TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.6K photos
1.43K videos
206 files
3.97K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
ሜጀር ጀኔራል ክንፈ ዳኘው‼️

መርማሪ ፖሊስ ሜጀር ጀኔራል #ክንፈ_ዳኘውን በተመለከተ እስካሁን በሰራው የምርመራ ስራ አገኘኋቸው ያላቸውን ተጨማሪ ማስረጃዎችን ለፍርድ ቤት አቅርቧል።

ፖሊስ በዛሬው እለት ግለሰቡን በተመለከተ ከዚህ ቀደም ካቀረባቸው ማስረጃዎች በተጨማሪነት አዳዲስ ያላቻውን ነው ያቀረበው።

በዚህም በ2003 ዓ.ም በሜቴክ ስም ከተለያዩ ተረፈ ምርቶች ወይም ቆሻሻ የናፍጣ ነዳጅ ማምረቻ ፋብሪካን ለመግዛት ያለ ምንም ጨረታ ኬዲቪ ከተባለ የጀርመን ኩባንያ ጋር የ8 ሚሊየን ዩሮ ግዥ ውል በመፈጸም፥ ከዚህ ውስጥ 4 ሚሊየን 800 ሺህ ዩሮ ለኩባንያው
እንዲፈጸም በማድረግ እንደጠረጠራቸውና ከዚህ ጋር የተያያዙ በርካታ የሰነድ ማስረጃዎች መሰብሰቡን ጠቅሷል።

በተጠቀሰው ዓ.ም ሜቴክ ከኢኳቶሪያል ቢዝነስ ግሩፕ ጋር በመመሳጠር ከመመሪያ ውጭና ያለ ግዥ ፍላጎት የ22 ሚሊየን ብር ዋጋ ያላቸው 20 ተሽከርካሪዎች ግዥ እንዲፈጸምና ለተፈጸመው ግዥ ክፍያ እንዲፈጸም ለኮርፖሬት ኢንቨስትመንትና ፋይናንስ ማኔጅመንት አላግባብ ትዕዛዝ ሰጥተዋል በሚል የተጠረጠሩ፤ ተጠርጣሪው የሜቴክ ዋና ዳይሬክተር በነበሩበት ወቅት ኮርፖሬሽኑ ከተቋቋመበት አላማ ውጭ ስልጣናቸውን አላግባብ በመጠቀም #የኢምፔሪያል_ሆቴል ግዥ በ71 ሚሊየን ብር ከአክሰስ ሪል ስቴት ባለቤት አቶ ኤርሚያስ አመልጋ እንዲፈጸም በማድረግ፣ ባለ አምስት
ወለል ህንጻ በ15 ሚሊየን ብር ከያማሉክ ኢንተርናሽናል ሃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር ግዥ እንዲፈጸም በማድረግና በማፅደቅ።

ባለ አራት ወለል ህንጻ በ24 ሚሊየን 56 ሺህ ብር ከአቶ አለሙ ደምሴ ግዥ እንዲፈጸም በማድረግ፣ ባለ አንድ ወለል የመኖሪያ ህንጻ በ5 ሚሊየን 700 ሺህ ብር ከአቶ ጌታቸው አቃኔ ግዥ እንዲፈጸም በማድረግ፣ ባለ ሁለት ወለል ህንጻ የመኖሪያ ህንጻ በ8 ሚሊየን 700 ሺህ ብር ከአቶ ሙላቱ ረዳ እና ከወይዘሮ ሄለን በለጠ ግዥ እንዲፈጸም በማድረግ እና ባለ ሶስት ወለል ህንጻ በ12 ሚሊየን 700 ሺህ ብር ከጌት ፋም ሃላፊነቱ የተወሰነ ማህበር ባለቤት አቶ ጌታሁን በሻህ ግዥ እንዲፈጸም ትዕዛዝ በመስጠት፥ ውሎችን በማፅደቅ ግዥ እንዲፈጸምና የህዝብና የመንግስት ሃብት እንዲባክን በማድረግ ከቆሻሻ የጄት ነዳጅ ማምረቻ ፋብሪካ ግንባታ ከግዥ መመሪያ ውጭ ጨረታ ሳይወጣ ኢ ቪ ጂቲዲሲ ዌስት ቱ ኢነርጅ ከተባለ የአሜሪካ ኩባንያ ጋር የ347 ሚሊየን 948 ሺህ የአሜሪካ ዶላር ውል ስምምነት ኮሎኔል ሙሉ ወልደገብርኤል 2005 ዓ.ም ላይ ውል እንዲዋዋል በማድረግና ውሉን በማፅደቅ፣ የውጭ ምንዛሪ እንዲፈቀድ ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ኤል ሲ በማስከፈት፣ ለባንክ አገልግሎት የሚውል ክፍያ 5 ሚሊየን 616 ሺህ 648 ብር ከ60 ሳንቲም የግንባታ ስራ ውል ስምምነት ከተፈጸመ በኋላ ውሉ ባልታወቀ ምክንያት በመቋረጡና ስራው ሳይሰራ ያለ አግባብ የመንግስት ገንዘብ እንዲባክን በማድረግ ለታላቁ የህዳሴ ግድብ የተከለለ ቦታ ላይ የሚገኘውን ጫካ ምንጣሮ ስራ ከኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ሃይል ኮርፖሬሽን ስራውን በመውሰድና 2 ቢሊየን 92 ሚሊየን 303 ሺህ 113 ብር ከ22 ሳንቲም በመቀበል፥ ስራውን በሌሎች ንዑስ ተቋራጮች ያለ ምንም ጨረታ በመስጠት የምንጣሮ ስራው በአግባቡ ተመንጥሮ ሳያልቅ ገንዘብ ወጪ በማድረግ ክፍያ በመፈፀምና ቀሪ ገንዘብ የት እንዳለ ባለመታወቁ ለግል ጥቅምና ሌሎች እንዲጠቀሙ በማድረግ ከዚህ ባለፈም የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ሃይል ኮርፖሬሽን ኮርፖሬሽኑ ከተቋቋመበት አላማ ውጭ እንዲሁም ከፋይናንስ ህግ ውጭ በሆነ ሁኔታ በነሃሴ ወር 2003 ዓ.ም ለአቤራ ኪነ ጥበባት ማዕከል ሃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር በስፖንሰር መልክ 536 ሺህ ብር በመስጠትና 306 ሺህ ብር በብድር መልክ መስጠትና የተበደረው ተቋም ገንዘብ ያልተከፈለ መሆኑ፥ የኮርፖሬሽኑ አባላት ያልሆኑትን አባላት እንደሆኑ በደብዳቤ በመግለጽ ለተጠርጣሪ #ፍጹም_የሽጥላ_በቀለ እና ለአቶ #ተስፋሁን_ሰብስቤ ለ30 ቀን የአሜሪካ ቆይታ 23 ሺህ ዶላር በሃምሌ ወር 2008 ዓ.ም እንዲከፈል በማድረግ፤ እንዲሁም ለአቶ #ዝናህብዙ_ፀጋዬ ለ20 ቀን የአሜሪካ ጉዞና ቆይታ 7 ሺህ 687 ከ50 ዶላር ከንግድ ባንክ እንዲከፈል በማድረግ ወጪው ከኮርፖሬት ፋይናንስ ኢንቨስትመንት እንዲሸፈን ደብዳቤ በመጻፍ፣ ለኮሎኔል አታክልት ወልደሚካኤል #ልጅ ዮናስ አታክልት የውጭ ሃገር ህክምና 86 ሺህ 889 ሺህ ከ54 ዶላር ክፍያ እንዲፈጸም በማድረግ፣ ለወይዘሮ ንግስቲ ከሰተ የውጭ ሃገር ህክምና 18 ሺህ 454 ሺህ 51 ዶላር ክፍያ እንዲፈጸምና ሌሎችም እንዲጠቀሙ ክፍያ እንዲፈጸም በማድረግ በ2004 ዓ.ም የግዥ ዘመን ከግዥ መመሪያ ውጭ አለም አቀፍ የጨረታ ውድድር ሳይደረግ ከመስሪያ ቤቱ ሃላፊዎቹ ጋር በመሆን የግዥ ውል በማፅደቅ 10 ሚሊየን 670 ሺህ 184 ዶላር በማውጣት፥ ኖሮኮን ከተባለው የቻይና ኩባንያ የኮንስትራክሽን ማሽነሪዎች ግዥ በህገ ወጥ መንገድ እንዲፈጸም በማድረግ መንግስት ከጨረታ ውድድር ሊያገኝ የሚገባውን ጥቅም በማሳጣት ከግዥ መመሪያ ውጭ አለም አቀፍ ጨረታ ውድድር ሳይደረግ ከመስሪያ ቤቱ ሃላፊዎች ጋር በመሆን የግዥ ውል በማፅደቅ 660 ሺህ ዶላር በማውጣት፥ ዳኑቢያን ኤርክራፍት ከተባለ አለም አቀፍ ድርጅት የአገልግሎት ግዥ በህገ ወጥ መንገድ እንዲፈጸም በማድረግ መንግስት ከጨረታ ውድድር ሊያገኝ የሚገባውን ጥቅም በማሳጣት፤ ሜቴክ ከ2001 ዓ.ም ጀምሮ ከ13 በላይ አለም አቀፍ ኩባንያዎችን ያለምንም ጨረታ እና ውድድር በሰላሳ የተለያዩ የውል ስምምነቶች ከአንድ ቢሊየን ዶላር በላይ የሚያወጡ ግዥዎች እንዲከወኑ ተደርጓል፤ ተጠርጣሪው እነዚህ ውሎች ውስጥ ለጊዜው የተረጋገጠ 15 የሚሆኑ ውሎችን አፅድቀዋል እንዲሁም ተፈራርመዋል።

የእርሳቸው #ወንድም የሆኑት አቶ ኢሳያስ ዳኘውን የተጠረጠሩባቸውን የሙስና ወንጀሎችም ፖሊስ ለፍርድ ቤቱ አቅርቧል። በዚህም ግለሰቡ የኢትዮ ቴሌኮም የኤን ጂ ፒ ኦ ፕሮግራም ዳይሬክተር ሆነው ሲሰሩ ለሜቴክ በሶማሌ ክልልና በባሌ ዞን የሞባይልና ሲ ዲ ኤም ኤ ሳይቶች ግንባታ ስራ፥ 204 ሚሊየን 981 ሺህ 630 ብር የተደረገው ውል ስራው ሳይጠናቀቅ ቫትን ጨምሮ 322 ሚሊየን 628 ሺህ 124 ብር ከ55 ሳንቲም ክፍያ እንዲፈጸም ለፋይናንስ ደብዳቤ በመጻፍ ደረጃውን ያልጠበቀና ጥራት የሌለው ስራ እንዲሰራ በማድረግ፣ እንዲሁም ስራው ሳይጠናቀቅ የመጀመሪያውን ውል በማሻሻል የቴሌ ታወር ግንባታና ተከላ ስራ 321 ሚሊየን 710 ሺህ 424 ብር ከ55 ሳንቲም ውል በማሻሻል ለሜቴክ በመስጠት የተጠረጠሩ ናቸው ብሏል።

ከዚህ ባለፈም በአቶ #ተስፋዬ_ኡርጌ_ላያ ባደረገው ምርመራ ተጠርጣሪው ፈጽመዋቸዋል ያላቸውን ድርጊቶች በጽሁፍ አቅርቧል፤ በዚህም ግለሰቡ የተለያ ሰዎችን የኦነግ ድርጅት አባል ናቸሁ በማለትና ያለአግባብ እንዲታሰሩ በማድረግ በስውር እስር ቤት በማሰርና በማሰቃየት እንዲሁም በማስፈራራት ከሌሎች ግብረ አበሮቻቸው ጋር 6 ሚሊየን ብር እና 22 ሺህ ዶላር በመቀበል ለግል ጥቅማቸው አውለዋል ሲል ለፍርድ ቤቱ አስረድቷል።

የደረሰውን ጉዳት ኦዲት ማስደረግ፣ ያለጥቅም የተቀመጠውን ፋብሪካ ያለበትን ደረጃ የባለሙያ ቃል መቀበልና የምስክሮች ቃልን መቀበልን ጨምሮ ሌሎች ቀሪ ስራዎች እንዳሉትም ለችሎቱ አስረድቷል።

ምንጭ፦ ፋና ብሮድካስቲንግ
@tsegabwolde @tikahethiopia