TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
59.4K photos
1.51K videos
215 files
4.12K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
ከዱራሜ🔝

"በከንባታ ጠንባሮ ዞን በዞኑ ዋና ከተማ ዱራሜ ህዝቡ በነቂስ ወቶ ከተማውን እያፀዳ ነው። አላማው "እየሰራን እንጠይቃለን!" የሚል ሲሆን ከተለያዩ የዞኑ ከተሞች በመምጣት ነው ዋና ከተማዋን እያፀዱ ያሉት።"

@tsegabwolde @tikvhethiopia
ሰበር ዜና‼️

ዋና ኦዲተር አቶ #ገመቹ_ዱቢሶ መንግስት የሰጣቸውን አዲስ ሹመት #እንደማይቀበሉት ገለጹ፡፡ አቶ ገመቹ አሁን ላይ ከሚገኙበት የፌዴራል ዋና ኦዲተር መሥሪያ ቤት የዋና ኦዲተር ኃላፊነት በተጎዳኝ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የቦርድ አባል እንዲሆኑ በዚህ ሳምንት የተሾሙ ቢሆኑም የቦርድ አባልነት ሹመቱን እንደማይቀበሉት ገልጸዋል፡፡

በዋናነት እሳቸው የሚመሩት የፌዴራል ዋና ኦዲተር መሥሪያ ቤት ኦዲት በሚያደርገው የመንግሥት ተቋም የቦርድ አባል ሆነው መሥራት የጥቅም ግጭት (conflict of interest) እንደሚፈጥር እና በዚህም ምክንያት ሹመቱን እንደማይቀበሉት አስታውቀዋል፡፡

ምንጭ፦ The Reporter
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update ጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ አህመድ የቀድሞውን የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዋና ስራ አስፈፃሚ የነበሩትን አቶ ግርማ ዋቄን የአየር መንዱ የቦርድ አባል በማድረግ ሾመዋቸዋል። ከአቶ ግርማም በተጨማሪ የሼህ አል አሙዲና አብነት ገብረ መስቀል ንብረት የሆነው ኖክ ዋና ስራ አስፈፃሚ የሆኑት አቶ ታደሰ ጥላሁን እና የውጭ ጉዳይ ሚንስቴር ሚንስትር ዲኤታ አቶ አክሊሉ ኃይለ ሚካኤልንም በቦርድ አባልነት ተሰይመዋል። ሶስቱም የቦርድ አባላት የአየር መንገዱ የቦርድ ሰብሳቢ ከሆኑት የቀድሞው አፈ ጉባኤ አባዱላ ገመዳና የአየር መንገዱ ቦርድ ምክትል ሰብሳቢና የኢንዱስትሪያል ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ቦርድ ሰብሳቢ ከሆኑት አርከበ ዕቁባይ (ዶ/ር) ጋር ተገናኝተው ተወያይተዋል።

Via The Reporter & Petros Ashenafi Kebede
@tsegabwolde @tikvahethiopia
የገናሌ ዳዋ III ከውሃ የኤሌክትሪክ ኃይል ማመንጫ ግድብ እውነታዎች
…………………////…………………
•ግድቡ በኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት በጉጂ ቦረና እና በባሌ ዞኖች አዋሳኝ ድንበር ላይ እየተገነባ ይገኛል፡፡
•ከአዲስ አበባ በ630 ኪ.ሜትር ኪ.ሜ ያህል ይርቃል።

•ግንባታው በ2003 ዓ.ም ተጀመረ፡፡

•የገናሌ ወንዝን ይጠቀማል፡፡

•የግድቡ አይነት ኮንክሪት ፌስ ሮክ ፊል (Concrete face rock fill) በመባል ይታወቃል፡፡

•የዋናው ግድብ ከፍታ 110 ሜትር፣ ከላይ ያለው የጎን ርዝመት( crust Length) 426 ሜትር እና ስፋቱ ደግሞ 8 ሜትር ነው፡፡

•የግድቡ ውሃ የማጠራቀም ከፍታ ከባህር ጠለል በላይ 640 ሜ ነው፡፡

•ግድቡ 2.6 ሚሊዬን ሜትር ኪዩብ ውሃ የመያዝ አቅም አለው፡፡

•254 ሜ.ዋ ያመነጫል።

•ዓመታዊ የኃይል ምርት አቅም በአማካይ በሰዓት 1640 ጊጋ ዋት ነው፡፡

•3 ተርባይኖች ያሉት ሲሆን እያንዳንዳቸው 84.7 ሜጋ ዋት ያመነጫሉ።

•ይርጋለም ከሚገኘው ባለ 400 ኪ.ቮ የኃይል ማከፋፈያ ጣቢያ ጋር በኃይል በመስመር ተገናኝቷል፡፡

•12.4 ኪ.ሜ የውሃ ማስገቢያ ዋሻ (Power Intake) ቁፋሮ ተከናውኖለታል፡፡

•380 ሜትር ርዝመት ያለው የውሃ መልቀቂያ ዋሻ (water release tunnel) ተገንብቶለታል፡፡

•በአሁኑ ሰዓት ለ390 ኢትዮጵያውያን ጊዜያዊ የሥራ ዕድል መፍጠር ችሏል፡፡

• የግንባታው ጠቅላላ ወጪ 451 ሚሊዬን ዶላር ነው።

•60 በመቶ የፋይናንስ ወጪ ከቻይናው ኢምፖርት ኤክስፖርት ባንክ (Exim Bank) በብድር እንዲሁም ቀሪው 40 በመቶ ደግሞ በመንግሥት እየተሸፈነ ይገኛል፡፡

•የፕሮጀክቱን የሲቪል እና የኤሌክትሮ ሜካኒካል ሥራዎችን እየሰራ የሚገኘው ሲጂጂሲ (CGGC) የተባለ የቻይና ኩባንያ ነው፡፡

•የማማከር (consultant) ተግባሩን ደግሞ የአሜሪካው ኤም.ደብሊው.ኤች (MWH) ከሃገር በቀሎቹ አኪዩትና ኢንተግሬትድ ጋር በጥምረት በመሆን እያከናወኑት ይገኛሉ፡፡

•በአሁኑ ሰዓት የፕሮጀክቱ አጠቃላይ አፈፃፀም 97.07 በመቶ ደርሷል፡፡

Via~EEP
@tsegabwolde @tikvahethiopia
አሳዛኝ ዜና‼️

የወልቂጤ ከተማ እግርኳስ ክለብን በአምበልነት እያገለገለ የነበረው መዝገቡ ወልዴ #በድንገተኛ ህመም ምክንያት በህክምና ሲረዳ ቆይቶ ትናንት ከዚህ ዓለም በሞት ተለይቷል።

ታኅሳስ 16 በ1982 ዓ.ም የተወለደው መዝገቡ ወልዴ የእግርኳስ ህይወቱን ከፕሮጀክት አንስቶ ህይወቱ እስከምታልፍ ድረስ በደቡብ ክልል ፕሮጀክት ቀጥሎም ወልቂጤ ከተማ ከተቋቋመበት ጊዜ አንስቶ ክለቡን በአምበልነት ለ11 ዓመታት አገልግሏል። በ2007 ለሲዳማ ቡና የመጫወት እድልም አግኝቷል፡፡ብዙም ሳይቆይ ወደ መጀመሪያ ክለቡ በድጋሚ ተመልሷል። በዚህ ዓመት ለኢትዮጵያ ወጣት ብሔራዊ ቡድን መጫወት ችሎም ነበር።

በክለቡ እና በስፖርት ቤተሰቡ ዘንድ በነበረው መልካም ባህርይ አንቱታ ያተረፈው መዝገቡ ከእግርኳሱ በተጨማሪ በትምህርቱ ገፍቶ በ2002 ከመደወላቡ ዩኒቨርሲቲ በኢኮኖሚክስ የመጀመሪያ ዲግሪ ማግኘት ችሎ ነበር።

የመዝገቡ ስርዓተ ቀብር ዛሬ በወልቂጤ ቅዱስ ሚካኤል ቤተ-ክርስቲያን ተፈፅሟል፡፡ ወልቂጤ ከተማ አስተዳደር በተጫዋቹ ሞት የተሰማውን ሀዘን ገለጿል። የውልቂጤ እግር ኳስ ቡድንም ተጫዋቹ ይለብሰው የነበረውን 2 ቁጥር ማልያም ለቀጣዮቹ ሁለት ዓመታት እንዳይለበስ መወሰኑ ታውቋል፡፡

ምንጭ፡-ሶከር ኢትዮጵያ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ዲያስፖራውን በቀን አንድ ዶላር በጠየቁት መሰረት በ28 ዓመት ከአንድ ሰው የሚጠበቀውን በቀለ ገለታ የሚባል ግለሰብ በአንዴ አስገብቶ ሀገር ወዳድነቱን አሳይቷል!!

ምንጭ፦ Wonde Mettu
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update አማራ ክልል ወሎ በኦሮሞና አፋር አዋሰኝ ድንበር ላይ ባለፉት ሦስት ቀናት በተባባሰው ግጭት ቢያንስ የስድስት ሰዎች ሕይወት ሲቀጠፍ፤ ሌሎች 12 ሰዎች ላይ ከባድ ጉዳት መድረሱን ነዋሪዎች ለDW ዛሬ ተግረዋል። የግጭቱ መንስዔ በባቲ ዙሪያ እና አፋር አጎራባች ቀበሌዎች ነዋሪዎች መካከል በተከሰተ የግጦሽ መሬት ይገባኛል ጸብ መኾኑ ተገልጧል።

Via~DW Amharic
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ፕሮፌሰር #ፍቅሬ_ቶሎሳ እንዲህ ብለዋል...

"ጀርመን ሄጀ የወለድኩት ልጅ ጀርመነኛ ቢናገር፣ እንግሊዝ የወለድኩት ልጅ እንግሊዘኛ ተናጋሪ ቢሆን፣ ጣሊያን ሀገር የወለድኩት ጣሊያንኛ ተናጋሪ ቢሆን ልጆቼ የተለያየ ቋንቋ ስለተናገሩ ወንድማማችነታቸው ይፋቃል ወይ? እኔስ ኦሮሞኛ፣ አማርኛና ትግርኛ ተናጋሪ በመሆኔ ወይም ልጆቼ የሚናገሩትን ቋንቋ ስላልተናገርኩ አባትነቴ ይፋቃል ወይ? የሚያዛምደን ስጋና ደማችን እንጅ #ቋንቋችን አይደለም፤ ስለዚህ እኛ #ኢትዮጵያውያን የተለያየ ቋንቋ መናገራችን ሊከፋፍለንና ሊያጋጨን አይገባም"

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ቤንሻንጉል ጉምዝ ክልል‼️

የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ምክር ቤት የተለያዩ የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ምክር ቤት ባካሄደው አስቸኳይ ጉባኤ የተለያዩ አዋጆችንና ሹመቶችን አፀደቀ።

ምክር ቤቱ 5ኛ ዓመት 4ኛ የስራ ዘመን 3ኛ አስቸኳይ ጉባኤውን ባካሄደበት ወቅት ለምክር ቤቱ የቀረበውን የክልሉን አስፈፃሚ አካላት እንደገና ለማደራጀት የቀረበ ረቂቅ አዋጅ አፅድቋል፡፡

በዚህም ከዚህ በፊት 18 የነበሩ የስራ አስፈፃሚ ተቋማት ወደ 14 ዝቅ ተደርገዋል፡፡ ምክር ቤቱ ሌሎች አዋጆችንም መርምሮ አፅድቋል፡፡

በዚህም የጠቅላይ አቃቢ ህግን ለማደራጀት የቀረበ ረቂቅ አዋጅ እና የከተማ አስተዳደር ፍርድ ቤቶች ማሻሻያ ረቂቅ አዋጅ መርምሮ አፅድቋል።

ምክር ቤቱ ከሰኔ 16ቱ የአሶሳ ከተማ ግጭት ጋር በተያያዘ የክልሉ ግብርና ቢሮ ሃላፊ የነበሩት አቶ ባበክር ሃሊፋን ያለመከሰስ መብት አንስቷል።

የክልሉ ምክር ቤት ዋና አፈ ጉባዔ አቶ ሙለታ ወንበር እንዲሁም ምክትል አፈ
ጉባዔ አቶ ደርጉ ዚያድ ለምክር ቤቱ የስልጣን መልቀቂያ ያቀረቡ ሲሆን በምትካቸዉ ዋና እና ምክትል አፈ ጉባዔ ተሸሟል፡፡

በዚህም መሰረት አቶ ሃብታሙ ታዬ ክልሉ ምክር ቤት ዋና አፈ ጉባዔ፣ አቶ ኢሳቅ አብዱልቃድር የክልሉ ምክር ቤት ምክትል አፈ ጉባዔ ተደርገዉ ተሸመዋል፡፡

በተመሳሳይም የክልሉ ዋና ኦዲት ቢሮ ሃላፊ የነበሩት ወ/ሮ ፀሃይ ሞርካ የስልጣን መልቀቂያ ደብዳቤያቸዉን ለምክር ቤቱ አቅርበዉ ተቀባይነት በማግኘቱ በምትካቸዉ አቶ ከማል ሃሰን የክልሉ ዋናዉ ኦዲት ቢሮ ሃላፊ ሆነዉ ተሸመዋል፡፡ በርእሰ መስተዳድሩ የቀረቡ የመንግስት አካላት ሹመት ምክር ቤቱ አፅድቋል፡፡

1ኛ. አቶ አድጎ አምሳያ ለክልሉ ምክትል ርእሰ መስተዳድር

2ኛ. አቶ አበራ ባየታ ለክልሉ የሰላም ግንባታና ፀጥታ ቢሮ ሃላፊ

3ኛ. አቶ ሙሳ አህመድ ለክልሉ ግብርና ቢሮ ሃላፊ

4ኛ. አቶ ዚያድ አብዱላሂ ለክልሉ ገንዘብና ኢኮኖሚ ቢሮ ሃላፊ

5ኛ. ወ/ሮ ፍሬህይወት አበበ ለክልሉ ጤና ጥበቃ ቢሮ ሃላፊ

6ኛ. አቶ ኢብራሂም ዑመር ለክልሉ ጠቅላይ አቃቤ ህግ

7ኛ. አቶ አሊ ኢብራሂም የክልሉ አከባቢ፣ደንና መሬት አስተዳደር ቢሮ ሃላፊ

8ኛ. አቶ ቀልቤሳ ኦልጂራ የክልሉ መንገድና ትራንስፖርት ቢሮ ሃላፊ

9ኛ. አቶ አካሻ ዑስማዔል የክልሉ ከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ቢሮ ሃላፊ

10ኛ. አቶ ፀጋዬ ተሰማ የክልሉ ዉሃ መስኖና ኢነርጂ ሃብት ልማት ቢሮ ሃላፊ

11ኛ ወ/ሮ ፀሃይ ሞርካ የክልሉ ባህልና ቱሪዝም ቢሮ ሃላፊ

12ኛ ወ/ሮ ሃጂራ ኢብራሂም የክልሉ ሴቶችና ህፃናት ጉዳይ ቢሮ ሃላፊ

13ኛ. አቶ ቶማስ ኪዊ የክልሉ ትምህርት ቢሮ ሃላፊ ሆነዉ ተሸመዋል፡፡

ምንጭ፦ etv
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ሀሰተኛ መረጃ🔝

"እነዚህ ሁለት ፎቶዎች እና አንድ ወይም ሁለት ሌሎች ቪድዮዎች በብዛት ሼር ሲደረጉ ነበር። አንዳንዶች #አልሻባብ የማረካቸው ኢትዮጵያውያን ናቸው ሲሉ ሌሎች ሀገር ውስጥ የሆነ ነው ያሉም ነበሩ። ሶማልያ ካለ አንድ ጋዜጠኛ ጓደኛዬ እና ከጋዜጠኛ ኤልያስ ገ/ስላሴ ጋር በመሆን ማጣራት የቻልኩት የሚከተለው ነው: በአሁን ሰአት ሶማልያ ውስጥ በሳድ እና ማሬሀን ጎሳዎች መሀከል በመሬት ምክንያት ግጭት ተቀስቅሷል። ቪድዮው ላይ ያሉት ኢትዮጵያውያን ከማሬሀን ጎሳ ጎን ሆነው ሲዋጉ የተያዙ ናቸው የተባሉ ሲሆን የሞቱም አሉ ተብሏል። ማሬሀን የአሁኑ ፕሬዝደንት ፎርማጆ ጎሳ ነው። አንዱ ቪድዮ ላይ ኢትዮጵያውያኑ ዜግነታቸው ኢትዮጵያዊ እንደሆነ እንዲያምኑ ሲገደዱ ያሳያል። ይህም ለፕሮፓጋንዳ ሆን ተብሎ የተደረገ ነው ተብሎ ሊታሰብ ይችላል። የአልሸባብ ታጣቂዎች ናቸው እና ኢትዮጵያ ውስጥ የተከሰተ ነው የተባለውን ግን ሀሰት ነው።"

Via~ELIYAS MESERET
@tsegabwolde @tikvahethiopia
አዲስ አበባ‼️

የአፍሪቃ መዲና ናት በምትባለዋ ትልቋ ከተማ መኪና አቁሞ መንገድ ላይ #መሽናት ምን ይሉታል?? ይህ እጅግ እየተለመደ የመጣ ድርጊትም ሆኗል። ይህ ጥሩ ተግባር አይደለም ቢቀርብንስ...!??

ፎቶ፦ ቴዲ አበራ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ቅሬታ‼️

"ቴሌ ስለነሱ የሚነሱ #ቅሬታዎች ቢዘረዘሩ አንድ ቀን እንኳን የሚበቃ አይመስለኝም። ህዝቡም አማራጭ ስላጣ እንጂ የነሱ አገልግሎት ተስማምቶት አደለም። አሁን ደግማ የADSL ወይንም የባለገመድ ኢንተርኔት አገልግሎት እናስገባለን ብለው ሲያስተዋውቁ የሰማችሁ ይመስለኛል አገልግሎቱም በፍጥነት እንሰጣለን ሲሉ እንዲሰማችሁ እርግጠኛ ነኝ ይህ ግን ከእውነታው የራቀ ነው እንኳን በፍጥነት ይቅርና በስርዓት እራሱ የሚያነጋግር የለም። በተለይ #በኮተቤ #መሳለሚያ ቴሌ ያለዉ ሁኔታ በጣም ያሳዝናል። ይኸው ከወር በፊት ያመለከቱት ለአገልግሎቱም ክፍያ ያጠናቀቁ እራሱ አገልግሎት ማግኘት አልቻሉም። ቅሬታ እንኳን የሚሰማ የለም። የሚገርመው ወር ሲማላ ክፍያ መጠየቃቸው ነዉ ላልተሰጠ አገልግሎት። ቴሌ ተቆጣጣሪ ያለው መስሪያ ቤት እራሱ መሆኑን እጠራለሁ። የሚመለከተው አካል ካለ ይህንን ቅሬታ ቢያተኩርበት መልካም ይመስለኛል ምክንያቱም ህዝብ የናንተን አገልግሎት ተስፋ በመቁረጥ እየጠበቀ ነዉና።"

@tsegabwolde @tikvahethiopia
“ኢትዮጵያ፦ ትላንት፣ ዛሬ እና ነገ” የሚል ርዕስ ያለዉን ስዕል ለ ጠ/ሚር ዐቢይ አሕመድ ሰዕሊ ተክለ ማርያም ዘውዴ አበርክቷል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia