TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.8K photos
1.44K videos
207 files
3.99K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#ኢትዮጵያ ከእንግዲህ ወደሗላ አትሄድም...
@tsegabwolde @tikvahethiopia
አሰላ🔝አክቲቪስት #ጃዋር_መሀመድ በዛሬው ዕለት በአሰላ ከተማ (አሰላ ስታዲየም) ደማቅ አቀባበል ተደርጎለታል። ከከተማው ነዋሪዎችም የተለያዩ ስጦታዎች ተበርክቶለታል።

©JE(አሰላ TIKVAH-ETH)
@tsegabwolde @tikvahethiopia
Fake News Report Alert‼️

ይህ ዛሬ አንዳንድ ሰዎች ሼር ሲያረጉት የነበረው "ነገር" የዋሽንግተን ፖስትን ገፅ በመውሰድ ከዛም ፌክ ዜና በማስገባት የተቀነባበረ ነው። የዋሽንግተን ፖስት የኢትዮጵያ ሪፖርተር #ፖል_ሺም ይባላል።

ምንጭ፦ ጋዜጠኛ ኤልያስ መሰረት(AP)
@tsegabwolde @tikvahethiopia
Alert‼️

"የትግራይን ህዝብ ከሌላው ብሔር ለማጋጨት የማይቆፍሩት ድንጋይ የለም። ዛሬ ደግም እውነታውን በphotoshop ቀይሮ ህዝብ ለማጣላት እየጣሩ ነው። ይህ ውሸት መሆኑን ህዝብ እንዲረዳ እንፈልጋለን!"

©Ya
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ሰበር ዜና‼️

የአፋር ብሄራዊ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ (አብዴፓ) የመከላከያ ሚንስትሯን ኢንጂነር አይሻ መሀመድን ሊቀመንበር አድርጎ መረጠ።

©Zinabu Tunu
@tsegabwolde @tikvahethiopia
አዲስ አበባ -ዝርፊያ018_sd 99_9 Trim.m4a
9.3 MB
አዲስ አበባ⁉️ በአዲስ አበባ ከተማ የዝርፊያው ነገር አሳሳቢ ደረጃ ላይ ደርሷል። ሰዎች በቀን በጠራራ ፀሀይ እየተዘረፉ ናቸው። ከሰሞኑን ግን አዲስ አበባ #ወጣ ያሉ ዝርፊያዎችን አስተናግዳለች። ኢትዮጵፒካሊንክ የተባለ የሬድዮ ዝግጅት ከሰሞኑን በአዲስ አበባ የተፈፀሙትን ዝርፊያዎች ዳሷቸዋል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ባህር ዳር የሚዘጉ መንገዶች!

ነገ እሁድ በባሕር ዳር ከተማ #የተመረጡ_ጎዳናዎች ይዘጋሉ፡፡ በባሕር ዳር ከተማ ‹‹ጤናማ የአኗኗር ዘይቤ ለጤናማ ህይወት›› በሚል መሪ ሃሳብ ከመኪና ፍሰት የፀዱ መንገዶች ቀን ከጠዋቱ 12፡00 እስከ 6፡00 ድረስ ይከበራል፡፡ በዚህ መርሃ ግብር ልዩልዩ የህብረተሰብ ክፍሎች የአካል ብቃት እንቅስቃሴ በማድረግ እና በብስክሌት በመጓዝ ጤንነታቸውን የሚጠብቁበት ስፖርታዊ እንቅስቃሴዎች ይካሄዳሉ፡፡

መርሃ ግብሩ የሚካሄድባቸውን ቦታዎች፦

• ምድብ አንድ፡- ከዲፖ እስከ ግራንድ ሆቴል አካባቢ

• ምድብ ሁለት፡- ከግዮን ሆቴል አደባባይ እስከ ጊዮርጊስ ቤተክርስትያን

• ምድብ ሶስት፡- ከጊዮርጊስ አደባባይ እስከ ኢትዮ-ስታር ሆቴል፡፡ በዕለቱ ከአሮጌው ዲፖ እስከ ርዕሰ መስተዳድር አደባባይ ከተሸከርካሪ ነፃ ይደረጋል፡፡

ምንጭ፦ አብመድ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
የአማራ ክልል ፖሊስ‼️

‹‹በጭለጋ እና አካባቢው ተፈጥሮ የነበረው ግጭት ወደ አንጻራዊ ሰላም እየተመለሰ ነው፡፡›› የአማራ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ዘላለም ልጃለም
.
.
ከሰሞኑ በማዕከላዊ ጎንደር ጭልጋ እና አካባቢው ላይ ተፈጥሮ የነበረው ግጭት ወደ አንጻራዊ ሰላም እየተመለሰ መሆኑን ኮሚሽነር #ዘላለም_ልጃለም ለአማራ ቴሌቪዥን አስታውቀዋል፡፡

ለግጭቱ ምክንያት በመሆን ያባባሱ 53 ተጠርጣሪዎች #በቁጥጥር ስር መዋላቸውንም ገልጸዋል፡፡

በቀጣይ ሰላምን ለማስፈን ከአካባቢው የሃይማኖት አባቶች እና ከሀገር ሽማግሌዎች ጋር እየሰሩ እንደሆነም ኮሚሽነር ዘላለም ልጃለም ተናግረዋል፡፡

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#Update ጂንካ ዩኒቨርሲቲ አዲስ ገቢ ተማሪዎችን በመቀበል ላይ ነው። 1 ሺህ 500 የሚሆኑት አዳዲስ የዩኒቨርሲቲው ተማሪዎች ዛሬ ሲገቡ የዞኑ አስተዳደርን ጨምሮ የዩኒቨርሲቲው ፕሬዝዳንት፣ አመራሮችና ሌሎች የህብረተሰብ ክፍሎች አቀባበል አድርገውላቸዋል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ🔝የተቋሙ ተማሪዎች ከሰሞኑን በቤንሻንጉል ጉምዝ ክልል እና ኦሮሚያ ክልል አዋሳኝ አካባቢዎች በጠፋው የሰው ህይወት የተሰማቸውን ሀዘን ገልፀዋል። ድርጊቱንም አውግዘዋል።

©Kiyu
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ሚናጋባህ!

"ንግድ ባንክ ከሚያስገነባው ባለ 48 ፎቅ ሕንፃ በቀን ሰራተኝነት ከተቀጠሩ አንዱን "በቀን ስንት #ይከፍሏችኋል?" ብዬ ብጠይቀው አጠገቡ የነበረ #ቻይናዊ "ሚናጋባህ" ብሎ ቀልቤን ገፈፈው። በCSCEC የሚገነባው ሕንፃ ከ6 ቢሊዮን ብር በላይ ይፈጃል ተብሏል።"

©እሸት በቀለ(የጀርመን ድምፅ ራድዮ ጋዜጠኛ)
@tsegabwolde @tikvahethiopia
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
አዲስ አበባ ከተሽከርካሪ ነፃ የሚሆኑ መንገዶች-Car Free Day-Ethiopia!
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ቄሱ የአሲድ ጥቃት ተፈፀመባቸው‼️

በመካከላኛው አሜሪካ የኒካራጓ ዋና መዲና በሆነችው ማናጓ የ59 ዓመቱ ቄስ በተፈፀመባቸው የአሲድ ጥቃት ክፉኛ እንደተጎዱ ተዘገበ። ቄስ #ሚጌል_ጉቫራ ጥቃቱ የተፈፀመባቸው በሜትሮፖሊታን ካቴድራል ውስጥ አማኞች የሰሩትን ኃጢያት ኑዛዜ ተቀብለው ሲጨርሱ ነበር።

በአሲዱ ፊታቸው፣ ክናዳቸው ላይና ትከሻቸው አካባቢ ቃጠሎ ያጋጠማቸው ሲሆን የህክምና ክትትል እያደረጉ ይገኛሉ።

በወቅቱ በቤተክርስቲያኑ ውስጥ የነበሩ አምላኪዎች ፖሊስ በአፋጣኝ እስከሚደርስ አሲዱን በመወርወር የደፋችባቸውን ሴት በቁጥጥር ስር አውለዋታል።

ፖሊስ እንዳለው ጥቃት አድራሿ ጥቃቱን ለማድረስ ምን እንዳነሳሳት እያጣራ ሲሆን፤ የአገሪቱ መገናኛ ብዙሃን እንደዘገቡት ግን ጥቃት አድራሿ በማህፀን ውስጥ ያለ ሽል የተሳለበት ካናቴራ ለብሳ የነበረች የሩሲያ ዜጋ ናት።

ቤተክርስቲያኑ ፀረ መንግሥት እንቅስቃሴዎች መደረግ ከጀመሩበት ካለፈው ሚያዚያ ጀምሮ እንቅስቃሴውን በመግታት ረገድ የሚጫወተው ሚና እዚህ ግባ የሚባል አይደለም ተብሎ በመንግሥት ወቀሳ ሲደርስበት ቆይቷል። ጥቃቱም ሆን ተብሎ የተፈፀመ እንደሆነ ፖሊስ አስረድቷል።

በተቃዋሚዎችና በፀጥታ ኃይሎች መካከል በተፈጠረ ግጭት በመቶዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ሕይወታቸው አልፏል፤ በዚህም ወቅት ቤተክርስቲያኗ ለመንግሥት ተቃዋሚዎች መሸሸጊያ ሆናለች በሚል በመንግሥት ደጋፊዎች ተከቦ ነበር።

ባለፈው የፈረንጆቹ ሐምሌ ወርም የኒካራጓ ቀሳውስት መንግሥትን ለመገልበጥ ለሚታገሉ ተቃዋሚዎች መጠጊያ ሆነዋል ሲሉ ፕሬዚደንት ኦርቴጋ ተችተዋል።

"ቀሳውስቱ መፈንቅለ መንግሥት ለማካሄድ አይተኙም" ሲሉም ፕሬዚደንቱ አክለው ተናግረዋል።

ምንጭ፦ BBC
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ለሚመለከተው አካል‼️

ከሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ የድህረ ምረቃ ተማሪዎች።

የፍትሕ ጥያቄ በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ በተደጋጋሚ እኛ የድህረ ምረቃ ተማሪዎች ያነሳን ቢሆንም ምንም አይነት ተገቢ መላሽ እንልተገኘም፡፡

ነገሩ እንዲህ ነው፦

በመላው የኢትዮጵያ ዩኒቨርሲቲዎች የ A ውጤት መነሻ 85 እንደሆነ እየታወቀ ነገር ግን የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ሴኔት ለድህረ ምረቃ ተማሪዎች ከ90 በላይ የሚል ፍታዊነት የጎደለው ህግ አውጥቶ ተማሪውን እየጎዳና ከተወዳዳሪነት እያገለለ ቆይቷል፡፡

ነገር ግን እኛ ተማሪዎች አግባብነት እንደሌለው ለማሳየትና የፍትሕ ጥያቄያችን ይመለስ በማለት ይህ ፍትሐዊነት የጎደለው ህግ ከወጣበት ጊዜ ጀመሮ ስንታገል ቆይተናል፡፡

ለአብነት ያክል እስከ ኢፌዴሪ ትምህረት ሚኒስተር (MoE) ድረስ ጥያቄው የሄደ ሲሆን ት/ት ሚኒስተሩ ችግሩን አምኖበት ጥያቄውን የዩኒቨርስቲው ሴኔት እንዲፈታው አቅጣጫ አስቀምጠው ነበር። ከብዙ ትግል በሁዋላ የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ እራሱን ፈትሾ ችግሩን አምኖ የA መነሻን እንደሌሎች ዩኒቨርሲቲዎች ከ 85 እንዲጀመር አፀደቀ፡፡

በዚህን ጊዜ የድህረ ምረቃ ተመሪዎች ጥያቄና ቅሬታ ተፈታ ተባለ፡፡ እርግጥ ነው የኛ የ3 አመት ትግል ፍሬ አፍርቷል ነገረ ግን እንደገና የኛን የ ነባር የ ድህረ ምረቃ ተማሪዎች ስሜት የሚነካ ውሳኔ ተወሰነ፡፡

አዲስ የወጣው የውጤት አሰጣጥ ነባር የድህረ ምረቃ ተመሪዎችን(ጥያቄውን ስንጠይቅ የነበርነዉን) አያካትትም ሲባል እኛ ነባር የ ድህረ ምረቃ ተማረዎች ህዳር 26 ጥዋት ደማቅ ሰላማዊ ሰልፍ አካሄደን ከሰአት መድረክ ተዘጋጅቶልን የተወያየንበት ሲሆን አምባገነናዊ በሆነ መልኩ የሴኔቱን ውሳኔ ብቻ አንፀባርቀው የተመሪውን ቅሬታ ሳይቀበሉ ቀርተዋል(academic vice president)፡፡

ይሁን እንጂ የኛ ጥያቄ መልስ አሰከሚያገኝ ድረስ ወደ ሁዋላ አንልም።

ፍትህ ለሁሉም!!!
ከ ቅሬታ አቅራቢዎች ኮሚቴ።
@tsegabwolde @tikvahethiopia