TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.8K photos
1.44K videos
207 files
3.99K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
ሲአን‼️

ኢትዮጵያ ውስጥ እየተካሄደ ያለውን የለውጥ ሂደት “ለመቀልበስ የሚደረጉ” ያላቸውን እንቅስቃሴዎች እንደሚቃወም የሲዳማ አርነት ንቅናቄ - ሲአን አስታውቋል፡፡

ለውጡን “ከፍተኛ መስዋዕትነት የተከፈለበት” ብሎታል ሲአን። የተለያየ ስብጥር ባላቸው #የሃዋሳ ከተማ ነዋሪዎች መካከል “አለመተማመን እንዲኖርና #ሁከት እንዲፈጠር የሚያደርጉ ኃይሎችን አወግዛለሁ" ብሏል ሲአን ትላንት በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ።

“በሃሳብ ልዕልናና በሰላማዊ መንገድ እንጂ ሁከት በመፍጠርና ሰላም በመንሳት የሚደረግ ትግል ተቀባይነት የለውም” ብሏል ንቅናቄው።

"የሲዳማ ህዝብ ጥያቄ ነው" ያለው የሲዳማ ክልልነት ጥያቄ ውሣኔ-ሕዝብ ሂደት የደረሰበትን ደረጃ መንግሥት ለህዝብ እንዲያሳውቅ ሲአን ጠይቋል፡፡

Via~VOA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ🔝

#የሃዋሳ_ዩንቨርሲቲ የህክምና እና የጤና ሳይንስ ኮሌጅ የህክምና ተማሪዎች 10ኛ ዙር #የምርቃት_ኘሮግራም በአሁን ሰአት በመከናወን ላይ ይገኛል።

©Suleyman&AMED(TIKVAH-ETH)
@tsegabwolde @tikvahethiopia