TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
59.4K photos
1.51K videos
215 files
4.12K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
እኛ የምንፈልገው ይሄን ነው!

ፋሲሎች መቀሌ ሲደርሱ በመቀለ እና ወልዋሎ ደጋፊዎች ደማቅ አቀባበል ተደረገላቸው!

የፋሲል ከነማ ልዑክን ቡድን አባላት መቀለ ሲደርሱ በመቀሌ እና ወልዋሎ ደጋፊዎች እንዲሁም በትግራይ ክልል ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች ደማቅ አቀባበል ተደርጎላቸዋል፡፡
የመቀሌ ከነማ እግርኳስ ክለብ ደጋፊዎች አፄዎቹን፤ " እንኳን በሰላም ደህና መጣችሁ!" የሚል የደስታ መልዕክት ጽሑፍ ባነር ይዘው ነበር አቀባበል ያደረጉላቸው፡፡

የጥላቻውን ግድግዳ ፋሲል ከነማ ፡#አፈራርሶታል፡፡ የወልዋሎና የመቀለ ደጋፊዎች የፍቅሩን ድልድይ ገንብተዋል፡፡

ፋሲል ከነማ በመቀሌ ሰማይ ሥር የሰላም መለከትን እየነፋ የሰላም እርግብ ሁኖ መቀሌ ላይ አርፏል፡፡

ሰላም ለሀገራችን ፡ ሰላም ለህዝባችን ፡ሰላም ለእናት ሀገራችን ኢትዮጵያ!

ምንጭ፦ ጌጡ ተመገን
@tsegabwopde @tikvahethiopia
#update እነዚህ ባለስልጣናት ወደሚከተሉት ሀገራት በአምባሳደርነት እንደተመደቡ ተሠምቷል፦

1. አምባሳደር አስፋው ዲንጋሞ ከህንድ ወደ ኩባ

2. አምባሳደር ዲና ሙፍቲ ከኬንያ ወደ ግብፅ

3. አምባሳደር አዛናው ታደሰ ከግብፅ ወደ ናይጄርያ

4. አምባሳደር ኩማ ደመቅሳ ከጀርመን ወደ ስዊድን እና

5. አምባሳደር ፍሰሀ ሻውል ከደቡብ ሱዳን ወደ እንግሊዝ

ምንጭ፦ ጋዜጠኛ ኤልያሥ መሠረት
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ከገና በዓል ጋር ተያይዞ ደንበኞቹ የባንክ አገልግሎት እንዲያገኙ በማሰብ #እሁድ (ታህሳስ 28 ቀን 2011 ዓ.ም) እስከ ቀኑ 6፡00 ሰዓት ድረስ በተመረጡ ቅርንጫፎቹ አገልግሎት እንደሚሰጥ አስታወቀ።

ከባንኩ የተገኘው መረጃ እንደሚያሳየውም የሚከተሉት ቅርንጫፎቹ ነገ ክፍት ናቸው።

1. አራዳ ጊዮርጊስ ቅርንጫፍ
2. ማህተም ጋንዲ ቅርንጫፍ
3. ሸገር ቅርንጫፍ
4. ስድስት ኪሎ ቅርንጫፍ
5. ሽሮሜዳ ቅርንጫፍ
6. ጥቁር አንበሳ ቅርንጫፍ
7. ፊንፊኔ ቅርንጫፍ
8. ንፋስ ስልክ ቅርንጫፍ
9. ጎተራ ቅርንጫፍ
10. አቃቂ ቅርንጫፍ
11. ባልቻ አባነፍሶ ቅርንጫፍ
12. ገዛኸኝ ይልማ ቅርንጫፍ
13. ገርጂ ቅርንጫፍ
14. ቦሌ መድሃኒዓለም ቅርንጫፍ
15. መስቀል ስኩዌር ቅርንጫፍ
16. ባምቢስ ቅርንጫፍ
17. ሰበታ ቅርንጫፍ
18. ዓለም ባንክ ቅርንጫፍ
19. ቤቴል ቅርንጫፍ
20. ዘነበ ወርቅ ቅርንጫፍ
21. ተስፋ ድርጅት ቅርንጫፍ

ምንጭ፦ epa
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ጠ/ሚር ዶ/ር #ዐቢይ_አህመድ ዛሬ ከመምህራን ጋር ውይይት ባደረጉበት ወቅት ስለህዳሴው ግድብ ፕሮጀክት ከተናገሩት የተወሰደ...
@tsegabwolde @tikvahethiopia
አማራ ክልል‼️

የአማራ ክልል ወጣቶች የአካባቢያቸውን ሰላምና ደህንነት ነቅተው በመጠበቅ በሃገሪቱ ለተጀመረው የለውጥ እንቅስቃሴ #ስኬታማነት ሊሰሩ እንደሚገባ የክልሉ የሰላምና ደህንነት ቢሮ ኃላፊ አስገነዘቡ።

የቢሮው ኃላፊ ብርጋዴል ጀነራል #አሳምነው__ጽጌ ትናንት ከወልድያ ከተማ ነዋሪዎች ጋር ባደረጉት ውይይት እንደገለፁት በአገሪቱ ለተጀመረው የለውጥ እንቅስቃሴ ስኬታማነት የወጣቶች ተሳትፎ ወሳኝ ነው፡፡

ባለፉት ዓመታት አማራው በክልሉ ውስጥም ሆነ በሌሎች ክልሎች ማንነቱን መሰረት ያደረጉ የሰብአዊ መብት ጥሰቶች ሲፈፀሙበት መቆየታቸውን ገልፀዋል፡፡

አሁን ላይ የዜጎችን ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ደህንነት ሊያረጋግጥ የሚችል የለውጥ ብርሃን እየታየ ቢሆንም ጥቅማቸው የተነካባቸው አካላት ለውጡን ወደ ኋላ ለመመለስ እየተንቀሳሱ መሆኑን አስታውቀዋል፡፡

Via~አብመድ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
አዲስ አበባ‼️

በአዲስ አበባ በህገወጥ መንገድ የውጭ ሀገር ገንዘቦችን #በሚመነዝሩ ላይ በተደረገ ድንገተኛ ፍተሻ ከ2 ሚሊየን የሚበልጥ የኢትዮጵያ ብር እና የተለያዩ ሀገራት ገንዘቦችን #መያዙን የከተማዋ ፖሊስ ኮሚሽን ገለፀ።

ታህሳስ 26 እና 27 ቀን 2011 ዓመተ ምህረት በቂርቆስ ክፍለ ከተማ በተለምዶ ኢትዮጵያ ሆቴልና ጋንዲ አካባቢ የብሄራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት እና የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን በጋራ ባደረጉት ድንገተኛ ፍተሻ ገንዘቦቹን መያዛቸውን ኮሚሽኑ ለfbc በላከው መግለጫ አስታውቋል።

ከዚህ በፊት በአካባቢዎቹ በተደረገ ድንገተኛ ፍተሻ ለምንዛሪ የተዘጋጁ የተለያዩ ሀገራት ገንዘቦችና የኢትዮጵያ ብር መያዙን ኮሚሽኑ በመግለጫው አስታውሷል።

ሁለቱ ተቋማት ባደረጉት ድንገተኛ ፍተሻ ተጠርጥረው የተያዙ አምስት ግለሰቦች በፖሊስ ቁጥጥር ስር ውለው ምርመራ እየተደረገባቸው መሆኑን ነው ያስታወቀው።
የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ህገወጥ የገንዘብ ዝውውርን ለመግታት ከባለድርሻ አካላት እና ከህብረተሰቡ ጋር በመሆን ተግባሩን እንደሚቀጥል በመግለፅ፥ የከተማው ነዋሪ ይህ ጥረት እንዲሳካ የበኩሉን አስተዋጽኦ እንዲወጣ ጠይቋል።

ምንጭ፦ ፋና ብሮድካሥቲንግ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update የኢትዮጵያ ፖሊስ ዩንቨርስቲ ኮሌጅ በተለያየ የፖሊስ ሣይንስ የትምህርት ዘርፍ ያስተማራቸውን ሲኒየር ኮማንደሮች፣ ሰልጣኝ መኮነኖችና፣ የጤና ባለሙያወችን ዛሬ አስመረቀ፡፡ ዩንቨርስቲ ኮሌጁ 26 ሲነየር ኮማንደር ኮርስ፣ በዲግሪ ፕሮግራም በወንጀል ምርመራ፣ በወንጀል መከላከልና በፖሊስ አስተዳደር በመጀመሪያ ዙር 128፣ በሁለተኛ ዙር ወንጀል ምርመራ በዲፕሎማ ፕሮግራም 51፣ ለ41ኛ ዙር መደበኛ ዲፕሎማ ፕሮግራም 110 ሰልጣኞችን አስመርቋል፡፡

@Tsegabwolde @tikvahethiopia
አቶ ቡልቻ ደመቅሳ…

"ኢትዮጵያ የአፍሪካ አገር አይነት አይደለችም፣ የፈረንጅ አገርም አይደለችም፣ ባህሏም ኑሮዋና ታሪኳም የአረብ አገር አይደለም፤  አትመስልም። ራሷን የቻለች #ብቸኛ አገር ነች፡፡"

@tsegabwolde @tikvahethiopia
“ኢትዮጵያ ውስጥ አንድ መንግሥት ነው፣ ያለው #እኔ የምመራው መንግሥት። አንድ ዓመት ተኩል በኋላ እኔ እና ድርጅቴን ካልመረጣችሁ አቅፌ ስሜ እሰጣችኋለሁ። ከምርጫ በፊት በ 3 ወር በ 5 ወር መንግሥት እሆናለሁ የሚል ቅዠት ኢትዮጵያ ውስጥ አይሰራም። ይሄ ቅዠት የማይሰራበት ምክንያት እኔ እንኳን ብፈቅድ አንድ ዓመት ተኩል ታግሶ ማሸነፍ ያልቻለ ፓርቲ ነገ መጥቶ እዚህ ቢገባ ያምሰናል እንጂ እንዴት ይመራናል? 30 ዓመት 20 ዓመት የኢትዮጵያን ምድር መርግጥ ያልቻሉ ሰዎች ይብቃ ብለን ሕግ ቀይረን፣ ባሉበት አናግረን፣ ለምነን አምጥተን ስናበቃ ልንወጋ አይገባም” ጠ/ሚ #ዐብይ_አሕመድ (ዶ/ር)
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ጠቅላይ ሚኒስትር #ዐቢይ_አሕመድ ታህሳስ 27 ቀን 2011 ከመምህራን ጋር በተወያዩበት ወቅት የተነሱ ነጥቦች።

#PMOEthiopa
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update የገቢዎች ሚኒስቴር የገናን በዓል ምክንያት በማድረግ ለአበበች ጎበና እና ለሙዳይ የበጎ አድራጎት ማህበራት የገንዘብና የቁሳቁስ ድጋፍ አደረገ። በዚህ ጊዜ የገቢዎች ሚኒስትር ወይዘሮ #አዳነች_አበቤ እንደገለጹት የገናን በዓል ምክንያት በማድረግ ለሁለቱ ማህበራት የ450 ሺህ ብር የገንዘብና የአልባሳት ድጋፍ ተደርጓል ብለዋል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
Audio
#update በወላይታና በሲዳማ ብሄር መካከል እርቀ ሰላም የማውረድ እንቅስቃሴ #ቀጥሏል፡፡ የወላይታ አገር ሸማግሌዎች በግጭቱ የተጎዱ #የሲዳማ_ተወላጆችን #ሃዋሳ ሄደው በባህላዊ ሥርዓት ያፅናኑ ሲሆን የሲዳማ ሸማግሌዎችም ወላይታ ሶዶ በመሄድ ጠይቀዋል፡፡ በቀጣይም እርቀ ሰላም የማውረድና የይቅርታ ሥርዓት ከህዝብና #ከወጣቶች ጋርም ይፈፀማል ተብሏል፡፡


ምንጭ፦ voa
@tsegabwolde @tikvahethiopia
አቶ ጌታቸው አሠፋ‼️

የህወሓት ማእከላይ ኮሚቴ በአቶ #ጌታቸው_አሰፋ ጉዳይ 'እየተወያየ እንዳልሆነ' የኮሚቴው አባል አቶ አማኑኤል አሰፋ ገልፀዋል፡፡ አቶ አማኑኤል "ፖለቲካዊ ችሎት ላይ አልተቀመጥንም፡ ከዚህ የሚበልጥ ብዙ አጀንዳዎች አሉን" ሲሉ በFB ገፃቸው ፅፈዋል፡፡

Via Mili Haileselassie
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ይለዩ!!

የዋልታ ሚዲያ እና ኮሚኒኬሽን ትክክለኛ የፌክቡክ ገፅ ይለዩ። ከዚህ ቀደም በተመሳሳይ ተቋሙ ያላሠራጨውን መረጃ እንደተቋሙ ተደርጎ #በሀሠተኛ ገፅ ሲሰራጭ ተስተውሏል።


@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update የኢትዮጵያ አየር መንገድ አቪዬሽን ቡድን የአዲስ አበባ ቦሌ ዓለም አቀፍ ኤርፖርት የመንገደኞች ማስተናገጃ ሕንፃ ማስፋፊያና ባለአምስት ኮከብ ሆቴል #ለማስመረቅ በዝግጅት ላይ  እንደሆነ ታውቋል፡፡

via Reporter
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update ወልዋሎ ከፋሲል ዛሬ የሚያደርጉት ጨዋታ በቀጥታ በአማራ ቴሌቪዥን እና በትግራይ ቴሌ ቪዥን ከ 9:00 ሰአት ጀምሮ የቀጥታ ሽፋን ያገኛል።

via ቴዎድሮሥ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ኧረ ለመሆኑ ምሁር ማለት ምን ማለት ነው ? ምሁርስ የሚባለው የትኛው ነው ? ኢትዮጵያ በተለያዩ ግጭቶች እንደንፍፊት በተወጠረችበት በአሁኑ ጊዜ ወይም የድህነት ማቅ እየሞዠቀ በእምብርክክ በሚያስኬድባት ጊዜ የምሁራኖቹ ሚና ምን ነበር ? የሚል ጥያቄ ይነሳል፡፡ ምሁራን መሽገውባቸዋል የሚባሉት #ዩኒቨርስቲዎቻችን በብሔር ዘውገኛነት እየተናጡ የሚገኙበት ምክንያት ሲታይ ወይም የሚሰጡዋቸው አስተያየቶችና ትንታኔ በጦዘ የብሔር ወገንተኝነት ተቆልምመው ሲነጉዱ ይታያሉ፡፡ እንደነዚህ ዓይነት ድርጊቶችም ኧረ ለመሆኑ ምሁር ማለት ምን ማለት ነው የሚል ጥያቄ ያጭራል፡፡

ምንጭ፦ ሸገር 102.1
@tsegabwolde @tikvahethiopia