TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.8K photos
1.44K videos
207 files
3.99K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#update በናይጄሪያ #ሰላማዊ_ምርጫ መካሄዱን የአፍሪካ ህብረት የምርጫ ታዛቢ ቡድን መሪ አቶ #ኃይለማሪያም_ደሳለኝ አስታወቁ፡፡ ባሳለፍነው ቅዳሜ በናይጄሪያ የተካሄደው ምርጫ ሰላማዊ እንደ ነበር የአፍካ ህብረት የናይጀሪያ ምርጫ ታዛቢ ቡድን መግለጹ ተነግሯል፡፡ ከምርጫ #ግብዓቶች ጋር በተያያዘ ለአንድ ሳምንት በተራዘመውና በሳለፍነው ቅዳሜ በተካሄደው የናይጄሪያ ምረጫ ላይ አስተያየቱን በመስጠት የህብረቱ ታዛቢ ቡድን የመጀመሪያው ነው ተብሏል፡፡

Via EPA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ወላይታ ሶዶ🔝

መንግስት በወላይታ ሶዶ ከተማ ዙሪያ ህገወጥ ናቸው #ባላቸው ግንባታዎች ላይ የማፍረስ #እርምጃ መውሰዱን ተከትሎ የተፈጠረው አለመረጋጋት ረገብ ብሏል። ከተማዋም ወደቀደመ #ሰላማዊ እንቅስቃሴዋ እየተመለሰች ነው።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ኒውዚላንድ🔝

በኒውዚላንድ #ክሪስትቸርች ከተማ ሁለት መስጊዶች ላይ ጥቃት በመፈፀም 49 #ሰላማዊ ዜጎችን ህይዎት በማጥፋት ከተጠረጠሩ ግለሰቦች ውስጥ አንደኛው በዛሬው ዕለት ፍርድ ቤት ቀርቧል።

ድርጊቱን የፈፀመው ተጠርጣሪ ብሬንቶን ታራንት የሚባል ሲሆን፥ በዜግነትም አውስትራሊያዊ መሆኑ ነው የተገለፀው።

የ28 ዓመቱ ብሬንቶን ታራንት በዛሬው ዕለት ፍርድ ቤት የቀረበውም በነፍስ ግድያ ወንጀል ተጠርጥሮ ነው ተብሏል።

ፅንፈኛ #ቀኝ_ዘመም_አሸባሪ የተባለው ተጠርጣሪ #ብሬንቶን_ታራንት ፍርድ ቤቱ ያቀረበበትን ክስ በዝምታና በአርምሞ አድምጧል ነው የተባለው ።

ፍርድ ቤቱ የተጠርጣሪውን የይግባኝ መብት በመከልከል ጉዳዩን በድጋሜ ለመመልከት ለፊታችን ሚያዝያ 5 ቀጠሮ ይዟል።

በሽብር ጥቃቱ የተጠረጠሩ ሁለት ተጨማሪ ግለሰቦች በቁጥጥር ስር የዋሉ ሲሆን ፥ ሁለቱም ከዚህ በፊት በምን አይነት የወንጀል ተጠርጥረው  ፍርድ ቤት ቀርበው የማያውቁ መሆኑ ተገልጿል።

የኒውዚላንድ ጠቅላይ ሚኒስትር #ጃሲንዳ አርደርን ድርጊቱን የሽብር ጥቃት በማለት ያወገዙ ሲሆን፥ በጥቃቱ የተጎዱ ዜጎችን ማንነት  የመለየት ስራ እየተሰራ መሆኑን አስታውቀዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ተጠርጣሪዎች  ድርጊቱን ለመፈፀም የተጠቀሙበት #መሳሪያ ዘመናዊና የተሻሻለ መሆኑን በመጥቀስ፥ የፀጥታ አካላት ባደረጉት #እርብርብ በፍጥነት በቁጥጥር ስር በማዋል የሚደርሰውን እልቂት ለመታደግ ተችሏል ብለዋል።

ምንጭ፦ ቢቢሲ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
የዛሬው ውሎ...

የዛሬው #የሀረማያ_ዩኒቨርሲቲ ውሎ #ሰላማዊ እንደነበር የTIKVAH-ETH ቤተሰብ አባላት ተናግረዋል። በግቢው ውስጥ መከላከያ ሰራዊት፣ የኦሮሚያ ክልል ልዩ ሀይል እና ፌደራል ፖሊስ ጥበቃ እያደረጉ እንደሚገኙ ጨምረው ገልፀዋል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ሰላም እና መረጋጋት እየታየ ነው...

በአማራ ክልል የፀጥታ ችግር ተፈጥሮባቸው የነበሩ የኦሮሞ ብሔረሰብ አስተዳደር እና በሰሜን ሸዋ ዞኖች #መረጋጋትና #ሰላማዊ ሁኔታ እንደሚታይ ተገለፀ።

የአማራ ክልል ሰላም እና ደህንነት ግንባታ ቢሮ ምክትል ኃላፊ ኮሎኔል አለበል አማረ እንደተናገሩት፥ የፀጥታ ችግሩ ተከስቶባቸው በነበሩ በሁሉም አካባቢዎች መረጋጋት እና ሰላማዊ ሁኔታ ታይቶባቸዋል።

የአካባቢውን ሰላማዊ እንቅስቃሴ ወደ ነበረበት ለመመለስ የፀጥታ አካላት ከህብረተሰቡ ጋር እየሠሩ እንደሚገኙ የገለፁት ኮሎኔል አለበል፥ አጥፊዎችን በሕግ ተጠያቂ ለማድረግ ጥረት እየተደረገ መሆኑ ተነግሯል።

አሁንም ቢሆን ግጭቱን ወደ ሌሎች አካባቢዎች ለማዛመት እና ችግሩን ለማባባስ የተለያዩ ያልተጣሩ መረጃዎችን የሚያሰራጩ ግለሰቦች በመኖራቸው ህዝቡ ከወዲሁ መጠንቀቅ እንዳለበት መልዕክት አስተላልፈዋል።

ግጭቶቹ የተከሰቱባቸው አካባቢ ነዋሪዎች በበኩላቸው፥ ችግር ተፈጥሮባቸው የነበሩ አብዛኛዎቹ አካባቢዎች የተሻለ መረጋጋት ላይ እንደሚገኙ ተናግረዋል።

እንደ አስተያት ሰጭዎቹ፥ ተፈጥሮ በነበረው ችግር ምክንያት ተደናግጠው አካባቢያቸውን ለቀው ወደ ፈረዶ ውኃ እና መሀል ሜዳ ሸሽተው የነበሩ የአጣየ ከተማ ቀበሌ 01፣ 02 እና 03 ነዋሪዎች ወደ ቀያቸው እየተመለሱ ነው፡፡

በማጀቴም ከትናንት የተሻለ ሰላማዊ ሁኔታ እንደሚታይ ተጠቁሟል።

ምንጭ፦ አብመድ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ከጅማ🔝

"የጅማ ዩኒቨርሲቲ የህክምና ተማሪዎች በድጋሜ #ሰላማዊ ሰልፍ ላይ ነን፡፡ ጥያቄአችን #ሳይመለስ አናቆምም!!" YZ ke JU(ጅማ ዩኒቨርሲቲ)

@tsegabwolde @tikvahethioia
የፊታችን ሀሙስ ሰልፍ ሊደረግ ነው...

#ጌታቸው_አሰፋ ሽልማት እንጅ #እስር አይገባውም' በሚል መሪ ቃል የፊታችን ሀሙስ በመቐለ ከተማ #ሰላማዊ_ሰልፍ እንደሚያደርግ የትግራይ ወጣቶች ማህበር አስታውቋል።

Via ELU/ድምጺ ወያነ/
@tsegabwolde @tikvahethiopia
የፊታችን አርብ ሰልፍ ሊደረግ ነው...

/Wolaita zone administration public relation office/

በወላይታ ዞን የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች #ሰላማዊ_ሰልፍ ለማድረግ ሲያቀርቡት የነበረው ጥያቄ ይሁንታ አግኝቷል።

ከዚህ ቀደም የህብረተሰቡን ሠላምና ፀጥታ ለማስጠበቅ ሲባል ሰልፉ ላልተወሰነ ጊዜ መራዘሙ ይታወሳል።

የወላይታ ሀገር ሽማግሌዎች፣ ምሁራን፣ ዬላጋ አደረጃጀት፣ የክብር ተሰናባች የሠራዊተ አባላት እና የንግድ ማህበራት ምክር ቤቶች ሠላማዊ ሰልፍ ለማካሄድ በግንቦት 5/2011 ዓ ም በጠየቁት መሠረት ሰላማዊ ሰልፉ መፈቀዱ ታውቋል።

ሰልፉ በግንቦት 9/2011 ዓም ከጧቱ 12:00 ሰዓት እስከ 4:00 ሰዓት ድረስ የሚካሄድ መነሻው አዲሱ የወላይታ ዞን አስተዳደር ሆኖ በፍሬው አልታዬ ጎዳና የወላይታ ጉታራ አዳራሽን አቋርጦ በወላይታ ሶዶ ሁለገብ ስታዲየም የሚዘልቅ መሆኑ ታውቋል።

ከነዚህ ከተፈቀዱ ቦታዎች ውጪ ሰላማዊ ሰልፍ ባለማድረግ እና ከፀጥታ አካላት ጋር በመቀናጀት ህብረተሰቡ የተለመደውን ትብብር እንዲያደርግ የዞኑ አስተዳደሩ አሳስቧል።

/Wolaita zone administration public relation office/

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ፎቶ👆በዛሬው ዕለት በኦሮሚያ ክልል የተለያዩ ከተሞች መምህራን #ሰላማዊ_ሰልፍ ሲያካሂዱ ውለዋል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#ጎንደር #Gondar

ጎንደር ከተማ #ሰላማዊ መሆንዋን ምክትል ከንቲባ በሪሁን ካሣዉ ገልፀዋል። ትላንት አነስተኛ ውዝግብ ከተማ ውስጥ መፈጠሩን ያነሱት ምክትል ከንቲባው የነበረውን አነስተኛ ዉዝግብ ተጠቅመዉ ረብሻ ለማስነሳት የሞከሩ እና አንዳንድ ያልተገባ ነገር ለመፈፀም የሞከሩ፤ ድርጊታቸዉን ሳይፈፅሙ በቁጥጥር ስር አውለናቸዋል፤ #ከጀርባቸዉ ማን እንዳለም እያጣራን ነዉ ሲሉ ለጀርመን ራድዮ ተናግረዋል።

Via #DW
🗞ቀን ሃምሌ 2/2011 ዓ/ም
@tsegabwolde @tikvahethiopia