TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.6K photos
1.43K videos
206 files
3.96K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#update ምክትል ከንቲባ ኢንጅነር #ታከለ_ኡማ አገልግሎት መስጠት ያቆመውን የሰንዳፋ ደረቅ ቆሻሻ ማስወገጃ ፕሮጀክትን ጎብኝተዋል። ፕሮጀክቱ ከ1 ቢሊዮን ብር በላይ ወጪ የተደረገበት ሲሆን፥ ለስምንት ወራት ብቻ አገልግሎት ከሰጠ በኋላ ከሁለት ዓመታት በፊት ስራ ማቆሙ የሚታወስ ነው፡፡

ምንጭ፦ fbc
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ🔝

በኢፌዲሪ ሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር የቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ አስተዳደር ካዉንስል የሰላማዊ መማር ማስተማር ማረጋገጫና መዝለቂያ ልዩ ዕቅድ ላይ ዉይይት በማድረግና ዉሳኔዎችን በማሳለፍ ተጠናቋል። ከትላንትናዉ በማስቀጠል ዛሬም ከቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ ምክር ቤት አባላት ጋር በመወያየት የተለያዩ አስተያዬቶችን በመቀበል በዉሳኔ ሃሳብ ዙሪያ የጋራ ስምምነት ላይ ተደርሷል።

ምንጭ፦ የቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ማስታወቂያ‼️ከቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ ለቃችሁ የወጣችሁ ተማሪዎች በሙሉ የዳግም ምዝገባ ጊዜ ጥር 2 እና 3 መሆኑን አውቃችሁ ከወዲሁ እንድትዘጋጁ!!

©በቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ የTIKVAH-ETH ቤተሰብ አባላት
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#Breaking የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ለኢትዮ-ቡና እና ቅዱስ ጊዮርጊስ ክለቦች የልምምድ መስርያ ቦታ ሊሰጥ መሆኑን አስታወቀ፡፡ ክለቦቹ የልምምድ መስሪያ ቦታ ችግር እንዳለባቸው ለአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ሲገልፁ መቆታቸውን የከንቲባው ጽ/ቤት ጠቅሷል፡፡ ጥያቄው አግባብነት ያለው በመሆኑ አስተዳደሩ ለሁለቱም ክለቦች የልምምድ መስርያ ቦታ ለመስጠት መወሰኑን ጽ/ቤቱ አስታውቋል፡፡ በውሳኔው መሰረት አስፈላጊው ድጋፍ ለማድረግ ዝግጁ መሆኑንም ጽ/ቤቱ ገልጿል፡፡

Via~etv
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#Breaking የሶማልያ ብሄራዊ የጦር ኃይል በዛሬው ዕለት ሁለት የውጭ ሀገር ዜግነት ያላቸውን ጨምሮ 30 የአልሻባብ ታጣቂዎችን መግደሉን ባለስልጣናት አስታውቀዋል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
በተማሪዎች ላይ እርምጃ ተወሰደ

የደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ በአማራና በኦሮሞ ተማሪዎች መካከል #ግጭት እንዲነሳ ያስተባበሩ ተማሪዎችን ለ1 አመት ከትምህርት እንዲታገዱ መወሰኑን አስታወቀ፡፡

የደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ እንዳስታወቀው በዩንቨርሲቲው ውስጥ ከሁለት ሳምንት በፊት በተማሪዎች መካከል በተፈጠረ አለመግባባት ግጭት ተከስቶ ሁለት ቀናት የመማር ማስተማር ሂደቱ መቋረጡን ገልጸው የሌሎችን አላማ ለማሳካት ተልእኮ ወስደው በአማራና ኦሮሞ ተማሪዎች መካከል ግጭት እንዲነሳ ያደረጉ 10 ተማሪዎች ለአንድ አመት ከትምህርት እንዲታገዱ መወሰኑን ገልጸዋል፡፡

በዩኒቨርሲቲው ግጭት በተከሰተበት ወቅት የሃይማኖት አባቶችና የሃገር ሽማግሌዎች ጨምሮ በአካባቢውና በዩኒቨርሲቲው ማህበረሰብ እርቀ ሰላም ለመፍጠር በተደረጉ ተከታታይ ውይይቶች ለብጥብጡ መነሳት ጉልህ ድርሻ የነበራቸው ተማሪዎች ተለይተው ተመጣጣኝ እና አስተማሪ እርምጃ ይወሰድባቸው በሚል የአካባቢው ነዋሪዎችና የዩኒቨርሲቲው ማህበረሰብ ያነሱትን ተደጋጋሚ ሀሳብ መነሻ በማድረግ መሆኑን ገልጿል፡፡

ይህንን መሰረት በማድረግ በዩንቨርስቲው በነበረው ግጭት አነሳሽ እና ባለቤት በመሆን ግጭቱን በመምራት ያስተባበሩ ተማሪዎችን በዩኒቨርሲቲው ህግ መሰረት ኮሚቴ በማዋቀርና በማጣራት 24 ተማሪዎችን በመለየት 10ሩ ለአንድ አመት ከትምህርት እንዲታገዱ፣ 5ቱ ከባድ የፁሑፍ ማስጠንቀቂያ፣ 9ተማሪዎች ደግሞ የመጨረሻ የፅሁፍ ማስጠንቀቂያ ተሰጥቷቸው ትምህርታቸውን እንዲከታተሉ በዩንቨርስቲው ሴኔት ውሳኔ አስተላልፏል።

አንድ አመት የተቀጡት ተማሪዎች ያጠፉት ጥፋት በዩኒቨርሲቲው ህግ መሰረት እድሜ ልክ ከትምህርት የሚያሰናብትና በማስጠንቀቂያ የታለፉትም ከሁለት ዓመት ያላነሰ ቅጣት የሚያስቀጣ ቢሆንም የሚከተሉት የቅጣት ማቅለያ ምክንያቶችን፦

1. ወቅታዊ ሀገራዊ ሁኔታው ገፊ ምክንያት ስለሆነ
2. ተማሪዎች ወጣቶች በመሆናቸው ሌሎች ኃይሎች በቀላሉ ሊገፋፏቸው የሚችሉበት ሁኔታ ከፍተኛ ስለሆነ
3. ዩኒቨርሲቲው እርምጃውን ሲወስድ ዓላማው ማስተማር ብቻ ስለሆነ
4. ተፈጥሮ የነበረውን ግጭት በማብረዱና የነበረውን ሁኔታ በመመለሱ ረገድ ተማሪዎች ራሳቸው ከፍተኛ ድርሻ የነበራቸው በመሆኑና ሌሎችን ጉዳዮች ታሳቢ በማድረግ እንደሆነ ገልጾ የተቀጡ ተማሪዎች ቅጣታቸውን ጨርሰው ሲመለሱ መልካም ስነ ምግባር ያላቸው መሆኑን የሚገልጽ ማስረጃ ከሚኖሩበት ቀበሌ ማምጣት እንደሚጠበቅባቸው ዩኒቨርሲቲው አስታውቋል፡፡

በሌላ በኩል በዩኒቨርሲቲው አጥፊ የሆኑ ተማሪዎች በጥፋታቸው መሰረት ባሉበት ዩኒቨርሲቲ ተገቢውን እርምት እንዲወስዱ ማድረግና ከሚኖሩበት ማህበረሰብ ጋር ተመሳስለው እና ተቻችለው እንዲኖሩ ማስተማር ሲገባ ወደ ሌላ ዩኒቨርሲቲ እንዲዛወሩ ማድረግ መርህ አልባ አሰራር ከመሆኑ ባሻገር ለዩኒቨርሲቲውም ሆነ ለሀገሪቱ መፍትሄ ነው ብሎ ዩኒቨርሲቲው እንደማያምን ገልጿል፡፡

ይሁን እንጅ ሰሞኑን ደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ ከሌላ ቦታ የዝውውር ደብዳቤ ለአንድ ተማሪ ተጽፎለት አልቀበለው አለ በሚል አንዳንድ የማህበራዊ ሚዲያ ተጠቃሚዎች መነሻ ምክንያቱን ሳይረዱ የሚሰጡት ትችት አዘል አስተያየት ትክክል ነው ብሎ አያምንም ብሏል፡፡ ለእያንዳንዱ ችግር በስሜት የምንወስደው የመፍትሄ አማራጭ በዩኒቨርሲቲዎች ያለውን የሰላማዊ መማር-ማስተማር እጦት ይበልጥ እያወሳሰበውና በሀገሪቱ የታየውን ተስፋ ለማጨለም ሌት ተቀን ለሚሰሩ አካላት ተጨማሪ ኃይል እንዳንሆናቸው ተገቢውን ጥንቃቄ ማድረግና ሁሉን ነገር በሰከነ መንገድ የማየት ልምድ ማዳበር አለብን ብሏል የሆነው ሆኖ ዩኒቨርሲቲው ተማሪውን ተቀብሎ ያስተናገደው መሆኑን መግለጽ እንወዳለን፡፡

የደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
"በፍቅር ልቃችሁ ተገኙ! በመደማመጥ ልቃችሁ ተገኙ! ሰውን በመጥላት ሳይሆን ሰውን በመውደድ በልጣችሁ ተገኙ።" ኦቦ #በቀለ_ገርባ

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update በደብረ ብርሃን ከተማ ኢትዮጵያ ኢዱኬሽን ኢኒሸቲቭ ኢን ኮርፖሬሽን በ10 ሚሊዮን ዶላር ወጪ የ “ኃይሌ ማናስ አካዳሚ አዳሪ ትምህርት ቤት” ግንባታን አስጀምሯል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ሰማያዊ ፓርቲ‼️

ሰማያዊ ፓርቲ ከኢዴፓ፣ አርበኞች ግንቦት ሰባት ንቅናቄ እና ከቀድሞው አንድነት ፓርቲዎች ጋር ለመዋሃድ መስማማቱ ተገለፀ።

ሰማያዊ ፓርቲ በትላንትናው ዕለት ባካሄደው ጠቅላላ ጉባኤ ከሶስቱ ፓርቲዎች ጋር ለመዋሃድ በሙሉ ድምፅ መወሰኑን የፓርቲው ሊቀመንበር አቶ #የሽዋስ_አሰፋ ለFBC ተናግረዋል።

"ትልቅ አገራዊ ፓርቲ ለኢትዮጵያ አንድነት" በሚል መሪ ቃል በተካሄደው ጠቅላላ ጉባኤ የኢህአዴግ፣ አርበኞች ግንቦት ሰባት፣ ኢዴፓ፣ መድረክ፣ አረና፣ የቀድሞው አንድነት እና ሌሎች ፓርቲዎች ተወካዮች በክብር እንግድነት መታደማቸው ተገልጿል።

ፓርቲው በጠቅላላ ጉባኤው ከሶስቱ ፓርቲዎች ጋር ብቻ ሳይሆን ከሌሎች በአላማ ከሚመሳሰሉ ፓርቲዎች ጋር ተዋህዶ ትልቅ አገራዊ ፓርቲ ለመመስረት መወሰኑን ሊቀመንበሩ ተናግረዋል።

በቀጣይም ሰማያዊ፣ ኢዴፓ፣ አርበኞች ግንቦት ሰባት እና የቀድሞው አንድነት ከወረዳ ጀምሮ መዋሃድ የሚጀምሩ መሆኑ ነው የተገለፀው።

የአራቱ ፓርቲዎች ጥምር አገራዊ ፓርቲም በአዲስ ስያሜ እስከ መጋቢት 30 ይፋ የሚደረግ መሆኑን ጠቁመዋል።

ሰማያዊ ፓርቲ በጠቅላላ ጉባኤው ባሳለፈው ውሳኔ እና በቀጣይ ስራዎቹ ዙሪያ ዛሬ መግለጫ የሚሠጥ መሆኑን አቶ የሽዋስ ተናግረዋል።

ምንጭ፦ ፋና ብሮድካስቲንግ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
FM_20181229_224505.ogg
8.5 MB
አዲስ አበባ‼️

የፍቅረኛውን #ብልት በክር የሰፋው ኢትዮጵያዊ...እጅግ በጣም ለመስማት የሚከብድ #ዘግናኝ ድርጊት አዲስ አበባ አስተናገደች!!

ምንጭ፦ ኢትዮፒካሊንክ የራድዮ ፕሮግራም(FM 98.1)
@tsegabwolde @tikvahethiopia
Forwarded from TIKVAH-ETHIOPIA (Tsegab Wolde)
ማስታወቂያ‼️ከቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ ለቃችሁ የወጣችሁ ተማሪዎች በሙሉ የዳግም ምዝገባ ጊዜ ጥር 2 እና 3 መሆኑን አውቃችሁ ከወዲሁ እንድትዘጋጁ!!

©በቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ የTIKVAH-ETH ቤተሰብ አባላት
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update ማሻሻያ ማድረጉን ተከትሎ ተከራዮች የበተለያየ መንገድ #ተቃውሞ በማሰማት ላይ ይገኛሉ። መኢአድ የተባለው የፖለቲካ ፓርቲም ጭማሪውን በመቃወም መግለጫ አውጥቷል። የፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ ረሻድ ከማል ለበርካታ አመታት ከገቢያ ዋጋ በታች በመክፈል ተጠቃሚ ነበሩ በማለት የተከራዮችን ተቃውሞ እንደማይቀበሉት አስታውቀዋል። ፒያሳ ባቅላባ ቤት 6 ሺ ብር፤ ጆሊ ባር 5 ሺ ብር፤ ቱሪስት ሆቴል 13 ሺ ብር፤ ሮሚና ካፌ 3 ሺ ብር፡ ሎመባርዲያ 1777ሺ ብር፤ ሃራምቤ ሆቴል 35 ብር፤ ብቻ ሲከፍሉ ቆይተዋል በማለት ሀላፊው ምሳሌ ጠቅሰዋል።

Via~ELU
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ሰበር ዜና‼️

ጉዞ ዓድዋ 6 ተጀመረ!! ታሪካዊቷ የሐረር ከተማ የዘንድሮ ጉዞ መነሻ ተደርጋ ተመርጣለች።

"ፍቅር ለኢትዮጵያ" የሚል መርሕ የያዘው የዘንድሮ የእግር ጉዞ መነሻውን ከሀረር ከተማ በማድረግ ጥር 7 ቀን 2011 ዓ.ም ከአዲስ አበባ የሚነሱ ተጓዦችን በመቀላቀል የካቲት 23 ቀን 2011 ዓ.ም. በታሪካዊቷ ዓድዋ ከተማ ይጠናቀቃል።

በትናትናው ምሽት በድሬዳዋ ከተማ በተካሔደው የመሸኛ ስነሥርዓት ላይ የተገኙት የድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አቶ ኢብራሂም ኡስማን ባደረጉት ንግግር "ዓድዋ የመላው ኢትዮጵያዊያን ህብረት ያታየበት ሁላችንም የምንኮራበት ድላችን መሆኑን ጠቅሰው፤ ይህንን ድል ለመዘከር በየአመቱ የሚዘጋጀውን የጉዞ ዓድዋ እንቅስቃሴ የከተማ አስተዳደሩ ቅድሚያ ሰጥቶ እንደሚያግዝ አረጋግጠው የዘንድሮው 123ኛ የዓድዋ ድል በዓል አከባበር መጀመሩን በይፋ አብስረው፤ ለተጓዦች መልካም መንገድ ተመኝተዋል።

በታላቁ የዓድዋ ጦርነት ወቅት የምስራቅ ኢትዮጵያን ጦር የመሩት የቀዳሚው ጦር አዝማች ልዑል ራስ መኮንን ከተነሱበት የሐረር ከተማ በ5 ተጓዦች የተጀመረው የዘንድሮው ጉዞ ዓድዋ በተለያዩ ደማቅ ሥነስርዓቶች ለመካሔድ በዛሬው እለት ታህሳስ 21 ቀን 2011 ዓ.ም. ተጀምሯል።
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ ኢንጂነር ታከለ ኡማ ለጉዞ ዓድዋ አዘጋጆች በስልክ እንዳረጋገጡት የከተማ አስተዳደሩ ከሀረር የተነሱ ተጓዦችን ተቀብሎ በመሸኘት እና ከአዲስ አበባ የሚነሱ ተጓዦችን አሰፈላጊውን ስንቅ አሟልቶ በመሸኘት የከተማ አስተዳደሩ አጋርነቱን ያሳያል።

፨፨፨
የፍቅር ዘመቻው ሠላምን እና አብሮነትን ሰንቆ በዓድዋ ተራሮች አናት ላይ የካቲት 23 ቀን በድል ይጠናቀቃል።
የጉዞ ዓድዋ አስተባባሪዎች
መሐመድ ካሳ
ያሬድ ሹመቴ
#ፍቅር_ለኢትዮጵያ
#ኢትዮጵያዊነት_ይለምልም !!
#ጉዞ_ዓድዋ_6
#ከሐረር_አዲስ_አበባ_ዓድዋ
#1540ኪ .ሜ

ምንጭ፦ ያሬድ ሹመቴ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ሰመራ ዩኒቨርሲቲ‼️

ወጣቱ #ከጎጠኝነትና #ከጎሰኝነት አጀንዳዎች ይልቅ በአገራዊ ራዕይ ላይ ማተኮር እንደሚገባው የሰብዓዊ መብት ተሟጋቹ አቶ ኡባንግ ሜቶ አሳሰቡ።

አቶ ኦባንግ ከሰመራ ዩኒቨርስቲ ተማሪዎች ጋር ባካሄዱት ውይይት እንደተናገሩት ወጣቱ ባለፉት 27 ዓመታት በልዩነቶች ላይ  ያተኮረው አመራር ይከተለው ከነበረው ከፋፋይ ፖሊሲ በመውጣት አገራዊ እሴቶችን አውቆ ወደሚተገብርበት ሁኔታ መሸጋገር አለበት።

ከራስ ጥቅምና መብት እኩል ስለሌሎች ብሄርና እምነት ተከታዮች ብሎም አገራቸው ሰላሟ ተረጋግጦ  በሚኖሩበት  ሁኔታ ላይ መሥራት ይጠበቅባቸዋል ብለዋል።

የጋራ አገሩን ለመገንባትና ለአንድነቷ በመታገል ራዕይዋን ለማሳካት መሥራት እንዳለበትም ተናግረዋል።

ባለፉት ዓመታት ዜጎች ለዘመናት የገነቧቸዉ ተከባብረው የመኖር አኩሪ እሴቶች መሸርሸራቸውን ገልጸው፣ይህም አለመተማመንና አንዱ ሌላውን በጥርጣሬና በስጋት እስከማየት የደረሰበት ሁኔታ መፈጠሩን አስታውሰዋል።

በአገሪቱ የተለያዩ አካባቢዎች የሚከሰቱ  ግጭቶች ባለፉት የዘር ተኮር ፖለቲካ  ድምር ውጤቶች ናቸው ያሉት አቶ ኦባንግ፣አሁኑኑ እልባት ካላበጀንላቸው የአገሪቱን ህልውና የሚያጠፉ ተጨባጭ ማሳያዎች መሆናቸውን ገልጸዋል።

በአገሪቱ የተጀመረው የለውጥ ጉዞ እንዲደናቀፍ ሀብታቸውን፤ እውቀታቸውንና አደረጃጀታቸውን ተጠቅመው አገርንና ሕዝብን በማተራመስ  የተጠመዱ አካላትን ወጣቱ ነቅቶ ሌላውንም ኅብረተሰብ የማንቃት አገራዊ ኃላፊነት እንዳለበትም የሰብዓዊ መብት ተሟጋቹ ተናግረዋል።

በመሆኑም ወጣቱ በሚያጋጥሙት ጥቃቅን ችግሮች  ሳቢያ በስሜታዊነት ወደግጭት በመግባት የሴራ ፖለቲከኞች መጠቀሚያ እንዳይሆን በሰከነ መንገድ መንቀሳቀስ እንዲሁም በግልጽ መነጋገርና መወያየት መጀመር አለበት ብለዋል።

የዩኒቨርሲቲዉ የአራተኛ ዓመት ምህንድስና ተማሪ  መሐመድ ኢድሪስ ወጣቱ አገራዊ ኃላፊነቱን ዘንግቶ ባልተረጋገጠ መረጃ በስሜት ተነስቶ ወደ ግጭት የሚገባበት ሁኔታን እንዲቀይር ጠይቋል።

ከማናቸውም አካላት የሚደርሱትን መረጃዎች በማጣራት እውነትም ከሆነ በስሜት ሳይሆን በሰከነ መንገድ በውይይት መፍታት ያስፈልጋል ብሏል።

ሌላው የዩኒቨርሲቲዉ የአራተኛ ዓመት ምህንድስና ተማሪ ጌታነህ ተስፋው በማህበራዊ ሚዲያም  ሆነ አክቲቪስቶች የሚያሰራጯቸውን ሚዛናዊነት የጎደላቸዉ መረጃ አጥርቶ መጠቀም እንደሚያስፈልግ አመልክቶ፣መረጃውን የሚያስተላልፉ ተቋማት ላይ እርምጃ ሊወሰድ እንደሚገባም አመልክቷል።

ምንጭ፦ ኢዜአ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update በአዳማ ኢንዱስትሪ ፓርክ የተመረቱ አምስት ሺህ ካርቶን የዋና አልባሳት ለመጀመሪያ ጊዜ ለውጭ ገበያ ቀረቡ። የቻይናው አንቴክስ ግሩፕስ ጨርቃጨርቅ አምራች ኩባንያ ምርቱን ትላንት በፓርኩ ውስጥ ያስተዋወቀበትን ሥነ ሥርዓት አካሂዷል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ኮንጎ ውስጥ ውጥረት ነግሷል‼️

የዴሞክራቲክ ሪፓብሊክ ኮንጎን ምርጫ ተከትሎ #ውጥረት ነገሷል፡፡ የመንግስት ባለስለጣናት ለመገናኛ ብዙሃን እንደገለጹት ማይ ማይ የተባለው ቡድን ተወጊዎች በምስራቅ ዴሞክራቲክ ሪፖፕሊክ ኮንጎ በሰሜን ኪቮ ግዛት ሉበርቶ ከተማ የድምፅ መስጫ ጣቢያዎችን በመውረር መራጮች ድምጽ እንዲቀይሩ አስገድደዋል፡፡

በደቡብ ኮቮ ዋሉንጉ በተባለው አካባበቢ ደግሞ ምርጫ ተጭበርብሯል ከሚል ጉዳይ ጋር በተያያዘ በተከሰተ ግጭት የፖሊስ አባላትና ንጹሃን ዜጎች ህይዎት ማለፉም ነው የተገለጸው፡፡

በትናትናው ዕለት በሀገሪቱ በተካሄደው በዚህ ምርጫ ጠዋት ላይ ከፍተኛ ዝናብ መጣሉን ተከትሎ የመራጮች ድምጽ አሰጣጥ ሂደት የተቀዛቀዘ የነበረ ሲሆን÷ ከሰዓት በኋላ በአንዳንድ አካባቢዎች ረጃጅም የመራጮች ሰልፎች ታይተዋል ተብሏል፡፡

በኬኒሻሳ በበርካታ የምርጫ ጣቢዎች በድምፅ መስጫ ማሽን እጥረት የድምጽ አሰጣጥ ሂደቱ መዘግየቱን ዘገባው ያመለክታል፡፡

በመዲናዋ ቡምቡ ከተማ አስተዳደር ከደህንነት ስጋት ጋር በተያያዘ መራጮች አካባቢቸውን ለቀው የወጡ ሲሆን÷ ከ12 የድምፅ መስጫ ጣቢዎች 10 ብቻ መከፈታቸውም ተነገሯል፡፡

በርካታ መራጮችም ከድምጽ መስጫ መዘገብ ላይ ሥማቸውን በማጣታቸውም ድምጽ ሳይሰጡ መመለሳቸውን ለመገናኛ ብዙሃን ተናግረዋል፡፡

እንደ አውሮፓዊኑ አቆጣጠር ከ2016 ጀምሮ እየተራዘመ በመጣው በዚህ ምርጫ ከ46 ሚሊየን በላይ መረጮች ድምጽ ለመስጠት የተመዘገቡ ሲሆን÷ ከተመዝጋቢወዎቹ መካከል 15 በመቶ ያህሉ በመዲናዋ ኬኒሻሳ እንሚገኙ ተጠቁሟል፡፡

ይሁን እንጂ 1ነጥብ2 ሚሊን ያህል ድምፅ ሰጪዎች የተመዘገቡበትና ሶስት ብርቱ የተፎካካሪ ተወዳዳሪዎች በሚገኙባቸው አካባቢዎች ምርጫው ያለመካሄዱ ነው የተገለጸው፡፡

ምንጭ፡- አል ጀዚራ(በfbc)
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ጥቆማ‼️

#ሱሉልታ አካባቢ ላለፉት ሁለት እና ሶስት ቀናት የኔትዎርክ ችግር እንዳለ ነዋሪዎች ጠቁመዋል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia