪም በኤሌክትሪክ ዝርጋታ፣ በወጣቶች ተጠቃሚነት፣ የፍትህ አሰጣጥ ስርዓት እና በመሬት አስተዳደር ዙሪያ ያሉትን ችግሮች በስፋት አንስተዋል፡፡

ዛሬ በአላማጣ የተጀመረው ውይይት በዞኑ ለሦስት ተከታታይ ቀናት ይቆያል ተብሏል፡፡

ምንጭ፦ fbc
@tsegabwolde @tikvahethiopia
አክሱም🔝የትግራይ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር ዶክተር #ደብረጽዮን_ገብረሚካኤል በማዕከላዊ ዞን ከአራት ወረዳዎች የተወከሉ የህብረተሰብ ክፍሎች ጋር በአክሱም ከተማ ትላንት ውይይት አካሂደዋል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
መቀለ🔝ሰላምና ዴሞክራሲ የሰፈነባት #ኢትዮጵያን ለመገንባት በሚደረገው ጥረት የትግራይ ህዝብ ከሌሎች ብሔር፣ ብሔረሰቦችና ህዝቦች ጋር በመሆን ያልተቆጠበ ጥረት እንደሚያደርግ የክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳድር ዶክተር #ደብረጽዮን_ገብረሚካኤል ገልፀዋል። ዶ/ር ደብረፅዮን ይህ ያሉት “ህገ-መንግስቱና የህግ የበላይነት ይከበር” የሚል መልዕክት ዛሬ በመቀለ ከተማ በተደረገ ህዝባዊ ሰልፍ ላይ ነው።
@tsegabwolde @tikvahethiopia
‹‹ወጣቶች የመልካም ተግባር አርአያ መሆን እንጂ በስሜት በመነሳሳት #አንድነትን በሚሸረሽሩ ተግባራት ላይ መሰማራትየለባቸውም!››

የትግራይ ምክትል ርዕሰ መስተዳድር ዶ/ር #ደብረጽዮን_ገብረሚካኤል

@tsegabwolde @tikvahethiopia
"የትግራይ ህዝብ #ህጋዊ በሆነው የመከላከያ ሰራዊት እንቅስቃሴ #ሊረበሽ አይገባም"--ዶክተር #ደብረጽዮን_ገብረሚካኤል

.
.
የትግራይ ህዝብ ህጋዊ በሆነው የመከላከያ ሰራዊት ከቦታ ወደ ቦታ መንቀሳቀስ ሳይረበሽ #በልማቱ ላይ ሊያተኩር እንደሚገባ የክልሉ ምክትል ርዕሰ-መስተዳደር ዶክተር ደብረጽዮን ገብረሚካኤል ገለጹ።

ምክትል ርዕሰ-መስተዳደሩ ዛሬ በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ እንዳመለከቱት የመከላከያ ሰራዊት ከቦታ ወደ ቦታ መንቀሳቀስ ህጋዊና #ኃላፊነቱንም ለመወጣት የሚያስችል ነው።

በመሆኑም የክልሉ ህዝብ ይሄንን ተገንዝቦ ያለምንም መረበሽ የልማት ስራውን #በተረጋጋ መልኩ ማከናወን እንዳለበት አሳስበዋል።

ህዝቡ የሚያነሳው የህገ-መንግስት ይከበርልን ጥያቄ እራሱ ከማክበር የሚጀምር መሆኑንም ምክትል ርዕሰ-መስተዳደር በመግለጫቸው አመልክተዋል።

የክልሉን ሰላምና ጸጥታ የማስከበርን ጉዳይም ህዝቡ በፈጠረው አደረጃጀት አንድነቱን ማስቀጠል እንደሚኖርበትም ጠቁመዋል።

የኢትዮጵያና የኤርትራ መንግስታት ባደረጉት የጋራ ስምምነት የሁመራ ኦምሃጀር መንገድ መከፈትም ለሁለቱ ህዝቦች ግንኙነት ጠቃሚ እንደሆነ ዶክተር ደብረጽዮን ተናግረዋል።

መንገዱ የሁለቱን ሃገራት የህዝብ ለህዝብ ግንኙነት ከማሳደግ ባለፈው ቀጣይ ህጋዊ መስመር ለማስያዝም ትልቅ አስተዋጽኦ እንደሚኖረው አመልክተዋል።

ምንጭ፦ ኢዜአ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update የአማራ እና የትግራይ ክልሎች ርዕሰ መስተዳድሮች በዝግ እየመከሩ ነው። ርዕሰ መስተዳድር #ገዱ_አንዳርጋቸው እና ምክትል ርዕሰ መስተዳድር ዶክተር #ደብረጽዮን_ገብረሚካኤል አዲስ አበባ ሂልተን ሆቴል ላይ እየተወያዩ ነው፡፡ በሁለቱ ክልሎች ወቅታዊ ሁኔታና ሠላም ላይ ነው እየተወያዩ ያሉት፡፡ የሀይማኖት አባቶች እና የሀገር ሽማግሌዎችም አብረው እያወያዩዋቸው ይገኛሉ።

ምንጭ፦ አብመድ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
አማራ🕊ትግራይ!!

‹‹አዲስ አበባ ስለሰላም ተናግሬ ከዚያ ሌላ ብናገር ይጠይቀኛል፤ ሄጄ የምሠራውም ከዚህ እንደምናገረው ነው፡፡›› የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ #ገዱ_አንዳርጋቸው

‹‹ይህች መሬት ሄደች ለኛ አጀንዳ አይደለም፤ ሊያጋጨንም አይገባም፡፡ ሕዝቡም ግጭት አይፈልግም፤ የአማራ ሕዝብ ከግጭትም አትርፎናል እላለሁ፡፡›› የትግራይ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር ዶክተር #ደብረጽዮን_ገብረሚካኤል
.
.
የአማራና ትግራይ ክልል ርዕሰ መስተዳድሮች በአዲስ አበባ ሂልተን ሆቴል ከሃይማኖት አባቶችና የሀገር ሽማግሌዎች ጋር እየተወያዩ ነው፡፡ በመድረኩም ሁለቱ ርዕሰ መስተዳድሮች ንግግር አድርገዋል፡፡

የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ገዱ አንዳርጋቸው ‹‹ስለሰላም ተጨንቃችሁና አስባችሁ ባሕር ዳርና በሌሎችም ክልሎች ተዘዋውራችሁ አስተምራችሁናል፤ መክራችሁናል፡፡ ይህ ደግሞ ከሃይማኖት አባቶች፣ ሽማግሌዎችና እናቶች የሚጠበቅ ነው፡፡ የሰላም አጀንዳ ይዛችሁ በዚህ ወቅት በመንቀሳቀሳችሁና እንድንገናኝ ጥረት ስላደረጋችሁ በአማራ ክልል ሕዝብ ስም አመሠግናለሁ›› ብለዋል፡፡

‹‹ኢትዮጵያ ሰላም እንድንትሆን የምንመኛው ስለሆነ አካል ብለን ሳይሆን ለሁሉም መሠረት ስለሆነ ነው፡፡ ትንሽ ጊዜ እንኳ ግጭቶች ሲኖሩ ምን ያህል ጉዳት እንደሚደርስ እያየነው ነው፡፡ የአማራ ሕዝብ ከወንድሞቹና ከጎረቤት ክልሎች፣ ከትግራይ ሕዝብ ጋር ሰላም መሆን ይፈልጋል፤ ለዚህ የሰላም አጀንዳችሁም አመሠግናለሁ፡፡ የምመራው ሕዝብም ሰላም ይፈልጋል፤ ለመሥራት፣ ለመኖር፣ ለመሻሻል… የሚፈልግ ነው፡፡ ይህንንም ስታወያዩት ነግሯችኋል፡፡ እኔም ዝግጁ ነኝ፡፡ ሰላምን የሚጠላው ሰይጣናዊ አስተሳሰብ የተጠናወተው ነው›› ነው ያሉት አቶ ገዱ፡፡

‹‹የአማራና ትግራይ ሕዝቦች ለሺህ ዘመናት የጋራ ሃይማኖት፣ ባሕልና እሴት ያላቸው አንዱ በአንዱ የሚሰጋ ሳይሆን የሚኮራ ሕዝቦች ናቸው፤ ይህ ግን ከጊዜ ጊዜ እየተሸረሸረ መጥቷል፡፡ ሕዝቡ ሰላማዊ ፍላጎቱ በሰላም እንዲፈታ እንጅ እንዲጋጭ በፍጹም አይፈልግም፡፡ ያሉ ጥያቄዎች በውይይት በሰላም የሚፈቱበትን ሁኔታ ነው የሚፈልገው›› ሲሉም ተናረዋል፡፡

የአማራ ክልል ሕዝብ የተጀመረው ለውጥ እንዳይቀለበስ የሚሰጋና ከፍተኛ ጉጉት ያለው መሆኑንም ነው የተናሩት፡፡ ‹‹እኛም የዚህ ሕዝብ መሪዎች ነን፡፡ እኔ የምመራው ሕዝብ ችግሮቹን በሰላማዊ መንገድ ከመፍታት ውጭ ብሔድ ይጠይቀኛል፡፡ ከክልሎች ጋር በሰላም መኖር ይፈልጋል፡፡ አዲስ አበባ ስለሰላም ተናግሬ ከዚያ ሌላ ብናገር ይጠይቀኛል፤ ሄጄ የምሠራውም ከዚህ እንደምናገረው ነው፡፡ አትጠራጠሩ የአማራ ሕዝብ ከትግራይ ሕዝብ ጋር ግጭት ጀማሪ አይሆንም፡፡ ከወንድሞቻችን የትግራይ አመራሮችና የትግራይ ሕዝብ ጋር በውይይት መፍታት እንችላለን፡፡ ቃሌ ፊርማዬ ነው ለሰላም እሠራለሁ›› ብለዋል አቶ ገዱ አንዳርቸው፡፡

የትግራይ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር ዶክተር ደብረ ጽዮን ገብረሚካኤም የሀገር ሽማግሌዎችንና የሃይማኖት አባቶችን አመስግነዋል፡፡ ‹‹በሕዝብ ብትመረጡም ባትመረጡም የሃይማኖት አባቶችና የሀገር ሽማግሌዎች ስለሆናችሁ አክብሬያችሁ ተገኝቻለሁ፡፡ እኛ የፖለቲካ መሪዎች መሥራት የሚገባንን ስላልሠራንና ስለተጨነቃችሁ አመሠግናለሁ፡፡ በታሪክ ያላየናቸውን ድርጊቶች እያዬን ስለመጣን አሳስቧችሁ ስለመጣችሁ አመሠግናለሁ›› ብለዋል፡፡

‹‹ግንኙነታችን ከወንድምነትም በላይ ነው፤ የፖለቲካ ጓዶች ነን፡፡ የሀገራችን እሴቶች ብቻ ሳይሆን የድርጅታችንም እሴት መሸርሸር ስላለ ነው እናንተንም ወደዚህ ጉዳይ የጋበዝናችሁ፡፡ ከዚህ ችግር ቶሎ መውጣት አለብን፤ መጨነቅ ብቻ ሳይሆን ብዙ ጉዳት የደረሰባቸው ወገኖች አሉ›› ነው ያሉት ዶክተር ደብረጽዮን፡፡

‹‹ተግባራችን ታሪካችንን የሚያስጠብቅ አይደለም፡፡ ወደኋላ ተመልሰን ታሪካችን ስናይ ከሀገራቸው የተሰደዱና በሃይማኖት የማይመስሉንን ሰዎች በመሆናቸው ተቀብለናል›› ነው ያሉት ዶክተር ደብረጽዮን፡፡

‹‹ፍትሕ ላጡ የሚረዳና ልዩነትን የማይቀበልና እንደ ሰው አብሮ መኖርን የሚያውቅ ታሪክ ያለን ነን፤ አሁን እየታዬ ያለው ድርጊት መጤ ነው፡፡ ባሕላችንና ታሪካችን አሁን ከሚታዬው የተለዬ ነው፡፡ የምንገኘው ከውርደትም ውርደት ውስጥ ነው፡፡ የድሮ የወላጆቻችንን መከባበር በመያዝ ብቻ ብዙ ርቀት መጓዝ እንችላለን፡፡ ለሌላው ዓለም የሚተርፍ ታሪክ ነው ያለን፤ እንዲህ ያለ ታሪክ እያለን ግን እንዲህ ወዳለው ሁኔታ እንዴት ገባን?›› ሲሉም ጥያቄ አዘል ሐሳባቸውን ዶክተር ደብረጽዮን ገልጸዋል፡፡

የድንበርም ሆነ የሰላም ጉዳይ በድርድር መሆን ያለበት ነው ያሉት ምክትል ርዕሰ መስተዳድሩ ‹‹መገዳደል ኋላ ቀርነት ነው፤ የአራዊት ሥራና ኃጢአትም ነው፡፡ ግን የአመራሩ አካል ስለሆንን የችግሩም አካል ነን፡፡ የተበላሸ ፖለቲካ ስላለ ወደኋላ ትተን ተደጋግፈን መሥራት እንዳለብን አምናለሁ›› ብለዋል፡፡

‹‹የተበላሸውየ እገሌ የእገሌ ነው ስለማይባል ፖለቲካችን ውለን አድረን ማስተካከል አለብን፤ የሰላም ጉዳይ ግን ለነገ አይባልም፡፡ የፖለቲካ ልዩነት አስቀድመን ሰላማችንን ማጣት የለብንም፡፡ በአማራ ላይ የምናነሳው የተለዬ ጥያቄ የለንም፤ ጥቂት ሰዎች ግን የሚያበጣብጡን አሉ፡፡ ይህች መሬት ሄደች ለኛ አጀንዳ አይደለም፤ ሊያጋጨንም አይገባም፡፡ ሕዝቡም ግጭት አይፈልግም፤ የአማራ ሕዝብ ከግጭትም አትርፎናል እላለሁ፡፡ ተፈናቅለው የመጡ የትግራይ ሰዎች አሉ፤ ግን የአማራ ሕዝብ ግጭቱን ቀንሶታል›› ነው ያሉት ዶክተር ደብረጽዮን፡፡

‹‹የአማራና የትግራይ ሕዝብ ዘመድ ብቻም አይደለም፤ ከዚያ በላይ ነው ግንኙነቱ፡፡ ችግር ያለው ፖለቲከኞች ላይ ነው፡፡ ሕዝቡ ወደግጭት አታስገቡን ነው እያለ ያለው፡፡ በእኛ በኩልም እንደ አመራር ለመጋጨት አንፈልግም፡፡ ከትግራይ የሚተኮስ ነገር አይኖርም፤ ግፊቶች ግን አሉ፡፡ ሁሉም ኃላፊነት ከወሰደ ግጭቶች አይኖሩም፤ ታሪካችንም አይፈቅድም፡፡ ፖለቲካችን በፖለቲካው መድረክ እናየዋለን፤ ድርጅትም መንግሥትም ሕዝብም እየተናበብን እየሠራን ነው፤ የምትመክሩንን እየሰማን እያስተካልን እንሄዳን›› ብለዋል፡፡

ምንጭ፦ አብመድ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update የትግራይ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር ዶክተር #ደብረጽዮን_ገብረሚካኤል ከኖርዌይ ዓለም አቀፍ ትብብር ልማት ሚኒስትር ዳግ ኢንጌ ዩሊስትዮ ጋር እየተወያዩ ነው። በውይይታቸውም በኢኮኖሚና ተያያዥ ጉዳዮች ዙሪያ እየመከሩ ይገኛሉ። የኖርዌይ ዓለም አቀፍ ትብብር ልማት ሚኒስትር ዳግ ኢንጌ ዩሊስትዮ በትናንትናው ዕለት ከውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዶክተር ወርቅነህ ገበየሁ ጋር በተለያዩ ጉዳዮች ዙሪያ መወያየታቸው ይታወሳል።

Via FBC
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ባድመ🔝

የሰሜን ዕዝ 7ኛውን የመከላከያ ሰራዊት ቀን “ህገ መንግስታዊ ተዓማኒነታችንና ህዝባዊ ባህሪያችንን ጠብቀን የተጀመረው ለውጥ እናስቀጥል” በሚል መሪ ቃል በባድመ ተከበረ። በበዓሉም የትግራይ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር ዶክተር #ደብረጽዮን_ገብረሚካኤል የክብር እንግዳ ሆነው የተገኙ ሲሆን ፥በከፍተኛ የሰራዊት አዛዦችና አባላት ደማቅ አቀባበል ተደርጎላቸዋል። ከዚህ ባለፈም ከትግራይ ክልልና አጎራባች ክልሎች ተወካዮች በበዓሉ መታደማቸው ነው የተገለፀው።

Via ENA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update የትግራይ ክልል መንግስት ለፓን አፍሪካ ዩኒቨርሲቲ ግንባታ 250 ሚሊዮን ብር ድጋፍ እንደሚያደርግ የክልሉ ምክትል ርዕሰ-መስተዳድር ዶክተር #ደብረጽዮን_ገብረሚካኤል ተናገሩ። ምክትል ርዕሰ-መስተዳድሩ እንዳሉት “የአድዋ አንፀባራቂ ድል አገራዊ ፋይዳ ያለው፤ ለውጭ ኃይል የማንንበረከክ፤ ለነፃነት ወደኋላ የማንል በማንነት ሳንለያይ ሊገመት የማይችል ውጤት ማስመዝገብ እንደሚቻል ማሳያ ነው”። የአድዋ ታሪክ ትልቅ ትምህርት የሚሰጥ ነው ያሉት ዶክተር ደብረጽዮን በአሁኑ ወቅት “የውጭ ተፅዕኖ በተዘዋዋሪ ሁኔታ ስለሚፈፀም አገሪቱን ከማንኛውም የውጭ ጣልቃ ገብነት መከላከል ይገባል” ብለዋል። አድዋ በተገቢው ሁኔታ መጠናትና መጠበቅ ይገባዋል በማለትም የቱሪስት መዳረሻ ለማድረግም መሰራት እንዳለበት አሳስበዋል። ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ከሌሎች ዩኒቨርሲቲዎች በተለየ የፓን አፍሪካ ዩኒቨርሲቲ ለመገንባት እንቅስቃሴ እየተደረገ እንደሚገኝ ገልፀው ዩኒቨርሲቲው በተለይም አፍሪካዊያን ምርምር የሚያደርጉበት ነው ብለዋል። ዩኒቨርሲቲውን እውን ለማድረግ ሁሉም ኢትዮጵያዊ መተባበር እንዳለበት መክረው የትግራይ ክልል ለዩኒቨርሲቲው ግንባታ 250 ሚሊዮን ብር ድጋፍ ለማድረግ መወሰኑም ይፋ አድርገዋል። የአድዋ ድል መታሰቢያ ሙዚየምን ጨምሮ ሌሎች ከድሉ ጋር ተያያዥ የሆኑ ፕሮጀክቶችን ለመተግበር ክልሉ ያልተቆጠበ ድጋፍ እንደሚያደርግ ማረጋገጣቸውን የዘገበው ኢዜአ ነው።

Via ኢዜአ
@tsegabwolde @tikvahethiopia