TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
59.4K photos
1.51K videos
215 files
4.12K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#update በደብረ ብርሃን ከተማ ኢትዮጵያ ኢዱኬሽን ኢኒሸቲቭ ኢን ኮርፖሬሽን በ10 ሚሊዮን ዶላር ወጪ የ “ኃይሌ ማናስ አካዳሚ አዳሪ ትምህርት ቤት” ግንባታን አስጀምሯል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ሰማያዊ ፓርቲ‼️

ሰማያዊ ፓርቲ ከኢዴፓ፣ አርበኞች ግንቦት ሰባት ንቅናቄ እና ከቀድሞው አንድነት ፓርቲዎች ጋር ለመዋሃድ መስማማቱ ተገለፀ።

ሰማያዊ ፓርቲ በትላንትናው ዕለት ባካሄደው ጠቅላላ ጉባኤ ከሶስቱ ፓርቲዎች ጋር ለመዋሃድ በሙሉ ድምፅ መወሰኑን የፓርቲው ሊቀመንበር አቶ #የሽዋስ_አሰፋ ለFBC ተናግረዋል።

"ትልቅ አገራዊ ፓርቲ ለኢትዮጵያ አንድነት" በሚል መሪ ቃል በተካሄደው ጠቅላላ ጉባኤ የኢህአዴግ፣ አርበኞች ግንቦት ሰባት፣ ኢዴፓ፣ መድረክ፣ አረና፣ የቀድሞው አንድነት እና ሌሎች ፓርቲዎች ተወካዮች በክብር እንግድነት መታደማቸው ተገልጿል።

ፓርቲው በጠቅላላ ጉባኤው ከሶስቱ ፓርቲዎች ጋር ብቻ ሳይሆን ከሌሎች በአላማ ከሚመሳሰሉ ፓርቲዎች ጋር ተዋህዶ ትልቅ አገራዊ ፓርቲ ለመመስረት መወሰኑን ሊቀመንበሩ ተናግረዋል።

በቀጣይም ሰማያዊ፣ ኢዴፓ፣ አርበኞች ግንቦት ሰባት እና የቀድሞው አንድነት ከወረዳ ጀምሮ መዋሃድ የሚጀምሩ መሆኑ ነው የተገለፀው።

የአራቱ ፓርቲዎች ጥምር አገራዊ ፓርቲም በአዲስ ስያሜ እስከ መጋቢት 30 ይፋ የሚደረግ መሆኑን ጠቁመዋል።

ሰማያዊ ፓርቲ በጠቅላላ ጉባኤው ባሳለፈው ውሳኔ እና በቀጣይ ስራዎቹ ዙሪያ ዛሬ መግለጫ የሚሠጥ መሆኑን አቶ የሽዋስ ተናግረዋል።

ምንጭ፦ ፋና ብሮድካስቲንግ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
FM_20181229_224505.ogg
8.5 MB
አዲስ አበባ‼️

የፍቅረኛውን #ብልት በክር የሰፋው ኢትዮጵያዊ...እጅግ በጣም ለመስማት የሚከብድ #ዘግናኝ ድርጊት አዲስ አበባ አስተናገደች!!

ምንጭ፦ ኢትዮፒካሊንክ የራድዮ ፕሮግራም(FM 98.1)
@tsegabwolde @tikvahethiopia
Forwarded from TIKVAH-ETHIOPIA (Tsegab Wolde)
ማስታወቂያ‼️ከቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ ለቃችሁ የወጣችሁ ተማሪዎች በሙሉ የዳግም ምዝገባ ጊዜ ጥር 2 እና 3 መሆኑን አውቃችሁ ከወዲሁ እንድትዘጋጁ!!

©በቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ የTIKVAH-ETH ቤተሰብ አባላት
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update ማሻሻያ ማድረጉን ተከትሎ ተከራዮች የበተለያየ መንገድ #ተቃውሞ በማሰማት ላይ ይገኛሉ። መኢአድ የተባለው የፖለቲካ ፓርቲም ጭማሪውን በመቃወም መግለጫ አውጥቷል። የፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ ረሻድ ከማል ለበርካታ አመታት ከገቢያ ዋጋ በታች በመክፈል ተጠቃሚ ነበሩ በማለት የተከራዮችን ተቃውሞ እንደማይቀበሉት አስታውቀዋል። ፒያሳ ባቅላባ ቤት 6 ሺ ብር፤ ጆሊ ባር 5 ሺ ብር፤ ቱሪስት ሆቴል 13 ሺ ብር፤ ሮሚና ካፌ 3 ሺ ብር፡ ሎመባርዲያ 1777ሺ ብር፤ ሃራምቤ ሆቴል 35 ብር፤ ብቻ ሲከፍሉ ቆይተዋል በማለት ሀላፊው ምሳሌ ጠቅሰዋል።

Via~ELU
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ሰበር ዜና‼️

ጉዞ ዓድዋ 6 ተጀመረ!! ታሪካዊቷ የሐረር ከተማ የዘንድሮ ጉዞ መነሻ ተደርጋ ተመርጣለች።

"ፍቅር ለኢትዮጵያ" የሚል መርሕ የያዘው የዘንድሮ የእግር ጉዞ መነሻውን ከሀረር ከተማ በማድረግ ጥር 7 ቀን 2011 ዓ.ም ከአዲስ አበባ የሚነሱ ተጓዦችን በመቀላቀል የካቲት 23 ቀን 2011 ዓ.ም. በታሪካዊቷ ዓድዋ ከተማ ይጠናቀቃል።

በትናትናው ምሽት በድሬዳዋ ከተማ በተካሔደው የመሸኛ ስነሥርዓት ላይ የተገኙት የድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አቶ ኢብራሂም ኡስማን ባደረጉት ንግግር "ዓድዋ የመላው ኢትዮጵያዊያን ህብረት ያታየበት ሁላችንም የምንኮራበት ድላችን መሆኑን ጠቅሰው፤ ይህንን ድል ለመዘከር በየአመቱ የሚዘጋጀውን የጉዞ ዓድዋ እንቅስቃሴ የከተማ አስተዳደሩ ቅድሚያ ሰጥቶ እንደሚያግዝ አረጋግጠው የዘንድሮው 123ኛ የዓድዋ ድል በዓል አከባበር መጀመሩን በይፋ አብስረው፤ ለተጓዦች መልካም መንገድ ተመኝተዋል።

በታላቁ የዓድዋ ጦርነት ወቅት የምስራቅ ኢትዮጵያን ጦር የመሩት የቀዳሚው ጦር አዝማች ልዑል ራስ መኮንን ከተነሱበት የሐረር ከተማ በ5 ተጓዦች የተጀመረው የዘንድሮው ጉዞ ዓድዋ በተለያዩ ደማቅ ሥነስርዓቶች ለመካሔድ በዛሬው እለት ታህሳስ 21 ቀን 2011 ዓ.ም. ተጀምሯል።
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ ኢንጂነር ታከለ ኡማ ለጉዞ ዓድዋ አዘጋጆች በስልክ እንዳረጋገጡት የከተማ አስተዳደሩ ከሀረር የተነሱ ተጓዦችን ተቀብሎ በመሸኘት እና ከአዲስ አበባ የሚነሱ ተጓዦችን አሰፈላጊውን ስንቅ አሟልቶ በመሸኘት የከተማ አስተዳደሩ አጋርነቱን ያሳያል።

፨፨፨
የፍቅር ዘመቻው ሠላምን እና አብሮነትን ሰንቆ በዓድዋ ተራሮች አናት ላይ የካቲት 23 ቀን በድል ይጠናቀቃል።
የጉዞ ዓድዋ አስተባባሪዎች
መሐመድ ካሳ
ያሬድ ሹመቴ
#ፍቅር_ለኢትዮጵያ
#ኢትዮጵያዊነት_ይለምልም !!
#ጉዞ_ዓድዋ_6
#ከሐረር_አዲስ_አበባ_ዓድዋ
#1540ኪ .ሜ

ምንጭ፦ ያሬድ ሹመቴ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ሰመራ ዩኒቨርሲቲ‼️

ወጣቱ #ከጎጠኝነትና #ከጎሰኝነት አጀንዳዎች ይልቅ በአገራዊ ራዕይ ላይ ማተኮር እንደሚገባው የሰብዓዊ መብት ተሟጋቹ አቶ ኡባንግ ሜቶ አሳሰቡ።

አቶ ኦባንግ ከሰመራ ዩኒቨርስቲ ተማሪዎች ጋር ባካሄዱት ውይይት እንደተናገሩት ወጣቱ ባለፉት 27 ዓመታት በልዩነቶች ላይ  ያተኮረው አመራር ይከተለው ከነበረው ከፋፋይ ፖሊሲ በመውጣት አገራዊ እሴቶችን አውቆ ወደሚተገብርበት ሁኔታ መሸጋገር አለበት።

ከራስ ጥቅምና መብት እኩል ስለሌሎች ብሄርና እምነት ተከታዮች ብሎም አገራቸው ሰላሟ ተረጋግጦ  በሚኖሩበት  ሁኔታ ላይ መሥራት ይጠበቅባቸዋል ብለዋል።

የጋራ አገሩን ለመገንባትና ለአንድነቷ በመታገል ራዕይዋን ለማሳካት መሥራት እንዳለበትም ተናግረዋል።

ባለፉት ዓመታት ዜጎች ለዘመናት የገነቧቸዉ ተከባብረው የመኖር አኩሪ እሴቶች መሸርሸራቸውን ገልጸው፣ይህም አለመተማመንና አንዱ ሌላውን በጥርጣሬና በስጋት እስከማየት የደረሰበት ሁኔታ መፈጠሩን አስታውሰዋል።

በአገሪቱ የተለያዩ አካባቢዎች የሚከሰቱ  ግጭቶች ባለፉት የዘር ተኮር ፖለቲካ  ድምር ውጤቶች ናቸው ያሉት አቶ ኦባንግ፣አሁኑኑ እልባት ካላበጀንላቸው የአገሪቱን ህልውና የሚያጠፉ ተጨባጭ ማሳያዎች መሆናቸውን ገልጸዋል።

በአገሪቱ የተጀመረው የለውጥ ጉዞ እንዲደናቀፍ ሀብታቸውን፤ እውቀታቸውንና አደረጃጀታቸውን ተጠቅመው አገርንና ሕዝብን በማተራመስ  የተጠመዱ አካላትን ወጣቱ ነቅቶ ሌላውንም ኅብረተሰብ የማንቃት አገራዊ ኃላፊነት እንዳለበትም የሰብዓዊ መብት ተሟጋቹ ተናግረዋል።

በመሆኑም ወጣቱ በሚያጋጥሙት ጥቃቅን ችግሮች  ሳቢያ በስሜታዊነት ወደግጭት በመግባት የሴራ ፖለቲከኞች መጠቀሚያ እንዳይሆን በሰከነ መንገድ መንቀሳቀስ እንዲሁም በግልጽ መነጋገርና መወያየት መጀመር አለበት ብለዋል።

የዩኒቨርሲቲዉ የአራተኛ ዓመት ምህንድስና ተማሪ  መሐመድ ኢድሪስ ወጣቱ አገራዊ ኃላፊነቱን ዘንግቶ ባልተረጋገጠ መረጃ በስሜት ተነስቶ ወደ ግጭት የሚገባበት ሁኔታን እንዲቀይር ጠይቋል።

ከማናቸውም አካላት የሚደርሱትን መረጃዎች በማጣራት እውነትም ከሆነ በስሜት ሳይሆን በሰከነ መንገድ በውይይት መፍታት ያስፈልጋል ብሏል።

ሌላው የዩኒቨርሲቲዉ የአራተኛ ዓመት ምህንድስና ተማሪ ጌታነህ ተስፋው በማህበራዊ ሚዲያም  ሆነ አክቲቪስቶች የሚያሰራጯቸውን ሚዛናዊነት የጎደላቸዉ መረጃ አጥርቶ መጠቀም እንደሚያስፈልግ አመልክቶ፣መረጃውን የሚያስተላልፉ ተቋማት ላይ እርምጃ ሊወሰድ እንደሚገባም አመልክቷል።

ምንጭ፦ ኢዜአ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update በአዳማ ኢንዱስትሪ ፓርክ የተመረቱ አምስት ሺህ ካርቶን የዋና አልባሳት ለመጀመሪያ ጊዜ ለውጭ ገበያ ቀረቡ። የቻይናው አንቴክስ ግሩፕስ ጨርቃጨርቅ አምራች ኩባንያ ምርቱን ትላንት በፓርኩ ውስጥ ያስተዋወቀበትን ሥነ ሥርዓት አካሂዷል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ኮንጎ ውስጥ ውጥረት ነግሷል‼️

የዴሞክራቲክ ሪፓብሊክ ኮንጎን ምርጫ ተከትሎ #ውጥረት ነገሷል፡፡ የመንግስት ባለስለጣናት ለመገናኛ ብዙሃን እንደገለጹት ማይ ማይ የተባለው ቡድን ተወጊዎች በምስራቅ ዴሞክራቲክ ሪፖፕሊክ ኮንጎ በሰሜን ኪቮ ግዛት ሉበርቶ ከተማ የድምፅ መስጫ ጣቢያዎችን በመውረር መራጮች ድምጽ እንዲቀይሩ አስገድደዋል፡፡

በደቡብ ኮቮ ዋሉንጉ በተባለው አካባበቢ ደግሞ ምርጫ ተጭበርብሯል ከሚል ጉዳይ ጋር በተያያዘ በተከሰተ ግጭት የፖሊስ አባላትና ንጹሃን ዜጎች ህይዎት ማለፉም ነው የተገለጸው፡፡

በትናትናው ዕለት በሀገሪቱ በተካሄደው በዚህ ምርጫ ጠዋት ላይ ከፍተኛ ዝናብ መጣሉን ተከትሎ የመራጮች ድምጽ አሰጣጥ ሂደት የተቀዛቀዘ የነበረ ሲሆን÷ ከሰዓት በኋላ በአንዳንድ አካባቢዎች ረጃጅም የመራጮች ሰልፎች ታይተዋል ተብሏል፡፡

በኬኒሻሳ በበርካታ የምርጫ ጣቢዎች በድምፅ መስጫ ማሽን እጥረት የድምጽ አሰጣጥ ሂደቱ መዘግየቱን ዘገባው ያመለክታል፡፡

በመዲናዋ ቡምቡ ከተማ አስተዳደር ከደህንነት ስጋት ጋር በተያያዘ መራጮች አካባቢቸውን ለቀው የወጡ ሲሆን÷ ከ12 የድምፅ መስጫ ጣቢዎች 10 ብቻ መከፈታቸውም ተነገሯል፡፡

በርካታ መራጮችም ከድምጽ መስጫ መዘገብ ላይ ሥማቸውን በማጣታቸውም ድምጽ ሳይሰጡ መመለሳቸውን ለመገናኛ ብዙሃን ተናግረዋል፡፡

እንደ አውሮፓዊኑ አቆጣጠር ከ2016 ጀምሮ እየተራዘመ በመጣው በዚህ ምርጫ ከ46 ሚሊየን በላይ መረጮች ድምጽ ለመስጠት የተመዘገቡ ሲሆን÷ ከተመዝጋቢወዎቹ መካከል 15 በመቶ ያህሉ በመዲናዋ ኬኒሻሳ እንሚገኙ ተጠቁሟል፡፡

ይሁን እንጂ 1ነጥብ2 ሚሊን ያህል ድምፅ ሰጪዎች የተመዘገቡበትና ሶስት ብርቱ የተፎካካሪ ተወዳዳሪዎች በሚገኙባቸው አካባቢዎች ምርጫው ያለመካሄዱ ነው የተገለጸው፡፡

ምንጭ፡- አል ጀዚራ(በfbc)
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ጥቆማ‼️

#ሱሉልታ አካባቢ ላለፉት ሁለት እና ሶስት ቀናት የኔትዎርክ ችግር እንዳለ ነዋሪዎች ጠቁመዋል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ቅሬታ‼️

"የወረቀት ዋጋ ንረት ከ60- 216 ብር ከፍ ብሏል። ለዚህም አስመጪዎች እና ነጋዴዎች በstore በማከማቸት ዋጋው እንዲንር አድርገውትል. ይህንን የዋጋ ንረት መንግስት እንዲመለከተው ጥሪ እንምቀርባለን።"

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update የአዳማ ኢንደስትሪያል ፓርኩ፣ አንቴክስ ኩባንያ 100,000 የአሜሪካ ዶላር የሚያወጡ የጨርቃ ጨርቅና አልባሳት ምርቱን ለውጭ ገበያ መላኩን ማየት አበረታች ነው ሲሉ የቀድሞው የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮምሽን ኮምሽነር አቶ ፍጹም አረጋ በትዊተር ገፃቸው አስፍረዋል፡፡ ኩባንያው ማሽነሪዎችን ለመግጠም እና 1500 ሰራተኞችን ቀጥሮ ለማሰልጠን የፈጀበት ጊዜ ሦስት ወራት ብቻ መሆኑን ምሳሌ የሚሆን ነው ያሉት የቀድሞው ኮምሽነር እያሽቆለቀለ ያለውን የሐገሪቱን የወጪ ንግድ እንዲያንሰራራ ለማድረግ መጣር ይገባል ብለዋል።

Via~Sheger 102.1
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update በራይድ ታክሲ ዙሪያ በተደረገ የ3 ሰአት ዝግ ስብሰባ ምክትል ከንቲባው ታከለ ኡማ ራይድ ህገወጥነት አልታየኝም ይስራ ቢሉም የከተማው ትራንፓርት ቢሮ ራይድ ህገ ወጥ ነው ብሏል።

ምንጭ፦ካፒታል ጋዜጣ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት‼️

የግል ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት የሚያነሷቸውን ችግሮች መቅረፍ የሚያስችል አሰራር መዘርጋቱን የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር አስታወቀ።

ሚኒስቴሩ በዛሬው እለት ከግል ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ጋር ምክክር አድርጓል።

በመድረኩ ላይ በግል ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት የመማር ማስተማር ሂደት ላይ የሚታዩ ችግሮች ላይ ውይይት ተደርጓል።

ተወዳዳሪና ብቁ ዜጋን ከማፍራት አንጻር፣ ተማሪዎችን ሳያስመርቁ መጥፋት፣ ብቁ መምህራንን አለመቅጠር እና መረጃን ከመስጠት አንጻር ክፍተት እንደሚስተዋልባቸው ሚኒስቴሩ ገልጿል።

የግል ከፍተኛ የትምህርት ተቋማቱ በበኩላቸው በመንግስት በኩል የሚደረገው ድጋፍና ክትትል አናሳ መሆኑን አንስተዋል።
የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስትሯ ዶክተር ሂሩት ወልደማርያም አሁን ላይ በግል ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት በኩል የሚታዩ ችግሮችን መፍታት የሚያስችል አሰራር መዘርጋቱን ተናግረዋል።

ለዚህም በተቋማቱ የሚስተዋሉ የአሰራር ክፍተቶችንና የህግ ጥሰቶችን መቆጣጠር የሚያስችል የህግ ማዕቀፍ መዘጋጀቱን ጠቅሰዋል።

ከዚህ ባለፈም በሁለቱ አካላት መካከል የሚስተዋሉ ክፍተቶችን ለማስተካከል የሚያግዝ የመማክርት ጉባኤ መቋቋሙን ገልጸዋል።

ጉባኤው የግል ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት እና ሚኒስቴሩ ተቀራርበው እንዲሰሩ የሚያግዝ ነው ተብሏል።
ከዚህ ባለፈም በመንግስት በኩል ለግል ከፍተኛ የትምህርት ተቋማቱ አስፈላጊውን ድጋፍና ክትትል ይደረጋልም ነው ያሉት።

ምንጭ፦ ፋና ብሮድካስቲንግ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
የኣፋልጉኝ ማስታወቅያ🔝

እኔ ቢንያም ኤልያስ ኤጉ የተባልኩ የትውልድ ቦታ እና እድገቴ ኣስመራ፡ኤርትራ ቢሆንም ኣባቴ ግን በደቡብ ክልል ጌዴኦ ዞን ዲላ ከተማ ተወላጅ ነው በ1991 ከተማረኩ መካከል ከኣስመራ ከሙሉ ቤተሰብ ጋ ሆነን ሸኝተነው ነበር ከዛ ቡሃላ ግን ላገኘው ብሞክርም ላገኘው ግን ኣልቻልኩም፡፡ የ ኣባቴ እናት ስማቸው ኣልፋንሶ ይባላል ፡፡ የ ኣባቴ ጋደኞች ኣቶ በቀለ ብሩ ሊቦ እና ኣቶ ኣሰሙ ገቢቦ ይባላሉ፡፡ ኣቶ ኣሰሙ ገቢቦ በወቅቱ የዱቀት ፋብሪካ ነበራቸው ፡፡ የ 8ተኛ ክፍል ምስክር ወረቀት እንደሚያሳየው ኣባቴ የተማረበት ት/ቤት ስም (princess tenagn work) ሃይሳ ቄጣ ገበሬ ማህበር እንደ ሚባል ከእናቴ ማወቅ ችያለው፡፡
0914379792
Forwarded from Tsegab W.
የምስራች🎊 ከረድኤት አስመጪ!!

Konica minolta 451/550/650 452/552/ 454 Riso rz 200 Canon color c2220i/c2025i/c2020i/ ምርቶችን በተመጣጣኝ ዋጋ ያገኛሉ። በጀምላ ለመግዛት የምትፈልጉ 10% ቅናሽ እናደርጋለን። የምናቀርባቸውን ምርቶች ሲገዙ በተመጣጣ ዋጋ ከሙሉ የጥገና ዋስትና ጋር እናስረክባለን!!

ይምጡና ይጎብኙን አድራሻችን፦ አዲስ አበባ ሜክሲኮ #ኬኬ_ህንፃ ግራውንድ ስር እንገኛለን

ስልክ፦
+251904141404
+251902477474
Forwarded from TIKVAH-ETHIOPIA (Tsegab Wolde)
የምስራች ለ ሳሙና አምራቾች!!

ለምታመርቱ ሳሙና የሽቶ ግብአት እጥረት አለብዎት? እንግጻውስ ይህን ችግር የሚቀርፍ የሳሙና ሽቶ ግብአት ህንጽ ከሚገኘው ሶናሮም በጥራት የተመረተ ግብአት በተለያዩ መአዛዎች አስመጥተናል:: ግብአቶቹ በከፍተኛ ጥንቃቄ እና ጥራት ስለተመረቱ ለፈሳሸም ሆነ ለደረቅ ሳሙና በአስተማማኝ ሁኔታ መጠቀም ይችላል:: ግብአቶቹን መግዛት ለምትፈልጉ በአድራሻችን
በ ሞባይል :- 0911240726 ወይም
በ ቢሮ:- +251 11 558 5384
ኢሜል :-www.akmase.com ማግኘት ትችላላችሁ ::
ከ አክማስ አስመጪና ላኪ::