TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
59.4K photos
1.51K videos
215 files
4.12K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
አማራ ክልል‼️

"ፋና በአማራ ክልል ምዕራብና ማዕከላዊ ጎንደር ዞኖች አንዳንድ አካባቢዎች የተከሰተውን ግጭት ለመፍታት እየተሰራ መሆኑን የክልሉ መንግስት አስታወቀ ሲል፤ ቤተሰቦቹ በአካባቢው የሚገኝ አንድ ጓደኛዬ በጉንትር ቀበሌ (ደምቢያ አካባቢ) 12 ሰዎች ህይወታቸው እንዳለፈ፣ 465 ቤቶች እንደወደሙ እና ከ6,000 በላይ ሰዎች እንደተፈናቀሉ ገልፃልኛል።"

©ጋዜጠኛ ኤልያስ መሰረት
@tsegabwolde @tikvahethiopia
"መቐለ ዩኒቨርሲቲን አመስግኑልኝ!
በአማራና በትግራይ ህዝቦች መካከል #ሰላምን ለማምጣት እንዴት ሰላማዊ ውይይት ማድረግ እንደሚቻል ጉባኤ አዘጋጅቷል፡፡ ተቋማት ለህብረተሰቡ ጥቀምና በጋራ መግባባት ላይ የተመሠረተ ህይወት እንዲኖረው ለማድረግ ሀላፊነት ያለባቸው ቢሆንም እስካሁን ዝምታ ውስጥ ነበሩ፡፡ ሌሎች አማራ ክልል ውስጥ ያሉ ዩኒቨርሲቲዎችም ይህንን እንደሚያደርጉ ተስፋ አለኝ፡፡"

via~Bekal Alamirew
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ🔝በግቢው ውስጥ የሚገኙ ተማሪዎች የዶቼ ቨለን ዘገባ አጣጥለውታል። አሁንም ግቢው ውስጥ አለመረጋጋት እንዳለ ገልፀዋል። የሚመለከተው አካል ችግሩ ሳይሰፋ ፈጣን የመፍትሄ እርምጃ እንዲወስድ ጠይቀዋል። ግቢውን እያመሱ ያሉ አካላትም አንድ በአንድ ተለይተው ለህግ ሊቀርቡ እንደሚገባም ተማሪዎች ገልፀዋል። አሁን ግቢው ባለበት ሁኔታ ትምህርታቸውን መከታተል እንደማይችሉ የተናገሩት ተማሪዎች ተቋም በግቢው አስተማማኝ ሰላም አስፍኖ ትምህርታቸውን እንዲያስቀጥላቸውም አልያም ወደመጡበት አካባቢ እንዲሸኛቸው ለTIKVAH-ETH በላኩት መልዕክት ገልፀዋል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#Update የስኳር ኮርፖሬሽን ስራ አስኪያጅ የነበሩት አቶ እንዳወቅ ሃብቴ ወ/ሮ ዳግማዊት ሞገስን በመተካት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ ሆነዋል፡፡

Via :- Addis Standard
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ቅዱስ ጊዮርጊስ ስፖርት ክለብ🔝

እርዳታ የሚያስፈልጋቸውን #በመደገፍ የመረዳዳት ባህላችንን ማጠናከር ይገባናል ሲሉ የቅዱስ ጊዮርጊስ ስፖርት ክለብ ደጋፊዎች ገለጹ።

ክለቡ 83ኛ ዓመት የምስረታ በዓሉን ምክንያት በማድረግ በ’ተስፋ አዲስ ፓረንትስ ቻይልድ ሁድ ካንሰር ማዕከል’ የሚገኙ ታማሚ ህጻናትን በመጎብኘትና አስፈላጊ ቁሳቁሶችን ድጋፍ በማድረግ አክብሯል።

በአሁኑ ወቅት በካንሰር ህሙማን ህፃናት መርጃ ማዕከሉ ከ5 ወር ጀምሮ እስከ 16 ዓመት የሚሆኑ ታማሚ ህጻናት ይገኛሉ።

በዚህም ከክለቡ  ደጋፊዎች በተሰበሰበ ከ30 ሺህ ብር በላይ ለታማሚ ህጻናት ምግብና መጠጦችን፣ የንጽህና መጠበቂያዎች፣ የትምህርት መሳሪያዎችና ሌሎችም አስፈላጊ ግብዓቶችን ድጋፍ አድርገዋል።

ምንጭ፦ ena
@tsegabwolde @tikvahethiopia
አ.ሳ.ቴ.ዩ🔝ተማሪዎች ከታህሳስ 2 ጀምሮ የመልሶ ምዝገባ አድርገው ወደ ትምህርት ገበታቸው እንዲመለሱ በጥብቅ አሳውቋል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#Update የፕሬዝዳንት #ኢማኑኤል_ማክሮን መንግስት በነዳጅ ላይ ተጨማሪ ቀረጥ አስከትሎ በፓሪስና አካባቢዋ ሰዎች ሰልፍ ወጥተዋል፡፡ የፈረንሳይ መንግስት በፓሪስ ከተማ ብቻ 8 ሺህ የፖሊስ አባላትን አሰማርቶ አመፁን ለማስቆም ያደረገው ጥረት ብዙም ውጤታማ አልሆነም ተብሏል፡፡ በሳምንቱ መጨረሻ ቀናት ብቻ ፓሪስ ውስጥ በሰልፈኞች በፖሊሶች መካከል በተፈጠረ ግጭት ከ135 በላይ ሰዎች #ቆስለዋል፡፡

ምንጭ፦ ሲ ኤን ኤን
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ከአ.ሳ.ቴ.ዩ🔝

"ከአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ዛሬ የተለያዩ ሚዲያዎች ግቢያችን ውስጥ እየሆነ ስላለው ነገር ለመዘገብ እና ተማሪዎችን ለማናገር እንደሚመጡ ተነግሮን ወደ ግቢው ስቴዲየም ሄደን እየጠበቅን የነበረ ቢሆንም ግቢው ሚዲያዎችን ከማግኘታችን በፊት ስብሰባው በፀጥታ ሀይል እንዲበተን አድርጓል።"

@tsegabwolde @tikcahethiopia
ቡራዩ‼️

በቡራዩና አካባቢው ተከስተው የነበሩ ግጭቶች የሽብር ወንጀል ተጠርጣሪዎች ላይ የግድያ ወንጀል ክስ ሊመሰረት ነው።

በአብረሃም ተረፈ በሞቲ ደሬሳ መዝገቦች የተጠረጠሩ 17 ግለሰቦች በከፍተኛው ፍርድ ቤት አራተኛ ወንጀል ችሎት ጉዳያቸው ሰታይ ቆይቷል።

አቃቤ ህግ ባለፈው ቀጠሮ ክስ መስርቶ እንዲቀርብ በታዘዘው መሰረት ተጠርጣሪዎቹ ዛሬ አራተኛ ወንጀል ችሎት ቀርበዋል።

ይሁንና ግለሰቦቹ የተጠረጠሩበት የሽብር ወንጀል የምርመራ መዝገብ በቂ ባለመሆኑ በግድያ ወንጀል ክስ እንዲመሰረትባቸው ተወስኗል።

በዚሁ መሰረት በአብረሃም ተረፈ መዝገብ የተካተቱ ተጠርጣሪዎች ጉዳይ በፌዴራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ሶስተኛ ወንጀል ችሎት በመዝገብ ቁጥር 227015 የሚታይ ይሆናል።

በአቶ ሞቲ ደሬሳ መዝገብ በችሎቱ ያልቀረቡ ሁለት ሰዎችን ጨምሮ ሰባት ግለሰቦች ጉዳይም በፌዴራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት 20ኛ ወንጀል ችሎት ይታያል።

በከፍተኛው ፍርድ ቤት አራተኛ ወንጀል ችሎት የዛሬ ውሎ ሲታይ የነበረው የተጠርጣሪዎቹ መዝገብ ተዘግቶ በ3ኛና በ20ኛ የወንጀል ችሎት በግድያ ወንጀል የክስ ሂደታቸውን እንዲከታተሉ ትዕዛዝ ተሰጥቷል።

ምንጭ፦ ኢዜአ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ሼር ‼️

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ቤቶች ልማትና ቢሮ በከተማ አስተዳደሩ ያሉ ብልሹ አሰራሮችን ለመቅረፍ የሚደረገዉ እንቅስቃሴ የቀበሌ ቤቶች ላይ እና በጋራ መኖሪያ ቤቶች ላይ መረጃዎችን በማሰባሰብ ላይ ይገኛል፡፡

ህጋዊ ዉል የሌላቸዉ፣ የጋራ መኖሪያ ቤት ደርሷቸዉ የቀበሌ ቤት ያለቀቁ፣ የተዘጉ ቤቶች፣ ዉል የሌላቸዉ፣ ክፍያ የማይፈፅሙ፣ ወደ ግል የዞሩ፣ የፈረሱ፣ የተቃጠሉ፣ የተሸነሸኑ እና መረጃ የሌላቸዉ የቀበሌ ቤቶች እንዲሁም በጋራ መኖሪያ ቤቶች ላይም በተደጋጋሚ እጣ ላይ የሚገቡ፣ ቤት እያላቸዉ ባለ እድል የሆኑ፣ የተዘጉ፣ ለህገ-ወጥ ተግባር እየዋሉ ያሉ እና መረጃ የሌላቸዉ የጋራ ቤቶች ስታስተዉሉ በቀጣይ ለእድለኞች ከለሚተላላፉ የጋራ መኖሪያ ቤቶች ጋር ለማካተት የኖዋሪዉ ህብረተሰብ ጥቆማ አስፈላጊ በመሆኑ ከላይ የተዘረዘሩትና መሰል ጉዳዮች ሲያጋጥማችሁ በዚህ የአጭር የስልክ ቁጥር 6813 በመጠቆም የዜግነት ግዴታዎን ይወጡ፡፡

በነፃ የሥልክ ጥሪ በ6813 ይደዉሉ፡፡

የአዲስ አበባ ቤቶች ልማትና አስተዳደር ቢሮ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#የግጭት ትርፉ፦

🔹ለቅሶ
🔹ስቃይ
🔹መከራ
🔹ረሀብ
🔹ስደት
🔹ሞት
🔹የሚወዱትን ማጣት
🔹ችጋር
🔹በሽታ
🔹እልቂት

ማስተዋል የሚችል ያስተውል!!
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#Update የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ 5ኛው የሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት 4ኛ ዓመት የስራ ዘመን 11ኛ መደበኛ ስብሰባውን ማካሄድ ጀምሯል፦

አጀንዳዎችም የሚከተሉት ናቸው፡፡

1. የም/ቤቱን 4ኛ አመት የስራ ዘመን 10ኛ መደበኛ ስብሰባ ቃለ ጉባኤ መርምሮ ማጽደቅ፣

2. የምግብ እና የመድኃኒት አስተዳደር ረቂቅ አዋጅ መርምሮ ለሚመለከተው ቋሚ ኮሚቴ መምራት፣

3. የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ጽ/ቤት ማቋቋሚያ አዋጅ ለማሻሻል የቀረበ ረቂቅ አዋጅ መርምሮ ለሚመለከተው ቋሚ ኮሚቴ መምራት፣

የሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት
@tsegabwolde @tikvahethiopia