TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.8K photos
1.44K videos
207 files
3.99K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
#UNHCR

በመላው አፍሪካ በሙዚቃ ስራዎቿ ተወዳጅነትንና እውቅና እያተፈረች የምትገኘው ወጣቷ ኢትዮጵያዊቷ ድምፃዊ ብሩክታዊት ጌታሁን [ቤቲ-ጂ] የተባበሩት መንግስታት የስደተኞች ድርጅት [UNHCR] የበጎ ፈቃድ አምባሳደር በመሆን መሰየሟ ተሰምቷል፡፡

#UNHCR #WALTAINFO
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
#SUDAN #UNHCR #Ethiopia

በኢትዮጵያ ትግራይ ክልል የነበረውን ግጭት ሸሽተው ወደ ሱዳን የተሰደዱ የሀገራችን ዜጎች ከ50,000 ይበልጣሉ።

#UNHCR እና የሱዳን ባለስልጣናት በመነጋገር 14,000 ስደተኞችን ከሃምደያት እና አብድራፊ ድንበር ሃም ራኩባ ካምፕ አዘዋውረዋቸዋል። ቦታው ከኢትዮጵያ ድንበር 70 KM ይርቃል።

አብዛኞቹ ስደተኞች ሴቶች እና ህፃናት እንደሆኑ የUNHCR መረጃ ያሳያል።

https://www.unhcr.org/news/stories/2020/12/5fd60c0f4/growing-needs-thousands-displaced-ethiopians-sudan.html

@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia
ፍሊፖ ግራንዴ የማይኣይኒ ካምፕን ጎበኙ።

የተመድ የስደተኞች ጉዳይ ከፍተኛ ኮሚሽነር ፊሊፖ ግራንዲ አብረዋቸው ከመጡት የተመድ ሉዑካን ቡድን ጋር በትግራይ ክልል የሚገኘውን የኤርትራ ስደተኞች መጠለያ ጣቢያን ዛሬ ጎበኝተዋል፡፡

ፊሊፖ ግራንዲ በማይአይኒ የኤርትራ ሰደተኞች መጠለያ ካምፕ ስደተኞችን ተዘዋውረው መመልከታቸውን ከARRA ያገኘነው መረጃ ያሳያል።

በዛሬው ጉብኝት ላይ የሰላም ሚኒስትር ወ/ሮ ሙፈሪያት ካሚል ጨምሮ ፣ የውጪ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን ፤ የስደተኞች እና ከስደት ተመላሾች ጉዳይ ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር አቶ ተስፋሁን ጎበዛይ ተገኝተው ነበር። #UNHCR

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#UNHCR

ፍሊፖ ግራንዴ ከምክትል ጠ/ሚ እና ከውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን ጋር ትላንት ውይይት ማደረጋቸው ታውቋል።

አቶ ደመቀ ከፍሊፖ ግራንዴ ጋር የነበራቸው ውይይት ፍሬያማ ነበር ሲሉ በፌስቡክ ገፃቸው ላይ አስፍረዋል።

መንግስት በትግራይ ክልል ስለሚሰጠው የሰብዓዊ ድጋፍ፤ ስደተኞችንበማስተናገድ ረገድ ያሉ ጥረቶች እንዲሁም በተለያዩ ወቅታዊ ጉዳዮች ዙሪያ በዝርዝር መወያየታቸውንም አቶ ደመቀ ገልፀዋል።

አቶ ደመቀ ፥ "የተመድ የስደተኞች ጉዳይ ኤጀንሲ የሚያደርገውን ድጋፍ ትርጉም ባዘለ መልኩ ለመጠቀም የኢትዮጵያ መንግሥት ቁርጠኛ መሆኑን አረጋግጫላቸዋለሁ" ብለዋል።

በሌላ በኩል ፍሊፖ ግራንዴ ከኢፌዴሪ ፕሬዚዳንት ሣህለ ወርቅ ዘውዴ ጋር ተወያይተዋል።

@tikvahethiopiaBot
#UNHCR

የተመድ የስደተኞች ተቋም (UNHCR)፥ ከስድስት ወር በፊት በትግራይ የተቀሰቀሰውን ጦርነት ተከትሎ በክልሉ የነበሩ 2 የስደተኞች ጣቢያዎች ከአገልገሎት ውጪ መሆናቸውን ተከትሎ በአማራ ክልል ደባርቅ ከተማ የስደተኞች መጠለያ ሊገነባ መሆኑን ለቢቢሲ አስታውቋል።

ተመድ (UNHCR) ከስደተኞችና የስደት ተመላሾች ኤጀንሲ ጋር በመሆን በትግራይ ክልል እንዲዘጉ በተደረጉት ሁለት የመጠለያ ጣብያዎች ምትክ በአማራ ክልል ደባርቅ ከተማ ለመገንባት ቦታ የመለየት ስራ መከናወኑን ገልጿል።

ተመድ በስፍራው ላይ ለኤርትራውያን ስደተኞች መጠለያ ለመገንባት ሕጋዊ ሰነዶች እስኪሟሉ እየጠበቀ ነው።

እንደ ድርጅቱ መረጃ ከሆነ የክረምቱ ወራት ከመጀመሩ በፊት ግንባታውን ለማካሄድ እና ስደተኞቹን በቦታው ለማስፈር እቅድ መያዙን ቢቢሲ በድረገፁ አስነብቧል።

@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBOT
#UNHCR #Ethiopia #UN

በተመድ የኢትዮጵያ ቋሚ መልዕክተኛ አምባሳደር ታዬ አጽቀስላሴ ከተመድ የስደተኞች ከፍተኛ ኮሚሽነር ፊሊፖ ግራንዲ ጋር እደተወያዩ በትዊተር ገፃቸው አሳወቁ።

ውይይቱ የነበረው ስደተኞችን ከመጠበቅ ፣ የሀገር ውስጥ ተፈናቃዮች እና ለስደተኞች እየተሰጠ ስለሚገኘው የኮቪድ 19 ምላሽን በተመለከተ መሆኑን በመልዕክታቸው ገልፀዋል።

አምባሳደር ታዬ አጽቀስላሴ፥ ኢትዮጵያ የስደተኞችን ደህንነት ለመጠበቅ እና ለመከላከል ለረጂም ጊዜ የሚዘልቅ ዝግጁነት እንዳላት ለፊሊፖ ግራንዴ ነግረዋቸዋል።

@tikvahethiopia
#UNHCR

የUNHCR ኮሚሽነር ፊሊፖ ግራንዲ በትግራይ በሚገኙ ኤርትራውያን ስደተኞች ላይ እየደረሰ ያለው ጥቃት በእጅጉ እንዳሳሰባቸው በመግለጽ በአስቸኳይ ሊቆም እንደሚገባ አሳስበዋል።

ኮሚሽነሩ በትግራይ የሚገኙ የኤርትራ ስደተኞች ደህንነትን በተመለከተ ዛሬ መግለጫ ሰጥተዋል።

በትግራይ ግጭት ከተጀመረ አንስቶ ስደተኞቹ በሁለት ተዋጊ አካላት መሃል ለመውደቅ መገደዳቸውን ፣ ሁለት የስደተኞች መጠለያ ጣቢያዎች መውደማቸውን እና በሺዎች የሚቆጠሩ ስደተኞች ሕይወታቸውን ለማትረፍ ዳግም ለመሰደድ መገደዳቸውን ገልጸዋል።

ኤርትራውያን ስደተኞች በአንድ ወይም ሌላ ወገን ደጋፊነት ተፈርጀው #የበቀል_ጥቃት እየደረሰባቸው እንዲሁም ተጠልፈው እየተወሰዱ እና እየተያዙ ስለመሆኑ የተጣሩ እና በማስረጃ የተደገፉ ሪፖርቶች ለኮሚሽኑ መድረሳቸውን ተናግረዋል።

በማይ አይኒ እና በአዲ ሃሩሽ የስደተኞች መጠለያ ጣቢያዎች ውስጥ በሚገኙ ስደተኞች ላይ በተለያዩ ታጣቂዎች በተለይ ማታ ማታ የሚፈፀሙ አጠቃላይ የወንጀል ድርጊቶች በእጅጉ ረብሸውኛል ብለዋል።

ባለፉት ሳምንታት ሽረ ውስጥ በመቶዎች የሚቆጠሩ ኤርትራውያን ለእስር ተዳርገዋል ያሉት ኮሚሽነሩ፣ በመቐለ የሚገኙ አካላት በጉዳዩ ላይ ማብራሪያ እንዲሰጡ እንዲሁም በሕገ-ወጥ መንገድ የታሰሩ ስደተኞች እና ጥገኝነት ጠያቂዎች በአፋጣኝ እንዲለቀቁ መጠየቃቸውን ገልፀዋል።

በተጨማሪ በኤርትራውያን ስደተኞች ላይ በጣም ከባድ የሆኑ የኃይል ጥቃቶች እየደረሱ ስለመሆኑ የሚጠቁሙ ሪፖርቶች እየወጡ በመሆኑ፣ የፌደራል መንግሥትም ሆነ በትግራይ ክልል ያሉ አካላት በእነዚህ ተዓማኒ ክሶች ላይ መደበኛ ምርመራ እንዲጀምሩ ጥሪ አቅርበዋል።

@tikvahethiopia
#UNHCR

UNHCR ኤርትራውያን ስደተኞችን ከትግራይ ክልል እያስወጣ ነው።

ለደይሊ ኔሽን ጋዜጣ በሰጠው ቃል ከ20,000 በላይ ኤርትራውያን ስደተኞችን ከትግራይ ክልል የማስወጣቱ ሂደት መጀመሩን አረጋግጧል።

የUNHCR ቃል አቀባይ Neven Crvenkovic "ከ20 ሺህ በላይ ኤርትራዊያን ስደተኞችን ከትግራይ ክልል የማስወጣት ሂደት መጀመሩን ገልፀው ስደተኞቹ ማይ ዓይኒ እንዲሁም አዲ ሐሩሽ በተባሉት ስደተኛ መጠለያዎች ተጠልለው የቆዩ እንደሆኑ አስረድተዋል።

ኤርትራውያን ስደተኞች አሁን ላይ የሚዛወሩት በአማራ ክልል " ዳባት ወረዳ " ወደተሠሩት አዲስ ስደተኛ መጠለያዎች ነው፡፡

አዲሱ የዳባት ስደተኞች መጠለያ ጣቢያ 25 ሺህ ስደተኞችን ማስተናገድ ይችላል።

#Nation

@tikvahethiopia
#Afar #Tigray #UNHCR #IOM

UNHCR ከትግራይ ክልል ውስጥ #ለአደጋ_ተጋላጭ ናቸው ያላቸውን 55 ኤርትራዊያን ስደተኞችን በIOM Ethiopia እገዛ ወደ አፋር ክልል ማዛወሩን አስታውቋል።

ወደአፋር ክልል ከተዘዋወሩት ስደተኞች መካከል ከግማሽ በላዩ ህጻናት ናቸው።

UNHCR ስደተኞቹ በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ ለወራት ከኖሩ በኃላ አሁን ላይ ምቹ ወደሆነ መጠለያ እንደሚገቡ እና አስፈላጊውን ሁሉ እርዳታ እንደሚያገኙ ገልጿል።

@tikvahethiopia
"...ሱዳን ውስጥ ያሉት የስደተኛ መጠለያዎች ለኢትዮጵያ አማጺያን መሸሸጊያ እንዲሆኑ አልፈቅድም" - UNHCR

[BBC]

ከሰሞኑን የኢትዮጵያ መንግስት በሱዳን ለስደተኞች የሚሰጥ መታወቂያን የያዙ ግለሰቦች ከህወሓት ጋር ሆነው እየተዋጉ ነው ማለቱ ይታወቃል።

የኢ.ፌ.ዴ.ሪ. የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ከቀናት በፊት #UNHCR የሚሰጠውን የስደተኞች መለያ መታወቂያ የያዙ ታጣቂዎች ከሱዳን ድንበር ተሻግረው ወደ ቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል እንዲሁም ወደ አማራ ክልል መግባታቸውን ገልጾ ነበር።

አማራ ክልል ፕሬዝዳንት የሆኑት አገኘሁ ተሻገርም ከሳምንት በፊት በሰጡት መግለጫ በሱዳን አቅጣጫ ጥቃት ሊያደርሱ ሲሉ እርምጃ የተወሰደባቸው የህወሓት ታጣቂዎች የተመድ (UN) የስደተኛ መታወቂያ የያዙ መሆናቸውን አሳውቀው ነበር።

ዛሬ ደግሞ UNHCR ባወጣው መግለጫ በሱዳን በሚገኙ ካምፖች ውስጥ የነበሩ ኢትዮጵያውያን ስደተኞች ቁጥር ቢቀንስም እነዚህ ስደተኞች የት እንዳሉ አላውቅም ብሏል።

UNHCR ከስደተኞች መጠለያ ጣቢያ የሚወጡት ስደተኞች የት እንደሚሄዱ የሚያረጋግጥበት መንገድ የለኝም ሲል ገልጿል።

UNHCR የመዘገባቸውና መታወቂያ የሰጣቸው ግለሰቦች በስደተኞች ማቆያ ካምፕ ውስጥ የሰብዓዊ እርዳታ መውሰዳቸውን አረጋግጦ ለዚህም ምዝገባ የሚሆን የራሱ አሠራር እንዳለው አመልክቷል።

"ወደ ኢትዮጵያ ተመልሰው በግጭቱ ተሳታፊ የሆኑ ግለሰቦች ስደተኛ ተደርገው አይወሰዱም" ሲል አሠራሩን አብራርቷል።

ስደተኛ የሚለው መለያ፤ ግጭት ውስጥ ተሳታፊ ለሆነ ሰው እንደማይሰጥም ገልጿል።

ያንብቡ : telegra.ph/UNHCR-09-08

@tikvahethiopia