TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.8K photos
1.44K videos
207 files
3.99K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
ቴዲ ማንጁስ‼️

ፍርድ ቤቱ አቶ #ቴዎድሮስ_አዲሱ (ቴዲ ማንጁስ) በቃሊቲ ማረሚያ ቤት እንዲቆዩ ወሰነ። ተከሳሹ ከሱማሌ ክልል ትምህርት ቢሮ በገባው ውል መሰረት ለመጀመሪያና ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተማሪዎች 578,274 የሚሆኑ መማርያ መጻህፍትን በ18,990,000 ብር አሳትሞ ለማቅረብ የግዥ ውል የገባ ቢሆንም #ስራው_ሳይሰራ ከቀድሞው ከክልሉ ትምህርት ቢሮ ኃላፊ፣ ከኒያላ ኢንሹራንስ አክሲዮን ማሕበር ጅግጅጋ ቅርንጫፍ ሥራ አስኪያጅ እና ከቀድሞው ከክልሉ ትምሕርት ቢሮ የፋይናንስና ሎጅስቲክስ የሥራ ሂደት ኃላፊ ጋር በመመሳጠር 15,306,803 ብር እንዲከፈለው በማድረግ በመንግስትና በሕዝብ ላይ ከፍተኛ ጉዳት የደረሰ መሆኑን በትናትናው ችሎት መዘገቡ ይታወሳል፡፡

ሆኖም ግን ተከሳሽ በመጀመሪያ ክሴ ላይ ከፍተኛ ፕሮፓጋንዳ ስለተሰራብኝ #ለድህንነቴ በሚያሰጋ ሁኔታ ልታሰር አይገባም በማለት ለፍርድ ቤቱ ትናንት አመልክቶ ነበር፡፡ ፍርድ ቤቱም የቀረበለትን የመብት ጥያቄ ግምት ውስጥ በማስገባት ተከሳሽ የቀረበባቸውን ክስ ተረጋግተው መከታተል ይችሉ ዘንድ ቃሊቲ ማረሚያ ቤት እንዲቆዩ ውሳኔ አስተላልፏል፡፡

ዐቃቤ ህግም በዚሁ የክስ መዝገብ ያልተያዙትን 1ኛ፣3ኛ እና 4ኛ ተከሳሾች ፖሊስ በአድራሻቸው እንዲያፈላግና ጉዳያቸውን ቀርበው እንዲከታተሉ ትዕዛዝ እንዲሰጥለት ፍርድ ቤቱን ጠይቋል፡፡

ፍርድ ቤቱም ያልተያዙትን ተከሳሾች ተይዘው እንዲቀርቡ ለመጠባበቅ ለመጋቢት 20/2011 ዓ.ም ቀጠሮ ይዟል፡፡

ሁለተኛ #ተከሰሽ የሆኑት ቴዎድሮስ አዲሱም(ቴዲ ማንጁስ) የክስ መቃወሚያቸውን ይዘው እንዲቀርቡ ለየካቲት 29/2011 ዓ.ም ተለዋጭ ቀጠሮ ተሰጥቷል ሲል EBC ዘግቧል።

ምንጭ፦ ebc
@tsegabwolde @tikvahethiopia