አሰላ🔝በሌሎች የኦሮሚያ ክልል ከተሞች የተደረጉ ሰልፎች ጋር ተመሳሳይ ሀሳብ ያለው ሰልፍ ዛሬ በአሰላ ከተማ ተደርጓል።
@tsegabwolde @tikvahethiopia
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ጅማ ዩኒቨርሲቲ🔝በተለያዩ የሀገሪቱ አካባቢዎች በተለይም በኦሮሚያ እና ቤንሻንጉል ጉምዝ ክልል አዋሳኝ አካባቢዎች በጠፋው የሰው ህይወት ያዘኑ የጅማ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ጥቁር ልብስ በመልበስ እና ምግብ ባለመመገብ ሀዘናቸውን ገልፀዋል።
@tsegabwolde @tikahethiopia
@tsegabwolde @tikahethiopia
ጅማ ዩኒቨርሲቲ🔝የመማር ማስተማር ሂደቱ መቋረጡን ተከትሎ ዛሬ 8:00 ከፌደራል ከመጡ የስራ ሀላፊዎች ጋር በመሆን ከተማሪዎች ጋር ውይይት ሊያደርግ ቀጠሮ ይዟል።
@tsegabwolde @tikvahethiopia
@tsegabwolde @tikvahethiopia
አዳማ‼️
በህገወጥ መንገድ ሲዘዋወር የነበረ 10ሺህ 200 የአሜሪካን ዶላር በአዳማ ከተማ #በቁጥጥር ሥር ማዋሉን የከተማው ፖሊስ መመምሪያ አስታወቀ።
የመምሪያው የህዝብ ግንኙነት ባለሙያ ሳጅን ወርቅነሽ ገልሜቻ እንደገለጹት ዶላሩ በህገወጥ መንገድ በግለሰቦች ሲዘዋወር ትናንት ማታ 3፡30 ላይ ሕብረተሰቡ ባደረገው ጥቆማ ሊያዝ ችሏል።
ገንዘቡ የሰሌዳ ቁጥሩ 2-17781 (አ.አ) በሆነ የቤት አውቶሞቢል ተሽከርካሪ ተጭኖ ከአዳማ ወደ አዲስ አበባ ከተማ በፍጥነት በመጓዝ ላይ እያለ በኦሮሚያ ፖሊስ ኮሌጅ ልዩ ስሙ “ናማልድ” በተባለ አካባቢ በቁጥጥር ስር ውሏል።
ከመኪናው ጋር በተያዙ ሁለት ግለሰቦች ላይ በፖሊስ በኩል ምርመራ እየተካሄደ መሆኑን ሳጅን ወርቅነሽ አመልክተዋል።
ህገወጥ የገንዘብ ዝውውሩን በተቀናጀ መልኩ ለመከላከልና ለመቆጣጠር ህብረተሰቡ እያደረገ ያለውን ትብብር በቀጣይም አጠናክሮ እንዲቀጥል አሳስበዋል።
ምንጭ:- የኢትዮጵያን ዜና አገልግሎት

ብርጋዴር ጄነራል አሳምነው ፅጌ‼️
‹‹በማዕከላዊ ጎንደር ዞን ጭልጋ አካባቢ የተፈጠረውን ግጭት ለማረጋጋት የክልሉ መንግስት እየሰራ ነው፡፡›› የአማራ ክልል የሰላም ደህንነት ግንባታ ቢሮ ኃላፊ ብርጋዴር ጀኔራል #አሳምነው_ጽጌ
.
.
ከትላንት በስቲያ በተፈጠረው ግጭት በንብረት ላይ ጉዳት ደርሷል፡፡ 34 ቤቶች ወድመዋል፤ 6 የእህል ወፍጮዎች ተቃጥለዋል ነው ያሉት ብርጋዴር ጄኔራል አሰማነው ጽጌ፤ ጭልጋ አካባቢ የተፈጠረውን ግጭት ለማረጋጋት የክልሉ መንግስት እየሰራ ነውም ብለዋል፡፡
የአማራ ክልል የሰላም ደህንነት ግንባታ ቢሮ ኃላፊ ብርጋዴር ጀኔራል አሳምነው ጽጌ ለአማራ ቴሌቪዥን በስልክ እንደገለጹት ለግጭቱ ምክንያቶች የሆኑት በአካባቢው የሌሎች እጅ እንዳለበትና የቅማንት አስተዳደር ራሱን ለማስተዳደር በህገመንግስቱ የተሰጠውን መብት ላለመጠቅም መፈለጉ ናቸው፡፡
በዚህም የመንገድ መዘጋት እና የሰው መታገት እያጋጠመ ነው፡፡ይህንን ችግር ለመቅረፍ ደግሞ እየሰራን ነው ብለዋል፡፡ስለሆነም የተዘጉ መንገዶችን መክፈት እና የማህበረሰቡን ሰላም መመለስ ላይ ትኩረት ተሰጥቶ እየተሰራ መሆኑን ተናግረዋል፡፡
ነዋሪዎች ዘላቂ የሰላም መፍትሄ እንዲያገኙ የክልሉ መንግስት እንቅስቃሴ እያደረገ መሆኑንም ጠቁመዋል፡፡ኃላፊው እንደገለጹት ከዚህ በፊትም በአካባቢው ተደጋጋሚ ግጭቶች በማጋጠሙ፣ ተሸከርካሪዎች እንዳይንቀሳቀሱ ሲደረግ መቆየቱንም ገልጸዋል፡፡
ትላንት ከማዕከላዊ ጎንደር ዞን በተገኘው መረጃ መሰረት ከጥቃቱ ጋር በተያያዘ 153 ሰዎች በተጠርጣሪነት ተለይተዋል፡፡
ምንጭ፦ አብመድ

#UpdateSport የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌደሬሽን በአምስተኛ ሳምንት የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ባህር ዳር ከነማ ከመቀሌ 70 እንደርታ ጋር በመቀሌ ከተማ የሚደርጉትን ጨዋታ አራዘመ።
@tsegabwolde @tikvahethiopia
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ወንጀል ነክ መረጃ‼️
ምንጩ ያልታወቀ ገንዘብ ያከማቸው ሾፌር በእስራት እና በገንዘብ መቀጮ ተቀጣ፡፡ ተከሳሽ #አንገሶም_ገብረሩፋኤል የሙስና ወንጀሎች አዋጅ ቁጥር 881/2007 ዓ.ም አንቀጽ 21/ለ/ የተመለከተውን ድንጋጌ በመተላለፍ ከሚያገኘው ገቢ ጋር የማይመጣጠን ምንጩ ያልታወቀ ገንዘብ በማከማቸት የሙስና ወንጀል ተከሷል፡፡
የወንጀሉ ዝርዝር እንደሚያስረዳው ተከሳሽ በፌደራል ፖሊስ ወንጀል መከላከል ዘርፍ የፈጥሮ ደራሽ ዳይሬክቶሬት አሽከርካሪ በመሆን
በሚኤሶ፣ አዋሽና ናዝሬት ከ2004 ዓ.ም ጀምሮ በሁለት ሺህ ዘጠኝ መቶ ብር ደሞዝ ተቀጥሮ ሲሰራ በነበረበት ወቅት በመንግስት ስራው ወይም በሌላ መንገድ ከሚያገኘው ወይም ሲያገኝ ከነበረው ህጋዊ ገቢ ጋር በማይመጣጠን ሁኔታ ከኢትጵያ ንግድ ባንክ ሚኤሶ እና ጀሞ
ቅርንጫፍ በተለያዩ ጊዜያት በስሙ በከፈተው የቁጠባ ሂሳብ ውስጥ ብር 542,087.74 (አምስት መቶ አርባ ሁለት ሺህ ሰማንያ ሰባት ብር ከሰባ አራት ሳንቲም ) እንዲሁም በአንበሳ ኢንተርናሽናል ባንክ 225,100.00 (ሁለት መቶ ሀምሳ አምስት ሺህ ብር) በአጠቃላይ ግምቱ 767,187.74 (ሰባት መቶ ስልሳ ሰባት ሺህ አንድ መቶ አንድ መቶ ሰማንያ ሰባት ብር ) ያለአግባብ ያከማቸ በመሆኑ በፈጸመው ምንጩ ያልታወቀ ገንዘብ በማከማቸት የሙስና ወንጀል ተከሶ ፍርድ ቤት ቀርቧል፡፡
የፌዴራል ዐቃቤ ህግም በጉዳዩ ላይ የሰዎችና የሰነድ ማስረጃዎችን በማጠናከር ለፍርድ ቤቱ አቅርቧል፡፡
የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 2ኛ ችሎት የግራ ቀኙን ክርክርና መዝገቡን መርምሮ ተከሳሽ ከዚህ ቀደም የወንጀል ሪከርድ አለመኖሩን እንደ ቅጣት ማቅለያነት በመያዝ በአንድ ዓመት ከሁለት ወር እስራት እና አምስት መቶ አስራ ሰባት ሺህ አንድ መቶ ሰማንያ ሰባት ብር እንዲወረስ በማለት ወስኗል፡፡
ምንጭ፦ የፌደራል ጠቅላይ አቃቤ ህግ

ሀዋሳ🔝በሀዋሳ ከተማ #የነዳጅ_እጥረት በመከሰቱ አሽከርካሪዎች መቸገራቸውን ለTIKVAH-ETH በላኩት መልዕክት ገልፀዋል። የሚመለከተው አካል ችግሩን እንዲፈታ ጥሪ አቅርበዋል።
@tsegabwolde @tikvahethiopia
@tsegabwolde @tikvahethiopia
አርባ ምንጭ🔝በነዳጅ እጥረት ምክንያት ረጃጅም የተሽከርካሪ ሰልፎችን ማየት ከጀመሩ 3 ሳምንት ሊሆናቸው እንደሆነ በአርባ ምንጭ ከተማ የሚገኙ የTIKVAH-ETH ቤተሰብ አባላት መግረውናል።
@tsegabwolde @tikvahethiopua
@tsegabwolde @tikvahethiopua
#update ከደቂቃዎች በፊት ከጠ/ሚሩ ፕረስ ሴክረታሪ ቢሮ ለጋዜጠኞች በተላለፈው መልእክት የሴክረታሪው ሀላፊዋን "ወይዘሮ" ወይም "ወይዘሪት" ማለት በመተው "ቢልለኔ ስዩም" ብቻ ብላችሁ ተጠቀሙ ተብሏል።
©ኤልያስ መሰረት
@tsegabwolde @tikahethiopia
©ኤልያስ መሰረት
@tsegabwolde @tikahethiopia
ከአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ የተሰጠ መግለጫ‼️
የሕዝባችንን ሰላምና ደኅንነት የማስጠበቅ ኃላፊነቱን መንግስት በአግባቡ ሊወጣ ይገባል!
***
ሰሞኑን በአማራ «ክልል» በማዕከላዊ ጎንደር ዞን ጭልጋ አካባቢ በተፈጠረ ግጭት በደረሰው የሰው ሕይወት መጥፋትና የንብረት መውደም የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ–አብን የተሰማውን ጥልቅ ኃዘን እየገለፀ ለተጎጅ ቤተሰቦች መፅናናትን እንመኛለን፡፡ አብን እስካሁን በደረሰው መረጃ መሰረት ከ50 በላይ ቤቶች ተቃጥለዋል፤ በርካቶች ቆስለዋል፡፡ እንዲሁም ውድ የሆነው የሰው ሕይወት አልፏል፡፡ ከሌላ አካል ተልዕኮ ተቀብለው በመጡና ራሳቸውን በቅማንት የማንነት ኮሚቴ ስም ባደራጁ እና ይሄን የጥፋት ተልዕኮ ተሸክመው በአማራ «ክልል» በሚገኙ የመንግሥት ተቋማት በሚሰሩ ግለሰቦች በአማራ ሕዝብ ላይ የተፈፀመ ጥቃት ከመሆኑም ባሻገር የቅማንት የማንነት ጉዳይ በክልሉ ምክር ቤት ተመልሶ ያደረና የመጨረሻ እልባት የተሰጠው በመሆኑ በሕዝባችን ላይ በተደጋጋሚ ጥቃት ሊያስፈፅም የሚችል ነገር አለመኖሩን አብን ያምናል፡፡ የፌደራል መከላከያ ሰራዊትም ግጭቱ በተከሰተበት አቅራቢ ቢኖርም ለሕዝባችን ተገቢውን ከጥቃት የመከላከል እርምጃ እየወሰደ አይደለም፡፡
ስለሆነም የ«ክልሉ»ም ሆነ የፌደራል መንግስት በሕዝባችን ላይ በተደጋጋሚ የሚፈፀመውን ጥቃት የማስቆምና የሕዝባችንን ሰላምና ደኅንነት የማስጠበቅ ኃላፊነቱን በሚገባ ሊወጣ ይገባል፡፡
በድርጊቱ ፈፃሚዎችና ጠንሳሾች ላይም የማያዳግም እርምጃ እንዲወሰድ አብን እየጠየቀ መላ ሕዝባችን ከመቼውም ጊዜ በላይ አንድነቱን በማጠናከር መሰል በኅልውናው ላይ የሚፈፀሙ ጥቃቶችን ለመመከት ዝግጁ ሆኖ እንዲጠብቅ አብን ያስገነዝባል፡፡
የፌደራልና የ«ክልሉ» መንግሥት የሕዝባችንን ሰላምና ደኅንነት ለማረጋገጥ በሚያደርጉት ጥረት በሙሉ አብን ሙሉ ድጋፍ እንደሚያደርግ እየገለፅን ይህ ሳይሆን ቀርቶ ግን በሕዝባችን ላይ የሚፈፀመውን ጥቃት መንግሥት ማስቆም ካልቻለ አብን መላውን አማራ በማንቀሳቀስ ራሱን የመከላከል ተፈጥሯዊ መብቱን እንዲጠቀም የሚያደርግ መሆኑን እንገልፃለን፡፡ በድጋሚ ለተጎጅ ቤተሰቦች መፅናናትን እንመኛለን።
አንድ አማራ ለሁሉም አማራ፥ሁሉም አማራ ለአንድ አማራ!
ኅዳር 26/2011 ዓ/ም
የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ
አዲስ አበባ፥ሸዋ፣ ኢትዮጵያ

አሶሳ‼️
በቤኒሻንጉል ጉሙዝ እና በኦሮሚያ ክልል አጎራባች አካባቢዎች ላይ ተፈጥሮ በነበረው ግጭት ተጠርጣሪ ናቸው ያላቸውን አምስት የክልሉ ከፍተኛ እና መካከለኛ አመራሮች በቁጥጥር ስር ማዋሉን የፌደራል ፖሊስ አስታወቀ።
የፌደራል ፖሊስ ግብረ ሀይል በዛሬው ዕለት ባካሄደው ተጠርጣሪዎችን የመያዝ ዘመቻ ነው ተጠርጣሪዎቹ ቁጥጥር ስር የዋሉት።
በቁጥጥር ስር ከዋሉት ውስጥ የክልሉ አስተዳደርና ፀጥታ ጉዳዮች ምክትል ሃላፊና የቀድሞ አሶሳ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ እንደሚገኙበት ግብረ ሀይሉ አስታውቋል።
እነዚህ ተጠርጣሪዎች በሰኔ 17ቱ የአሶሳ ከተማ ግጭት እንዲሁም በኦሮሚያና ቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል አጎራባች አካባቢዎች ላይ ተፈጥሮ በነበረው ግጭት የችግሩ አባባሾች ሆነው የተጠረጠሩ ናቸው ብሏል ፌደራል ፖሊስ።
ተጨማሪ ተጠርጣሪዎችን በቁጥጥር ስር የማዋል ሂደቱ ተጠናክሮ እንደሚቀጥልም ግብረ ሀይሉ አስታውቋል።
ምንጭ፦ etv