TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
59.4K photos
1.51K videos
215 files
4.12K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
አብዴፓ‼️

ኢንጂነር #አይሻ_መሃመድ የአፋር ብሄራዊ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ/አብዴፓ/ ሊቀ መንበር ሆነው ተመርጠዋል።

አብዴፓ የአፋር ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አቶ #አወል_አርባ ደግሞ የድርጅቱ ምክትል ሊቀመንበር ሆነው ተመርጠዋል።

አብዴፓ የፓርቲውን ስራ አስፈፃሚዎች ኮሚቴ አባላት ምርጫንም አካሂዷል። በዚህም መሰረት፦

1.ኢ/ር አይሻ መሃመድ
2.አቶ አወል አርባ
3.አቶ ኢብራሂም ዑመድ
4.አቶ አህመድ ሱልጣን
5.ወ/ሮ ዘሃራ ዑመድ
6.አቶ መሃመድ ሃሠን
7.አቶ መሃመድ ጠይብ
8.አቶ ጣሃ አህመድ
9.አቶ ዓሊ ሁሴን ዌኢሳ
10.አቶ ኤላማ አቡበከር
11.አሊ ሁሴን ዑመር የስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባል በመሆን ተመርጠዋል።

ከህዳር 23 ጀምሮ በሰመራ ሲካሄድ የቆየው የአብዴፓ 7ኛ መደበኛ ድርጅታዊ ጉባዔም ባለፉት አመታት በክልሉ በነበረው አፈፃፀም እና በወደፊት የልማት አቅጣጫዎች ላይ ያተኮረ ባለ 9 ነጥብ የአቋም መግለጫ በማውጣት ተጠናቋል።

©fbc
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ዶ/ር አብይ🔝ጠ/ሚር ዐቢይ አሕመድ ዛሬ ህዳር 30 ቀን 2011 በባሌ ለሚያካሂዱት የልማት እንቅስቃሴዎች ጉብኝት የቀድሞ የእንግሊዝ ጠ/ሚርና የቶኒ ብሌር ተቋም ዋና ሥራ አስፈፃሚ የሆኑትን ቶኒ ብሌርን ተቀበሉ።

#PMOEthiopia
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ🔝የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ(IoT) ተማሪዎች ትላንት ህዳር 29/3/2010 ከምሽቱ 1:30 ጀምሮ ከሰሞኑን በቤንሻንጉል ጉምዝ ክልል እና ኦሮሚያ ክልል አዋሳኝ አካባቢዎች በጠፋው የሰው ህይወት የተሰማቸውን ሀዘን ሲገልፁ አምሽተዋል። ድርጊቱንም አውግዘዋል።

©ፈይሳ(ሀዋሳ TIKVAH-ETH)
@tsegabwolde @tikvahethiopia
TIKVAH-ETH TIPS!

ከምግብ በኋላ #ማድረግ_የሌሉብን 5 ነገሮች፦

1- ሻይ መጠጣት

ምግብ እየበላንም ሆነ ከበላን በኋላ ወዲያው ሻይ መጠጣት የሚመከር አለመሆኑን የተለያዩ ጥናቶች በማሳየት ላይ ይገኛሉ፡፡ ምክኒያቱም ሻይ ውስጥ የሚገኘው ታኒክ አሲድ የተባለው ውህድ ሰውነታችን የምንመገበው ምግብ ውስጥ የሚገኘውን አይረን መጠቀም እንዳይችል
ያደርገዋል፡፡ ይህም የሰውነታችንን 85 በመቶ አይረን የመውሰድ አቅም ይቀንሰዋል፡፡ ስለዚህ እየበላን መጠጣት ሚኖርብን ከሆነ የምንመገበው ምግብ በተለየ መልኩ በ አይረን የበለፀገ መሆን ይኖርበታል፤ ወይንም ደግሞ እስከ 30 ደቂቃ የሚደርስ ፋታ ልንወስድ ይገባናል፡፡

2- መተኛት

ብዙዎቻችን ከተመገብን በኋላ አረፍ ማለትን እናዘወትራለን፡፡ ይሁንንና ይህ ተግባር አደገኛ ለሆነ ሁኔታ ሊያጋልጠን ይችላል ምክኒያቱም በምንተኛበት ወቅት ምግብ የሚፈጩት ኬሚካሎች በ መሬት ስበት ምከኒያት ወደ ላይኛው የሰውነታችን ክፍል ይሳባሉ ይህ አጋጣሚ አሲዳማ የሆነውን ውህድ ወደ መተንፈሻ አካላችን ሊወስደው በመቻሉ ሳቢያ ለከፍተኛ ቃር ያጋልጣል፡፡

3- ገላ መታጠብ

ምግብ እንደበላን ወደዚያውኑ ገላችንን መታጠብ የሰውነታችንን የመፍጨት ሂደት ያስተጓጉለዋል፡፡ ምክኒያቱም ደማችን እየተፈጨ ያለውን ምግብ ለተለያ የሰውነታችን ክፍል የማቀበል ስራውን ትቶ የሰውነታችንን የሙቀት መጠን ወደ መቆጣጠር የሚሸጋገር በመሆኑ ነው፡፡
ስለዚህ ጥናቶች ከበሉ በኋላ ቢያንስ እስከ 30 ደቂቃ ያህል መጠበቅ ይመከራል ይላሉ፡፡

4- ፍራፍሬ መመገብ

ምንም እንኳን ፍራፍሬ ለጤና እጅግ ጠቃሚ ቢሆንም ሳይንስ ከምግብ በፊት እንጂ ከምግብ በኀዋላ አትውሰዱ ይላል፡፡ ምክኒየቱም ከሌሎቸ ምግቦች አንፃር ፍራፍሬዎች በቀላሉ የሚፈጩ ስለሆኑ ከምግብ በኋላ ወዲያውኑ ከተወሰዱ የመፍጨት ሂደታቸው ከመስተጓጎሉ ጋር አንጀት ጋር መድረስ ባለባቸው ጊዜ መድረስ ያቅታቸዋል ይህ የተራዘመ ጉዞ እንዲመረዙ ከማረጉም በላይ አንጀታችን ውስጥ የሚገኘውን ምግብም የመመረዝ ዓቅም እንዲኖራቸው ያደርጋል፡፡

5- ቀዝቃዛ ውሃ መጠጣት (በረዶ)

ሰውነታችን ምግብ በቀላሉ ለመፍጨት የውሃ እገዛ የሚያስፈልገው ቢሆንም በረዶ ሲሆን ግን በተቃራኒው ስራውን ያስተጓጉልበታል ይህም የሆነበት ምክኒያት በቅዝቃዜው የተነሳ የምግቡን ይዘት ሊቀይረው በመቻሉ ነው፡፡ ስለዚህ መሀከለኛ ደረጃ ላይ ያለን ውሃ መጠጣት ይመከራል፡፡

ምንጭ፦ Information Science and Technology(በኢ.ፕ.ኤ የቀረበ)
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ባሌ ዞን🔝የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር #አብይ_አህመድ በባሌ ዞን ጉብኝት በማድረግ ላይ ናቸው። ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከብሪታኒያ የቀድሞ ጠቅላይ ሚኒስር ቶኒ ቢሊየር ጋር በመሆን ነው በዞኑ በክላስተር የለሙ እርሻዎችን እየጎበኙ ያሉት።

ምንጭ፦ ፋና ብሮድካስቲንግ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ሀረር!

ከተሽከርካሪ ፍሰት ነፃ የሆነና የአካል ብቃት እንቅስቃሴ በሀረር ከተማ ተካሄደ። የክልሉ ጤና ጥበቃ ቢሮ ከጤና ጥበቃ ሚኒስቴር ጋር በመተባበር በተዘጋጀው በዚሁ ዝግጅት ላይ የክልሉ ከፍተኛ አመራሮችና የተለያዩ የህብረሰብ ክፍሎች የተሳተፉበት ነበር።

በሀረር ከተማ ከራስ ሆቴል እስከ ስላሴ ቤተክርስቲያን አደባባይ ድረስ ለተሽከርካሪ ፍሰት ዝግ በማድረግ ሰዎች በእግር እንዲጎዙና ስፖርታዊ እንቅስቃሴ እንዲያደርጉ የተመቻቸ ሲሆን ተሳታፊዎችም ተላላፊ ካልሆኑ ካበሽታዎች መካከል ስኳርና የደም ግፊትን የነፃ ምርመራ እንዲያደርጉ ተደርጓል።

"የአካል ብቃት እንቅስቃሴ በማድረግ ተላላፊ ያልሆኑ በሽታዎችን በጋራ እንከላከል ጤናማ የአኗኗር ዘይቤ ለጤናማ ህይወት " በሚል መሪ ቃል በተካሄደው በዚሁ ከተሽከርካሪ ፍሰት ነፃ እንቅስቃሴ ላይ የሀረሪ ክልል ጤና ጥበቃ ቢሮ ኃላፊ አቶ ኢብሳ ኢብራሂም በዚሁ ወቅት እንደተናገሩት ዘወትር የአካል ብቃት እንቅስቃሴዎችን በማድረግ ጤና የአኗኗር ዘይቤን በመከተል ተላላፊ ካልሆኑ በሽታዎች እራሳችንን ልንጠበቅ ይገባል ሲሉ መልዕክት አስተላልፈዋል።

ለመጀመሪያ ጊዜ በተካሄደው ከተሽከርካሪ ፍሰት ነፃ በሆነው የእግር ጉዞና ስፖርታዊ እንቅስቃሴ ዝግጅት ላይ የተሳተፉ በሰጡት አሰተያየት በጋራ ስፖርታዊ እንቅስቃሴና የእግር ጉዞ በማድረጋቸው እንዲሁም የጤናቸውን ሁኔታ ለማወቅ በመቻላቸው ደስተኛ መሆናቸውንና በቀጣይም በወሩ መጨረሻ በሚካሄደው ተመሳሳይ ዝግጅት ላይ ለመሳተፍ ቁርጠኛ ስለመሆናቸው ተናግረዋል።

ምንጭ፦ ተሾመ ሀይሉ(ሀረር TIKVAH-ETH)
@tsegabwolde @tikvahethiopia