TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.8K photos
1.44K videos
207 files
3.99K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
#አስቸኳይ “ አጋቾቹ ወደ ታች ዘቅዝቀው እየገረፉት ቪዲዮ ላኩልኝ። ‘1.7 ሚሊዮን ብር ካላስገባሽ ልጅሽን #ገድለን ቪዲዮ እንልክልሻለን’ አሉኝ ” - የታጋች እናት በሊቢያ ደላሎች የታገተው የሀዋሳው ተወላጅ ኢትዮጵያዊ ወጣት ጌድዮ ሳሙኤል፣ በአጋቾቹ ልዩ ልዩ ድብደባዎች እየተፈጸሙበት እንደሚገኝ ፣ አጋቾቹ ወጣቱን ለመልቀቅ 1.7 ሚሊዮን ብር እንደጠየቁ፣ ገንዘቡ በፍጥነት ካልገባ “ እንገድለዋለን ”…
#Update

“ ልጄን ለመልቀቅ ቀነ ገደብ አልሰጡም ” - የታጋች ጌድዮን እናት

ሊቢያ ውስጥ የታገተው የሀዋሳ ከተማው ወጣት ጌድዮን ሳሙኤል እናት በሰጡን ቃል ፣ “ አጋቾቹ ወደ ታች ዘቅዝቀው #እየገረፉት ቪድዮ ላኩልኝ። ‘ 1.7 ሚሊዮን ብር ካላስገባሽ ልጅሽን #ገድለነው ቪዲዮ እንልክልሻለን ’ አሉኝ ” ማለታቸውን ከሁለት ሳምንታት በፊት መረጃ አድርሰናችሁ ነበር።

አሁንስ ታጋቹ ተለቀቀ ? በምን ሁኔታ ላይ ይገኛል ሲል ቲክቫህ ኢትዮጵያ ለታጋቹ እናት ጥያቄ አቅርቧል።

እሳቸውም ፥ “  ‘#እንለቀዋለን’ ብለዋል። በፊት በየጊዜው ማግኘት እንችል ነበር አሁን ላይ ግን ማገናኘት ከልክለዋል ” ሲሉ ገልጸዋል።

“ ግን በቅርብ ጊዜ ያየሁት ለውጥ ግንባሩ ላይ #ተፈንክቷል። ለመልቀቅ ቀነ ገደብ አልሰጡም ” ብለዋል።

ቅድሚያ 800 ሺሕ ብር ለአጋቾቹ እንዳስገቡ፣ ቀሪውን ታጋቹ ሊለቀቅ ቀናቶች ሲቀሩት ለመላክ ከአጋቾቹ ጋር መነጋገራቸውን አክለው ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጸዋል።

ታጋቹን የሚለቁት የበርካታ ታጋቾች ቤተሰቦችም የተጠየቁትን ገንዘብ አሟልተው ሲልኩ 20፣ 20 ታጋቾችን በማሳፈር እንደሆነ፣ ቢያንስ የ20 ታጋች ቤተሰቦች የተጠየቁትን ገንዘብ ካላኩ መኪና ስለማይሞላ፣ የከፈሉትም ያልከፈሉትን መጠበቅ ግድ እንደሚላቸው እንደገለጹላቸው አስረድተዋል።

የወጣት ጌድኦን እናት ባስተላለፉት መልዕክትም፣ “ ልጆቻችን የሚሰደዱበት ምክንያት አላቸው። ከዩኒቨርሲቲ ተመርቀው መጥተው ወላጅ ጋር ነው የሚቀመጡት። እኛ ደግሞ ሲቸግረን ሲያዩ አይችሉም። ይህንን መንግሥት በትኩረት መስራት አለበት ” ብለዋል።

“ ወጣቱ አሁንም ከሀገር #እየተሰደደ ነው። እስቲ ወላድ ምን እንሁን ? እነዚህ ልጆች ለአገራቸው አይጠቅሙም ? ” ሲሉ ጠይቀው፣ “ ቢያንስ እንኳ መንግሥት ተበድሮም ቢሆን የሆነ ፋብሪካ ከፍቶ ወጣቱን ቢያሰራ እኮ ወጣቱ አይሰደድም ” ሲሉ አስገንዝበዋል።

#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia