TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.9K photos
1.44K videos
207 files
3.99K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#update ፌደራል ፖሊስ-አልታገስም አለ⬆️

ወደ ሀገር ቤት የሚገቡ የድርጅት አመራሮችን ለመቀበል በሚደረግ ቅድመ ዝግጅት ላይ በወጣቶች መካከል እየተፈጠረ ያለውን ግጭትና ህገወጥ ተግባር ከዚህ በኋላ #እንደማይትገስ የፌደራል ፖሊስ አስታወቀ።

የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ጀነራል ዘይኑ ጀማል ከአርበኞች ግንቦት 7 ንቅናቄ ሊቀመንበር ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ እና ከኦሮሞ ነጻነት ግንባር የስራ አስፈጻሚ አባል አቶ ኢብሳ ነገዎ ጋር በመሆን መግለጫ ሰጥተዋል።

በመግለጫው ላይም ኮሚሽነር #ዘይኑ_ጀማል፥ በትናንትናው እለት እና ዛሬ ወደ ሀገር ቤት የሚገቡ የድርጅት አመራሮችን ለመቀበል በሚደረግ ቅድመ ዝግጅት ላይ በወጣቶች መካከል ግጭት መፈጠሩን አስታውቀዋል።

በአቶ ዳውድ ኢብሳ የሚመራውን #የኦነግ ቡድን ለመቀበል እየተደረገ ባለ ቅድመ ዝግጅት ወቅት ወጣቶች የድርጅቱን አርማ ለመስቀል ዝግጅት እያደረጉ ነበር፤ ይህንን የከለከላቸው አካል የለም ያሉት ኮሚሽነር ዘይኑ፥ ሆኖም ግን አስፋልትን ጨምሮ የተለያዩ ተቋማትን እንዳያቀልሙ ተከልክው፤ ይህንንም ተወያይተን እሺ ብለው ተቀብለው ትተው ነበር ብለዋል።

ሆኖም ግን ማንም ያልፈቀደላቸው አካላት የእነሱን ባንዲራ አውርደው የሌላ ለመስቀል ሲሉ ግጭት ተፈጥሯል ሲሉም ገልፀዋል።

ግጭቱ ለማንም ጠቃሚ አይደለም ያሉት ኮሚሽነር ዘይኑ፥ ችግሩን #በውይይት መፍታት ሲቻል ወደ አላስፈላጊ ግጭት መግባት ተገቢ አይደለም ሲሉም ተናግረዋል።

ፖሊስ የህግ የበላይነትን የማስከበር ሀላፊነት ስላለበት ከዚህ በኋ እንዲህ አይነት #ግጭቶችን በትእግስት እንደማያልፍም ኮሚሽነር ዘይኑ አሳስበዋል።

የአርበኞች ግንቦት ሰባት ንቅናቄ ሊቀመንበር ፕሮፌሰር #ብርሃኑ_ነጋ፥ የዴሞክራሲ ስርዓትን እንገንባ ብለን ስንሰና ስርዓቱን ለመገንባት የሚያስፈልግ እነዚህን ባህሪያትን ተቀብለን ካልተነሳን ግን ስርዓቱን መገንባት እንችልም ብለዋል።

የዴሞክራሲ ስርዓት ግንባታ ውስጥ ልዩነቶችን መቀበል የግድ ነው ያሉት ፕሮፌሰር ብርሃኑ፥ ልዩነቶቹ ደግሞ ሀሳቦችን፣ አርማዎችን እና ባንዲራዎችን ሊያጠቃልል ይችላል ብለዋል።

ትናንትና እና ዛሬ በአዲስ አበባ የተስተዋሉ ችግሮች ደግሞ ከዚህ ጋር የሚፃረሩ ነው ያሉት ፕሮፌሰር ብርሃኑ፥ ማንኛውም አካል ስሜቴን ይገልፅልኛል ያለውን አርማ የመያዝ እና የማውለብለብ #መብት አለው ሲሉም ተናግረዋል።

የኦሮሞ ነጻነት ግንባር የስራ አስፈጻሚ አባል አቶ #ኢብሳ_ነገዎ በበኩላቸው፥ ሰሞኑን በአዲስ አበባ እና አካባቢዋ የተስተዋለው ችግር #ተቀባይነት የሌለው መሆኑን አንስተዋል።

ወጣቱም ከዚህ አይነት እንቅስቃሴዎች ሊቆጠብ እንደሚገባም አቶ ኢብሳ ጥሪ አስተላልፈዋል።

አሁን ላይ እየታየ ያለው ግጭት እና ያልተገባ #ፉክክር ድርጅታቸውን የማይወክል መሆኑንም ነው አቶ ኢንብሳ ተናግረዋል።

©Fbc
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update ኦነግ(ABO)፣ አግ 7...⬇️

በሀገሪቱ የሚገኙ 7 የፖለቲካ ፓርቲዎች ሰሞኑን በአዲስ አበባና በሌሎች የሀገሪቱ አካባቢዎች የተከሰቱ #ግጭቶችን አወገዙ።

የፖለቲካ ፓርቲ መሪዎቹ አሁን ላይ በሀገሪቱ በተለይም በአዲስ አበባ እየታየ ያለው ወቅታዊ ግጭት ላይ መስከረም 6 እና 7 ውይይት ካደረጉ በኋላ ዛሬ ከሰዓት በኋላ የጋራ #መግለጫ ሰጥተዋል።

የጋራ መግለጫውን የሰጡት የፖለቲካ ፓርቲወችም የኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረንስ (ኦፌኮ)፣ ኦሮሞ ነፃነት ግንባር (ኦነግ)፣ የኦሮሞ ዴሞራሞክራቲክ ግንባር፣ የኦሮሞ አንድነት ለነጻነት፣ የኦሮሞ አንድነት ግንባር፣ ሰማያዊ ፓርቲ እና የአርበኞች ግንቦት ሰባት ለአንደነትና
ዴሞክራሲ ንቅናቄ መሆናቸውም ነው የተገለጸው።

የፖለቲካ ፓርቲ መሪዎቹ ባለፉት 2 ቀናት ባደረጉት #ግምገማ መሰረትም ግጭቱ አሳሳቢና አሳዛኝ መሆኑን ነው በጋራ መግለጫቸው ያመለከቱት።

በዚህም በሰዎች ህይወት፣ አካልና ንብረት ላይ የደረሰውን ጉዳት በጽኑ ማውገዛቸውን ነው በጋራ መግለጫቸው ያስታወቁት።

የግጭቱ #ተዋናያን እና ከጀርባ ሆነው ግጭቱን የሚያስተባበሩ የውጭና የሀገር ውስጥ ሃይሎች ከዚህ ድርጊታቸው በአስቸኳይ እንዲቆጠቡም በጋራ መግለጫቸው አሳስበዋል።

#ወጣቱም በማወቅም ሆነ ባለማወቅ በራሱ መስዋትነት የመጣውን ሃይል #ለመቀልበስ ከሚሰሩ ሀይሎች ጎን #እንዳይሰለፍም ጥሪያቸውን አስተላልፈዋል።

በዚህ አስቸጋሪ ወቅት በሀገሪቱ የመጣውን ለውጥ የመምራት ሃለፊነት የተጣለባቸው የመንግስት አካላትም የሀገርንና የህዝብን ደህንነት ለመጠበቅ ሲሉ እንዲህ ዓይነቱ ግጭት #ከመከሰቱ በፊት የመከላከል እርምጃ እንዲወስዱ እና ወንጀለኞችን #በአስቸኳይ ለህግ እንዲያቀርቡ ጠይቀዋል።

አሁን ላይ በሀገሪቱ ሀሳብን በነጻነት ለማራመድ የሚያስችል ሰላም መስፈኑና ለዘመናት የታገሉለትና ሁሉንም ለማስተናገድ የሚያስችል የፖለቲካ ምህዳር መፈጠሩንም አስረድተዋል።

ስለሆነም ልዩነቶችን በሰላማዊ መንገድ ለመፍታት የሚያስችል የዴሞክራሲ ባህልን በጋራ ማዳበሩ ጠቃሚ መሆኑ ነው በመግለጫው የተመላከተው።

ልዩነቶችን በሃይል ለመፍታት የሚደረጉ ጥረቶች ለማንኛውም አካል ጠቃሚ ያለመሆኑን በመግለጫቸው ያመላከቱት የፖለቲካ ፓርቲ መሪዎቹ፥ ሀገሪቱን የፍትህ፣ የዴሞክራሲና የአንድነት ተምሳሌት ለማድረግ መስራት እንደሚገባም በመግለጫው ጠቁመዋል።

ለሰላም፣ ዴሞክራሲና ለህዝቦች አንድነት መጠናከር የበኩላቸውን ለማበርከት ዝግጁ መሆናቸውንም የፖለቲካ ፓርቲ መሪዎቹ በጋራ መግለጫቸው አስታውቀዋል።

ለዚህም ለፖለቲካ ፓርቲ አባሎቻቸው፣ ደጋፊዎቻቸውና ለመላው ህዝብ ጥሪያቸውን አስተላልፈዋል።

©fbc
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update መገናኛ ብዙሃን  ከጥላቻና መለያየት ይልቅ በኢትዮጵያ ሰላምና አንድነት ላይ ትኩረት ሰጥተው እንዲሰሩ የሰላም ሚኒስቴር ጥሪ አቀረበ። “ሚዲያ ለሰላም” በሚል አገር አቀፍ የሚዲያና ኮሙኒኬሽን አካላት የፓናል ውይይት ትላንት ተካሂዷል። በኢትዮጵያ ዘላቂ ሰላም ለማስፈን የመገናኛ ብዙሃን ባለሙያዎች ስራቸውን በትኩረት መስራት እንዳለባቸው የሰላም ሚኒስትሯ ወይዘሮ #ሙፈሪያት_ካሚል አሳስበዋል። መገናኛ ብዙሃን በህዝቦች መካከል #ግጭቶችን ከመፍጠርና ከማራራቅ ይልቅ አንድነትና መተባበርን በሚያጠናክሩ ጉዳዮች ላይ በትኩረት ሊሰሩ ይገባል ብለዋል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update በአገሪቱ #አንዳንድ አካባቢዎች የተነሱ #ግጭቶችን ለማስቆም የሃይማኖት አባቶችና የአገር ሽማግሌዎች ሚና ከፍተኛ መሆኑ ይታወቃል። ነገር ግን ይህንን ሚናቸውን እንዲወጡ ምቹ ሁኔታ ባለመፈጠሩና #ተቀባይነታቸውም በመቀነሱ የሚጠበቅባቸውን ኃላፊነት እየተወጡ አለመሆኑን ባሙያዎች ተናግረዋል።

ሙሉውን አንብቡት...
https://telegra.ph/የሐይማኖት-አባቶችና-የአገር-ሽማግሌዎች-ሰላም-የመፍጠር-ሚና-ኮስሷል-01-14
ወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ🔝

የሰላም ሚኒስቴር ከወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ ጋር የግጭት አፈታትና የሰላም ባህል ግንባታን ላይ በጋራ ለመስራት በሰላም ሚኒስቴር የሰላም ግንባታ ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ወ/ሮ #አልማዝ_መኮንን እና የወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ የምርምርና ማኅበረሰብ አገልግሎት ም/ፕሬዚዳንት ዶ/ር #ሲሳይ_ሸዋአማረ አማካኝነት የስምምነት ሰነድ ተፈራርሟል።

የሰላም ባህልን ማሳደግና የሚፈጠሩና የተፈጠሩ #ግጭቶችን መፍታት አንዱ የማኅበረሰብ አገልግሎት ስራችን ነው ያሉት ዶ/ር ሲሳይ ግጭቶችን ሳይንሳዊ በሆነ መንገድ በማጥናትና የመፍትሔ ሀሳቦችን ለውሳኔ ሰጪ አካላት በማቅረብ ለዘላቂ መፍትሄ እንደሚሰሩ ተናግረዋል፡፡

የሰላም ግንባታ ዘርፍ ሚኒስቴር ዴኤታ ወ/ሮ አልማዝ መኮንንም ዩኒቨርሲቲው በሰላም ባህል ግንባታ ላይ አለመግባባቶችን በሰላማዊና ዴሞክራሲያው መንገድ ለመፍታት የሚችል ማኅበረሰብ መፍጠር የሁሉም ምሁራን ድርሻ በመሆኑ ሊበረታታ ይገባዋል ብለዋል፡፡

ምንጭ፦ የሰላም ሚኒስቴር
©ዳንኤል መኮንን(ከወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ)
@tsegabwolde @tikvahethiopia
አንድነት ለፍትህና ዴሞክራሲ ፓርቲ፦

#ኢትዮጵያዊነትን የሚፈታተኑ #ችግሮችን ለመከላከል ህዝቡ ለአንድነቱ ፀንቶ መታገል እንዳለበት አንድነት ለፍትህና ለዲሞክራሲ ፓርቲ አሳሰበ፡፡

ከዘረኝነትና ከማንነት ጋር ተያይዞ የሚከሰቱ #ግጭቶችን በአገራችን ታይቶ በማይታወቅ ሁኔታ የዜጎች #መፈናቀልና ሞት መፈጠሩ አሳስቦኛል ያለው ፓርቲው መንግስት ከሰብዓዊ መብትና ከፀጥታ ጋር ተያይዘው ያሉ ህጎች ባአስቸኳይ ሊያስፈፅም ይገባል ብሏል።

በሃገሪቱ እዚህም እዚያም ያሉ #ግጭቶችን የሚፈጥሩ ግለሰቦችንም ሆነ ፖለቲከኞች የመለየት ስራ የህዝቦችም ሃላፊነት ነው ያለው ፓርቲው በየትኛውም አካል ጥፋት ህዝቡ መጎዳት እንደሌለበት ገልጿል።

መንግስት #ህጎችን በማስከበር ዜጎች በፈለጉት ክልል በነፃነት የመኖርና የመንቀሳቀስ መብታቸውን የማስከበር ህገ መንግስታዊ ሃላፊነቱን መወጣት እንዳለበት ተገልጿል።

ምንጭ፦ ebc
@tsegabwolde @tikvahethiopia
የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር የከፍተኛ ትምህርት ተቋማትን አደጋና #ግጭቶችን የመከላካልና የመቋቋም አቅም ለማጎልበት እየሰራ መሆኑን አስታወቀ። በሚኒስቴሩ የአስተዳደርና ሪፎርም ዋና ዳይሬክተር አቶ ጌታቸው ተፈራ እንደገለጹት በዩኒቨርሲቲዎች ግጭት፣ የንብረት መውደም የሰው ህይወት መጥፋትና ሌሎች ድንገተኛ አደጋዎች እየተከሰቱ ይገኛል። የአደጋ ስጋት አስተዳደር በዕቅድና ዝግጁነት መምራት አስፈላጊ በመሆኑም የከፍተኛ ትምህርት ተቋም የሰው ሰራሽና ተፈጥሯዊ አደጋዎችን የመከላከልና የመቋቋም አቅማቸውን የማጎልበት ስራ እየተሰራ ነው ብለዋል።

Via #ኢዜአ
@tsegabwolde @tikvahethiopia