TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.6K photos
1.43K videos
206 files
3.96K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
ከጅማ🔝

"ዛሬ የጅማ ኢንደስትሪ ፓርክ በድምቀት ተመርቋል። በስነ ስርአቱ ላይ የኢትዮጵያ፤ ጅቡቲ እና የ ሱዳን መሪዎችን ጨምሮ ዲ/ን ዳንኤል ክብረት፥ ወ/ሮ ፍሬሕይወተ/ኢትዮ ቴሌኮም፥ ጋዜጠኛ ግሩም እና ሌሎችም ተገኝተው ነበር።"

©GDG(TIKVAH-ETH)
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ዶ/ር ዐብይ🔝ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ኅዳር 29 ቀን 2011 ዓ.ም ለጅማ ዩኒቨርሲቲ የሕክምና ተመራቂዎች በምረቃ ሥነ ሥርዓት ያስተላለፉት መልእክት።

#PMOEthiopia
@tsegabwolde @tikvahethiopia
Audio
ሰማያዊ ፓርቲ!
ሰማያዊ ፓርቲ‼️

ሰማያዊ ፓርቲ በኢትዮጵያ የተጀመረው የለውጥ ሂደት፣ በዞንና በወረዳ ደረጃ #አልወረደም አለ፡፡ ሰላምን በማናጋት የመንግሥትና የገዥው ፓርቲ ባለሥልጣናት የነበሩና ዛሬም በሥልጣን ላይ የሚገኙ ሰዎች፣ ዋና ተዋንያን ናቸው ሲልም ፓርቲው ከሷል፡፡ መንግሥት ህግ #የማስከበር ሥራውን እንዲያጠናክና ሕዝቡም እንዲተባበር ጥሪ አቅርበዋል፡፡

ምንጭ፦ VOA አማርኛው አገልግሎት
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#Udate የሚዲያ ሕጎች የውይይት መድረክ ከሁሉም ተፉካካሪ የፖለቲካ ፖርቲ እና የሚዲያ ተቋማት አመራሮች ጋር ዛሬ በካፒታል ሆቴል ውይይት ተካሂዷል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ቢቢሲ ኢሳትን በተመለከተ የሰራጨው #የተሳሳተ ዘገባ ማረሙን ለኢሳት የላከው ደብዳቤ!
ኢሳት‼️

የእንግሊዙ የዜና ማሰራጫ ቢቢሲ ኢሳትን በተመለከተ የሰራጨውን #የተሳሳተ ዘገባ ማረሙን ለኢሳት በጻፈው ደብዳቤ ገለጸ።

የቢቢሲ አለም አቀፍ አገልግሎት ዳይሬክተር ጄሚ አንገስ ኢሳት ለጻፈው የቅሬታ ደብዳቤ ትናንት በላኩት ምላሽ ቢቢሲ ባለፈው ወር ባሰራጨው ዘጋባ ኢሳት ሆን ብሎ #የዘር_ግጭት የሚጭር ቪድዮ #አዘጋጅቶ አሰራጭቷል በሚል በቢቢሲ ያቀረበው ዘገባ ያስተላለፈው መልዕክት ትክክል አለመሆኑን በመገንዘብ ማስተካከያ መደረጉን በደብዳቤያቸው ገልጸዋል።

በዚህም መሰረት በእንግሊዝኛ፣ አማርኛ፣ ትግርኛ እና ኦሮምኛ ቢቢሲ ያቀረበውን ዘገባ ማስተካከሉን አስታውቀዋል።

በማስተካከያውም የተባለው ቪድዮ የተዘጋጀው በሌላ አካላት እንደነበርና ኢሳት ወዲያውኑ ቪድዮውን ማውረዱንና #ይቅርታ መጠየቁን በቢሲ በማስተካከያው ላይ ጨምሯል።

ዳይሬክተሩ ቢቢሲ ማስተካከያ ለማድረግ በመዘግየቱ ይቅርታ ጠይቀው በዚሁ እንግሊዝኛ ተናጋሪ የቢቢሲ ጋዜጠኛ ተሰራ ያሉትን የተሳሳተ ዘገባ ኢሳትን ለመጉዳት ያለመ ነው የሚል እምነት እንደሌላቸው እምነታቸውን ገልጸዋል።

ምንጭ፦ የኢትዮጵያ ሳተላይት ቴሌቪዥን
@tsegabwolde @tikvahethiopia
እየመጡ ነው🛫ጋዜጠኛ ሳዲቅ አህመድን እና ጋዜጠኛ አብዱረሂም አህመድን ወደ ኢትዮጵየ እየመጡ ነው። ነገ ማለዳ አቀባበል እንደሚደረግላቸው ተሰምቷል።
@TIKVAHETHIOPIA @TSEGABWOLDE
ጅማ🔝ጠ/ሚር ዶ/ር #ዐቢይ_አሕመድ ከሱዳንና ከጂቡቲ መሪዎች ጋር በጅማ የነበራቸዉን ጉብኝት አጠናቀቁ::

#PMOEthiopia
@tsegabwolde @tikvahethiopia