#update ጠ/ሚ ዶ/ር ዐብይ አህመድ⬇️
በኢትዮጵያ እና ኤርትራ ድንበር ላይ የሰፈረው የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት ከዛሬ ጀምሮ ወደ #ጦር ሰፈሩ መሰብሰብ እንደሚጀምር ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ አስታወቁ።
በሁለቱ ሀገራት ድንበር አካባቢ ያለው ውጥረት የተሞላበት የጦርነት ስሜት ከአሁን በኋላ “በከፍተኛ ሁኔታ” #እንደሚቀንስም ተናግረዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ ይህን የተናገሩት የኢትዮጵያን የዘመን መለወጫ በዓል ምክንያት በማድረግ በቡሬ እና በዛላምበሳ ግንባሮች ያሉ የኢትዮጵያ እና የኤርትራ የመከላከያ ሰራዊት አባላትን ጎብኝተው ከተመለሱ በኋላ በቦሌ አየር ማረፊያ በሰጡት መግለጫ ነው።
“የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት ከዛሬ ጀምሮ ድንበር አካባቢ ላይ #ውጥረት የነበረውን #የጦርነት ስሜት በከፍተኛ ደረጃ ቀንሶ ወደ ካምፕ በመሰብሰብ የሚያገግምበት፣ የሚሰለጥንበት፣ ራሱን የሚያበቃበት ሁኔታ ይፈጠራል” ብለዋል ጠቅላይ ሚኒስትሩ ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ።
ምንጭ፦ Dw Amharic
@tsegabwolde @tikvahethiopia

#update አዲስ አበባ⬇️
ቦሌ መንገድ በሚገኘው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት በሚኖሩበት ሕንፃ አካባቢ መስከረም 24 ቀን 2011 ዓ.ም. ሌሊት በነበረ ተኩስ የአራት ሰዎች ሕይወት አለፈ፡፡ የፓርላማ አባላቱ በሚኖሩበት ሕንፃ በጥበቃ ላይ የነበረ አንድ የፌዴራል ፖሊስ ባልታወቀ ምክንያት ከሌሊቱ 7፡00 ሰዓት አካባቢ ጀምሮ በከፈተው ተኩስ የሦስት ሰዎችን ሕይወት ሲያጠፋ፣ ሌሎች የፀጥታ አስከባሪዎች #ጥቃቱን በፈጸመው የፖሊስ አባል ላይ #ዕምርጃ በመውሰድ የአባሉ ሕይወት ማለፉ ታውቋል፡፡
የፌዴራል ፖሊስ አባሉ የሦስቱን ሰዎች ሕይወት ከማጥፋቱ ባሻገር፣ አሥር ያህል የፌዴራል ፖሊስ አባላት ላይ ጉዳት አድርሷል፡፡ ጉዳት የደረሰባቸው የፖሊስ አባላትም በፌዴራል ፖሊስ አጠቃላይ ሆስፒታል ሕክምና እያገኙ መሆኑ ታውቋል፡፡
ጥቃቱን የፈጸመው የፌዴራል ፖሊስ አባል ሌሊቱን ሙሉ በተለያዩ አቅጣጫዎች #ሲተኩስ ስለነበር፣ አካባቢው #ውጥረት ነግሶበት ማደሩ ታውቋል፡፡ በጥቃቱ ምክንያትም የቦሌ ዋና መንገድ እስከ ማለዳው 3፡00 ሰዓት ድረስ ተዘግቶ ቆይቷል፡፡
ምንጭ፦ ሪፖርተር

ኮንጎ ውስጥ ውጥረት ነግሷል‼️
የዴሞክራቲክ ሪፓብሊክ ኮንጎን ምርጫ ተከትሎ #ውጥረት ነገሷል፡፡ የመንግስት ባለስለጣናት ለመገናኛ ብዙሃን እንደገለጹት ማይ ማይ የተባለው ቡድን ተወጊዎች በምስራቅ ዴሞክራቲክ ሪፖፕሊክ ኮንጎ በሰሜን ኪቮ ግዛት ሉበርቶ ከተማ የድምፅ መስጫ ጣቢያዎችን በመውረር መራጮች ድምጽ እንዲቀይሩ አስገድደዋል፡፡
በደቡብ ኮቮ ዋሉንጉ በተባለው አካባበቢ ደግሞ ምርጫ ተጭበርብሯል ከሚል ጉዳይ ጋር በተያያዘ በተከሰተ ግጭት የፖሊስ አባላትና ንጹሃን ዜጎች ህይዎት ማለፉም ነው የተገለጸው፡፡
በትናትናው ዕለት በሀገሪቱ በተካሄደው በዚህ ምርጫ ጠዋት ላይ ከፍተኛ ዝናብ መጣሉን ተከትሎ የመራጮች ድምጽ አሰጣጥ ሂደት የተቀዛቀዘ የነበረ ሲሆን÷ ከሰዓት በኋላ በአንዳንድ አካባቢዎች ረጃጅም የመራጮች ሰልፎች ታይተዋል ተብሏል፡፡
በኬኒሻሳ በበርካታ የምርጫ ጣቢዎች በድምፅ መስጫ ማሽን እጥረት የድምጽ አሰጣጥ ሂደቱ መዘግየቱን ዘገባው ያመለክታል፡፡
በመዲናዋ ቡምቡ ከተማ አስተዳደር ከደህንነት ስጋት ጋር በተያያዘ መራጮች አካባቢቸውን ለቀው የወጡ ሲሆን÷ ከ12 የድምፅ መስጫ ጣቢዎች 10 ብቻ መከፈታቸውም ተነገሯል፡፡
በርካታ መራጮችም ከድምጽ መስጫ መዘገብ ላይ ሥማቸውን በማጣታቸውም ድምጽ ሳይሰጡ መመለሳቸውን ለመገናኛ ብዙሃን ተናግረዋል፡፡
እንደ አውሮፓዊኑ አቆጣጠር ከ2016 ጀምሮ እየተራዘመ በመጣው በዚህ ምርጫ ከ46 ሚሊየን በላይ መረጮች ድምጽ ለመስጠት የተመዘገቡ ሲሆን÷ ከተመዝጋቢወዎቹ መካከል 15 በመቶ ያህሉ በመዲናዋ ኬኒሻሳ እንሚገኙ ተጠቁሟል፡፡
ይሁን እንጂ 1ነጥብ2 ሚሊን ያህል ድምፅ ሰጪዎች የተመዘገቡበትና ሶስት ብርቱ የተፎካካሪ ተወዳዳሪዎች በሚገኙባቸው አካባቢዎች ምርጫው ያለመካሄዱ ነው የተገለጸው፡፡
ምንጭ፡- አል ጀዚራ(በfbc)

የዛሬ ውሎ(ድሬዳዋ በፎቶ)🔝
ዛሬ #ውጥረት_ነግሶባት የዋለችው #ድሬዳዋ ከተማን ከላይ ባሉት ጥቂት ፎቶዎች መመልከት ትችላላችሁ።