TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.5K photos
1.43K videos
206 files
3.96K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
የተመድ ማስጠንቀቂያ‼️የአለም ሀገራት የምድራችን ሙቀት እንዳይጨምር አስፈላጊውን እርምጃ ካልወሰዱ እስከ አውሮፓዊያኑ 2030 ባለው ጊዜ የከፋ የአየር ንብረት ለውጥ አደጋ ሊከሰት እንደሚችል የተባበሩት መንግስታቱ ድርጅት/ተመድ/ #አስጠነቀቀ፡፡

ድርጅቱ ይሄን ያስታወቀው ከአውሮፓዊያኑ 2030 ወዲህ የአለም ሙቀት ከ1 ነጥብ 5 ዲግሪ ሴልሺየስ በላይ #ሊጨምር እንደሚችል ከተነበየ በኋላ ነው ተብሏል፡፡

ይሄም ሁኔታ እውን ከሆነ በአለም በሚሊዮን በሚቆጠሩ ሰዎች ላይ የከፋ ድርቅ፣ ሰደድ እሳት፣ ጎርፍ እና የምግብ እጥረት እንደሚከሰት የመንግስታቱ ድርጅት የአየር ንብረት ለውጥ ፓናል ገልጿል፡፡

ድርጅቱ እዚህ መደምደሜያ ላይ የደረሰው ለአለም ሙቀት መጨመር ምክንያት የሆነው የሙቀት አማቂ ጋዝ ልቀት አሁን ያለበትን ደረጃ ጥናት በማድረግ እንደሆነ ተነግሯል፡፡

አሁን ላይ የአለም ሙቀት በ1 ዲግሪ ሴልሺየስ እየጨመረ ሲሆን ይህን ሁኔታ እንዳይባባስ በሚቀጥሉት ጥቂት ዓመታት የአለም መንግስታት አስፈላጊውን እርምጃ ሊወስዱ እንደሚገባ ተመልክቷል፡፡

የአለም ሙቀት ከ1 ነጥብ 5 ድግሪ ሴልሺየስ የዘለለ እንዳይሆን እስከ 2030 ባለው ጊዜ ውስጥ የአለም የካርቦን ዳይ ኦክሳይድ ልቀት በ45 በመቶ ሊቀንስ እንደሚገባ ተጠቁሟል፡፡

ምንጭ፦ ሲኤንኤን
@tsegabwolde @tikvahethiopia
የኮማንድ ፖስቱ ማስጠንቀቂያ!

<<በደቡብ ክልል በተለያዩ አካባቢዎች በመንግስት እውቅና ሳይሰጣቸው ተሰቅለው የሚገኙ አርማዎችና ሰንደቅ ዓላማዎች በአስቸኳይ እንዲነሱ>> ሲል የደቡብ ክልል ጊዜያዊ ኮማንድ ፖስት #አስጠነቀቀ

ኮማንድ ፖስቱ ዛሬ በክልሉ መንግስት ራዲዮ ጣቢያ አማካኘነት ባስሳተላለፈው ማሳሰቢያ፤ ኮማንድ ፖስቱ በክልሉ አንዳንድ ዞኖች እና ወረዳዎች በህግ የማይታወቁ አርማዎችን፣ ሰንደቅ ዓላማዎችን፣ ባነሮችን እና የአድራሻ ማስታወቂያዎችን (ታፒላዎችን) የሰቀሉ አካላት ከዛሬ ጀምሮ ባሉት ሁለት ተከታታይ ቀናት ውስጥ በአስቸኳይ እንዲያነሱ ሲል አሳስቧል።

በክልሉ አንዳንድ አካባቢዎች የክልሉን #ህጋዊ ሰንደቅ ዓላማ በማውረድና የመንግስት ተቋማት የአድራሻ ማስታወቂያዎችን በመንቀል በምትኩ እውቅና የሌላቸውን የመትከል ሙከራዎች መከናወናቸውን ኮማንድ ፖስቱ በመግለጫው አስታውቋል።

በመሆኑም «ህገ ወጥ»ያላቸውን አርማዎችን፣ ሰንደቅ ዓላማዎችን እና የአድራሻ ማስታወቂያዎችን በተሰጠው የሁለት ቀናት የጊዜ ገደብ ውስጥ በማንሳት ህጋዊ» የሆኑትን በአስቸኳይ ወደ ቦታቸው እንዲመለሱ ሲል ኮማንድ ፖስቱ አሳስቧል።

በተጨማሪም መግለጫው ከተሰጠበት ቀን ጀምሮ በክልሉ ሁሉም ዞኖች ፣ ወረዳዎች ፣ በከተሞች አና በቀበሌዎች የመስተዳድር ክልል ውስጥ የሚገኙ የመንግስት መስሪያ ቤቶች፣ የግል ተቋማት እና መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች #ትክክለኛ የአድራሻ ማስታወቂያዎችን (ታፒላዎችን) እና ህጋዊ የክልሉን ሰንደቅ ዓላማ ብቻ እንዲጠቀሙ አመልክቷል።

እንዲሁም በተለያዩ የህትመት ውጤቶች የተዘጋጁና በህግ የማይታወቁ አርማዎችንና ሰንደቅ ዓላማዎችን መልበስ ፣ ይዞ መዘዋወር ፣ መሰቀልም ሆነ መለጠፍ በጥብቅ የተከለከለ ነው ሲል አስታውቋል። በተጠቀሰው ቀናት ውስጥ መመሪያውን ተፈፃሚ በማያደርጉ ግለሰቦች፣ ተቋማት እና ድርጅቶች ላይ በየደረጃው በተዋቀሩ የኮማንድ ፖስት አማካኝነት #ህጋዊ_እርምጃ ይወሰዳል ሲል አስጠንቅቋል።

በደቡብ ክልል የሀዋሳ እና የወላይታ ሶዶ ከተሞችን ጨምሮ በክልሉ የተለያዩ አካባቢዎች በክልል መደራጀትን ለመጠየቅ በተዘጋጁ ሰልፎች ላይ ወደፊቱ ለሚመሰርቷቸው ክልሎች በሰንደቅ ዓላማነት ሊያገለግሉ ይችላሉ በሚል የዘጋጁቸውን አርማዎችን ሲያውለበልቡ እንደነበር አይዘነጋም። በተለይም በሲዳማ ዞን ከባለፈው ሐምሌ 11 ቀን 2011 ዓም ወዲህ በዞኑ የሚገኙ አንዳንድ የወረዳዎች መስተዳድር ፅህፈት ቤቶች የሲዳማ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት የሚሉ የአድራሻ ማስታወቂያዎችን በጎዳናዎች በመትከል በማህበራዊ የመገናኛ ዘዴ አውታሮች እያሰራጩ እንደሚገኙ ይታወቃል።

ምንጭ፦ የጀርመን ራድዮ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Update የአማራ ክልል ይፋዊ ምላሽ ሰጠ። * " የዛቻና የጠብ አጫሪነት የሆነውን የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ካቢኔ መግለጫ ተመልክተነዋል " - የአማራ ክልል የአማራ ክልል መንግሥት ዛሬ ሀሙስ ባወጣው ይፋዊ መግለጫ ፤ " የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ካቢኔ መጋቢት 16 ቀን 2016 ዓ/ም የአማራ ክልል ተማሪዎች መማሪያ መጻህፍትን እንደሰበብ ተመርኩዞ ያወጣውን የዛቻ እና የጠብ አጫሪነት…
" ... ከለመደው አጓጉል የካርታ ፖለቲካ ጨዋታ እንዲወጣ እንመክራለን " - የአማራ ክልላዊ መንግሥት

የአማራ ክልል መንግሥት ባወጣው መግለጫ ፤ " የትግራይ ክልል ግዜያዊ አስተዳደር ለሀገሪቱ ቋሚ ቀውስ ምንጭ ከሚያደርጉት ተግባራት እንዲታቀብ " ሲል #አስጠነቀቀ

የክልሉ መንግሥት ፥ በአሁን ሰዓት የወልቃይት  ጠገዴ ፣ ጠለምት እንዲሁም የወፍላ ወረዳዎች እና የራያ የማንነት ጥያቄ ያለባቸው ወረዳዎች ህዝብ ለረጅም ዓመታት በ " ህወሓት " በኃይል ተገፍፎባቸው የነበረው የማንነትና ጥያቄና ራስን በራስ የማስተዳደር ነጻነት የተመለሰበት እንደሆነ ጠቁሟል።

ህዝቡም እንደማንኛውም የሀገሪቱ ሕዝብ ሁሉ የልማቱ ተሳታፊና ተጠቃሚነት መብቱ ሊቀለበስ የማይችል ነው ብሏል።

" የፕሪቶሪያው የሠላም #ስምምነት ከመፈረሙ በፊት ጀምሮ የአማራ ክልል እንደሌሎቹ ዞኖችና የልማት ትሩፋቶች ሁሉ የአካባቢው ሕዝብም #በትምህርቱም_መስክ ተጠቃሚ እንዲሆን አድርጓል " ሲል ገልጿል።

ክልሉ ፤ እንደሌሎቹ አካባቢዎች የነዚህ አካባቢ ህፃናትም የመማር መብታቸው እንዲከበር ግዴታውን መወጣቱን ገልጿል።

የትምህርት ስርዓቱን ሰበብ በማድረግ የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር በአማራ ክልል ላይ ጥቃት ከመፈጸም የማይመለስ መሆኑን የሚገልጽ የጠብ አጫሪ መግለጫ እንዳወጣ ጠቁሟል።

ይህም " ካለፉት ድርብርብ ውድቀቶች ትምህርት አለመውሰድን ከማሳየት የዘለለ ፋይዳ አይኖረውም " ሲል ተችቷል።

የአማራ ክልል መንግሥት ፥ " ጊዜያዊ አስተዳደሩ ሀገራችንን እና ሁለቱን ክልሎች ወደ #ቀውስ ከሚያስገቡ ተግባራት በመቆጠብ ከለመደው አጓጉል የካርታ ፖለቲካ ጨዋታ እንዲወጣና የህዝብን ፍላጎት ማዕከል ባደረጉ ውይይቶች ላይ እንዲያተኩር  እንዲሁም አንድ ሀገር ለመገንባት ለሚፈለገው ዘላቂ ሠላምና ለሕዝቦች አንድነት መጽናት በሚበጅ ሐሳብና ተግባር ላይ እንዲያተኩር እንመክራለን " ብሏል።

ሙሉ መግለጫ ፦ https://t.iss.one/tikvahethiopia/86444

@tikvahethiopia